ይህ ጽሑፍ መሪ ራስ አማን በላይ ‹የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ› በሚል ርዕስ ከመጽሐፈ ሱባኤ ተረጎምኩት ብለው በ1985 ዓ.ም. ካሳተሙት መጽሐፍ ከምዕራፍ ሦስት በሙሉ የተወሰደ ነው፡፡ ጽሑፍ እሳቸው እንዳዘጋጁት ነው እንጂ የተጨመረበት ወይም ኤዲት የተደረገ ነገር የለውም፡፡ መጽሐፉ በያዛቸው መረጃዎችም ሆነ በምንጩ በተለምዶ ከሚታወቀው የታሪክ መጽሐፎች ይለያል፤ ስለ መጽሐፉ ይዘት፣ ምንጭና አስፈላጊነት ብዙ ማለት ቢቻልም፤ መጽሐፉ ብዙ ሰዎች በቀላሉ አግኝተውት ያላለነበቡት በመሆኑ አንዱን ምዕራፍ ብቻ እንደነበረ እንደማሳያ ማቅረብ የተሻለ መስሎ ታይቶኛል፡፡ ለማንኛውም ስለ መጽሐፉ ሁኔታ ለማወቅ በመግቢያውና በመጽሐፉ ጀርባ ከጻፉት ላይ ቀንጭቦ ማየት ጠቀሜታ ይኖረዋልና እነሆ!
(ከመግቢያው የተወሰደ)
‹‹ይሄን የጥንቷ የኢትዮጵያ ታሪክ ሱዳን አጥባራ በነበርኩበት ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጽሐፈ ሲራክ እያነበብኩ ስለ ድንጋይ ጥበብና ስለሌላም ስከታተል እንደቆየሁ ጀቢል ኩራርና ጀቢል ኦባ ወደሚባለው ሃገር ሄጄ የጥንት ቤተክርስቲያን ፍርስራሽና የክርስቲያን መቃብር አገኘሁ፤ ከዚያም ጀበል ኦባ ለአንድ ሰባት ወር እንደተቀመጥኩ አንድ ሽማግሌ ሰው እንዲህ ካለ ዋሻ ውስጥ የክርስቲያኖች መጽሐፍ አለ ብለውኝ አብረን ሄድን፤ ብዙ በብራና የተጻፉና የተቀዳደዱ መጽሐፎች አገኘን፤ እንደገና ከሌላ ዋሻ ሄደን ስንቆፍር ብዙ ፅላቶችንና ቁርጥራጭ ካባዎችን፣ ቁመቱ ክንድ አንድ መቶ ስልሳ አራት ብራና የአክሱማይ ሲራክን መጽሐፍ፣ የሱባን ቋንቋና የሱባን ታሪክ የያዘ መጽሐፈ ሱባኤ፣ እንደዚሁም በጣም የረዳኝ ሁለት መቶ ብራና አራት መቶ ገጽ ያለው የኢትዮጵያ ነገሥታት ታሪክ ዘግዱር ዘእንዳ ቤት በተፈለፈለ የድንጋይ ጉድጓድ ከተልባና ከአመድ ጋር ተቀብሮ ተገኘ፡፡
መጽሐፈ ሱባኤ ከአዳም እስከ ቀዳማዊ ምኒልክ መፀሐፈ አክማይ
ሲራክ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ዮዲት መጽሐፈ ታሪክ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዘግዱር ዘአንደበት የተጻፈ ከዮዲት እስከ በካፋ ልጅ ዳግማዊ ኢያሱ ከዳግማዊ ኢያሱ ወዲህ እስከ ኃይለ ሥላሴ ማህፀወ ነገሥት ከመሪጌታ ጉባኤ ጎጃም ሊበን ውስጥ ከተገኘ መጽሐፍ በብዙ ችግርና ድካ ለማሳተም ወደ ኢትዮጵያ በ1966 ዓ.ም. ይዤው ገባሁ፡፡››
(ከመጽሐፉ ጀርባ የተቀነጨበ)
‹‹… በጊዜው የነገሥታትን ታሪክ ማሳትና ማወደስ አደገኛ ነበር፡፡ ሁኔታውም በጣም አሰጋኝ፤ እናም ብዙ ሺ ማይልስ ከኔ ጋር ለብዙ ዓመታት ተንከራተተ፡፡ አሁን ጊዜውና አጋጣሚው ፈቅዶ አቋርጦ ከሄደበት ከምድረ አሜሪካ በሀገሩ በኢትዮጵያ በወንድሞቼ ብርታት ለመታተም በቃ፡፡ በዚህ አጋጣሚ አፈር የተጫናቸው መጻሕፍትና ንዋየ ቅዱሳት ቀስ በቀስ እየወጡ እውነተኛ ታሪካችን እየታወቀ እንደሚሄድ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡››


ምዕራፍ ሦስት፡- ነገደ ኢትዮጵያ
‹‹ኢያስጴድ-ኢ፡ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግሥት
ስሙ፣ አልፋ አየን አማን ኤል ኢያስጴድ፤
ፊደሉ፡ /እ/፣ /አ/፣ /ኣ/፣ /ኤ/፣ /ኢ/
/ኢትኤል ማለት የአምላክ ሥጦታ ማለት ነው፡፡/
የክህነቱ ስም ኢትኤል የተባለው ኢትዮጵ የአበ መለክስ ናምሩድ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ናምሩድ አዳማን ወለደ፤ አዳማ ራፌልብን ወለደ፤ ራፌልብ ኬናን ወለደ፤ ኬና ወይም ቄና ጌራራን ወለደ፤ ጌራራ ወይም ጌራ ሃሙራቢ የክህነት ስሙ መልከጼዴቅ የተባለው ታላቁ የሰላም ንጉሥና የአምላክ አገልጋይ በደብረሣሌም ኢትን ወለደ፤ ኢትም እንዳባቱ አምላኩን ወዳድና ለፈጣሪው ታዛዥ ተገዥ ስለነበረ ኢትኤል ተባለ፤ ኢትኤል ማለት የአምላክ ሥጦታ ማለት ነው፡፡
ኢትኤልም በአምላኩ መንፈስ እየተመራ ግዮን ወንዝ ወደሚፈስበት ምድር ሄዶ ተቀመጠ፤ ያንም ምድር ኢያስጵድያ የሚባለውን ድንጋይና ከጥራቱ የተነሣ የሚያንፀባርቀው ኢያስጵድ ክርስቶ ድንጋይ ክብር ዮጵ ድንጋይ የሚገኝበት ነው፡፡ ስለዚህ ዮጵ በሚባለው ወርቅና በእንቁ ድንጋይ ሃብታም ስለነበረ ኢትኤል መባሉ ቀርቶ ኢትዮጵ ተባለ፤ ሚስቱም ሲና መባሉዋ ቀርቶ እንቅዮጳግዮን ተብላለች በነገደ ዮቅጣን አግአዝያን የሚባሉት አቡሳውያን እንቆ እንቁጳግዮን የሚባለው ስም እንቆዮጳዝዮን ብለውታል፤ ይሄውም የአባይ ወርቅ ማለት ቀርቶ የፅዮን ወርቅ እንዲባል ብለው ነው፡፡
ኢትኤልም ግዮን ወንዙን ለወንዝ አጠራቅሞና ሰብስቦ እስከሚገናኝበት ያለውን ምድር ሁሉ በስሙ ኢትዮጵያ እንዲባል አድርጓል በግዮን ዳርቻ ሄዶ የልጅ ልጆቹ በሚነግሡበት ጊዜ በዚህ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ቅባአ መንግሥታቸውን እንዲቀቡና እንዲነግሡ ሲል ኤለንኤል ብሎ በክብር ለማሳሰቢያ ትልቅ የድንጋይ ዙፋን አስቀምጧል፡፡ ይህም ምድር ከሳሌም እስከ ግዮን ድረስ የኢትዮጵ ልጅ አዜብ ይገዛው ስለነበረ አዜብ ይባላል፡፡
አዜብ መልከዘቦ ንጉሥ በግራ ክፍል የሚገኘውን የግዮን ገባሪ ሰማያዊ ግዮን ወንዝ እስከሚፈልቅበት ምድር ድረስ ግዛቱን አስፋፍቶ ስለነበረ ያ ምድር እስከ አሁን አዜብ ወይም አዘቦ ይባላል፡፡ አዜብያ በሚለው ሃገር ውስጥ አብርሃም ሳይባል አብራም ብዙ ቀናት በእንግድነት ተቀምጦበት ነበር አብራም በዚሁ ወርቅና በብር ከብሮበት ነበር፤ ይህም ታሪክ በሴም ነገዶች ተጽፎ ይገኛል፡፡ አዜብ 132 ዓመት ገዝቶ የኢትዮጵያ ታላቅ ልጅ አቲባ ወርካዘቦ ንጉሥ በቀኝ በኩል ያለውን የግዮን ገባሪ ወንዞች የሚፈልቁበትን ሃገሮች እንዲገዛ አንግሦ ሰደደው፤ አቲባም በአባቱ በኢትዮጵ ሥር ሆኖ እስከ ታላቁ ባህር በሚገኙት ጎሣዎች ላይ በሱባ አቆጣጠር ሰባት ሱባኤ ገዝቷል፡፡
ካህኑ ኢትኤልም በኢትዮጵያ ምድር ሆኖ ምድሪቱን ከባረካትና ለልጆቹም የመገናኛ ዘዴ ጽፎ ከአስተማራቸውና ሥርዓተ መንግሥት ከአሳያቸው በኋላ ንጉሥ ነገሥት በተባለ በአሥራ አራት ሱባኤ (98 ዓመት ማለት ነው)በተወለደ በአንድ መቶ አምሣ አንድደ ዓመት አንቀላፋ፤መልከጼዴቅ ከአስፈለፈለውና ከአሠራው ዋሻ ውስጥ ወስደው አስቀመጡት፤ በኢትዮጵ መጨረሻ የግዛት ዘመን እረሃብ ነበረና እብራውያን ወደ ምስር የተሰደዱበት ዘመን ነው፡፡
ኢትዮጵያ የተባለው ኢትኤል በፋቱራ የተድኦልን ልጅ እንቁጳን አግብቶ አሥር ወንዶች ሦስት ሴቶች ወለደ፡፡ የወንዶቹ ስማቸው አቲባ፣ ቦኦር፣ ቢኦራ፣ ተምና፣ ኤቴር፣ አሻን፣ አክለብ፣ መሪሣ፣ ቴስቢ፣ ቶላ፣ አቤሜሌክ የተባለው አዜብ ናቸው፡፡ ሴቶች ደግሞ ሎዛ፣ ሚልካና ሱባ ናቸው፡፡ የአቲባና የመጨረሻው ልጅ የአዜብ ዘሮች ነገሥታት ናቸው፡፡ የቢኦር ዘሮች መናፍስት በመጥራት፣ የተምና፣ የኤቴር፣ የአሻን ዘሮች የተለያዩ ቅርጾች በመሥራት የሰው ልጆች የሚያገናኙበትን፣ የሃሣባቸውን የሚገልጹበት ምልክት ወይም ጠልሰም ታሪክ የሚያቆዩበትን ጽሕፈት የሚያቆዩ ፈላስፎች ናቸው፡፡ ይሔውም ለመጀመሪያ ጊዜ በአምላክ ስም ፊደል የቀረጸ፣ ለእያንዳንዱ ቃል ትርጓሜ አቅርቦ ያስተማራቸው አባታቸው ኢትኤል ነው፤ ከዚያ በፊት የትውልድ ታሪክ በቃል ሲነገር በልብ ሲጻፍ ቆየ እንጂ ሌላ ዘዴ አልነበራቸውም፤ የአክዚብና የመሪሣ ዘሮች ናቸው፤ የቴስቤ ዘሮች የአምላክ አገልጋዮች፣ ትንቢት ተናጋሪ፣ መጭውን በማወቅ የታወቁ ናቸው፡፡ ከነዚህ ዘር የተወለደው ታላቁ ነቢይ ቴሰቢያዊ ኤልያስ ነበር፡፡ የቶላ ዘሮች አንጠረኞች፣ ግመሹ ነገዴዎች ነበሩ፡፡
ቢአር አራምን ወለደ፤ አራም ናጊን ወለደ፤ ናጌ ሃጌን ወለደ፤ ሃጌም ሁለተኛውን ቢኦርን ወለደ፤ ቢኦር በለአምን ወለደ፤ በለአም ከምሥር ዕብራዉያን ሲወጡ በእሥራኤል ላይ በመንፈስ እየተመራ ትንቢት ተናገረ፤ የተናገረው ቃልም እንዲህ አለ ‹አየዋለሁ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ በእሥራኤል በትር ይነሣል፡፡ ከያዕቆብ የሚመጣ ገዥ ይሆናል› ሲል ስለ መሲሁና ስለ እረሱ ነገድ ደግሞ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናግሯል ‹ማደሪያህ የፀና ነው፤ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቷል፤ ነገር ግን አሶር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊ (ኬናዊ) አንተ ለጥፋት ባርነት ትሆናለህ፤ አምላክህ ይህን ሲያደርግ አወደ፤ በሕይወት ማን ይኖራል፤ ከኪቴም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤ ያስጨነቅህን አሦርንም ያስጨንቃሉ፤ ነገር ግን እርሱም ደግሞ ይጠፋል፡፡› ብሎ የተናገረውን ልጁ ደሸት ትንቢቱን ሲከታተል በቀትር ጊዜ ከምንጩ ዳር ተቀምጦ ፍልስፍናውን በአዝዋሪት ውሃ ሲያናና ሲፈለስፍ ለብልአም የታየው ኮከብ እንደገና ለደሸት ታየው የአዝዋሪቱን አረፋ ኮከብ እየተከታተለ ሲጽፍ ድንግል ሴት ያለ ዘር የተወለደ ልጅ ታቅፋ አያት፤ ወዲያውኑ ያየውንና ወደ ድንግሊቱ የመራውን ኮከብ ሥዕል በናስ ሰሌዳ ሥሎና ቀርጾና ድንግሊቱን፣ ልጅዋን እንደታቀፈች በወርቅ ሰሌዳ ሥዕሉን ቀርጾ ለልጆቹ አስቀመጠው፤ ሊሞት ሲል ‹ይህ ኮከብ የሚመስል በምሥራቅ በኩል ሲወጣ ዐይታችሁ፤ ጨረሩን ወደሚያመለክታቸሁ ምድር ተጉዛችሁ፣ ከምድራችሁ ከምታገኙት ከምታገኙት የምድር አበል ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ፣ ልብስ ይዛችሁ ይህን አምላካችን ለአባታችን ለአዳም ለሔዋን እዲሰጣት የሰጠውን፣ አብርሃም ለአባታችን ለመልከጼዴቅ አሥራት ብሎ የሰጠውን እንአርያ በክብር ይዛችሁ፣ የኮከብ ብርሃን ለስግደት ሰግዳችሁ ስጡት፤ ሉልና ዮጴ የወርቅ ሃመልመላል ለእናቱ ስጡለት፤ ይህ እስከሚሆን ድረስ እንቆ አርያውን ተመልከቱት፤ እርሃብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ይጠቁራል፤ የጥጋብ ዘመን ሊሆን ሲል መልኩ ያበራል፤ ቅባቱ ይጭረቀረቃል ሲል እናተም ማርና ወተት ወደሚስባት ምድር ሔዳችሁ ትኖራላችሁ› ብሎ ለልጆቹ በተለመደ በአሥራ አንድ ሱባኤ ሞቷል፡፡ ይህም ዘመን በእሥራኤል ንጉሥ አልነበረም፡፡ በእሥራኤል ላይ የነገሠው ንጉሥ ዳዊትም በመንፈስ የታየውን ትንቢት እንዲህ ሲል ተናጋገረ ‹በፊቱ ኢትዮጵያውያን ይሰግዳሉ ጠላቶቹም አፈር ይለብሳሉ፤ የተርሲስና የደሴቶች ነገሥታት ሥጦታን ያመጣሉ፤ የአረብና የሳባ ነገሥታ እጅ መንሻን ያቀርባሉ፡፡ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ አህዛብ ሁሉ ይገዙለታል፡፡› ሲል ከደሸት በኋላ ተናግል፤ ይህም ትንቢት ለመሲህ እንጅ ለሰለሞን አይደለም፡፡ ነገር ግን ከወርቅ በፊት ሰም ስለሚቀርብ ሰም የሰለሞን ወርቅ የመሲህ ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡
በልአም ሙት የምታስነሣ የነበረች የሸምሸልን አባት ቀራሚድን ወለደ፤ ዘጠኝ ወንዶችና ሴት ሸምሽልን ወለደ፤ ሸምሽል ፈላስፋው ደሸትን ወለደች፤ አባቱ አይታወቅም ይባላል (እዚህ ታሪክ አልፋለሁ)፤ የደሸት ልጆች ማጂ፣ ጅማ፣ መንዳና መደባይ ናቸው፡፡ የማጂ ዘሮች በኮከብ የሚያመልኩ፣ መንፈሰ ኃይል የተሰጣቸው መጭውን የሚናገሩ፣ በመንፈስ ስለመነጋገር የሚያምኑ ናቸው፤ ማጂ ማራን፣ ዣማን፣ ጂየማን ይወልዳል፤ ጂማ አረርቲን፣ ገነቲን፣ ሞረን ይወለዳል፤ እነዚህ ሁሉ የግዮን ምንጭ በሚፈልቅበትና በሚከበው ምድር ሄደው ሠፈሩ፤ በአባታቸው ስም ምድሩን ደሸት አሉት፤ ነገሥታት ደግሞ በንጉሥ ጎዣም በዳሞው ልጅ ስም ጎዣም ተብሏል፤ ይህም ስም የተቀየረ በዐፄ ዘመነ መንግሥት በአራት ሽህ አምስት መቶ ዓመት ከተቆጠረ (500 ዓመት ከክ.ል.በፊት) ነው፤ ማራ ከወገኖቹ ተልይቶ ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ ፀሐይ መውጫ በተራሚው ሀገር ውስጥ ሄዶ ተቀመጠ፤ ገነት ኦዶምን ይወልዳል፤ ኤዶም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደሚገኘው ባሕር ሄዶ መኖሪያውን አደርገ፡፡
ቀለመ ዮጵ የተባለው ዘግዱር የዣማን ነገዶች ግማሹን ታሪክ ፀሐፊ አድሮጎ ቤተአንዳ የዛሬ አንዳ ቤት ግማሹን የመደባይ ነገዶች ቦረኖች ወደሞኖሩበት ቤተማራ የዛሬው መርሃቤቴ ላካቸው፤ ያንም ሃገር በአባታቸው ስም ወንዙን ዣማ አሉት፤ በዚያንም ሃገር የማሩ ነገዶች ይኖሩበታል፤ እነዚህ ማሩ የተባሉ ሁለተኛው ዘግዱር አሚንሆ የተባለውን የእብነልሃኪም የልጅ ልጅ በግብጾች ጋር በአደረገው ጦርነት ለእርዳታ ሄደው በዚያው ቀርተዋል፡፡ ያም የሠፈሩበት ሃገር አማርና ይባላል፡፡ ከሁለት ሺህ ዓመታ በላይ ከኖሩ በኋላ በዐፄ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በቤተሃማራ ከሚኖሩት ጎሣዎቻቸው ጋር ተቀላቅለው ኖሩ እነዚህም የዛሬዎች አማራዎች ናቸው፤ ከነገደ አማራ ኢትዮጵ አቲባን ወለደ፤ አቲባ ሁለትኛው አዜብን ከሣዱንያ ልጅ ቂቂ ከምትባል ንግሥት ወለደ፤ አዜብ ሰቢን ወለደ፤ ሰቢ በግዮን ዳርቻ ስመ መንግሥቱ ሞረሽ መለከ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በሃያ አንድ ነገሥታ በአርባ አምሰት ሀገሮች ላይ ነገሠ፤ ግዛቱም በስሙ ሞሪያ ከተባለው ተራራና እስከ ከሱኪ ባሕር ድረስ ነው፡፡ ሞረሽ መለከ ሠራዊቱን ሃገር እንዲያቀኑ፣ ግዛት እንዲያስፋፋ ወደ መካከለኛው ግዮንና ወደ ታላቁ ባሕር ላካቸው፤ እነሱም ምድሩን እርስት አድርገው በዚያው ቀርተዋል፤ በስሙ ምድሩን ሙርታንያ፣ ሕዝቡም ሞረቴ ተብለዋ፤ ግዛቱም ሰባ ሰባት ዓመት ነው፤ በፈንታው ልጁ ልብና ነገሠ፡፡ ሞረሽ መለክ የተባለው የአዜብ ልጅ ሳቢ በሙርታንያ ልብናን ወለደ፤ ልብና በግዮን ዳርቻ ስመ መንግሥቱ ሊባኖ ተብሎ በኢትዮጵያ ምድር ሁሉ አርባ አራት ዓመት ነገሠ፤ ልብና ከፍልስጢሞችና ከአማሌቅ ጋር ሲዋጋ በጌራራ ሞተ፤ ለልብና አንድ ልጅ ስለነበረው በፈንታው ሱካውያንን፣ አዜባውያን አነገሡለት፤ በነገሠ በሦስት ዓመት የአባቶችን ሕግና ሥርዓት ለመፈጸም በግዮን ዳርቻ እንደገና ነገሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ ዳግመኛ ነገሠ፤ ግዛቱም ሦስት ሱባኤ ተኩል (ሃያ አራት ዓመት) ነው፡፡ አቤሜሌክ የተባለው መሌክ ጋዝያን በጌራራ ወለደ፤ ጋዜያም በአባቱ ፈንታ አበሰኒ ተብሎ በሲና አዜባውያንና ሱካውያን አነገሡት፤ በጋዝያ ዘመነ መንግሥት ብዙ ሕንፃ ተመሠረተ፤ ያነንም ምድር በስሙ ጋዛ ተባለ፤ ግዛቱም ሰባት ሱባኤ ነው፡፡ ይህም አርባ ስምንት ነው፡፡ አቢሲኒ የተባለው ጋዝያ አድያምን ወለደ፤ አድያም በግዮን ዳርቻ ስመ መንግሥቱ ላክንዱን ተብሎ በኢትዮጵያ ምድር ነገሠ የግዛቱም ዘመን ሰማንያ ሦስት ዓመት ነው፤ ላክንዱን የተባለው አድያም ታላቁ ንጉሠ ነገሥትን ታንዛን ወለደ፡፡
እንደዚህ ሆነ የአድያም ልጅ ታንዛን አሥራ ሁለት ወንዶች፣ አሥራ ሁለት ሴቶች ከአራት ሚስት ወለደ፤ የወንዶች ሰማቸው ስኒ፣ ጉሚዚ፣ ጉድሪ፣ ኩንፍ፣ ከፊን፣ ጎም፣ ከሬች፣ ጉፍ፣ ሓማ፣ ዝሪ፣ ሣምሪ፣ ዮቶሮ፤ የሴቶቹ ስም ካሳኪ፣ ቲካ፣ ዩኒና፣ ብሌኒ፣ ቢሸሎ፣ ችልጋ፣ ልሄም፣ ሳለታ፣ ኤፍራታ፣ ወልቃ፣ ቆቂና፣ ነገዶች ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባታቸው ኢትዮጵ ንኤል የሚባል ታላቅ ድንጋይ ለማሳሰቢያ በአስቀመጠበት በግዮን ዳርቻ ሳለ ተወለዱለት ታንዛን ስመ መንግሥቱን ንርአስ አሰኝቶ በግዮን ዳርቻ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በነገሠ ጊዜ በሥሩ አራት ንጉሦች ሲያነግሡ ታላቁ ልጁን ሲኒን በኩርነት የመጨረሻውን ልጁን ክህነትን አምላኩን እንዲያገለግል ሁለቱን የአባቶችን አፅም እንዲጠብቁና በቦታው እንዲተኩ ወደ እርስታቸው ወደ ምድያም ላካቸው፤ ሌሎቹን ሴቶችና ወንዶችን ይዞ ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ተራራማው ሃገር ሄዶ ቤተ መንግሥቱን ቆረቆረ፤ ስምዋንም ዋይዝ አላት፤ የታንዛንያ ልጆች ያገኙት ምደር ዝፍ፣ የምንጭ ውሃ፣ ታላላቅ ወንዞች የሚገቡበት ለምለም መሬት ሆኖ የዛፍ ፍሬ ለመልቀም አመቺ ስለነበረ በመካከላቸው ጠብና ግጭት እንዳይኖር ለሃያ ሁለት የታንዛኒያ ልጆች ተካፈሉት፤ ከነሱ ቀጥለው የማጂ ልጅ ሄደ፤ መደባይ የማራን ልጆች ሃገር አልምተው ነበርና ጦርነት ቢያነሱ ሊተባበሩ በታላቅ ተራራ ሥር በደጋው መሬት ቃል ኪዳን አደረጉ፤ በየደረጃቸው የታላቅነትና የታናሽነት ምልክት የሚገልጽ የማንኛው ልጅ መሆናቸውን የሚያስረዳ ክትባት አደረጉ፤ ፊታቸውን ተቆረጡ፤ የመጀመሪያው ልጅ ሲኒ ወደ ምድያም ስለሄደ የቁርጡ ክትባት ምልክት በሁለት ይጀምራል፤ ይሄውም የመጀመሪያውና የሁለተኛው ልጆች መሆናቸውን የሚገልጹትበት ቁጥር ነው፡፡ II-III እያለ እስከ ሰባት ሲደርስ እንደገና በግንባራቸው ላይ ክብ ዓይነት ቆረጣ ያደርጋሉ፡፡
ከነዚህም ሖማ የተባለው የገላው ቆዳ በጣም የጠቆረ ቁመቱ ረጂም አስፈሪና አስደንጋጭ ነበረ፤ ሖማ ማለት በሱባ ‹የእውነት ዛፍ ነህ› ማለት ነው፡፡ የሖማ ልጆች ጎጂ፣ ጂን ሻቃ፣ ጅንጀር፣ማሴሻ ናቸው፡፡ ሻቃ ጠንካራና እንደአባቱ አስፈሪ ጥቁር ነው ትርጓሜውም የአምላክ ትንፋሽ ማለት ነው፤ ሻቃም በአባቱ ሥር ሆኖ በግዮን ዳርቻ እስከ ደሸት ድረስ አራት ሱባኤ ተኩል ገዝተዋል፡፡ የሆማ ልጅ ጀንጀር ፈጣኑ ርዋጭ ናይጀርን ወለደ፤ ናይጀርም አያቱ ታንዛን ባርኮና አንግሦ ግዛ ብሎ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ፈቀደለት፤ ንጉሥ ናይጀርም የሄደበትን ሃገር ወንዝ በስሙ ናይጀር እንዲባል አድርጓል፡፡ አልጀር ብሂል ርዋጭ የሖማ ልጅ ማሊ መሣይ ካህን ስለነበረ አያቱም እንደ ቶርአብም ክህነትን ስለባረከለትና በፈቀደውና በወደደው መሬት እንዲቀመጥ ስለፈቀደለት የሄደበትን ሃገር በአያቱ ስም ታንዛን አለው፤ ልጆቹ የቡራኬን ሥራ አጥብቀው የሚወዱና የሚፈቅዱ ናቸው፤ መሣይ በቡራኬ ቀን ንፅሕ ተላጭተው በጆሯቸው ጌጣጌጥ እንጥልጥል አድርገው ይቀርባሉ፤ ሕግና ሥርዓት ሆኖ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ሖማ በግዮን ዳርቻ መኖሪያውን አደረገና ከዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ መልኩዋ የሚያምር የሚያንፀባርቅ ልብስ ለብሳ አንዲት ሴት ልጅ ከባሕሩ ውስጥ ወጥታ ከአለበት ዛፍ መጥታ እንደጥላ ሆና ስትገባ አያትና ቢፈልግ አጣት፡፡
ከዚያ ወደቤቱ ሳይሔድ ከወገኖቹ ተለይቶ በዛፍ ሥር ለብዙ ቀን ከኖረ በኋላ ተገለፀችለትና ለምንድነው ይሄን ያክል ቀን የተቀመጥከ አለችው፤ አፍቅሬሽ አላት፤ ከአፈቀርከ(ኝ) አግባኝ ብትለው አፍቅሯት ነበርና እሺ አላት፤ ስምህ ማነው ብትለው ሖማ አላት፤ ይህም ዛፍ ሖማ ነው አለቸው፤ ያንቺስ ሺባ እባላለሁ አለችው፤ ተጋብተው ብዙ ዓመታት ከሆናቸው በኋላ የወገኖቹ ሴቶች ልጆች ጂና፣ ጃንካ የሚባሉ አደን ሄደው ሳለ አገኙትና ለምን እንደጠፋና ወደ ቤቱ የማይሔድበትን አጥብቀው ጠየቁት፤ እሱም ሁሉን ነገር ገልጾ ነገራቸው፤ እነሱም አብረው እንዲኖሩ ቢጠይቁት ሺባ ባለቤቱን አስፈቅዶ አብረው ከወገኖቻቸው ተለይተው እንዲኖሩ አደረገ፤ ከዚያም ሁለቱን በሥጋ አጋባቸውና ልጅ ወለዱለት የሖማ የልጅ ልጆች እየበዙ እንደሄዱ ሲያውቁ በዘራችን ያለአምልኮት አንኖርምና ስለዚህ ከወገኖቻችን ሄደን የምናምልክበትን ነገር እናምጣ አሉዋት ለሺባ፤ እሷም እኔን ብታመልኩ መአት ቢመጣ እስወራችኋለሁ፤ የምትፈልጉትን ሁሉ እሰጣችኋላሁ፤ ስለአምልቱ ሥርዓት አባታችሁ ያሳያችኋል አለቻቸው፡፡
ሆም ሆማም እሚያመልኩበትን ጌጥ በጥቁር እንቁ አሠርቶ ሸባሻንቃ ለወንዶች ልጆች፣ ሻንቀል ለሴቶች ልጆች ማለኪያ አደረገላቸው፤ ወደ ሻበሻንቅና ወደ ሻንቀል ለአምልኮት የሚገቡ ሁሉ ክሰል ፈጭተው፣ አልመው ከቡልቃ ፍሬ ጋር ለውሰው ተቀብተው መግባት አለባቸው፤ ሴቶች ደግሞ ጥቁርና ቀይ አፈር ከቡልቃው ፍሬ ዘይት ጋር ለውሰው ተቀብተው ይገባሉ፤ ይህም የአምልኮ ባሕልና ልማድ እስከዛሬ ድረስ አለ፤ ከቡዳና ከሂንዱ ሃይማኖት ጋር ይስማማል፤ ከነዚህ እንደመነጨ የሚያስረዳው የህንዶች እምነት ከዚህ የተያያዘና ሺባ በጣም በህንዱ የታወቀች ናት፤ ሺባ የምትባለው ነጭ ነገር ስለምጠላ ዛፍ ደርቆ ቅርፊቱን በሚጥልበት ሰዓት በቶሎ እንዲጠቁር ያቃጥሉታል፤ ከነሱ መሃል ነጭ ቆዳ ሰው ቢወለድ ገለው ይቀብሩታል ወይም ያቃጥሉታል፤ ይችውም የመንፈስ ዛር ታምርን በመሥራት ከአደጋ ነገር በመሰወር የታወቀች ስለነበረች ሃንዲ የሚባሉ ጎሣዎች ወርቅና ልጃቸውን ስእለት በየጊዜው ይሰጡዋት ነበር፤ ሻቃ የሚባለው በመንፈስ እናቱ ሸበሻንቃ በተባለው ማምለኪያ የታመነ ስለነበረ ወርቅና በከብት የከበረ ሆኖ መቀመጫውን በግዮን ወንዝ አደረገ ልጆቹም በአባታቸው ስም ሻንቅላ ተባሉ፤ ወንድሞቹም ጀንና ሉቅ በዋሻና በድንጋይ ሥር ቤታቸውን አደረጉ፤ ባህላቸውም ከታላቁ ወንድማቸው ጋር ተመሳሳይ ሆነ፤ በጋብቻቸው ጊዜ ከጂን፣ ከሉቅ ልጆች ጋር ሴት በሴት ተቀያይረው ይጋባሉ፤ ሴት እህት ከሌለው አንዱ ከነሱ ዜጋ ውጭ የሆነውን ሰው ገሎ ሰለባ በማድረግ ሰለባውን አሳይቶ ሴት ማግባት ይችላል፡፡ ጀግንነቱ፣ ክብሩ፣ ሹመቱ ሁሉ በነሱ ዘንድ ሰለባ ብቻ ነው፤ ሌላ በኩርነት ያለው አለቃ መሪ ሊሆን ይችላ፡፡
እነዚህ ጎሣዎች የዛፍ ፍሬ ለቅመው ሥር ቆፍረው የአገኙትን አውሬና በራሪ ወፍ አሞራ ገድለው ከመብላት በስተቀር ከብት አርብተው አታክልት ተክውለው አያውቁም ነበር ነገር ግን የሚሠሩት ነገር ሁሉ በህብረት ነው፡፡
ኖርኡስ ታንዛን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በተባለ በሰማኒያ አምስት ዓመቱ ዕብራውያን ከግብፅ አርነት ነፃ ወጡ ወደ ከነዓን ርስታቸው በተመለሱ በሦስተኛው ዓመት በተወለደ በመቶ ሠላሳ አንድ ዓመት አንቀላፋ፤ በፈንታውም በሲና በረሃ የሚኖረው ራጉኤል የተባለው ታናሹ ልጅ ዮቶር በግዮን ዳርቻ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ ነገሠ፤ በምድያምና በሲና ምድር የኤልሻዳይ ካህን የክህነቱ ራጉኤል የተባለ የታንዛን ልጅ ዮቶርአብ የሚባል ነበር፡፡
ለዮቶርአብ አሥር ወንዶች፣ ሰባት ሴቶች ነበሩት፤ ወንዶች ኤልሳ፣ ዛሆ፣ ኡሪኤል፣ ንስኤል፣ አልባኤል፣ አልባ፣ ኤልሃ፣ ዙርባኤል፣ ተውሳ፣ አባብሂር፤ ሴቶች ሲፖራ፣ ልሂ፣ ዘሃራ፣ ተምና፣ ለውይዛ፣ እሰድ፣ ዘኒባ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ በምድያም ምድር ተወለዱለት፡፡
የኤል አገልጋይ፣ የምድያም ካህን ራጉኤል በምድያም ምድር የአባቶችን ታሪክና ስም የያዙና፣ የፈጣሪን ቸርነትና ረዳትነት የሚገልፁ መጻሕፍትን በበግ፣ በፍየል፣ በፈረስ ቆዳ ጻፈ፤ ጽሕፈት በኢትኤል ተጀምሮ በልጆቹ በሥነ ሥርዓት ቢያዝም ከአጥንትና ከእንጨት ከተሠራ ሰሌዳ ላይ ከመጻፍ በስተቀር በብራና ተፅፎ አያውቅም ነበር፡፡ ራጉኤል በብርና በወርቅ በከብትም ከመክበሩ ሌላ በአስተዋይነቱና በጥበቡ ብዛት በሞአብና በአሞን ልጆች በአማሌቅም ሎጆች በፌርዛውያውን፣ በአሞራውያን፣ በከነአናውያ፣ በአቡሳውያን ታውቆ ነበር፡፡ ጥበቡን ለማየት፣ ዕውቀቱን ለመማር ወደ እርሱ ይሄዱ ነበር፡፡ ከነዚህም ከግብፅ ተነሥቶ ወደ ራጉኤል ከሄዱት አንዱ ሙሴ ነበር፡፡ ሙሴም በራጉኤል ቤት ሳለ የአምላክ አገልጋይ ካህንና ትሁት ሰው ለመሆን ይተጋ ነበር፡፡ የምድያም ካህን ራጉኤልም የአምላክ ሰው መሆኑን አስተውሎ ታላቋን ሴት ልጁን ሲፖራን ለሙሴ አጋብቶ በቤተ መቅደሱ ላይ ሾመው፤ ሙሴም ብዙ ቀናት አብሮት ተቀመጠ፡፡
እንደዚህም ሆነ፣ ግብፃውያን በዕብራውያን ላይ የሚያደርጉትን ግፍ የእሥራኤል አምላክ ተመለከተ፤ የዕብራውያን ሃዘንና ጸሎት ወደ አምላክ ደረሰ፤ ስለዚህ አምላክ በግብፃውያን አርነት እጅ ሕዝቡን እሥራኤልን ያወጣ ዘንድ ለሙሴ በአምላክ ተራረራ በኮሬብ በነበልባል ውስጥ የአምላክን መላክ ዐየ፤ ሙሴም ወደዐየበት ዛፍ ተጠጋ፤ በነበልባሉም ውስጥ እንደዚህ የሚቃል ሰማ ‹ሙሴ ሙሴ ሆይ ወደዚህ አትቅረብ፤ የቆምክበት ሥፍራ የተቀደሰ መሬት ነው፤ በቅድሚያ የአቡውያን ትምህርት የሆነ ጫማህን ከእግረልቦናህ ፈጽመህ አውጣ፤ ደግሞም እኔ የአባቶችህ አብረሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ› አለው፡፡
‹ሕዝቤን ዕብራውያንን ከግብፅ ምድር ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርኦን እልክሃለሁ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም የላክሁህ ምልክቱ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብፅ ምድር ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለአምላካችሁ ትገዛላችሁ› አለው፡፡ ሙሴም የአባቶችን አምላክ ቃል ሰምቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ ከዚያም በብዙ ታምር ዕብራውያን ከግብፅ አርነት አውጥቶ በአምላክ ረዳትነት ተመልሶ መጣ፤ በዚያም አማቱ ራጉኤል በአምላክ ተራራ በኮሬብ ወደ ሠፈረ ሙሴ መጣ፤ ሙሴንም እኔ አማትህ ዮቶር አብ፣ ሚሰትህ ሲፓራ ፣ልጆችህ ጌርሳም አልኣዛር መጥንልሃል አለው፤ ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ከድንኳን ወጣ፤ ሰገደም ሳመውም፤ እረስ በራሳቸው ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፤ ወደ ድንኳን ገቡ፤ ሙሴም አምላካቸው በግብፅ ባለሥልጣኖችና በፈርኦን ላይ ስለ ዕብራውያ ያደረገውን ሁሉ በመንገድም ያገኛቸውንም ድካም ሁሉ ኤልሻዳይ አምላክ እንዳዳናቸው ለአማቱ ነገረው፡፡
ካህኑ ራጉኤልም ለዕብራውያን ስላደረገው ቸርነት ሁሉ ደስ አለው፡፡ ራጉኤል በሙሴና በዕብራውያን ስላደረገው ቸርነት ሁሉ ከግብፅውያን አርነት ስለዳናቸው ደስ አለው፡፡ ራጉኤልም በሙሴና በዕብራውያ ሽማግሌዎች መካከል ቁሞ፤ እጁን ዘርግቶ እንዲህ አለ ‹ከግፅውያና ከፈርኦን እጅ ሕዝቡን ያዳነ የእሥራኤል አምላክ ይባረክ፤ አልሻዳይ አምላክ ከአማልክት ሁሉ የበለጠ የእሥራኤል አምላክ እንደሆነ አሁን አወቅኩ› አለ፤ እንደዚህም ብሎ የእህል መስዋእት ስንዴና ወይን በአባታቸው በመልከጼዴቅ የታዘዘውን ሁሉ የሚቀጠለውንም የሚጤሰውንም ለአምላ ወሰደ፤ ሁለቱም በአንድ ላይ መሥዋዕትን አቀረቡ፤ ኤልሻዳይ አምላካቸው መስዋዕታቸውን ተቀበለ፤ የሚቃጠለውን ሁሉ ከሰማይ እሳት ወርዶ በላው፤ በአምላካቸው ፊት ከሙሴ ከአማት ጋር የዕብራውያን ሽማግሎዎች የመሥዋዕት እንጀራ ሊበሉ መጡ፡፡
እንደዚህም ሆነ በነጋው ሙሴ በሕዝብ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ በሙሴ ፊት ቁመው ነበረ፤ ራጉኤልም በሕዝቡ ሙሴ ያደረገውን በየጊዜው ይህ በሕዝብ የምታደርገው ምንድነው? ሙሴም አማቱን ሕዝቡ አምላክን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፤ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፤ የአምላክ ሕግና ሥርዓትንም አስታውቃቸዋለሁ አለው፡፡
ራጉኤልም አለው ‹አንተ የምታደርገው ይህ ነገር መልካም አይደለም፤ ይህ ነገር ይከብደሃል፤ ሕዝቡም ይከብደዋል፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችለም፤ አሁንም እመክርሃለሁ፤ ቃሌን ስማ፤ አምላክ አንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በአምላ ፊት ለሕዝቡ ሁን፤ ነገራውንም ወደ አምላ አድርስ ሥርዓቱንም፣ ሕጉንም አስተምራቸው፤ የአምላን ሕግና ሥርዓቱን በቃልህ ሰምተው የሚጽፉ ጸሐፊዎች አዘጋጅላቸው፤ በጆሯቸው ጠዋትና ማታ የሚነግሯቸውና የሚያስተምሯቸው ዐዋቂዎችን ምረጥላቸው፤ የሚያደርጉትንም ሁሉ ለአስተማሪዎች አስተምራቸው፤ ስለነጋራቸውም ደግሞ እንደዚህ አድርግ ከሕዝቡ ሁሉ ዐዋቂዎችን አምላክን የሚፈሩ፣ የታመኑ፣ የግፍን ሥራ የሚጠሉ ሰዎች አስመርጥ፤ ከእነሱም የበላይ አዛዥ፣ የሺህ፣ የመቶ፣ የዓምሣ፣ የአሥር አለቆች ሹምላቸው በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ ለመፍረድ የማይችሉትን ወደ አንተ ያምጡት፤ ታናሹን ነገር ሁሉ እነሱ ይፍረዱ› አለው፤ ‹ይህ ነገር ለአንተ መልከም ነው፤ ይቀልሃል፤ ይህንም ፈጽመህ ብታደርግ አምላክ ቢያዝህ መቆም ትችላለህ፤ ይህ ሕዝብ ደግሞ በሰላም ወደ ሥፍራው ይደርሳል፤ የነመልከጼዴቅ፣ የነኢትኤልም ሕግና ሥርዓት እንደዚህ ነው› አለው፡፡
ሙሴም የአማቱን የራጉኤልን ቃል ሰማ፤ ያለውንም ሁሉ አደረገ፤ ሙሴም ዐዋቂዎችን ሁሉ መርጦ በሕዝቡ ላይ የበላይ አዛዥ፣ የሺህ አለቃ፣ የአምሣ፣ የአሥር አለቃዎች፣ጸሐፊዎችና አስተማሪዎች ሁሉ አዘጋጀና ሾመላቻ፤ በሕዝቡም ላይ ፈረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ግን ወደ ሙሴ አመጡ፤ ከዚያም ሁለቱ በሰላልም ተሰነባበቱ፡፡
ከዚያም የክህነቱ ስም ራጉኤል የተባለው ዮቶር አብ በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ ዕብረውያን ከግብፅ በወጡ በሦስት ዓመት አባቱ ኖርኦስ ታንዛን ስለሞተ በግዮን ወንዝ ዳርቻ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ ነገሠ፤ በነገሠ በሃያ ሁለት ዓመቱ አንቀላፋ፤ ከእሱ ቀጥሎ በፋንታው ልጁ አባብሂር ዕብራውያን የረዳ መንገድ የመራቸው ስለነበር ከዕብራውያ ወገን የምትሆን የአሚን አዳብ ልጅ ሩት አሚን የምትባለውን አግብቶ ወደ ግዮን በሚያወርደው ምድር ተቀመጠ፤ በዚያም ኢትዮጵስን ወለደ፤ ስመ መንግሥ ሰንደቅ ዣን ተብሎ በግዮን ዳርቻ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ታላቁን ከተማ ሱባን ሠራ፤ በሱባም ታላላቅ ግንቦች ተገነቡ፤ የውሃ መከማቻ ጉድጓዶች ተዘጋጁ፤ በምድርም እንደሱባ ያለ ከተማ አይገኝም ነበር፡፡
ኢትዮጵስ የሱባውያ ንጉሥ ናኦድ በእሥራኤል ላይ መስፍን በነበረ ጊዜ በሳሌምና በአካባቢዋ የሚኖሩ መንደሮች ያለ ጦርነት በሰላም ኖሩ፤ በሱባ የሱባ ንጉሥ ኢትዮጵስ በዘመኑ ምድር ከማካፈልና ከተማ ከመቆርቆር የሀገር ስም ከማውጣት በስተቀር ጦርነት አድርጎ አያውቅም፤ ልጁን ሄቤርን በቃዴስ፣ በፀእናይ መካከል አንግሦት ስለነበር ዕብራውያንና የቃዴስ ንጉሥ ቃል ኪዳን ስለነበራቸው የሄቤር ሚስት ኢያኤል የምትባለው የኢያቤስን የጦር መሪ ሢሠራን ገደለችና የግድያውንም ምልክት እራሱን ለእሥራኤል ልጆች ሰጠች፤ በዚያም ዕብራውያን ስለተደረገላቸው እርዳታ አምላካቸውን አመሰገኑ፤ በሄቤርቤትና በእሥራኤል ልጆች ቤት ወዳጅነታቸው ፀና፡፡ ኢትዮጵስ ሰንደቅ ዣን በየ በርሃው መንደር እየቆረቆረ ሴት አግብቶ በቆረቆረው መንደር ሁሉ ማስቀመጥ ይወድ ነበር፡፡ ስለዚህ ንግሥት የተባሉት ሰባት ሰለነቡ አምሣ ልጆች ከነሱ ወለደ፡፡ እነዚህም አሥራ ሦስት የነገሡ ናቸው፡፡ እነዚህም የኤብያ ንጉሥ ኦማም በአዜብ በርሃ የምትገኝ መንደር የመጀመሪያቱ ሳባ፣ የሳባ ንግሥት ቲራ፣ የኦፊር (የዛሬው ውጋዴን) ንጉሥ ሸሚዳ፣ የኤውላጥ ንጉሥ ሃሺሞን፣ የመደባይ ንጉሥ እናርያ ኋላ በስሙ እናሪያ የተባለው የዛሬው ሊሙ፣ መደባይ መንዲ የሚባሉት የዛሬዎቹ ኦሮሞ አልብኖ ናቸው፤ የመንዲ ንጉሥ ኢያቢስ፣ የኪና ንጉሥ ጂማ፣ የልብስኖ ኑጉሥ ስልባኖን፣ የቃዲ ንጉሥ ሄቤር፡፡
በሰንደቅ ዣን ሰር ወይም ዙፋን ወራሹ ኤልካኖ፣ በሰብያ የሱባ ኑግሥ ሲሆኑ አሥሩ ወንዶች ናቸው፤ ሴቶች ደግሞ የአዲን ንግሥት በለሣ፣ የኤደን ንግሥት አሊና፣ ከሁሉም ልጆቹ በላይ ይወዳት የነበረችውን ኢትግዝያ ከግዮን መገናኛ እስከ ሱኪ ድረስ ባለው በሊብያ ምድር ሁሉ አነገሣት፤ ንግሥተ ነገሥታ ዘኢትዮጵያ የሚል የማረግ ዘውድ በራስዋ ላይ ደፋች ኢትግዝያም በአባትዋ ሥር ሆና አርባ አምስት ዓመት ከገዛች በኋላ በተራራማው ሃገር ዋሻ ውስጥ ሄዳ ተቀመጠች፤ ያንንም ሃገር ያማራ ዜጎች የሚኖሩበት ምድር ነው፡፡
ሰንደቅዣን የተባለው ኢትዮጵ ስም አርባ ስድስት ዓመት በክህነት እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ አሥር ዓመት ገዝቶ በመልካም ገዜ አረፈ፤ በፈንታውም ልጁን ኤልካኖን ስም መንግሥቱን በአባቱ ስም ኢትዮጵስ ተብሎ በግዮን ወንዝ ዳርቻ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከኪቲም እስከ ታላቁ ባሕር ውስጥ በሚገኙት ደሴቶች ሁሉ ላይ ነገሠ፡፡››
Source: http://kassahunalemu.wordpress.com/
ከዘጠኝ ዓመት በፊት በተካሄደው የግንቦት 1997ቱ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጐሜዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ፡፡
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የመጡት አና ጐሜዝ፣ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የጋራ ስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የመጡት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባልና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት አና ጐሜዝ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ምንም ዓይነት የቪዛ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልጸው ይህም አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ በኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ አተያይ አለ ያሉት አና ጐሜዝ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው ምህዳር ግን ከ1997ቱ ምርጫ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የባሰ ነው የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ «ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ተስፋ ይታይበት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ምህዳር በምርጫው ምክንያት በተፈጠረው ቀውስ ከምርጫው በፊት ወደነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተመልሷል፤» በማለት መንግሥትን ተችተዋል፡፡
ለዚህም እንደ መከራከሪያ የሚያነሱት ከምርጫው በኋላ የወጡትን ሕጐች በምሳሌነት በማቅረብ ነው፡፡ «ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት መታሰራቸው፣ የሲቪክ ማኅበራት መፈናፈኛ ማጣታቸው፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የመሳሰሉት ነገሮች በአሉታዊነት የሚነሱ ናቸው፤» በማለት ተናግረዋል፡፡
«ከሁሉም በተለየ ሁኔታ ግን መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን ያለአግባብ በመጠቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማድረግ እያዋለው ነው፤» በማለት አና ጐሜዝ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ከአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳና  ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር እንደተወያዩ አብራርተዋል፡፡
ምንም እንኳን የውይይቱን ዐበይት ነጥቦች በዝርዝር ከመግለጽ ቢቆጠቡም ውይይቱ ግን ገንቢ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ውይይቱ በዋነኛነት የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፣ የፖለቲካ እስረኞችን ማስፈታት፣ ለሲቪክ ማኅበረሰቡ የምርጫ ሜዳውን ማስፋት፣ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማጠናከር የሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ በዝርዝር የተወያዩ መሆኑን ከመግለጽ ውጪ፣ አና ጐሜዝ ከመንግሥት ወገን ያገኙትን ምላሽ ምን እንደሆነ ከማብራራት ተቆጥበዋል፡፡ 
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስተዳደር የተሻለ ሊሆን እንደሚችል የገለጹት አና ጐሜዝ፣ በተለይ ሙስናን በተመለከተ የተጀመረው እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባው አስታውቀዋል፡፡
የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራ ስብሰባው ጥያቄ መቅረቡን ያመለከቱት አና ጐሜዝ፣ የመንግሥትን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም አክለው አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን በተመለከተ ምንም ዓይነት ግለሰባዊ ችግር እንደሌለባቸው የገለጹት አና ጐሜዝ፣ ሥራዬን ግን በአግባቡ የመወጣት ግዴታ አለብኝ ብለዋል፡፡
የጋራ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ በአባል አገሮች ሕገ መንግሥታት ላይ የሥልጣን ክፍፍል እንዲሰፍንና የፖለቲካ ምህዳሩ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሰፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰቡን ለመደገፍ፣ ፍትሕና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመዋጋት እንዲሁም የሥነ ዜጋ ትምህርትን ለማስፋፋትና ለማጐልበት ተቋማዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በእነዚህ ዙሪያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በጥምረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ግንኙነቱ ግን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ሳያሳስቡ አላለፉም፡፡
የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ስብሰባ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ 
Source: Reporter

ጥንታዊ ስልጣኔን ለታሪክ ትተን ከድህነት ወለል በታች ከሚፈረጁት የዓለማችን ኣገራት ተርታ ተሰልፋ የምትገኘው ኢትዮጵያ ግን ደግሞ ይህ ነው የማይባል የተፈጥሮ ሀብትም እንዳላት ይታወቃል። 
  ከተፈጥሮ ሀብቷ መካከልም ኣንደኛው የውኃ ኃብቷ ሲሆን ወንዞቿ ደግሞ ድንበር ዘለልም ጭምር ናቸው። ከዚሁ የተነሳ የምስራቅ ኣፍሪካ የውኃ ምንጭ በመባልም ትታወቃለች። ኣንዱና ዋናው ደግሞ ጥቁር ዓባይ ወይንም በውጪው ኣጠራር ብሉ ናይል ነው። 75 በመቶ የሚሆነው የናይል ውኃም የሚመጣው
ከዚሁ ከብሉ ናይል ወይንም ከኢትዮጵያው ጥቁር ዓባይ ነው። በኣንጻሩ ግን እስከዛሬ ግብጽና ሱዳን እንጂ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ኣልነበረችም። ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን የኢትዮጵያ መንግስት በዓባይ ወንዝ ላይ የህዳሴ ግድብ ሲል የሚጠራውን እጅግ ግዙፍ የሆነ የኃይል ማመንጫ ግድብ መጀመሩ ይታወቃል። ፕሮጀክቱ ደግሞ የታችኛው ተፋሰስ ኣገሮችን በተለይም ግብጾችን ማሳሰብ የጀመረው ገና ከጅምሩ ነበር ማለት ይቻላል።

ከአዲስ ኣበባ በስተ ምዕራብ 620 ኪ ሜ ያህል ርቆ እና ከሱዳን ድንበር ደግሞ 20 ኪ ሜ ገደማ ብቻ ገባ ብሎ በቤኒሻንጌል ጉሙዝ ክልል እየተገነባ ያለውን ታላቁን የዓባይ ግድብ ባለስልጣናቱ የህዳሴ ግድብ የሚል ስያሜ ተሰተውታል። የሚሊኒየም ግድብ እያሉም ይጠሩታል። እኣኣ በታህሳስ ወር 2011 ሳሊኒ ከተባለ የኢጣሊያ ተቐራጭ ኩባኒያ ጋር በተፈረመ ውል መሰረት ግንባታው እስከኣሁን 26 በመቶ መድረሱ ተነግሯል። ከ5 ዓመታት በኃላ በ2018 ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል። እንደ ውጥኑ ከተጠናቀቀ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በኣፍሪካ ደረጃም ትልቁ ግድብ መሆኑ ነው።
60 እስከ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ እንደሚይዝ የሚነገርለት የህዳሴ ግድብ 6000 ሜጋ ዋት የዓኬትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረውም ይገመታል። የሚፈጀው ወጪም በመንግስት ስሌት 4,8 ቢሊየን ዶላር ሲተመን ኣንዳንድ ባለሙያዎች ደግሞ የኢሌትሪክ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ የፕሮጀክቱን ወጪ ከ6 እስከ 7 ቢሊ,ን ዶላር ያደርሱታል።
ኣንደኛው ጥያቄ የዓለም ባንክም ሆነ ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቐም ብድር በነፈጉበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ዓቅም እንዴት ይዘለቃል የሚለው ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ግን በህዝባችን ትብብር በሚል በድፍረት ይዞታል። ግንባታው በኣንድ ወይንም በሌላ መልኩ ከተጠናቀቀ ባኃላም ቢሆን ለዚህን ያህል ከፍተኛ የኤሌትሪክ ኃይል የውጪ ገበያ የማግኘቱ ጉዳይም ሌላው ተዛማጅ ጥያቄ ነው። ምክኒያቱ ደግሞ እንደ ዋና ገበያ የሚታሰቡት ግብጽ እና ሱዳን የታችኛው ተፋሰስ ኣገሮች በመሆናቸው ፕሮጀክቱ ገና ከውጥኑ ስጋት ሆኖባቿልና። የውኃውን ፍሰት ይቀንስብናል በሚል። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት በUS አሜሪካ የዊስካንሲን ዩኒቨርሲቲው የስነ ውኃ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፓውል ጄ ብሎክ እንደሚሉት የግብጾች ስጋት ተደጋግሞ እንደሚሰማው የግድቡ ግንባታ የውኃውን ፍሰት ይቀንስብናል የሚል ሲሆን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በበኩላቸው የግድቡ ዓላማ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት ብቻ በመሆኑ እና ወደ ግድቡ የገባው ውኃ የኃይል ማመንጫውን ካንቀሳቀሰ በኃላ ተመልሶ ወደ ወንዙ ስለሚለቀቅ በፍሰቱ መጠን ላይ የተለየ ተጽዕኖ ኣይኖረውም ሲሉ ይከራከራሉ። ሌላው ቀርቶ ግብጾች ይህን የመሰለ ግዙፍ ግድብ እስኪሞላ ድረስ ባሉት ዓመታትም ቢሆን ስለሚኖረው የውኃ ውስንነት ስጋት ኣላቸው። በኢትዮጵያ መንግስት መግለጫዎች መሰረት ግን የሙሌቱ ሂደት በየዓመቱ አነስተኛ የውኃ መጠን ብቻ ወደ ግድቡ በማስገባት የሚከናወን ሲሆን ጠቀም ያለ ውኃ በመያዝ በአጭር ጊዜ ለመሙላት ቢፈለግም እንኩዋን የግብጹ የአስዋን ግድብ የኣገሪቱን ኣጠቃላይ የውኃ ፍጆታ ለ 3 ዓመታት ያህል የሚሸፍን የመጠባበቂያ ክምችት ስላለው በእነዚያ ጊዜያት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉ ባለስልጣናቱ ኣማራጭ መከራከሪያም ያቀርባሉ። ባለሙያው ፕሮፌሰር ፓውል ግን ኣስታራቂው ሀሳብ ዓለም ዓቀፍ የሆነው የሙሌት ፖሊሲ ነው ይላሉ።
የሙሌት ደምቡ ፕሮፌሰር ፓውል እንደሚሉት ሁለት መልክ ኣለው። ኣንደኛው በየወሩ ወይንም በየዓመቱ በጣም አነስተኛ የውኃ መጠን ብቻ ወደ ግድቡ በማስገባት በረጅም ጊዜ እስኪሞላ መጠበቅ ሲሆን ይህ ግን ባለ በሌለ ኣቅሟ እያስገነባች ላለችው ኢትዮጵያ ኣዋጪ ኣይመስልም። ጠቀም ያለ ውኃ ተይዞ በኣጭር ጊዜ ለመሙላት ቢሞከር ደግሞ የታችኞቹን የተፋሰሱን ኣገሮች ስለሚጎዳ በሙሌት ደምቡ መሰረት ሊያስማማ ባይችል ሊያቀራርብ የሚችሉ ኣማራጮችን መፈለጉ የግድ ይሆናል ይላሉ ፕሮፌሰር ፓውል ጄ ብሎክ።
እናም ይላሉ ተመራማሪው ከዚህ የተለየ የሙሌት ደምብ ኣማራጮችን መፈተሹ የግድ ይሆናል። ለምሳሌም ያህል ይላሉ ፕሮፌሰር ፓውል፣
የዚህ ኣይነቱ የሙሌት ደምብም ቢሆን ኢትዮጵያን የሚጎዳበት ኣጋጣሚ እንደሚኖረው የጠቀሱት ፕሮፌሰር ፓውል ምክንያቱ ደግሞ የአየሩ ጸባይ ከዓመት ወደ ዓመት ተለዋዋጭ በመሆኑ ዝናብ ኣጠር በሆኑ ዓመታት ኢትዮጵያ ኣጠቃላዩን ውኃ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ኣገራት ለመልቀቅ ያስገድዳታል ይላሉ። የሆነ ሆኖ የሙሌት ፖሊሲው ሌሎች የተለያዩ ኣማራጮችም እንዳሉት የጠቀሱት ፕሮፌሰር ፓውል ወሳኙ ነገር የሶስቱ ኣገሮች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ስምምነት እንደሆነ ይመክራሉ።
ባለፈው ወር የኢትዮጵያ የግብጽ እና የሱዳን የውኃ ሚኒስትሮች ካርቱም ላይ ተገናኝተው ኣንድ የጋራ ቴክኒካዊ ኮሚቴ ለማቐቐም መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን በኮሚቴው አባላት ኣሰያየም ላይ ግን ግብጽ እና ኢትዮጵያ በልዩነት መለያየታቸው ኣይዘነጋም። ኢትዮጵያ ኮሚቴው ከሶስቱ ኣገሮች በተወከሉ ባለሙያዎች ብቻ እንዲዋቀር ትፈልጋለች። ግብጽ ደግሞ ገለልተኛ የሆኑ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ተወካዮችም እንዲካተቱ ትሻለች።
ሌላው ተዛማጅ ጥያቄ በመግቢያችን ላይ እንደተጠቀሰው የግድቡ ወጪ በኢትዮጵያ አቅም ብቻ መሸፈን ስለመቻሉ ሲሆን ኣሁን ባለው ሁኔታ ለዚህ ፕሮጀክት ብድር የማግኘቱ ዕድል የመነመነ ቢሆንም ባለፈው ጥቅምት ወር ጠ/ሚ ኃ/ደሳለኝ መንግስታቸው ታላቁን የህዳሴ ግድብ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር በሽርክና ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገልጸው ነበር። ይህንኑ ተከትሎ የግብጽ ባለስልጣናትም እየተለሳለሱ መምጣታቸው ይሰማል። እናም ይህ ከሆነ ተንታኞች እንደሚሉት ለኢትዮጵያ ይህን ከፍተኛ የግንባታ ወጪ ለመሸፈን ከማገዙም ባሻገር ኣገሪቱ ከግድቡ ለምታመነጨው የኤሌትሪክ ኃይል የውጪ ገበያ ያስገኝላታል። ለግብጽ እና ለሱዳንም ቢሆን የሚፈልጉትን የኤሌክትሪክ ኃይል በቅናሽ ዋጋ እንዲገዙ ያስችላቿል። ከሁሉም በላይ የወንዙን ውኃ በጋራ እያለሙ በጋራ እንዲጠቀሙ እድል ይፈጥርላቿል ተብሎ ይታመናል። በተለይም ግብጽ እና ኢትዮጵያ ይህንን ካደረጉ ፕሮፌሰር ፓውል ጄ ብሎክ እንደሚሉት ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቐማትም ፕሮጀክቱን ሊደግፉ ይችላሉ።
እንዲያውም ይላሉ ፕሮፌሰር ፓውል የግብጽ እና የሱዳን ግድቦች በየዓመቱ ከፍተኛ የውኃ መጠን በትነት መልክ ያባክናሉ። የህዳሴ ግድብ ግን የትነት መጠኑ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ሶስቱ ኣገሮች ከተስማሙ በዚህ ብቻም ሳይወሰኑ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ተቸማሪ ግድቦችን በጋራ እያስገነቡ እና እያስተዳደሩ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆንም ይችላሉ። ይህም በክረምት ወራት ከፍተኛ የሆነ የውኃ መጠን ኢትዮጵያ ላይ በመያዝ በበጋ የናይል ወንዝ በሚመነምንበት ወቅት ተጨማሪ ውኃ ይዞ ይዞ ወደ ሱዳን እና ግብጽ በረኃዎች እንዲዘልቅ ማድረግም ይቻላል ይላሉ ፕሮፌሰር ፓውል።
በተያያዘ ዘገባ የቻይና መንግስትም ከግድቡ ኣንስቶ እስከ አዲስ ኣበባ ከተማ ድረስ ያለውን የ619 ኪ ሜ የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ወጪ ለመሸፈን የ1 ቢሊየን ዶላር ብድር መፍቀዱ ታውቐል። ግብጽም ብትሆን ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከ20 እስከ50 በመቶ የሽርክና ድርሻ ለመግዛት እያሰበች መሆኑ ተሰምቷል። ይህ ግን የሚሆነው በኢትዮጵያ መልካም ፈቃደኝነት ነው ተብሏል።
ግብጽ የናይል ወንዝን በተመለከተ እኣኣ በ 1891 እና 1959 ዓ ም የተፈረሙ ዓለም ዓቀፍ ውሎችን መነሻ በማድረግ ልዩ የባለቤትነት መብት ኣለኝ ስትል ቆይታለች። ኢትዮጵያ በበኩልዋ ከሱዳን በስተቀር ሌሎች የተፋሰሱ ኣገሮች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተፈራረሙት የጋራ ስምምነት መሰረት አሮጌው የግብጽ የተናጠል ውል ዋጋ እንደማይኖረው ትከራከራለች።
ጃፈር ዓሊ
ሒሩት መለሰ
Source: www.dw.de

ኢራን ድብቅ የኑክሌር ተቋም እንዳለት ከታወቀበት ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ በቴሕራንና በምዕራባዉያን ሐገራት ፖለቲከኞችን መካከል የደራዉ ዉዝግብ ለመጀመሪያ ጊዜ-አንድ እልባት አግኝቷል። የእስራኤል-ምዕራባዉያን ልዩነት፥ የኢራን-እስራኤል ዉዝግብስ ነዉ?-የዛሬዉ ጥያቄ 
የአያቶላሕ ሩሑላሕ ሆሚኒዋ «ታላቅ ሠይጣን» የድብቅ ዲፕሎማቶች፥ ከጆርጅ ዳብሊዉ ቡሿ «የሰይጣን ዛቢያ» ስዉር መልዕክተኞች ጋር በዓለም የፖለቲካ መድረክ ብዙም በማትታወቀዉ ሐገር፥ በድብቅ ሆቴል፥ በዘወርዋራ አሳንስር ወይም ሊፍት ዉስጥ የጀመሩት ድርድር ቅዳሜ-ለዕሁድ አጥቢያ በይፋ ዉል ተቋጠረ።ዤኔቭ።
«ከከባድ ድርድር በሕዋላ ለረጅም ጊዜ፥ አጠቃላይ መፍትሔ በሚያደርሰን የጋራ የድርጊት መረሐ-ግብር ላይ ዛሬ ተስማምተናል።»
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ካትሪን አሽተን።የድብቅ፥ ይፋዉ ድርድር ሒደት፥ የስምምነቱ ይዘት፥ የተቃዉሞዉ እንዴትነት ያፍታ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።አብራችሁኝ ቆዩ።

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦቦማ በ2009 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣን ሲይዙ በተለይ በዉጪዉ መርሕ ሊፈፅሙት ከገቡት ቃል ብዙዉ እያቃታቸዉ፥ ሌላዉ እየከዳቸዉ፥ ወይም አያሟለጫቸዉ መምጣቱን ሲገነዘቡ ለቃል-እምነታቸዉ ገቢራዊነት «ስስ ብልት» የሚባል አይነት ሲያፈላልጉ-ኢራንን አገኙ።ኦባማ የዲፕሎማሲዉን ስስ ብልት ሲያማትሩ የኢራን አያቶላሆች በሐገራቸዉ ላይ የተጣለዉ ተደጋጋሚ ማዕቀብ፥ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እያደቀቀ፥ የሕዝቡን ምሬት እያናረ ያገዛዝ ሐይል ጉልበታቸዉን እየተፈታተነ መምጣቱን በቅጡ ተገንዝበዉታል።
ከ1979 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የኢራን እስላማዊ አብዮት ወዲሕ በጠላትነት የሚፈላለጉ፥ በሰይጣንነት የሚወጋገዙ፥ በተዘዋዋሪ የሚቆራቆሱት ሐገራት መሪዎች የጥላቻ-ዉርቁሳቸዉ ክረት ጨርሶ ከመበጠሱ በፊት ለየራሳቸዉ መላ ሲሹ-ተገናኙ።ቅዳሜ-ለዕሁድ አጥቢያ በአሜሪካኖቹ በኩል ዉል ፈራሚዉ ጆን ኬሪ ናቸዉ።ምናልባት ካስወቀሰ፥ ተወቃሽ ተመስጋኙ፥ ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ ናቸዉ።
«ዛሬ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ከቅርብ ወዳጆቻችን እና ተሻራኪዎቻችን ጋር ሆነን የኢራን እስላማዊት ሪፐብሊክ የኑክሌር መርሐ-ግብር የፈጠረብንን ሥጋት ለማስወገድ ከአጠቃላይ መፍትሔ ለመድረስ የሚረዳ የመጀመሪያ እርምጃ ወስደናል።ሥልጣን ከያስኩበት ጊዜ ጀምሮ ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት ለማገድ ያለኝን ቁርጠኝነት ግልፅ አድርጌያለሁ።ብዙ ጊዜ እንዳልኩት ይሕን ጉዳይ ለማስወገድ ጠንካራ ምርጫዬ ሰላማዊ መንገድ ነዉ።እና የዲፕሎማሲ እጃችንን ዘርግተናል።»
«የዲፕሎማሲ እጅ» የተዘረጋዉ በማይታወቁት ዲፕሎማቶች፥ በዓለም የፖለቲካ መድረክ ስሟ በማይጠራዉ ሐገር በኩል ነበር።መጋቢት-ሁለት ሺሕ አስራ-ሰወስት።ሙስካት-ኦማን ጦር ሠፈር ያረፈዉ የአሜሪካ የጦር አዉሮላን ያሳፈራቸዉ ሠዎች ያዉ እንደተለመደዉ የአሜሪካ የጦር መኮንኖች ወይም ረዳቶቻቸዉ እንጂ የአሜሪካ ትላልቅ ዲፕሎማቶች መሆናቸዉን ያወቀ-የጠረጠረ፥ ዓላማቸዉን የገመተም ታዛቢ-ጋዜጠኛ አልነበረም።
ቀለል ያለ ልብስ፥ ጠቆር ያለ መነፅር አጥልቀዉ ከጦር አዉሮፕላኑ፥ በጥቋቁር መስታዎቶች ከተጋረዱት መኪኖች ከተጋቡት አሜሪካዉያን ቢንስ ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዉልያም በርንስ እና የምክትል ፕሬዝዳት ጆ ባይደን ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን ነበሩ።የተቀሩት የቴክኒክ አማካሪዎች።
በኢራን በኩል የጄኔቩ ዉል እንዲፈረም አዛዡ ልዕለ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሚኒ፥ ሥልት ቀያሹ ፕሬዝዳት ሐሰን ሩሐኒ፥ ዉል ፈራሚዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር መሐመድ ሳሪፊ ናቸዉ።
«እኛ ሁላችንም የማያስፈለግ ቀዉስ የሚወገድበትን አጋጣሚ መመልከቱ ጠቃሚ ነዉ ብዬ አምናለሁ።እና የኢራን ሕዝብ መብትን በማክበርና ኢራን ፍፁም ሠላማዊ ለሆነ አገልግሎት በምታዉለዉ የኑክሌር መርሐ-ግብር ላይ ጥርጣሬን በማስወገድ ላይ ተመሠረተ አዲስ አድማስ መክፈቱ (ጠቃሚ) ነዉ።
እንደገና መጋቢት፥-የትልቂቱ ሐገር ትላልቅ ዲፕሎማቶች እንደ ጦር መኮንን በጦር አዉሮፕላን ተጭነዉ በዘመኑ ዓለም የፖለቲካ መድረክ ብዙም ከማትታወቀዉ ሐገር ከመግባታቸዉ በፊት፥ «በተራ» የመንገደኞች አዉሮፕላን ተሳፍረዉ ሙስካት የገቡትን ሠዎች ያየ-ያስተዋላቸዉ ከነበረ፥ አንድም የፋርስ ቱጃር ነጋዴዎች አለያም አስተማሪ፥ ወይም ጠበቆች እንጂ የእስላማዊቷ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኞች ናቸዉ ብሎ መጠርጠሩ ሲበዛ አጠራጣሪ ነበር።

የሁለቱ ሐገራት ዲፕሎማቶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ከማጋቢት ጀምሮ ቢያንስ ስድስት ጊዜ ሙስካት ዉስጥ በድብቅ ተደራድረዋል።ተደራዳሪዎች የታዛቢ ትኩረትን በተለይ የጋዜጠኞችን አይን፥ ጆሮ ላለ መሳብ ሆቴል ክፍሎች፥ አሳንስር-ወይም ሊፍት ዉስጥ ተደብቀዉ እስከ መነጋገር ደርሰዋል።ከስድስት ወራት በፊት በድብቅ የተጀመረዉ ድርድር ከዕሁድ አጥቢያዉ ስምምነት መድረሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ እንዳሉት ለዓለም ሠላም ጠቃሚ ነዉ።#

«ዛሬ፥ ዲፕሎማሲ፥ ዓለም ይበልጥ አስተማማኝ የምትሆንበትን አዲስ ጎዳና ከፍቷል፥ ለወደፊቱ የኢራን የኑክሌር መርሐ ግብር ለሠላማዊ አገልግሎት የሚዉል መሆኑን፥ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማትሠራ የምናረጋግጥበትን (ሥልት) ከፍቷል።የዛሬዉ ዉል የመጀመሪያዉ ደረጃ ቢሆንም፥ ታላቅ እመርታ ነዉ።»
ለኢራን ታዳላለች ተብላ የምትጠረጠረዉ ሩሲያም፥ የሐገሪቱ ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት ስምምነቱ ለዓለም ሠላም ከመጥቀሙ ባለፍ ዉዝግብ፥ ግጭት፥ አለመግባባትን በድርድር መፍታት እንደሚቻል ጥሩ አብነት ነዉ።የቻይና ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ባወጣዉ መግለጫዉም ጄኔቭ ላይ የተፈረዉ ዉል ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን ድርድር ዉይይቱ በተጀበረበት መንፈስ መቀጠል አለበት።
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጆች ያሏቸዉ የብሪታንያና የፈረንሳይ ባለ ሥልጣናትም ስምምነቱን አድንቀዋል።በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ባይኖራትም በአሜሪካ ወዳጅነቷ፥ በምጣኔ ሐብት አቅሟም በድርድሩ፥ የድርድሩን ዉጤት በፊርማ በማፅደቁም የተካፈለችዉ ጀርመንም የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ እንዳሉት ስምምነቱ ኢራን የኑክሌር ቦምብ እንዳትታጠቅ ለማከላከል የሚደረገዉ ጥረት ዲፕሎማሲያዊ ዉጤት ነዉ።
«አንድ ግብ አለን።ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳትታጠቅ ማገድ።ከዚያ ግባችን ለመድረስ በዤኔቩ ሥምምነት አንድ ጠቀም ያለ እርምጃ ወደፊት ተራምደናል።ከግባችን በፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመድረስ እንፈለግለን፥ ባካባቢዉ ዉጥረት እንዳይባባስ በየትኛዉም መንገድ መታገድ አለበትና።»

ስምምነቱ ለስድስት ወር የሚፀና ነዉ።በዚሕ ስድስት ወራት ኢራን ዩራኒየም የማብላላት ወይም የማንጠር ሥራዋን ወደ ሃያ-በመቶ ዝቅ ታደርጋለች።የኑክር ተቋማቷን የዓለም አቀፉ የአዉቶሚክ ሐይል ተቆጣጠሪ ባለሥልጣን (IAEA) ባለሙያዎች እንዲፈትሹ ክፍት ታደርጋለች።
ለኢራን ባንፃሩ በተከታታይ ከተጣለባት ማዕቀብ በመኪና ኢንዱስትሪዎችዋ፥ በጌጣጌጥ ወይም በዉድ ማዕድናት፥ ከዉጪ ሐገር ባላት የገንዘብ ልዉዉጥ እና ከነዳጅ ዘይት ተዋፅኦ በጣም በጥቂቱ ላይ የተጣለዉ ገደብ ይነሳላታል።በጥቅሉ ሚቀጥሉት ስድስት ወራት ኢራን ሰባት ቢሊዮን ዶላር ያክል ማስገባት ትችላለች።
የኢራን የኑክሌር ተቋማት የሚያብላሉት ወይም የሚያነጥሩት ዩራኒየም ወይም የፑሉቱኒየም መጠን በሃያ በመቶ ከተገታ ባለሙያዎች እንደመሠከሩት እስላማዊቷ ሪፐብሊክ «የሚፈራዉን» የኑክሌር ቦምብ ማምረት አትችልም።የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር «ዉጥረት እንዳይባባስ» ያሉለት ያ-አካባቢ ግን ከስምምነቱ በፊት እንደነበረዉ ሁሉ ከስምምነቱም በኋላም ከዉጥረት የመለየት ተስፋ አለማሳያቱ ነዉ-ዚቁ።
እርግጥ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ጀምሮ ከዉጥረት ተለይቶ አያዉቅም።ዉጥረት በያማያጣዉ ምድር፥ ከዉጥረት፥ ግጭቱ ተዋኞች አንዷ-ከዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጆች ሁሉ ልዩ ወዳጅ፥ ከምዕራብ አዉሮጳዉያን ወዳጆች ሁሉ የወዳጆች ወዳጅ የሆነች አንዲት ሐገር አለች።እስራል።የኑክሌር ቦምብ መታጠቅዋ «የአደባባይ ሚስጥር» የሚባል አይነት ነዉ።
የዋሽግተን ብራስልስ ልዩ ወዳጆችዋ ለአካባቢዉ አይደለም ለዓለምም ሠላም ይጠቅማል በማለት ያንቆለጳጰሱትን ያሁንን ስምምነት እስራኤል አጣጥላ ነቅፋዋለች።እንዲያዉም የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ እንዳሉት ስምምነቱ «ታሪካዊ ስሕተት» ነዉ።
«ትናንት ማታ ጄኔቭ የተደረሰዉ፥ ታሪካዊ ስምምነት ሳይሆን ታሪካዊ ስሕተት ነዉ።ዛሬ ዓለም ይበልጥ አደገኛ ሥፍራ ሆኗል፥ ምክንያቱም በዓለም እጅግ አደገኛዉ ሥርዓት በዓለም እጅግ አደገኛዉን ጦር መሳሪያ ለማግኘት አንድ ከባድ እርምጃ ወስዷልና።የዓለም ትላልቅ ሐይላት፥ እራሳቸዉ ያስፀደቁትን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔን ዘንግተዉ ኢራን ዩራንየም እንድታነጥር ተስማሙ።»

ኔታንያሁ ኢራን ዩራንየም እንድታነጥር ተፈቀደላት ባይ ናቸዉ።የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ግን ኢራን ዩራንየም ማንጠር ትችላለች ያለዉ ማነዉ ባይ ናቸዉ።

«ይሕ የመጀመሪያዉ ደረጃ፥ ኢራን ዩራኒየም ማንጠር መብት አላት አይልም።እንደፈለገ እየተተረጎመ የፈለገዉ አስተያየት ቢሰጥም በዚሕ ሰነድ ዉስጥ፥ በአደገኛ ጦር መሳሪያዎች መከላከያ (ሕግ) በአራቱም መአዘናት መሠረት ዩራኒየም የማንጥር መብት (ለኢራን) የሚፈቅድ ነገር የለም።ሰነዱ አይፈቅድም።»
ስምምነቱ-ከስድስት ወር ባላይ አይፀናም።ያም ቢሆን በተለይ እስራኤልን እንደማያሰጋ ከፕሬዝዳት ኦባማ እስከ ጆን ኬሪ፥ ከፍራንሷ ኦላንድ እስከ ሎሯ ፋቢዮን፥ ከጊዶ ቬስተር ቬለ እስከ ዋንግ ዪ የሚገኙ የዓለም መሪ፥ ዲፕሎማቶች አረጋግጠዋል።ፕሬዝዳት ኦባማ በይፋ ከሰጡት ማረጋገጪያ ባለፍ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ሥልክ ደዉለዉ የስምምነቱን ይዘትና ዉጤት በግል አስረድተዋልም።
ኔታንያሁ ግን እስራል እራስዋን ለመከላከል መዘጋጀት አለባት በማለት ዝተዋል።በልዩ የፀጥታ አማካሪያቸዉ የሚመራ የመልዕክተኞች ቡድን ወደ ዋሽግተን እንደሚልኩም አስታዉቀዋል።ኢራን ድብቅ የኑክሌር ተቋም እንዳለት ከታወቀበት ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ በቴሕራንና በምዕራባዉያን ሐገራት ፖለቲከኞችን መካከል የደራዉ ዉዝግብ ለመጀመሪያ ጊዜ-አንድ እልባት አግኝቷል። የእስራኤል-ምዕራባዉያን ልዩነት፥ የኢራን-እስራኤል ዉዝግብስ ነዉ?-የዛሬዉ ጥያቄ። ሥለ ማሕደረ ዜና ያላችሁን አስተያየት ወይም ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ የምትሉትን ሐሳብ፥ በደብዴቤ፥ በስልክ፥ በፌስ ቡክ፥ በኤስ. ኤም ኤስ ና በኢሜይል አካፍሉን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ለዛሬ ይብቃን።
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ
 Source: www.dw.de

እኛ ተርፈናል፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው
ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተገደው እየተደፈሩ ነው !
እስር ቤት አንዲት ነፍሰ ጡር ሞታብናለች
- የስደት ተመላሾች 
ሳኡዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ ወደ አገሯ የገቡ ስደተኞችን በሃይል ማስወጣት
ከጀመረች ሁለተኛ ሳምንቷን ያስቆጠረች ሲሆን ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደአገራቸው የመመለስ ዘመቻው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ዜጐችን ከሳኡዲ ለማምጣት ባለፈው ሳምንት በቀን ሰባት በረራዎች ይደረጉ እንደነበር ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ በዚህኛው ሳምንት በቀን 12 በረራዎች እየተደረጉ ዜጐችን ማምጣቱ እንደቀጠለና እስከትላንት ድረስ ከ19ሺ በላይ ዜጐች መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቦሌ አየር ማረፍያ ተገኝተው ተመላሾቹን ያነጋገሩ ሲሆን፤ ስደተኞቹን ለማቋቋም ከክልል መንግስታት ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ ሁለት ሌሎች ቦታዎች ለስደተኞቹ በጊዜያዊ መጠለያነት እያገለገሉ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ከሶስት የሳኡዲ ተመላሾቹ ጋር ባደረገችው ቆይታ የስደት መከራቸውን እንደሚከተለው ነግረዋታል፡፡
“ኤምባሲያችን አይሰማም እንጂ ደጋግመን ነግረናል”
ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡
ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው?
ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤  የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡
እንዴት ነበር የሄድሽው?
በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡
ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ?
ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡
እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ …
ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ…ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡
ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ  አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት?
የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/
አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው?
ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡
እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ?
ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር  አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡
የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል…
አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡ ሚስቱንኧ እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡

“የሁለት ሰው መርዶ ይዤ መጥቻለሁ”
ስምሽ ማን ነው?
ፀጋ ኪዳኔ ገብረኪዳን
ምን እየጠበቅሽ ነው?
ዘመድ አለችኝ አዲስ አበባ የምትኖር፤ እስዋ እስክትመጣ እየጠበቅሁ ነው፡፡
ሳኡዲ ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ?
ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ነው ከሪያድ/ሞንፋ የመጣሁት፡፡ ከኢትዮጵያ ስሄድ በኮንትራት ቢሆንም በባህር ከሄዱት ስደተኞች የተለየ ክብር አላገኘሁም፡፡ ጭቅጭቅ፣ ስድብና ድብደባ  ሲበዛብኝ ከተቀጠርኩበት ቤት በስምንተኛ ወሬ ወጥቼ ጠፋሁ፡፡ የሄድኩት ለአንድ ስራ ብቻ ተዋውዬ ነበር። የምተኛው ግን ከሁለት ሰዓት አይበልጥም ነበር፡፡ ሥራ ብቻ ነው 24 ሰዓት!
እስቲ ስለደረሰብሽ ችግር በዝርዝር ንገሪኝ..
በ700 ሪያድ ተቀጥሬ ነበር ከዚህ የሄድኩት፡፡ አሰሪዬ ቤት አራት ትላልቅ ወንድ ልጆች አሉዋት። የእህትዋ ልጆችም እዚያው ነው የሚኖሩት፡፡ ‹‹ወሲብ ካልፈፀምን..›› ብለው ያስቸግራሉ፡፡ በጣም ተሰቃየሁ፡፡ ከአቅሜ በላይ … ለህይወቴ በጣም አስፈሪ….ሲሆንብኝ ወጣሁ፡፡
ከአቅሜ በላይ ስትይ …
ልጆቹ ወሲብ ካልፈፀምን ብለው አሻፈረኝ ስላቸው፣ “በቢላ እናርድሻለን” እያሉ ያስፈራሩኝ ነበር፡፡ እምነቴን እንድቀይር ሁሉ ይፈልጋሉ። አፈር ድሜ በላሁ፡፡ ሰርቼ ለፍቼ … በዚያ ላይ ነፃነት አልነበረኝም፡፡ ወገቤ፣ ዓይኔ ታመመ፡፡ እነሱ እኮ ሃያ አራት ሰዓት እየበሉ እየጠጡ ነው፡፡ በዚያ ላይ በእጅሽ ላይ ስልክ ማየት አይፈልጉም፡፡ ሁሉ ነገር ሲያንገፈግፈኝ ሁለት ወር የሰራሁበትን ገንዘብ ጥዬ ወጣሁ፡፡ ከዛ ኤጀንሲው ለሌላ ሰው ሸጠኝ፤ በአስር ሺህ ሪያድ፡፡ እዚያም ግን  አልተመቸኝም። ስራው ሃያ አራት ሰዓት ነበር፡፡ አምስት ሰው እንኳን የማይችለው ስራ ነበር፡፡ አንድ ኩንታል ሊጥ አብኩቼ፣ ለሱቅ የሚሸጡት ብስኩት ጠብሼ፣ ሰባት መቶ ሪያል ነበር የሚከፈለኝ፡፡ ሁለት ወር ሙሉ እንደምንም ድምጼን አጥፍቼ ሰራሁ… በእንቅልፍ እጦት ልወድቅ እየተንገታገትኩ፡፡ እፊታቸው ላይ ግን ደስተኛ እመስል ነበር፡፡ ሰውነቴ እየመነመነ መጣ፡፡ ይሄኔ ድጋሚ ለመጥፋት ተዘጋጀሁ፡፡
“ለሌላ ሰው ሸጠኝ” ያልሽው … ኢትዮጵያዊ ነው?
/እንባዋ እየፈሰሰ/አረብ ነው፡፡ ወደ ሳኡዲ ከላከኝ ኤጄንሲ ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ የረመዳን ጊዜ ደግሞ ሱቃቸው ወሰዱኝ፤ የአንድ ሰዓት መንገድ ተጉዞ ሌላ ቤት አላቸው፡፡ እዛ ይዘውኝ ሲሄዱ  ስራ ይቀልልኛል ብዬ ነበር፡፡ … ግን የባሰ ሆነብኝ፡፡ ለካ ጓደኞቻችን ወደው አይደለም ራሳቸውን የሚያጠፉት፤ አብደው ጨርቃቸውን ጥለው በየጎዳውና የወጡትና መንገዱ የወደቁት ... የወገብና የአእምሮ በሽተኞች የሆኑት? “ምነው እናቴ ስትወልጅኝ በመሃፀንሽ ውስጥ ደም ሆኜ በቀረሁ? እናቴ እባክሽ መልሰሽ ዋጪኝ” አልኩኝ፡፡ ራሴንና ቤተሰቤን ልረዳ ስንገታገት ከፊታቸው ድፍት ብል እኮ … እንደሰው ከቆጠሩኝ ... ሬሳዬን ለእናቴ ይልኩላት ይሆናል፡፡ ያለዚያ ግን የሀገራቸው መንግስት አውጥቶ ይቀብረኛል፡፡
ከዚያ ሁሉ በፊት ጠፍቼ መውጣት እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ አንድ ቀን ረመዳን ካፈጠሩ በኋላ ቤተሰቡ ተሰብስቦ ሊዝናኑ ወጡ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ቶሎ ብዬ የሴትየዋን ሙሉ ልብስ ለብሼ፣ ሽፍንፍን ብዬ ወጣሁ፡፡
ሻንጣ ምናምን ሳትይዢ?
ባዶ እጄን ነው የወጣሁት፡፡ የሰራሁበት ገንዘብ እንኳን በእጄ የለም፡፡ በቃ ዝም ብዬ ወጣሁ፡፡ ፓኪስታናዊ የታክሲ ሾፌር አገኘሁ፡፡ ‹‹ምን ሆንሽ?›› ብሎ ሲጠይቀኝ በዝርዝር ነገርኩት፤ አዘነ፡፡ ‹‹ሪያድ የሀበሻ ሃገር ነው፤ ብዙ ኢትዮጵያዊ አለ›› ብሎ እዛ (በነፃ) ወሰደኝ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አገኘሁ፡፡
እዚያ መኖር ጀመርሽ ማለት ነው?
ሳያቸው በጣም ነው ያለቀስኩት፡፡ አገሬ የገባሁ ይመስል..መሬት ሁሉ ስሚያለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ በባህር (በህገወጥ መንገድ) የመጡ ሴቶች ነበሩ። ከእነሱ ጋር አንድ ቤት በስድስት መቶ ሪያድ ለስድስት ወር ተከራይተን አብረን እየኖርን እንሰራ ጀመር፡፡
ቤቱን ለስንት ተከራያችሁ?
አስር ነበርን፡፡ ሁለት ወር እንደሰራሁ ግን በአካባቢው ግጭት ተነሳ፡፡ እግሬ አውጪኝ ብለን በየፊናችን ተበታተንን፡፡
ምን ዓይነት ግጭት?
መንግስት የሌለበት አገር ይመስል ጐረምሶች በር እያንኳኩ በሽጉጥ፣ በካራ፣ ሰው መግደል ጀመሩ፡፡ ስለዚህ ‹‹እጃችንን እንስጥ›› ብለን ተማከርን፡፡ ሌላው ችግር ፖሊስ፤ ትዳር መስርተው የሚኖሩትን የአበሻ ወንዶች እየወሰደ፣ ሴቶችን ለብቻቸው ይተዋቸው ነበር፡፡ በቤቱ ወንድ አለመኖሩን የተገነዘበ የአገሩ ዱርዬዎች (እንኳን ለአበሻው ለመንግስትም ልባቸው ያበጠ ነው) ሴትዋን ለአራትና ለአምስት እየሆኑ መድፈር ያዙ፡፡ ከእኛ ጎን የነበሩትን ሲያሰቃይዋቸው አይተናል፡፡ ወንዶቹን ፖሊስ ሲወስዳቸው ጎረምሶቹ ተከትለው ይገቡና ሴቶቹን መጫወቻ ያደርጓቸዋል/ለቅሶ/፡፡ አንድ ያየሁትን ልንገርሽ../ረጅም ትንፋሽ/እነዚህ ጐረምሶች…ሶስት ሴቶች ያሉበት ክፍል ውስጥ ገብተው ለሰባት ደፈሯቸው፡፡ /ማውራት አልቻለችም፤ ሳግና እንባዋ እያቋረጣት/..ከሶስቱ አንዷ የሰባት ወር ነፍሰጡር ነበረች፤ ሲገናኝዋት ሞተች፡፡ አንዷን ደግሞ ለሰባት ደፈሯትና ገድለው ጥለዋት ሊወጡ ሲሉ ሽርጣ/ፖሊስ መጣ፡፡ ከፖሊስ ጋር ተኩስ ገጥመው እርስ በርስ ተገዳደሉ፡፡ የሀበሻ ወንድ ከእህቱ ወይንም ከሚስቱ ሊለዩት ሲመጡ አልለይም ይልና ይገደላል፤ ይደበደባል … በቃ እልቂት ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ ብለሽ ካራ ቆሬ እንደምትይው..ሪያድ ብለሽ ሞንፋ የሚባል አካባቢ በርካታ አበሾች ይኖራሉ፡፡ እኔ እንኳን የማውቀው … ከአምስት በላይ ሴቶች እንደተገደሉ ነው፡፡  መላ አካላቸውን ቆራርጠው ነው የጣሏቸው፡፡ ግን ይሄ ሁሉ መከራ ምን አድርገን ነው?
አንቺ እንዴት መጣሽ ወደ አገርሽ?
እጄን ሰጠኋ፡፡ አሰሪዬ ‹‹የት ልትሄጂ ነው?›› ብላ ስትጠይቀኝ፡፡ ‹‹አንድ ጓደኛዬ ልትወልድ ነውና ልጠይቃት ..›› ብዬ የሰራሁበትንም ሳልቀበል ወጣሁ፡፡ ምክንያቱም ብትገለኝስ ብዬ ፈራሁ፡፡ አብዛኛው አበሻ ከስራ ወደቤቱ ሲሄድ እየተያዘ ነው የሚመጣው፡፡ የሰራበትን የለፋበትን ሳይዝ ባዶ እጁን፡፡ እና እኛም ነገሩ ስላስፈራን እጃችንን ሰጠን። በቃ እኔም ወደ እዚህ መጣሁ፡፡
ዛሬ ላይ ሆነሽ ስታስቢው ወደዛ በመሄድሽ ምን ይሰማሻል?
መጀመሪያ ከዚህ ስሄድ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር፤ የራሴንና የቤተሰቤን ህይወት ላሻሽል እንደሆነ ተስፋ በማድረግ፡፡ ከዛ በኋላ ግን  ከስራው ብዛት የተነሳ ከጥቅም ውጪ ልሆን ነው ብዬ እጅግ አምርሬ አለቅስ ነበር፡፡ በጣም ስጋት ያዘኝ፡፡ ግን ከሞት ተርፌ ወደዚህ ስመጣ አምላኬን አመሰገንኩ፡፡
ቤተሰብሽ መምጣትሽን አውቀዋል?
አላወቁም፡፡ ምን እያሰቡ ይሆን? ይሄን ሁሉ ነገር እየሰሙ፡፡ እናቴ መንገድ መንገድ እያየች ይሆናል፡፡ ደሞ ከእኛ አካባቢ ልጆች ብዙ የሞቱ አሉ፡፡..አሁን እኔ ራሴ የሁለት ሰው መርዶ ይዤ መጥቻለሁ፡፡ እናቴም ሰው ሲመጣ ‹‹ልጄን አይታችኋል?›› ትል ይሆናል፡፡ እኔስ መጣሁ..በረሃ ላይ ተደፍተው ለመምጣት ወረፋ እየተጠባበቁ ያሉ ህጻናትና ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ እዚህ የመጣነው እኮ ግማሽ አንሞላም፡፡ በሳኡዲ የኢትዮጵያውያን እንባ ያሳዝንሻል፡፡ ብዙዎቹ በሃዘን ላይ ናቸው፤ ድረሱላቸው፡፡

“ሰባት ያበዱ ሴቶችን አይቻለሁ”


ስምሽን ንገሪኝ..?
ሀያት አህመድ
እስቲ አካሄድሽን ንገሪኝ …
ከደሴ ነው በኤጀንሲ የሄድኩት፡፡ የምሰራው በጠለብ/በህጋዊ መንገድ ነበር፡፡ ሰዎቹ ሳይመቹኝ ሲቀሩ..ብዙ ጓደኞቻችን ችግር ሲደርስባቸው ሳይ፣ ስልካችንን ቀምተው ቤተሰቦቻችን በሃሳብ ሲያልቁ፣ እኔም ነገሩ ስላልተመቸኝ ጥዬ ጠፋሁ፡፡ ከዛም በሃጂና ኡምራ የሄድኩ አስመስዬ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ፡፡
በጠለብ ስንት ጊዜ ሰራሽ?
ሶስት ወር ነው የሰራሁት፡፡
አሰሪዎችስ ቤት የሚደርስብሽ ችግር ምን ነበር?
በቤት ውስጥ ያሉ ወንዶች ያስቸግሩኝ ነበር፤ አስገድዶ ለመድፈር ይተናነቁኛል፡፡ አሰሪዬ በስራዬ  አትደሰትም፣ ያጠብኩትን ነገር እንደገና እጠቢ ትለኛለች፡፡
“የኢትዮጵያ ሰራተኞች ሞያ የላቸውም፣ “ሞዴስ እንኳን በአግባቡ መጠቀም አይችሉም፣ በዚያ ላይ ወንዶቻችንን ያባልጋሉ” የሚል ክስ ከሳኡዲ ሴቶች ይሰማል፡፡ አንቺ ምን ትያለሽ?
በጭራሽ! እኛ ደልቶን ይሄን ልናስብ? አንገታችንን ቀና አድርገን እንኳን ለመሄድ እንቸገራለን እኮ፡፡ እዛ ቦታ ላይ እኛን ብታይ ኢትዮጵያዊነት ያስጠላሻል፡፡ አለባበሳችን ምንድን ነው፣ ሁኔታችንስ፣ ኑሮዋችንስ..እኛ የእነሱን ባል የምናባልግ ምን አምሮብን፣ እንዴት ሆነን ነው?  እኛን እኮ ይጠየፉናል፡፡ በምን አንገታችን ቀና ብለን ነው የእነሱን ወንዶች የምናባልገው? እኛ እኮ ለህይወታችን እየሰጋን ነው… እያንዳንዷን ቀን የምናሳልፈው፡፡ በርግጥ የገጠር ልጆችም ይሄዳሉ። እንግዲህ በንፅህና የሚታሙት እነሱ ናቸው፡፡ ግን ስንቱን አእምሮውን አሳጡት…. ወይኔ!!..አሁን ስንመጣ እንኳን ጅዳ ኤርፖርት ውስጥ ሰባት ያበዱ ልጆችን አይቻለሁ፡፡ ‹‹ይዛችኋቸው ሂዱ›› ሲሉን ነበር፤ እንዴት አድርገን እንይዛቸዋለን? ጥለናቸው ነው የመጣን፡፡ አይ ዜጎቻችን! እየቀወሱ፣ እየተደፈሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተጣሉ ነው ሜዳ ላይ ….ተመልካች አጥተው፡፡
ጣትሽ ላይ የጋብቻ ቀለበት አያለሁ … ባለትዳር ነሽ?
ፈትቻለሁ፡፡ የአስር ዓመትና የስምንት ዓመት ልጆች አሉኝ፡፡ እነሱን ላሳድግ ብዬ ነው በሰው አገር የተንገላታሁት፡፡ ገንዘብ እልክ ነበር፡፡ ሆኖም እኔም አልተለወጥኩም፤ ለልጆቼም አልሞላልኝም፡፡ አንድ ጊዜ ሆድ ብሶኝ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ነበር፡፡ ታውቂያለሽ… ልጆቼ በዓይን በዓይኔ መጡብኝና … ከድርጊቴ ታቀብኩ፡፡
አይኔ እንቅልፍ ካጣ ስንት ጊዜው ሆነ መሰለሽ… አይኔ ስር ጥቁር ብሎ የምታይው፣ የበለዘ የሚመስለው እኮ በእንቅልፍ እጦት የተፈጠረብኝ ነው፡፡ ጀርባዬን ያመኛል፡፡ ብዙ ሰዓት የምቆምበት እግሬንም እጅግ ታምሚያለሁ፡፡ አሁን ለትንሽ ጊዜ  ማገገም አለብኝ፡፡
ጂዳ ኤርፖርት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የሚጠባበቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አሉ ይባላል…?
በጣም ብዙ እንጂ! ‘ኢትዮጵያዊ ሁሉ አገር ነቅሎ ነው እንዴ የወጣው ብዬ ተደንቄያለሁ፡፡ በጣም ያዘንኩት ግን ወደዚህ ስመጣ ኤርፖርት ሰባት ያበዱ ልጆች ስመለከት ነው፡፡ እዛ ያለው ኤምባሲያችን እንዴት  ወደ አገራቸው አይመልሳቸውም? ‹‹እህ›› ብሎ ችግራቸውን የሚያደምጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ እስቲ አስቢው…ሰባት ሴቶች አብደው አይቻለሁ፤ በአይኔ በብረቱ፡፡ አንዷ ልጅዋ ሞታባት (በረሃብ ነው) የቀወሰችው፡፡ ስድስቱ ደግሞ በስራ ቦታቸው ቀውሰው፣ አሰሪዎቻቸው ናቸው አምጥተው የጣልዋቸው፡፡ የምናየው ነገር ሁሉ ለዓይን ይዘገንናል፡፡
ከዕረፍት በኋላ ምን  ልትሰሪ አቀድሽ…?
አሁን ጤንነት አይሰማኝም፤ ካገገምኩ በኋላ እንግዲህ … እንጃ ምን እንደምሰራ፡፡ አንድ ዓመት ከሶስት ወር ተቀምጬ ነው የመጣሁት፡፡ ከአስርና አስራ አምስት ዓመት በላይ የኖሩትም ‹‹ምንድነው የምንሰራው..›› የሚል ነው ጥያቄያቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኖረው ቢመጡም ምንም የያዙት ነገር የላቸውም፡፡ በጣም ያሳሰበኝ እሱ ነው፡፡
ከአሁን በኋላ ወደ ሳኡዲ የመመለስ ሃሳብ አለሽ?
አላህ ያውቃል፡፡ 
Source: Addis Admass

(ተመስገን ደሳለኝ)
የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው

ጀሀድ ያወጀው አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ባመጣው ዕዳ በድሃ ወንድም-እህቶቻችን ጀርባ ላይ ያረፈ ምህረት የለሽ ብትር እንጂ፡፡ …ይህ ግን ለምን ሆነ? ጥያቄ ነው፡፡
ርግጥ ነው፣ እንዲህ አይነቱ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ መነሻ ሀገሩ ግን ሳውዲ አረቢያ ወይም ሊቢያ አይደለም፤ እዚሁ ኢትዮጵያችን ምድር ላይ እንጂ…
ዘ-ፍጥረት…
የየካቲቱ አብዮት ድንብዥታ (ሀንግኦቭር) ዛሬም ድረስ ዘመን ተጋሪዎቼን እያሳደደና እያሰደደ ይገኛል፡፡ ያኔ ያ ትውልድ ‹ኑ እንነሳ፣ ከተማውን እንውረር፤ አሮጌውንም ቅፅር በጩኸት አፍርሰን፣ አዲሱን እንፍጠር!› የሚል መለከት መንፋቱ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ባይሆንም ‹የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ጥቂቶች› እንዲል መፅሀፉ፣ እፍኝ ለማይሞሉ ‹ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖች› የተናጠል አሸናፊነት፣ የወል ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ? ስለተከሰተው ታሪክ ይሆናል መልሱ፡፡ በርግጥም ‹ፓርቲ› የሚባል የ‹ጦስ ዶሮ› ባነበረው ልዩነት በጥይት ደብድበው ሲያበቁ፣ አፈር ፈጭቶ፣ ውሃ ተራጭቶ ባደገበት መንደር እንደ መናኛ በየመንገዱ አስጥቶ ማዋል፣ ለግብዓተ መሬቱ የጥይት ዋጋ ማስከፈል፣ ወላጆችን እርም መከልከል… ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣ ኖሯል? …ከተኛበት አልጋ እያነቁ መስቀል፣ ከገሀነም በከፋው ቅጣት ‹ወፌ-ላላ› ገልብጦ ማሰቃየት፣ በአንድ ጉድጓድ ስልሳውን አነባብሮ መቅበር… ከዚህ ሌላ ምን ሊያስገኝ ኖሯል? …የሆነውም ይህ ነበር፡፡ እነሆም ያ ትውልድ የፀነሰው የተገነባውን መናድ፣ የተሰራውን ማፍረስ፣ በራስ ወገን ላይ መከራ ማዝነብን የሚመክረው የዘ-ፍጥረት መፅሀፍ ምዕራፍ እዚህ ጋ ነበረ የጀመረው፡፡
አዲስ ታሪክ አልተሰራም!
‹አዲስ ንጉስ እንጂ፣ ለውጥ መቼ መጣ!› እንዳለው ከያኒው፣ ታጋዮቹ በወታደሮቹ ቦታ ከተቀመጡ በኋላ የነበረው-እንደነበረው ነው የቀጠለው፤ ‹ባለሙያ› ገራፊዎች በአሸናፊዎቹ ከመተካታቸው በቀር፣ ማሰቃያ ጎሮኖቹ ዛሬም ወደ ሙዚየምነት አልተቀየሩም፣ መገረፊያው፣ መገልበጫው፣ መግደያው፣ መጋዣው… አሁንም የቀድሞውን ግልጋሎታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ማን ያውቃል? ነገም በዚሁ ይቀጥሉ ይሆናል፤ ለአጎራባች መንደሮች መቀጣጫ በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣ የአማፅያን ኮሽታ የተሰማበትን መንደር ሁሉ ዶግ አመድ ማድረግም፣ የጄነራሎቻችን የጦር ‹ጠበብ›ነት መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፤ በሀውዜን፣ አርባ ጉጉ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ አዋሳ፣ ኦጋዴን፣ ቀብሪ-ደሀር፣ ደገ-ሀቡር… የፈሰሰው የግፉአን ደም፣ የተከሰከሰው የንፁሀን አጥንት ታሪክ ነጋሪ ጥቁር ሀውልት መሆኑን ማን ይክዳል? ይህንን ሁሉ ምድራዊ ፍዳ፣ ዓለም እንደ ማንኛውም አሳዛኝ ዜና ሰማው እንጂ፣ ሰለባዎቹን ለመታደግ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ አልነበረም፤ በራስ መንግስት፣ በራስ ወገን መናቅ፣ ክብር መነፈግ፣ ለ‹ምርኮኛ ሕግ› ማደር… ክፋቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ የዛሬዎቹ አረቦቹም በወገኖቻችን ላይ የጭካኔ እጃቸውን እንዲያነሱ የልብ ልብ የሰጣቸው፣ ይኸው የእኛው የእርስ በእርስ አለመደጋገፍና አለመከባበር ነው፡፡ ትላንትና በጉራ ፈርዳና ቤንች ማጂ ዞን ጎሳ መመዘኛ ሆኖ ‹ውጡ የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም› በሚል በገዛ ወገኖቻቸው እንደጠላት ሀገር ሰው በጦር መሳሪያ ተከበው፣ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው ስለተባረሩ ኢትዮጵውያኖች፣ የሰሙ አረቦች ‹ሳወዲያ አረቢያን ልቀቁና ውጡ› ብለው ይህ አይነቱን መዓት ቢያወርዱ ምን ይደንቃል? የባዕድ ሀገር ሰው የትንኝ ነፍስ ያህል እንኳ ሳይጨነቅ እንደዘበት ህይወታችንን ቢነጥቀን በእርሱ ላይ መፍረድ እንዴት ይቻለናል? አሳልፈው የሰጡን እነማን ሊሆኑ ነው?
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
እመነኝ፣ በሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች የሰው ራስ ቅል እንደ በግ በመጥረቢያ ሲከሰከስ፣ እንደ ጦስ ዶሮ ተጋድሞ ሲታረድ፣ በቁሙ እሳት ሲለቀቅበት፣ ህፃናት የወታደር መለዮ በለበሱ አረመኔዎች ሲረገጡ… ልብህ እያለቀሰ፣ ፊትህ በእንባ እየታጠበ ያየኸው አይነት ጭካኔ ምንጩ ይህ ነው፤ ይህም ነው የኢትዮጵያን ሰው በአልባሌ ምክንያት መግደል፣ እያፏጩ ጉዞን የመቀጠል ያህል ያቀለለው፤ ለዚህም ነው በሙስሊሞች ቅድስቲቷ መዲና ላይ በድንጋጤ የጨው አምድ የሆነ አካለ-ቁመና፣ በሽብር ተውጣ አቅሏን የሳተች እህት፣ ስጋት ያናጠበው ወንድም ተመልክተህ በሀዘን የተቆራመድከው፤ ‹‹ወይኔ ወገኔ!›› ብለህ ደም እንባ የተራጨኸው፡፡ …እናስ! ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተመጣጣኝ ዋጋ መክፈል ያለበት ማን ነው? ንጉሥ አብደላና ዕኩይ ተከታዮቹ ብቻ? ወይስ እንዲህ የፊጥኝ አስሮ ለአረብ ሀገራት መቀለጃ የዳረገህ መንግስትህም ጭምር?
ከችጋርና ጭቆና ያልተፋታ ሕዝብ ዳቦና ነፃነት ፍለጋ እግሩ ወዳደረሰው ሀገር ተሰዶ መኖሩ በእኛ የተጀመረ አይደለም፤ እንዲያውም ስደተኞችን ካስተናገዱ ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀሰው የእኛዋ የአቢሲኒያ ምድር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የሩቁን ትተን እስከ የኃ/ስላሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን ተጨባጭ ሁነት ብንመለከት እንኳ፣ ‹አረብ ቤት› በሚል ተቀፅላ የሚታወቁት ብዙዎቹ ሱቆችና የንግድ መደብሮች፣ በስደት መጥተው እኩል እንደ ዜጋ ሀገራችን መኖር በቻሉ አረቦች የተያዙ ነበሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህች ገናና ሀገር ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦች የነፃነትና የክብር ተምሳሌትም ነበረች፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በፈሪሐ እግዚአብሔርነቷ፣ በፍትሐዊነቷና በርትዓዊነቷ ስሟ ተደጋግሞ የተወሳና የተመሰከረላት፣ የታላቅ ሕዝብ ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ ማዕድን በልፅጋ የሀበሻ ስደተኞች መናኸሪያ ለመሆን በበቃችው ሳውዲ አረቢያ የተወለዱት ነብዩ መሀመድ የዛሬ 1400 ዓመታት ገደማ በስደት መጠለያነት የመረጧት፣ ሀገሪቷም ተከታዮቻቸውን እጇን ዘርግታ በመቀበል ከራሷ ዜጋ እኩል ተንከባክባ ያኖረቻቸው ስልጡን ሀገር ነበረች፡፡ ማን ነበረ ‹ወርቅ ላበደረ…› ያለው? እነሆም ዘመኑ ተቀያየረና ‹‹የኋላኞቹ ፊተኞች፣ የፊተኞቹ ኋለኞች›› ይሆኑ ዘንድ ግድ በማለቱ ዛሬ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራ ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እየተጎነፀፉ ሲመጡ፣ እኛ የኋሊት ተንሸራተን ቁልቁል ለመውረድ በቃን፡፡
ምንም እንኳ እነዛ ሁሉ መልካም መገለጫዎቻችን ዛሬም ድረስ ባናጣቸውም፣ በብሔር ክፍፍልና በእርስ በእርስ ሹኩቻ የተነሳ ግን በደህነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቀን፣ እኛም በተራችን መሰደድ ዕጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ወጣት በሀገሩ የመኖር ተስፋው በመሟጠጡ፣ በስደት ወጀብ የሚንገላታ፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ሲናወዝ መሽቶ የሚነጋለት ብኩን ሆኗል፡፡ በሀገሩ እጅግ ከመመረሩም የተነሳ ራሱን ለሻርክ ጥርስ፣ ለእንግልት፣ ለግርፊያና ለበልዓ-ሰቦች አሳልፎ እስከ መስጠት በሚያደርሰው የስደት ጉዞ ለማለፍ የማያመነታ ትውልድ ለመሆን ተገዷል፡፡ ይህ ከድህነት ወለል ስር ያሳደረን የዘመን ግርሻ፣ ይህ ከመንግስት ጋር አይንና ናጫ ያደረገን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ለዚህ ሁሉ አሳረ-መከራ ዳርጎን፣ ከሀፍረት ጋር አንገታችንን እስደፋን… ውለታን ከማስረሳቱም በላይ ለከፋ በደል አጋልጦ ቁጭት አስታቀፈን፡፡
ሰሞኑን ‹‹የበላችበትን ወጪት…›› ከሰበረችው ሳውዲ አረቢያ የተሰማው አሰቃቂ ዜናም የእዚህ የኢትዮጵያን ስደተኞች ተከታታይ ፍዳ ጉትያ ነው፡፡ እርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት መሬቱ ሰለጠነ እንጂ ሕዝቡ ገና ጨለማ ዘመን ውስጥ ነው፤ ሌላ ሌላውን ወደጎን ብለን የሰሞኑን አውሬአዊ ባህሪያቸው እንኳን እንደ አይነተኛ ማሳያ ልንወስደው እንችላለን፤ ይህ ድርጊትም እንሰሳዊ ባህሪያቸው የስነ-ዝግመት ለውጥን ገና አለማገባደዱን ያመለከተ ነው፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ፣ ያውም ሀገራቸውንና ዙፋናቸውን በጦር ኃይል ለመንጠቅ የጎመዠችው ሮም ያዘመተቻቸው ወታደሮች፣ እልፍ አእላፍ ሠራዊታቸውን ፈጅተው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸው የሆኑ የጦር አበጋዞቻቸውን ገድለው የማታ ማታ የሽንፈትን ፅዋ አስጎንጭተው ከማረኳቸው በኋላ በርህራሄ ተንከባክበው እንደያዟቸው የዓለም ታሪክ ያውቀዋል፡፡
በሀገሩ ኑሮ አልቃና ብሎት፣ በሰው ምድር የሰው አደፋ አፅድቶ፣ ቆሻሻ ለቅሞ… ፋታ የማይሰጠውን የእህል ውሃ ጥያቄ ለመሙላት በማሰነ፣ ሆድቃን በሳንጃ መዘርገፍና የዱር አውሬ እንኳ የማይፈፅመው የጋርዮሽ ሴት ደፈራ መፈፀም… ምን አይነት ‹ኢብሊሳዊ› (ሠይጣናዊ) ተግባር ነው? የተቸነፈን መልሶ ማቸነፍ፣ የወደቀን መርገጥስ ‹ከመክፈር› (ፈጣሪን ከመካድ) በምን ይለያል?
አሁንም እደግመዋለሁ፡- ይህ ፖለቲካ አይደለም፤ እየፈሰሰ ስላለ የንፁሀን ደም፣ የወላድ መሀን ስለሆኑ እናቶች፣ ጧሪ ቀባሪ ስላጡ የተራቡ አባቶች፣ አሳዳጊ አልባ ስለሆኑ ህፃናት፣ ያለሚስት ስለቀሩ አባወራዎች፣ ባላቸውን ስለተነጠቁ የቤት እመቤቶች … የሰቆቃ እሪታ ነው፡፡ በወጡበት ሰው ሀገር ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ ወገኖቻችን ዋጋ ስለመጠየቅ ነው፤ ለነጋዴው መንግስታችን ኢትዮጵያዊው ዜጋ ዋጋው ስንት እንደሆነ የመሞገት ጉዳይ ነው፡፡
ሀገር ማለት…
ሀገር ምን ማለት ነው? ‹ሀገር› የሚለውን ቃል የኢህአዴግ መራሹ-መንግስት መዝገበ ቃላት ምን ፍቺ ሰጥቶት ይሆን? ሉዓላዊነትስ በ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ቀዩ መፅሀፍ አንደምታው ምን ይሆን? …ቀለብ ሰፍረን የምናሳድረውን ሠራዊት ሞቋዶሾ ድረስ ልኮ፣ የባራክ ኦባማን ስጋት ማቃለል? በ‹ተባበሩት መንግስታት› ስም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳናዊያን የውስጥ ችግር ላይ-ታች እንዲማስን ማድረግ? የሕዝብ ደህንነት መ/ቤትስ ኃላፊነቱ የእናንተንና የቅምጦቻችሁን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ ነውን? የአምባሳደሮቻችን የሥራ ድርሻ ፓስፖርት ማደስና የመግቢያ ፍቃድ መስጠት ብቻ ነው? በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ‹ጊንጥ ሰላይ› መሆን? ቦንድ መሸጥ? ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› እያሉ መስበክ? …ወይስ የዜጎችንም ደህንነት መከታተልና መጠበቅንም ጭምር? …ይህ ነው የወቅቱ ዓብይ ጥያቄ፡፡
የዲፕሎማሲ ግንኙነትስ ምን ማለት ነው? አገዛዙ በአንድ ወቅት ተቀማጭነቱ ኳታር-ዶሀ የሆነው ‹አልጄዚራ› ቴሌቪዥን ‹ስሜን አጠፋ› በሚል የኳታርን ኢምባሲ እንደ ዘጋው አይነት ስራን ብቻ የሚመለከት ይሆን? ከዋነኞቹ ለጋሽ ሀገራት በግንባር ቀደምነት የምትመደበው ኖርዌይስ ኢምባሲዋ የተዘጋው ለማን ትርፍ ነበር? ለብሔራዊ ጥቅም መቆርቆርስ ‹ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አልተከበረም› ብለው ዘገባ ባወጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያንን ሁሉ አቧራ ማስነሳት ይሆን?
ሌላው ቢቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለምን እንደ ተመሰረተ ይዘነጋል? አባቶቻችን ኮሪያና ኮንጎ ድረስ የዘመቱት ለዓለም ዜጎች ሰላም መሆኑስ እንዴት ይረሳል? የድርጅቱ አባል ሀገራት የፈረሙት ስምምነትስ የሳውዲ አረቢያን ሽፍትነት እንኳ ለመከላከል አቅም አይኖረውም? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እልፍ አእላፍ ወታደሮቻችን ካለቁብን በኋላ ከባረንቱ የተመለስነው፣ ባድሜ ላይ የቆምነው፣ በዛላንበሳ የታገድነው… የማንን ሕግ አክብረን ነበር? ያውም ‹በስለላ ስራ ሊሰማሩ ይችላሉ› ተብለው የተጠረጠሩ ኤርትራውያን እንዲያ በክብርና በእንክብካቤ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተሸኙት፣ በጦር ሜዳ የተሸነፈው ሻዕቢያ ተፈርቶ ነበር እንዴ? …ይህ ነው እንቆቅልሹ፡፡
ዛሬስ መንግስታችን የስደተኛ ዜጎችን ደህንነት በምልዓት የማይከታተለውና የድረሱልኝ ጩኸታቸውን ሰምቶ ፈጥኖ እጁን የማይዘረጋላቸው ለምን ይሆን? ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት? ወይስ በለመደው የንቀት መነፅር አይቶ እንዳላየ በቸልተኛነት አልፎት ነውን? በርግጥ ይህንን የበደል ማማ ካለፈው ታሪኩ አንፃር ከገመገምነው ምክንያቱ ሀገራዊ ስሜቱ ደካማና ከሥልጣኑ ሌላ ምንም የሚያሳስበው ነገር ባለመኖሩ ብቻ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሠማያዊ ፓርቲ የአረቦቹን ወደር የለሽ ጭካኔ ለማውገዝ በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በር አጠገብ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያገደው ‹ይህ አይነቱ ሀገራዊ መቆርቆር ነገ ደግሞ መስቀል አደባባይን በሕዝብ ሱናሚ ለማጥለቅለቅ መነቃቃት የሚፈጥር ገፊ ምክንያት ሊሆን ይችላል› ብሎ በስጋት ስለተጠፈነገ ይመስለኛል፡፡
የሆነው ሆኖ የመንግስት ህልውናም ሆነ አቅም በእንዲህ አይነቱ ወቅት ነውና የሚፈተነው ኢህአዴግም በዚህ ተግባሩ ዜጎቹን የመታደግ ገት እንዳሌለው አስመስክሯል፡፡ መቼም በሲ.አይ.ኤ ተላላኪነቱ በ‹ዋይት ሀውስ› ማህደረ-መዝገብ ውስጥ ከጊዜ ጊዜ እየዳጎሰ የመጣው የ‹ውለታ›ው ዶሴ ለእንዲህ አይነቱ ፈታኝ ወቅት መሆን ይሳነዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሳውዲ ነጋዴዎች፣ ሀገራችን ውስጥ በበርካታ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው አትርፈው ማደራቸው፣ በሰፋፊ እርሻዎች ዘርተው ማጨዳቸውስ እንደምን ተዘነጋ? ይህ ቢያንስ በነፍስ-ውጪ ነፍስ-ግቢ ለተያዙ ወገኖቻችን እንዴት የመደራደሪያ ጉልበት መፍጠር ሳይችል ቀረ? …በርግጥ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከጎራ ፈርዳ ስላፈናቀላቸው አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በተጠየቀበት ጊዜ ‹‹ደን ጨፍጫፊዎች ናቸው›› ሲል የስላቅ መልስ እንደሰጠው ሁሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም የሳውዲውን እልቂት በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ‹‹የማባረር ሥራው በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ተረድተናል›› በማለት መቀለዱ፣ ስርዓቱ ‹አስተዳድረዋለሁ› ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ሥልጣኑንና ተያይዘው የሚመጡ ጥቅሞቹን በዜጎች ሕይወት ጭምር ተደራድሮ ከማስከበር እንደማይመለስ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እንደ መንግስት በሀገር ሀብት እንደአሻው እየተምነሸነሸ፣ ‹ግዴታዬ የባቡር መንገድና ኮንዶሚንየም ቤት መስራት ብቻ ነው› ማለቱ ይህንኑ ይመሰክራል፡፡ አሊያማ ፋሺስቱ ጣሊያን እንዲያ በርካታ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ ቤቶች… ገንብቶ ሲያበቃ፣ ‹ሀገር› ማለት ሕዝብ የሰፈረበት ሉዓላዊ ግዛት ማለት ነው ተብሎ ያ ሁሉ መስዕዋትነት ተከፍሎ በኃይል እንዲባረር ባልተደረገ ነበር፡፡
‹ሕዝቤን ልቀቅ!›
በዘመነ-ኦሪት በግብፅ ዙፋን ላይ በተፈራረቁ ፈርኦኖች፣ ለባርነት የተዳረጉ ዕብራዊያንን ነፃ ያወጣ ዘንድ በፈጣሪ ተመርጦ የተላከው ሙሴ ‹‹እግዚአብሄር ‹ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!› ብሎሀል›› ማለቱ በቅዱሳት መፃህፍት መገለፁ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ራሱን ‹ኢህአዴግ› ሲል በሚጠራው ‹አምሳለ-ፈርኦን› ለመከራና ለሀፍረት የተዳረጉ ሕዝቦች አርነት ይጎናፀፉ ዘንድ ‹የሙሴ ያለህ!› የሚለው
ጩኸታቸው ከተራራ ተራራ እያስተጋባ መሆኑ ሌላ እውነታ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵውያን ደምም ዋይታ እየተበራከተ ነው፤ ስርዓቱ እንዲህ አይነቱ ሰቆቃን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመበት መሆኑንም ሰሞኑን የመንግስት እና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች የሚያሰራጩትን ዘገባ መመልከት በቂ ነው፡፡ መቼም መሬት ልሰው፣ አፈር ቅመው ያፈሩትን ንብረት ተነጥቀው፣ ባዶአቸውን እየተመለሱ ያሉ ስደተኞችን ‹በሀገራችን መስራት ይሻለን ነበር› እንዲሉ ማስገደድ ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ካልሆነ በቀር ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ አስከፊው ድህነታችን ጉርሻ እስከ መግዛት፣ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ቅልጥም እስከ መምጠጥ፣ የወደቀ ምግብ ከውሻ ጋር ተጋፍቶ እስከ መመገብ… በደረሰበት በዚህ የችጋር ዘመናችን ላይ በምን አመክንዮ፣ ከየትኛው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመዝኖ ሊታመን ይችላል ተብሎ ነው ‹ሀገር ውስጥ ሰርቶ በሰላም መኖር ይቻላል› የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነጋ-ጠባ የሚደሰኮረው? ምንድር ነውስ የሚሰራው? እዚህ እኛ ሀገር የማንን መፀዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቅ ይሆን የአረቦቹን ያህል ዳጎስ ያለ ክፍያ ማስገኘት ቀርቶ፣ በቀን ሁለቴ ለመብላት የሚያግደረድረው? ቅጥ አንባሩን ያጣው የግብር ፖሊሲያችን፣ እንጀራ ቸርቻሪዎችን ሳይቀር አሳድዶ የእለት ጉርሻቸውን እየነጠቀና በተንሰራፈው ድህነት ላይ ተጨማሪ እልቂት አውጆ ድሆችን ለማጥፋት ሰይፉን በሚያወናጭፍበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ እንዴት ብሎ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር ይችላል የሚባለው? ገና ጀንበር ከማዘቅዘቋ ጎዳናውን የሚያጥለቀልቁት ህፃናት ሴተኛ አዳሪዎችንስ ምን እንበላቸው? የትኛው ተቀጣሪስ ነው በደሞዙ የወር ቀለቡን ሳይሳቀቅ መሸመት የቻለው? …ሁላችንም የመዳፋችንን ያህል አብጠርጥረን የምናውቀው በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ይህ ነው፡፡
እነሆም በመጨረሻ እንዲህ ማለት ወደድኩ፡- ስርዓቱ ሰባኪው እንዳለው ‹የከንቱ ከንቱ፣ ከንቱ› ቢሆንም፣ አቶ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የመጀመሪያው የነፃነት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝቶ በአስመራ ሳባ ስታዲዮም ለተሰበሰበው ህዝብ በደርግ የደረሰባቸውን በደል በማስታወስ ‹‹በእናንተ ጀርባ ላይ ያለው ጠባሳ በእኛም ላይ አለ›› ሲል ሀዘኑንና መቆርቆሩን እንደገፀላቸው ሁሉ፣ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆናችሁ ወንድም-እህቶቼ ሆይ! የእናንተ ሰቆቃና በደል፣ በእኛም ግንባር ላይ ተቸክችኮ ሀፍረታችችንና ውድቀታችንን የጋራ እንዳደረገው የታሪክ ፍርድን መጠበቁ አይቀሬ ነው፡፡ እመኑኝ ያች ዕለትም አብረን የምንነሳበት፣ ከፍ ብለን የምንበርበት ትሆናለች፡፡›
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
በተለያዩ ከተሞች በራሳቸው፣ በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ስም 17 ቦታዎችንና ቤቶችን ይዘዋል ከሚለው ክስ ነፃ ሆነዋል፡፡
ከባለቤታቸው ጋር ምንጩ ያልታወቀ 490ሺ ብር በባንክ አንቀሳቅሰዋል ከሚለው ክስ ነፃ ናቸው ተብሏል:: የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ያረጋል አይሸሹም፤ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ከቀረቡባቸው አምስት ክሶች መካከል በአንዱ ብቻ “ጥፋተኛ ናቸው” የተባሉ ሲሆን፣ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አካብተዋል በሚል ከቀረበባቸው ክሶች ነፃ ሆኑ፡፡
አቶ ያረጋል አይሸሹም እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ሃብታሙ ሂካ፣ ከሁለት የግል ድርጅት ሃላፊዎች ከአቶ ጌዲዮን ደመቀና ከቶ አሰፋ ገበየ ጋር “ጥፋተኛ ናቸው” የሚል ውሳኔ የተላለፈባቸው፤ ለሦስት የትምህርት ተቋማት ግንባታ ከወጣው ጨረታ ጋር በተያያዘ ክስ ነው፡፡ ህገወጥ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር  ለመምህራን ኮሌጅ፣ ለአዳሪ ት/ቤት እና ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የግንባታ ጨረታ ከመንግስት መመሪያ ውጪ እንዲከናወን አድርገዋል በሚለው ክስ 4ቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው እንደተገኙ የከፍተኛው ፍ/ቤት ችሎት ሐሙስ እለት ገልጿል፡፡ 
አቶ ያረጋል እና አቶ ብርሃኑ ለተቋማቱ ግንባታ  የተመደበው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን እያወቁ በግልጽ ተወዳዳሪዎችን ጋብዘው ማጫረት ሲገባቸው፣ የሶስቱንም ፕሮጀክቶች የዲዛይን፣ የቁጥጥር እና የኮንትራት ጨረታ በህገወጥ መንገድ ለጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት በጥቅሉ በ250ሺህ ብር ሰጥተዋል ይላል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያቀረበው ክስ፡፡ አቶ ያረጋል ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም ጨረታዎቹ  አቶ ሃብታሙ በሚመሩት የትምህርት ቢሮ በኩል እንዲከናወኑ አድርገዋል የሚለው የኮሚሽኑ ክስ፣ መመሪያ ከሚፈቅደው ውጪ ስራው  በ “ውስን ጨረታ” እንዲከናወን በደብዳቤ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ብሏል፡፡  ለዚህ ወረታም አቶ ያረጋል ከ3ኛ ተከሳሽ ከአቶ ጌዲዮን ደመቀ፤ 50ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ሃብታሙ 75ሺህ ብር እጅ መንሻ መቀበላቸው በክሱ ተገልጿል፡፡
“ጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት” ፕሮጀክቶቹን የመምራት አቅም እንደሌለው እያወቁ ውል የፈረሙት አቶ ጌዲዮንና ወኪላቸው አቶ አሰፋ ገበየሁ፤ ስራውን ለ5 ዓመታት በማጓተት መንግስትን ለ2.8 ሚ.ብር ተጨማሪ ወጪ ዳርገዋል ብሏል - የፀረ ሙስና ኮሚሽን፡፡
ፍ/ቤቱም በአራቱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ባለስልጣናቱና ፕሮጀክቶቹን እንዲመራ የተደረገው አማካሪ ድርጅት፤ በህገወጥ የጥቅም ትስስር፣ የትምህርት ተቋማቱን ግንባታ ለሦስት ድርጅቶች ሰጥተዋል የሚለው ፀረ ሙስና ኮሚሽን፤ የሚመሩት “ጋድ ኮንስትራክሽን” በ40 ሚ. ብር የአዳሪ ት/ቤትና በ18ሚ ብር የመምህራን ኮሌጅ እንዲገነባ፣ አቶ መክብብ የሚመሩት ንብረት ለሆነው “ኮለን ኮንስትራክሽን” ደግሞ በ17 ሚ. የቴክኒክና ሙያ ተቋም እንዲገነባ በመስጠት ስራው አጓትተዋል ብሏል፡፡
አቶ ያረጋል አይሸሹም ከዚህ ክስ ነፃ መሆናቸውን ፍ/ቤቱ ገልፆ፣ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና አራቱ የግል ድርጅት ሃላፊዎች ግን ጥፋተኛ ናቸው በማለት ወስኗል፡፡
ሌላኛው ክስ፣ አቶ ያረጋል፣ እንዲሁም የትምህርት ቢሮ ሃላፊውና ወንድማቸው ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አካብተዋል የሚል ነው፡፡
ርዕሠ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ደሞዛቸው 4500 ብር እንደነበረና ከዚያም  የፌደራል የህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲሠሩ 5670 ብር ደሞዝ ይከፈላቸው እንደነበረ የሚገልፀው የኮሚሽኑ ክስ፣ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ሃብት አካብተዋል በማለት ከሷቸዋል፡፡
አቶ ያረጋል በራሳቸው ስም በአዲስ አበባ በተለያዩ ከተሞች አራት ቦታዎችንና ቤት ይዘዋል የሚለው የክስ ዝርዝር፣ በባለቤታቸው ስም ደግሞ በ7 ሚሊየን ብር የሚገመት ሆቴልና ድርጅት እንዲሁም ስምንት ቦታ፣ የንግድ ሱቆችና ቤቶችን ቦታዎችን በተለያዩ ከተሞች ይዘዋል ይላል፡፡ በቤንሻንጉል ውስጥም በሁለት ልጆቻቸው ስምም 5 ቦታዎች ይዘዋል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ቅርንጫፎች በራሣቸው እናበባለቤታቸው ስም ከ490 ሺ ብር በላይ አንቀሳቅሰዋል ብሏል - ፀረ ሙስና ኮሚሽን፡፡
የባለስልጣናት ሃብት ምዝገባ ሲከናወን ሃብታቸውን ሙሉ በሙሉ አላሣወቁም የተባሉት አቶ ያረጋል፤ “ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አካብተዋል” የሚለውን ክስ በበቂ ማስረጃ መከላከል በመቻላቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ፍ/ቤቱ ወስኗል፡፡
የትምህርት ቢሮ ሃላፊውም እንዲሁ ከወንድማቸው ጋር ከተመሳሳይ ክስ ነፃ ሆነዋል፡፡ ፍ/ቤቱ በሁሉም ክሶች ላይ ውሳኔ ያስተላለፈበትን ባለ 170 ገጽ ትንተና በንባብ ለማሰማት ሁለት ቀን ፈጅቶበታል፡፡
የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠባቸው ክሶች ላይ ከከሳሽ እና ከተከሳሽ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለህዳር 26 ቀን ተቀጥሯል፡፡
Source: Addis Admass
(ተመስገን ደሳለኝ)
በረዥሙ የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ታሪክ፣ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ አንድም ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሁሉም መንግስታት የተወገዱት በአመፅ አሊያም በተፈጥሮ ሞት ነውና፡፡ በ1983 ዓ.ም ወርሃ ግንቦት በጠብ-መንጃ ኃይል ሥልጣን የተቆናጠጠው ኢህአዴግ-መራሹ መንግስትም ቢሆን፣ በቀድሞዎቹ ገዥዎች ‹የብረት ጫማ› ውስጥ ተከልሎና ተደላድሎ ዕለተ-ስንብቱን በመጠባበቅ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ ዕ
ለተ-ስንብቱ መቃረቡን የሚጠቁመው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልክ እንደ ደርግ የመጨረሻዎቹ ወራት ሁሉ፣ ግንባሩና አጋር ፓርቲዎቹ ለየት ባለ መልኩ በራሳቸውና በሹማምንቶቻቸው ላይ በአደባባይ የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት መጀመራቸው ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም ይህ ነውና ተጨባጭ እውነታውን ለማብራራት በቂ የሆኑ አስረጂዎችን በአዲስ መስመር በዝርዝር ለመመልከት እሞክራለሁ፡፡

አስረጅ አንድ
በ2005 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዓመታዊ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ባቀረበበት ወቅት ከአገዛዙ የተለየ ድምፅ የተሰማው እንደ ወትሮው ሁሉ፣ በም/ቤቱ ተቃዋሚ ፓርቲን ከወከለው ‹አንድ ለእናቱ› አቶ ግርማ ሰይፉ ብቻ አይደለም፤ ኢህአዴግ በአምሳሉ ከፈጠራቸው አጋር ፓርቲዎችም ጭምር እንጂ፡፡
በዕለቱ ሚንስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በመንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን አስመልክቶ ‹አክራሪ› ካላቸው መነኮሳትና ‹ጥቂት› መዕምናን ‹ግርግር የመፍጠር ሙከራ› ባለፈ የተከሰተ የጎላ ችግር አለመኖሩን በሪፖርቱ መጥቀሱን ተከትሎ የአፋር ክልል ተወካዩ በአጋርነት ያነበረውን ስርዓት እንዲህ ሲል ነበር የተቸው፡-
‹‹ለፋብሪካው ግንባታ ተብሎ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዲሰፍሩ የተደረገበት ቦታ ውሃና መብራት ያሌለው ነው፤ ይህ ለምን ሆነ? ብለን ስንጠይቅ ‹ድሮም የነበሩበት ቦታ መብራትና ውሃ የለውም› በማለት ይመልሱልናል፡፡ በአጠቃላይ በአፋርና አካባቢው በሪፖርቱ ያልተካተቱ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡››
የሶማሌ ክልል ተወካይም በበኩሉ በዚሁ ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹የሰብዓዊ መብት አያያዝ›ን በተመለከተ አድበስብሶ ማለፉን የተቃወመው በሚከተለው አኳኋን ነበር፡-
‹‹በእኛ አካባቢ የሰብዓዊ መብት አይከበርም፤ ሰዎች ይገደላሉ፤ ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፡፡›› (በርግጥ በመልከዓ ምድር ለአካባቢው ከማንም በላይ የሚቀርበው የሀረሪው ተወካይ ብዙውን ጊዜ በምክር ቤቱ ስለማይገኝ በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ቅሬታ ይኑረው ድጋፍ ማወቅ አልተቻለም)
አስረጅ ሁለት
ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቦይ ስብሃት ነጋ፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለውጭ፣ መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የዓመቱን በጀት ለማፀደቅ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ጋር ተግባብተው መስራት አለመቻላቸውን በግልፅ ተናግረዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የተመሰረተበት አቢይ ዓላማ ‹‹የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በሚያስገኘው ውጤት ዙሪያ ጥልቅ ጥናት ለማካሄድ›› መሆኑ ቢታወቅም፣ ውጭ ጉዳይ ‹‹ይህንን አጥኑልን›› ብሎም ሆነ አቅጣጫ አሳይቶ እንደማያውቅ ከረር ባለ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት የበጀተለትን ይህንን ተቋም በኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ በዶ/ር ክንፈ አብርሃ ህልፈት ማግስት የተሾሙት አቦይ ስብሃት፣ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ፡- ‹‹ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ የተቀመጠለትን ዓላማ ከማስፈፀም አኳያ ቀደም ሲልም አልነበረም፤ አሁንም የለም›› ማለታቸው የሚያመላክተው የስርዓቱን ዝቅጠት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በአንድ ፓርቲና በተመሳሳይ ርዕዮተ-ዓለም የሚመሩት መንግስታዊ ተቋማትም እንኳ እርስ በእርስ ተግባብተው መስራት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም ጭምር ነው፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
አቦይ ስብሃት በመደምደሚያቸው ላይ ለችግሩ ተጠያቂ አድርገው ያቀረቡት (ምንም እንኳ ምክንያቱን ዘርዝረው ባያብራሩትም) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በራሱ በኢንስቲትዩቱ መካከል ሰፊ ክፍተት መፈጠሩን ነው፡፡ ኢህአዴግ ተቋሙን አዛዥ-ናዛዥ እንዲሆኑበት ለእሳቸው አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት፣ በጀቱ የሚሸፈነው በዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እንደነበረ ይታወሳል (በነገራችን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ከሌሎች አክራሪ የህወሓት ታጋዮች የሚለይበት መልካም ጎኖች ቢኖሩትም፣ በ‹ቲውተር ገፁ› የተሰማውን ሃሳብ የማንፀባረቅ ድፍረት ቢኖረውም፣ ከሙስና ጋር ገና እንዳልተላመደ ቢነገርለትም፣ ከሴራ ፖለቲካ የፀዳ፣ ከዘረኝነትም የነፃ ቢሆንም፣ ከ2007ቱ ምርጫ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ቢወራለትም… ከቁምነገር ይልቅ ወደማፌዙ ያመዘነ ይመስለኛል፡፡ ሌላው ቀርቶ በመካከለኛው ምስራቅ ምድራዊ ፍዳን እየተቀበሉ ያሉ እህት ወንድሞቻችንን ይታደግልናል ብለን ስንጠብቅ፣ ሰራተኞችን ሰብስቦ ‹ዛሬ… ልዩ… ልዩ… ቀን ነው…፣ ልዩ…› እያለ ሲዘፍን ይውላል፤ ብሔራዊ ዕርቅ ለመፍጠር ብርሃኑ ነጋንና ኦባንግ ሚቶን ይጠራል ብለን ስንጠብቅም አንገብጋቢ ባልሆነው ጉዳይ ገብቶ ኳስ ተጨዋች ሲጠራ ታይቷል)
አስረጅ ሶስት
መቼም አርብ ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የበጀት ዓመት ዕቅዱን ባቀረበበት ወቅት፣ ተጠባበቂ ዳይሬክተሩ አቶ ኃ/ማርያም አለምሰገድ በባለስልጣናቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ያደመጠ ሰው፣ ሀገሪቱ በገሃድ ከለየላቸው ‹ማፍዎች›ም በከፉ ስግብግብ ሹማምንት መዳፍ ስር መውደቋን ለመረዳት አይቸግረውም፡፡
‹‹አንዳንዱ ባለሥልጣን አስፓልት ይሰራልኝ ይላል፤ ይህንን በቃል ቢሆንም ለጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ነግረናል፤ ግማሹ እምነ-በረዱን አንሳልኝ ይላል፤ መፀዳጃ ቤቱ እንዲህ መሆን የለበትም የሚልም አይጠፋም፡፡ የኪራይ ቤቶች ቤት የተሰራው ከሰባ ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን ዱባይ እንዳዩት አዲስ አይነት ባኞ ቤት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ በግዥ እንጨናነቃለን፤ ይህ ካልተደረገ ያለውን የስልክ ጩኸት ለመግለፅ ይከብዳል፡፡››
ዳይሬክተሩ ከዚሁ ጋር አያይዞ እንደገለፀው ባለስልጣናቱ አንድ ነገር ሲበላሽ ስልክ ደውለው እንደሚያስፈራሩ፣ ቤቱን ለመንግስት እንዲያስረክቡ በሚጠየቁበትም ጊዜ የጦር መሳሪያ ታጥቀው ኤጀንሲው ቢሮ ድረስ በመምጣት በዛቻ እየፎከሩና እየሸለሉ ከህግ በላይ መሆናቸውን የሚያሳዩበት አጋጣሚ እጅግ በርካታ መሆኑን ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ከዚህ ስርዓት መቼም ቢሆን ታማኝ የሕዝብ አገልጋይ ተቋም ማግኘት እንደማይቻል አስበን በተስፋ መቁረጥ እንድንሞላ የሚያደርገን አሳዛኙ ነገር ደግሞ፣ ኤጀንሲው ይህ አይነቱ ወሮበላነት ከሙስና ጋር ይያዛል በሚል ለኮሚሽኑ ኃላፊዎች ባሳወቀበት ጊዜ የተሰጠውን ምላሽ ስንሰማ ነው፡-
‹‹ከሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋርም በጋራ ጠንካራ ሥራ ለመስራት እንፈልጋለን፤ ነገር ግን እነርሱንም ስናማክራቸው የራሳቸው የቤት ፍላጎት አላቸው፤ እናም ቤት ይሰጠን፣ ቤቱን በስማችን አድርጉልን እና ሌሎችም ጥያቄዎች እያቀረቡ ነው፡፡ ስለዚህም መጀመሪያ እነርሱም መስመራቸውን ሊያጠሩት ይገባል፡፡››
ጉዳዩን በሕግም ለመፍታት እንዳልተቻለ በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው፡- ‹‹ፍርድ ቤትም ቤቱን አንለቅም ከሚሉት ሰዎች በላይ ለእነርሱ እየተከራከረ ነው›› በማለት ነው፡፡
አስረጅ አራት
ብዙ የተወራለት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዋና አካል ሆኖ በ2002 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመው ‹‹የብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ልማት ኢንስቲትዩት››ንም በተመለከተ ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ዳይሬክተሩ አቶ ደሳለኝ ወርቅነህ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ባቀረበበት ወቅት፣ ስራዎቹ ከተጠበቀው በታች ከመሆኑም በላይ የማስፈፀም ብቃት ማነስና የአመራሩ አቅም አስተማማኝ አለመሆኑ እንደ ዋነኛ ችግር ተገልጿል፡፡
ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አስመልክቶ በተካሄደው ውይይት ላይም የቀረበው መደምደሚያ ተስፋ አስቆራጭ ነው፤ እንዲሁም ጥቅምት 27 የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ መንግስት ‹‹ልዩ ድጋፍ አደርግላቸዋለሁ›› ከሚላቸው አፋር፣ ቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ሀረሪ ክልሎች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በርካታ ችግሮችና ድክመቶች የተጠቀሱበት ከመሆኑም በላይ ኃላፊነቱን መወጣት አለመቻሉ የማያስተባብለው ጥፋት ሆኖ ቀርቦበታል፡፡
ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ.ም የሩብ ዓመት አፈፃፀሞቻቸውን ያቀረቡት ‹‹የህዝብ እንባ ጠባቂ››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን››፣ ‹‹የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ›› እና ‹‹የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት››ም በተመሳሳይ መልኩ በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ተውስቷል፡፡ በተለይ ማሪታየም ‹‹የስትራቴጂክ ዕቅድ የሌለው፣ የተገልጋይ ቅሬታን የማያስተናግድ፣ የትራንስፖርት ክፍያዎችን በወቅቱ የማይከፍል፣ ክፍት የስራ ቦታዎችን የማይሞላ፣ ዕቃዎችን ከወደብና ተርሚናል በጊዜ እንዲነሱ የማይጥር…›› እና የመሳሰሉት ችግሮች የተጠቀሱበት ሲሆን፤ መስሪያ ቤቱ ያቀረበው ሪፖርትም አሉታዊ ጎኑ እንደሚያመዝን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገምግመዋል፡፡
የሆነው ሆኖ በዕለቱ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃና በሪፖርታቸው ላይ፡- ‹‹በ2007ቱ ምርጫ ዘመናዊና ልዩ የድምፅ አሰጣጥ ዘዴን በመተግበር ሁሉም ለምርጫ የደረሱ የአገሪቱ ዜጎች ተሳታፊ እንዲሆኑ አደርጋለሁ›› ያሉት በግልፅ ተብራርቶ የቀረበ ባለመሆኑ ምን ለማለት እንደተፈለገ ለመረዳት ያዳግታል (መቼም ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› ከሚሉ አማኝ ሹማምንት አንዱ የሆኑት እኚህ ፕሮፌሰር የሚመሩት ምርጫ ቦርድና ገዥው ፓርቲ ‹ሰምና ወርቅ› ሆነው ከዚህ ቀደም የ‹ድምፅ ካርድ›ን ከኮሮጆ የሚመነትፉበትን አስማታዊ ጥበብ፣ በሚቀጥለው ምርጫ ከመራጭ ኪስ ወደመስረቅ ለማሳደግ እየተጋን ነው ቢሉም አይደንቅም)
አስረጅ አምስት
ጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ‹‹ሀገራዊ የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ መድረክ›› በሚል ርዕስ በተካሄደ ውይይት ላይ ፍትህ፣ ንግድ፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ እና የከተማ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መ/ቤቶች-በሚኒስትሮቻቸው፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በዳይሬክተሩ አማካኝነት ሪፖርት ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡
በዚህ መድረክ በተለይም በራሱ በፍትህ ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዩ አንደበት የተገለፀው ችግር ‹በሀገሪቱ መንግስት የለም› ወደሚል ጠርዝ ይገፋል፡፡ እነበረከት ስምዖንና አባይ ፀሀዬ መርጠው የሾሙት ሚንስትር ‹‹የፍትህ ስርዓቱ አድሎኛ፣ የማይታመን፣ ቅንነት የጎደለው፣ በትውውቅ የሚሰራ፣ በብሔር የሚያደላ፣ በሙስና የተተበተበ…›› መሆኑን (ያውም እነርሱም ከፊት ወንበር በተኮለኮሉበት አዳራሽ) በግልፅ እየመሰከረ ባለበት ሁኔታ ‹ሀገር እያስተዳደርን ነው› ሊሉ አይችሉም፤ ባይሆን በሀገሪቱ ሀብት ‹ቤተሰቦቻችንንና ዘመድ አዝማዶቻችንን እያስተዳደርንበት ነው› ቢሉን፣ ቢያንስ ለግልፅነታቸው ፅዋችንን ከፍ እናደርግላቸው ነበር፡፡
የፍትህ ሚኒስትሩ በየቦታው በአሰቃቂ ሁኔታ ስለታጎሩ እስረኞች የተናገረውም፣ እንኳንስ የወገኖቹ ሰቆቃ የሚያሳምመውን ተቆርቋሪ ዜጋ ቀርቶ፣ ልበ-ደንዳናውንም ቢሆን በስቃይ ‹መስቀል› የሚቸነክር መራራ እውነታ ነው፡-
‹‹በሕግ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ተጠርጣሪዎች ላይ፣ በአንዳንድ ፖሊሶችና መርማሪዎች አማካኝነት መረጃ ለማግኘት በሚል ድብደባ ይፈፀምባቸዋል፤ ታሳሪዎች ንፁህ የማረፊያ ቦታ፣ ህክምናና ጥሩ ምግብ አያገኙም፤ በአንዳንድ ቦታዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትም አለ፡፡››
በርግጥ ሚኒስትሩ እንዲህ በግልፅ ከማመኑ ከዓመታት በፊት እኛ ኢትዮጵያውያን ቀርቶ፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ደጋግሞ ብሎ፣ ብሎ የሰለቸው ጉዳይ ነው፤ ይህ በርካታ ተጨባጭ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚቻልበት ትልቁ የመንግስት ጥፋትም ይመስለኛል፤ የእስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ከቤተሰብ ውጪ ሌላ ጠያቂ መከልከል፣ የርዕዮት አለሙ የህክምና እርዳታ መነፈግ፣ የአቡበከር መሀመድና ውብሸት ታዬ በመርማሪ ፖሊሶች መደብደብ፣ በበቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳ ላይ የተፈፀመውን ሥቅየት (ቶርቸር) መጥቀሱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡
ሌላው ድንጋጤ ውስጥ የሚከተው በወንጀል ምርመራ፣ በክስ አዘገጃጀትና በችሎት ክርክር ላይ የሚሳተፉ መርማሪዎችና ዓቃቢያን ሕጎች ያለባቸው የዕውቀት ማነስ፣ የአመለካከትና የሥነ-ምግባር ችግር መጠቀሱ ነው (መቼም በሽብርተኝነት በተፈረጁ ድርጅቶች ስም እያመኻኙ በሀሰተኛ ክስ እልፍ አእላፍ ንፁሀን ዝነኛውን የቃሊቲ ወህኒ ቤት ጨምሮ በተለያዩ ማጎሪያዎች እንዲማቅቁ ከመደረግ የበለጠ ሌላ ዓይነተኛ ማረጋገጫ መፈለግ ያለብን አይመስለኝም) በአናቱም ሕዝብን በአገልጋይነት ስሜት በክብር አለማስተናገድ፣ ውሳኔን በፅሁፍ አለመግለፅ እና ሌሎች መሰል ችግሮች በሀገሪቱ መንሰራፋታቸው የፓርቲው ጉምቱ መሪዎች በተሰበሰቡበት ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
የውሃና መስኖ ኢነርጂ ሚንስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑም ያቀረባቸውን ችግሮች በጥሞና ላስተዋለ፣ ስርዓቱ ለመጪዎቹም 40 እና 50 ዓመታት እንኳ በስልጣኑ ቢቀጥል መፍትሄ የሚያገኝላቸው አይደሉም (እዚህች ጋ ፈገግታን የሚያጭር አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር፤ ይኸውም አቶ አለማየሁ የኤሌክትሪክ ኃይል ያላገኙ የሀገሪቱ ቀበሌዎችን መጥቀሱን ተከትሎ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረፅዮን
ገ/ሚካኤል፡- ‹‹አገልግሎት ያላገኙት ቀበሌዎች ሶስት ሺህ ናቸው ያልኩት ለማጠጋጋት ነው እንጂ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ናቸው›› የሚል ምላሽ መስጠቱ ነው፡፡ በርግጥ ኃ/ማርያም ደሳለኝም በጉዳዩ ላይ ያቀረበው መከራከሪያ እንዲሁ ተጨማሪ ሳቅ የሚፈጥር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡- ‹‹ከማንኛውም የአፍሪካ ሀገር በበለጠ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረብን ነው!››
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ደግሞ፣ መላኩ ፈንቴና ገብረሃዋድን ጨምሮ ዛሬም በሞቀ አልጋቸው ላይ ሚስቶቻቸውን አቅፈው በነፃነት የሚምነሸነሹ ባለሥልጣናት መጫወቻ የሆነውን የገቢዎች መስሪያ ቤትን አስመልክቶ በዋናነት ከዘረዘራቸው ጉድለቶች መሀል ‹‹አድርባይነት፣ ችግሮችን እያወቁ ከመፍታት ይልቅ በቸልተኝነት መተው፣ ቅን ያለመሆን፣ ግብር ከፋይን ማስበርገግ፣ ጫና ማድረግ፣ ማስፈራራት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት…›› ይጠቀሳሉ፡፡
አስረጅ ስድስት
እዚህ ጋ የማነሰው ጥቅምት 2006 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ከታተመው መንግስታዊው ‹‹ዘመን›› መፅሄት ጋር ቃለ-መጠይቅ ያደረጉ ባለሥልጣናትን ምስክርነት ነው፡፡
የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ የተጋነነውን የዋጋ ንረት ተከትሎ የተፈጠረውን የኑሮ ወድነትና የመንግስት ሰራተኛ ደመውዝ እንደማይጨመር መገለፁን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ‹‹ሁሉም ዜጋ ችግሩን ተቋቁሞ ነገ የሚመጣውንና አሁንም እየመጣ ያለውን የተሻለ ሁኔታ እንዲያይ ነው የሚፈለገው›› ሲል ከቀለደ በኋላ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ረገድ በርካታ ችግሮችና ድክመቶች መኖራቸውን፣ በአዲስ አበባ ከተማም የትራንስፖርት ችግር መኖሩን አልሸሸገም፤ አያይዞም፡-
‹‹በከተሞች አካባቢ ሰፊ የሥራ አጥነት ችግር አለ፤ መረጃው የሚያሳየንም እንደዚያ ነው፡፡ ከ17 በመቶ በላይ (ቁጥሩን ሆነ ብሎ አሳንሶታል) መስራት የሚፈልግ የከተማ ነዋሪ የሥራ ዕድል አላገኘም፡፡ በጣም ብዙ ኃይል ነው ይሄ›› ማለቱ ለስርዓቱ ፖሊሲዎችና ዕቅዶች መክሸፍ ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡
አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም የትውልድ ቦታው በሆነው ወለጋ የተንሰራፋውን ድህነት የገለፀው እንደሚከተለው ነበር፡-
‹‹…በሰብል በተለይ ገብስና ጥራጥሬ ከፍተኛ ምርት ሊሰጥ የሚችል አካባቢ ነው፡፡ የሰዉ የኑሮ ሁኔታ ግን የምጠብቀውን ያህል የሚያመረቃ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡››
የመፅሄቱ ሌላኛዋ እንግዳ የማዕከላዊ ስታስቲክና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያም በበኩሏ ‹‹እውነት እውነት የሚመስለኝ ሥራ ይሄ ነው›› ያለችበት አውድ፣ መንግስት ዛሬም ድረስ ለሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ራሱን የቻለ ምፀት ይመስለኛል፡፡
የመውጫው በር
ስርዓቱ ከሚመራው ህዝብም ሆነ ከምሁራን ዘንድ የሚሰነዘርበትን ድክመትና ችግሮች ለዓመታት ሲያጣጥል የቆየ ቢሆንም፣ እነሆ አሁን ግን በዚህ መልኩ በራሱ ሰዎች አንደበት አምኖ መቀበሉን ይፋ አድርጓል (በርግጥ ‹ተሳስቼአለሁ› ማለቱ ለለውጥ ተዘጋጅቶ ወይስ አንዳች ሊያስቀይስ ያሰበው ጉዳይ ስላለ? የሚለውን በሌላ ዕትም በስፋት እንፈትሸዋለን) አሁን ግን በብልሹ አስተዳደር ሳቢያ የተፈጠሩት እነዚህንና እነዚህን መሰል ችግሮችና ድክመቶች እስከ መቼ ነው የሚቀጥሉት? መፍትሄውስ ምንድር ነው? የሚለውን ጥያቄ በደምሳሳው ለመመለስ በቅድሚያ ከሀገራችን ታሪክ አንድ ምሳሌ ላቅርብ፡-
በ1910 ዓ.ም በንግስት ዘውዲቱና በልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ዘመን ‹ሚኒስትሮቹ በሀገሪቱ ላይ በደል እያደረሱ ነው› በሚል ህዝቡ በጃንሜዳ ተሰብስቦ ምክክር ካደረገ በኋላ ለአልጋ ወራሹ እንዲህ የሚል ደብዳቤ መፃፉን በ‹‹ዝክረ ነገር›› መፅሀፍ ውስጥ ተገልጿል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ልዑል ራስ ተፈሪ ሆይ፡-
እኛ ባሮችዎ የኢትዮጵያ ህዝብ በንግሥታችን በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ፣ በእርሶም በልዑል አልጋ ወራሻችን በኩል ተበድለናል፣ ተጎድተናል የምንለው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ታላቁ ንጉሥ ዳግማዊ ምኒሊክ ሕዝቤን ይጠብቁልኛል፣ የዠመርኩትን ሥራዬን
ይፈፅሙልኛል ሲሉ የሾሟቸው ሚኒስትሮች ራሳቸው ሕዝብ መበተን፣ አገራችንን ማጥፋት፣ አገርንና ገንዘብን ለራሳቸው መካፈልና ዕውቀትን ማጥፋት፣ ትምህርት መድፈን ሆነ እንጂ ለመንግስታችን የረዱት የጠቀሙት ነገር የለም፡፡ ስለዚህም ከመበደልና ከመገፋት፣ ከውርደትና ከመበሳጨት፣ ድኻው ከመዘረፉ መንግስታችን ካለመጠቀሙ የተነሳ ለንግሥታችንና ላልጋ ወራሻችን እናመለክታለን፡፡››
ልዑል ተፈሪ መኮንንም ሕዝቡ ላቀረበው ጥያቄ አርኪ መልስ ሰጡ፡-
‹‹…እንድጋ የሕዝቡ መሰብሰብ ምን ያኽል የሚያጎድል ይመስላችኋል? እንደዚሁ ባለ ምክንያት መስኮብን ያኽል ታላቅ መንግስት… ከተማው ባንድ ቀን ጠላቶች ገቡበት፤ ሰዋቸውም ተከፋፍሎ ርስ በርሱ ተላለቀ፤ አሁን እናንተ ሚኒስትሮች ይሻሩልን ማለታችሁ የተሾሙት ሰዎች ይሻሩልን ብላችሁ ነው እንጂ የተነሳችሁት፤ የበደላችሁ ሥራው አይደለም፡፡
‹‹…የመንግስት ኃይልና የሕዝብ ኃይል ትክክል ነው፡፡ አሁንም ለሹም ሽሩና ለሌላው ሥራ እኛም ብንጨርሰው፣ ሰው ከእኛም መካር አግኝተን ብንጨምር እንደ ሚያስፈልግ እያየን እናደርገዋለን፤ አሁን ያሉትን ሚኒስትሮች ግን ሽረንላችኋል፤ ይህነንም በዝግታ ብታሳውቁን እንደሚሆን አድርገን ሕዝቡም ተሰበሰበ ሳይባል እንጨርስላችሁ ነበር፡፡
መጋቢት ፲፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ተጻፈ፤ አዲስ አበበ ከተማ››
የልዑሉ ተፈሪ ምላሽ ሙሉ በሙሉ ለህዝብ መገዛትን ያሳያል፤ እንደሚታወሰው በወቅቱ ሕዝቡ ፈቅዶም ይሁን ተገዶ የንጉሠ ነገሥቱ ሹመት ‹ሠማያዊ ነው› የሚል እምነት ነበረው፤ ልዑሉም ‹የመንግስት ኃይል› ሲሉ የገለፁት ንጉሡንና ወራሾቹን እንደሆነ የሚሳት ነገር አይደለም፡፡ ስለዚህም እነርሱ ይሻራሉ ተብሎ አይጠበቅም፤ በግልባጩ ሚኒስትሮቹ የተሾሙት በንጉሠ ነገሥቱ በመሆኑ ሕዝባዊ ተቃውሞ በቀረበባቸው ጊዜ ‹የሕዝብ ኃይል ትክክል ነው› ብለው በሚሸነግሉ ነገሥታት እስከመሻር ይደርሳሉ፡፡
እነሆም ከመቶ ዓመታት በኋላም ይህ ጥያቄ መቅረቡ አልቀረም፤ በርግጥ ዛሬ ‹ሠማያዊ ሹመት› የተበላበት ማጭበርበሪያ ካርታ በመሆኑ፣ ‹መረጥከኝ› ለሚለው ዘመናዊ የ‹ዲሞክራሲ› ስርዓት ቦታውን ለቋል፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ ምድር ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሚያካሄደው ምርጫ ጊዜ ያለፈበት የማጭበርበሪያ ‹ካርታ› ለመሆኑ ብዙ ተብሎለታል፤ ምክንያቱም ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ እንደልጅነት ዘመን ‹‹ዳቦ ተቆረሰ፣ ጨዋታው ፈረሰ›› አይነት ስለመሆኑ በርካታ ማስረጃዎች ቀርቦበት በመላ ዓለም ዘንድ የታመነበት የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ቆይቷልና፡፡
በአናቱም የሚኒስትሮቹ ‹አለቃ› ኃይለማርያም ደሳለኝ ሕዝብ የተቃወማቸውን ቀርቶ፣ ራሳቸውም እንዲህ በአደባባይ ሥራው እንዳቃታቸው የተናገሩ ባለሥልጣናትን፣ የልዑል ተፈሪን ያህል ሥልጣን ኖሮት ‹ሽሬአቸዋለሁ› ሊል አይችልም፤ እነርሱም ቢሆኑ እንደሰለጠነው ዓለም መንግስት ሕዝብን ‹ይቅርታ› ጠይቀው ራሳቸውን ከኃላፊነት ያነሳሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እንዲያውም ሁሉም አይናቸውን በጨው አጥበው ለሚቀጥለው ምርጫ ሽር-ጉድ እያሉ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እንደቀደሙት ምርጫዎች ሁሉ ኢህአዴግ በዝረራ ማሸነፉን ሊያበስሩን (ሊሚያሳምኑን) ያሰፈሰፉ ‹ልማታዊ ጋዜጠኞች› እንኳ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው እንዲጠብቁ ከታዘዙ ሰነባብቷል፡፡ በዚህም የተነሳ ለህዝብ ብሶትና ጩኸት ጆሮ የሚሰጥ አንድ እንኳ አልተገኘም፡፡
እናም ቀሪው የመፍትሄ መንገድ አንድና አንድ ይመስለኛል፤ የኢትዮጵያን ‹ታህሪር› አደባባይ ፈልጎ ከሰማይ ከፍታ በላይ ጩኸትን በማስተጋባት ተራሮችን ማንቀጥቀጥ፣ ምድሪቷን ማራድ!
አስራት አብርሃም
የሳውዲ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ባለው ግድያ እና ግፍ ምክንያት በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰልፍ በመንግስት በእኩል ይሁንታ እንዳላገኘ ብንሰማም የሆነው ይሁን እነርሱ በሰው ሀገር መከራና ስቃይ እየተቀበሉ አይደለ በሚል ነው ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር ወደ ሰልፉ ለመሄድ የቆረጥነው። ችግር ሊኖር እንደሚችል ገምተናል።
ከሰማያዊ ፓርቲ ብርሀኑ ተክለያሬድ ጋር የት ደረሳችሁ እየተባባልን እየተደዋወልን ነበርና በመሀሉ ስልኩ ጠፋኝ። መጨረሻው ግን አራት ኪሎ እንደታገቱ ሰማንና እኔና ሌሎች ሶስት ጓደኞቼ ሆነን ወደ ሰልፉ ቦታ መሄድ ጀመርን። ከኋላችን ብዙ ሰው ቀስ እያለ እየመጣ ነበር። ወደ ሰልፉ እየተጠጋን ስንመጣ ብዙ ሰው ወደእኛ አከባቢ እየሸሸ ሲመጣ ተመለከትን። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወጣት ሴት ልጆች እያለቀሱ ወደ እኛ እየመጡ ነው። በዚህ ጊዜ እነ ዳዊት ከበደ፣ ኤልያሰ ገብሩ እና እስክንድር ፍሬው አግኝተናቸው ስለሁኔታው
ስንጠይቃቸው ፌደራል ፖሊሶች ሰልፉን በኃይል እየበተኑት መሆኑ፣ ብዙ ሰውም ክፉኛ እየተደበደበ መሆኑንና ሰውም እያፈሱ እንደሆነ ነገሩን። ፌደራል ፖሊስ ያገኘውን ሰው ሁሉ እየመታ እንደሆነና ወደኋላ መመለሱ እንደሚሻልም ነገሩን።
እስኪ ትንሽ ወደፊት ገፍተን የሚሆነውን እንይ ብለን ወደፊት ትንሽ እንደሄድን በፖሊስ የተያዙ የምናውቃቸው ልጆች አገኘንና ሰላም እንዳልናቸው እኛም በዚያው በቁጥጥር ስር ዋልንና ወደ አንድ ግቢ ውስጥ አስገቡን። እዚያ ትንሽ ካቆዩን በኋላ የፖሊስ መኪና አስመጥተው እያዳፉ እና እየተሳደቡ ጫኑን። አልጫንም ብሎ ያስቸገረ ሰው የለ! በዚያ ሰዓት ለምን እንደሚማቱና እንደሚሳደቡ ባስብ ባስብ ሊመጣልኝ አልቻለም። ለማንኛውም ዱላው እንዳረፈብን ፈጠን ፈጠን ብለን ተሳፈርን። ከኋላው በክፍቱ ነው የተጫንነው፤ ሶስት ፖሊሶችም ከእኛ ጋር ተጭነዋል፤ የተወሰኑ ደግሞ ከጋቤናና ከውስጥ ገቡ። ከዚያ በኋላ መኪናዋ ዋናውን መንገድ ትታ በመንደር ውስጥ ለውስጥ በፍጥነት እየበረረች ከፊት ያገኙት ሰው ሁሉ “ዞር! በል ዞር በል!” እያሉ አጣደፉት። በመንገድ ላይ የነበረው ሰዉ ሁሉ በድንጋጤ ወደ ጉድጓድም ወደ ገደልም እየዘለለ ገባ። አንዱ ግን ፈጠን ብሎ መሸሽ ባለመቻሉ ፖሊሰቹ እያዳፉ ከእኛ ጋር ቀላቀሉት።
ከእኛ ጋር ከተጫኑት ሶስት ፖሊሶች ውስጥ አንዱ አዛዥ ነው መሰል ሽጉጥ ታጥቋል። በጣም ተናዷልም። “አሁን በዚህ ቀዳዳ ተጠቅማችሁ መንግስት ልትጥሉ ነው አይደለ የፈለጋችሁት! የኢትዮጵያ ሰራዊት አንድ ባንድ ሞቶ ሁሉም ሳይልቅ ይሄ መንግስት አይወድቅም! ይሄ ህገ መንግስት እንዴት እንደመጣ ታውቃላችሁ?! አታውቁም! ስለማታውቁ ነው! ልብ ካላችሁ ጫካ አትገቡም! ፈሳም ሁላ!” ብዙ ብዙ እዚህ ለመግለፅ የሚከብዱኝ ስድቦች ሁሉ ይሳደባል። ከእርሱ ጋር የነበሩት ሌሎች ሁለት ፖሊሶች ደግሞ እርሱን ተከትለው ይሳደባሉ፤ እርሱ ሲማታም ተከትለው እንደሚማቱ ያወቀኩት ትንሽ ቆይቼ ነው። ቢያንስ አንድ ሰው ለመማታት ወይም ለመሳደብ ጊዜ እንኳ በራሴ ጊዜ አያስብም እንዴ! ስድቡ መቆሚያ አልነበረውም። በእውነቱ እኔ ይህ ሰው የህግ ሰው ነው ብዬ ለማሰብ ከበደኝ። ፍፁም በንዴትና በጥላቻ አቅሉን ስቷል።
በዚህ ጊዜ እኔ ያረጋገሁ መስሎኝ “አንተ ፖሊስ ነህ ቢያንስ የለበስከውን ልብስ እንኳ ማክበር አለብህ እኛ ሰልፍ ነው የወጣነው የፈፀምነው ወንጀል የለም። አሁን ደግሞ በህግ ቁጥጥር ውለን በሰላም እየሄድን ነው፤ ስድቡና ዱላው ለምን አስፈለገ? ይሄ እኮ ትርፍ ነገር ነው” ብዬ ተናግሬ ሳልጨርስ “ምን አባትህ ታመጣለህ?” ብሎ ሊማታ እጁን ሰነዘረ። እነዚያ ፖሊሶችም እርሱን ተከትለው እጃቸውን ሰነዘሩ። ፖሊሱ የሚችለውን ስድብ ሁሉ አወረደብኝ። ሁኔታው ስላልፈቀደለት እንጂ እንደ ደርግ ጊዜው አሰልፎ ቢረሽነን የሚጠላ አይመስልም። በትግራይ እንዲህ ዓይነቱ ሰው “ደርጊ” የሚል መጠርያ ነው የሚሰጠው። በእውነቱ እነም ይሄ ሰው “ደርጊ” ከሚል ቃል ሌላ የሚመጥነው ስም አላገኘሁለትም። በኋላ ከሌሎች ፖሊስ ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ ረዳት ሳጂን ክንፈ ነው የሚባለው፤ የአባቱን ስም ለማግኘት አልቻልኩም። የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ ነው። በግዕዝ ክንፈ ማለት ራሱን የቻለ ቃል አይደለም ሙሉ ለመሆን የሆነ ቅጥያ ያስፈልጋል። ብዙውን ጊዜ የመላዕክት ስም ነው የሚከተለው። ለምሳሌ ክንፈ ሚካኤል፣ ክንፈ ገብርኤል ወዘተ እየተባለ እንደሚጠራው ማለት ነው። የዚህ ሰው ስም ግን ከተግባሩ ተነስቼ ስገምት ክንፈ ሳጥናኤል መሆኑን አለበት። አሁን ይሄ ሰው ለምን እንደዚያ ያደርገዋል? ከፈለጋችሁ ጫካ ግቡ የሚለን የጫካ መንገድ ጠፍቶን እኮ አይደለም እዚያ የተገኘነው፤ የወገኖቻችን ሰቆቃና መከራ ሰምተን ዝም ብሎ መቀመጥ ስላለቻልን ቢያንስ እዚህ ካለው የሳውዲ ኤምባሲ ላይ ተገኝተን ድምፃችንን በማሰማትና አጋርነታችን ለማሳየት ነው እንጂ መንግስት ለመገልበጥ አይደለም ሰልፍ የወጣነው። ለመሆኑ የጫካው መንገድ ካለኢህአዴግ ሌላ የሚያቅው የለም እንዴ። ጫካ ቢገባ ያው የድሃ ልጅ ነው የሚሞተው፤ የድሃ እናት ናት የምታለቅሰው ብለን ነው እንጂ የጫከ መንገድ ጠፍቶኝ አይደለም። በኃይል የሚሆን ነገር የሰው ህይወት እና የንብረት ውድመት ስለሚያስከትል ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ዘላቂ ሰላም ስለማያስገኝ እንጂ መንገዱማ በጣም ቀላል ነው።
ደራሲ አስራት አብርሃም
አንዱ ፖሊስም “አሁን ተስልፋችሁ ምን አመጣችሁ?” ብሎናል ተደበደባሁ እንጂ የሚል ቅላፄ አለው ከአነጋገሩ። የሰልፉ አላማ እኮ መንግስት ለመገልበጥ አልነበረም። እንዲያውም ሰልፉማ ከታለመው በላይ ተሳክቷል። አንደኛ ለሳውዲ መንግስት ቁጣችን ለመግለፅ ነበር የፈለግነው እነርሱን ሆኖ የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲፋለምላቸው በቪድዮ ሁሉ ሲቀርፁ ነበር። ስለዚህ ፈደራል ፖሊስ ባይኖር ብለው ማሰባቸውና መስጋቸው አይቀርም። ስለዚህ ህዝቡ በሳወዲ ድርጊት ምን ያህል እንደተቆጣ መገንዘባቸው አይቀርም። ሁለተኛ ኢትዮጵያውያን ለሀገሩ የሚቆረቆር መንግስት እንደሌለን በድንብ ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ህዝብ በሰው ሀገርም በሀገሩም በፖሊስ የሚደበደብ የሚታሰርና የሚዋረድ መሆኑ ታይቷል። መንግስት የለንም ቢባል እንዴት ማጋነን ሊሆን ይችላል። መንግስት ቢኖረን ኖሮማ ቢያንስ እንደዚህ ሊሆን አይችልም ነበር።
እንዲያ እያዋገቡና እየሰደቡ ላንቻ በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስገቡን። እዚያ ቀድሞውን እዚያ ከደረሱ ሌሎች ሰልፈኞች ጋር ቀላቀሉን። ኢዮብ አራጋው የተባለ ልጅ መሬት ላይ ያጣጥራል። “ኧረ እባካችሁ አስቸኳይ ህክምና ያስፈልገዋልና ወደ ህክምና ውሰዱት” እያለ እዚያ የነበረ ሰው ሁሉ ይጨሀል። የሚገርመው ነገር አንዱ ፖሊስ “በመጀመርያ ቃሉ ይሰጥና ከዚያ በኋላ ወደ ህክምና ይሄዳል” አለ። በዚህ ጊዜ እንኳን ቃሉን ሊሰጥ በአጋባቡ እንኳ መተንፈስ አይችልም ነበር። በኋላ ከተወሰነ ቆይታ ልጁ ወደ ህክምና ተወሰደ። አንዴት የሰባ ዓመት እናት ከመንገድ ላይ አፍሰው እኛ ጋር አምጥተው ቀላቀሏቸው። ከዚያም አንዲት ልጅ “እማማ ምን ሆነው ነው?” አለቻቸው። “የሆንኩትንማ እናንተው ንገሩኝ እንጂ” ብለው በዚያ ጭንቅ ሰዓት ላይ አሳቁን። እናቷ ሞታባት ጥቁር የለብሰች ሁሉ ከመንገድ ታፍሳ መጥታለች። ወይዘሮ አዜብ መንስፍን እንኳን ያን ቀን በዚያ አላለፉ፤ ከእኛ ጋር ታሳሪ ይሁኑ ነበር፤ ቢያንስ ማንነታቸው እስኪጣራ ድረስ!
አንዴ በክፍለ ከተማ፣ ሌላ ጊዜ በፆታ እየከፋፈሉ ከቆጠሩን በኋላ አስራ አምስት የምንሆን ሰዎች ብቻ መርጠው ለብቻችን አውጥተው መርማሪዎች ቃል ወደ ሚቀበሉበት ክፍል በረንዳ ላይ ወስደው አስቀመጡን። እዚያ ቁጭ ብዬ ዙርያውን ቃኘሁት። ከፊት ለፊታች ካለው መስኮት ላይ በVECOD የተዘጋጀ “ጭጭ በል!” የሚል ርዕስ ያለው ፖስተር ተመለከትኩ፤ አባት ልጁን ሲገርፍ የሚያሳይ ስዕልም ከጎን ይታያል። ከዚያ ትንሽ ወረድ ብሎ ደግሞ “ቅጣት የበዛበትና በደሉን የማያሰማ ልጅ ነፃነቱን የሚያስከብር ዜጋ ሊሆን ይችላል?” የሚል ፅሁፍ ይነበባል። እርግጠኛ ነኝ ረዳት ሳጂን ክንፈ “ጭጭ በል!” ከሚለው ርዕስ በታች ያለውን ፅሁፍ ያየው ወይም ያነበበው አይመስለኝም። ሲያዩት በጣም ችኩል ሰው ይመስላል። ስለዚህ ይህን ለማንበብ የሚያስችለው ሰከን ያለ ቀልብ ስለሌለው ነው ሊያነበው የማይችለው። ትዕግስቱን እንዲሰጠው ብንፀልይለትስ! አሁን እንዲህ ያለ ሰው ከራሱ በስተቀር ማንን ሊወክል ይችላል! ግፋ ቢል ስርዓቱን ሊወክል ይችል ይሆናል፤ ለዚህም እርግጠኛ አይደለሁም፤ ምክንያቱም እዚያ በጣም ብዙ ፖሊሶች ነበሩ የእርሱ ግን ከሁሉም በጣም የተለየ ነው። በሆነ ጥላቻ በሆነ ስሜት ውስጥ ገብተዋል። ከራሱ ጋር ጠብ ከሌለው በስተቀር አንድ ሰው እንደዚያ ሊሆን አይችልም። በአብዛኞቹ ታሳሪዎች ዘንድ ግን ለእርሱ ስድብ ብዙም ቦታ የሰጠው ሰው አልነበረም። እንዳያያቸው ብቻ አጎንብሰው የሚስቁ ሁሉ ነበሩ፤ እኔ ነኝ እንጂ አዲስ የሆነብኝ እነርሱ ሁሌም ሲታሰሩ የሚባሉት ነገር መሆኑ በኋላ ላይ ነገሩኝ።
ወደሌላኛው ግድግዳ ስመለከት ደግሞ “ብልሁና ቁርጠኛው መሪያችን ቢለዩንም የተጀመሩትን የልማት ስራዎች በቁርጠኝነት እናስቀጥላለን” ይላል፤ ልማት የሚሉት ዜጎችን ማስርና ማንገላታት የሆን ብዬ እያሰብኩ ወደ ሌላኛው ግድግዳ ሳማትር ወደ አንዱ ከፍል መግቢያ ላይ “ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆኑ የአፍሪካ ኩራትና የቁርጥ ልጅ ናቸው” የሚል አገኘሁ። ነገሩን በደንብ ያልገባው አንባቢ “ይሄ ፅሁፍ ስለየትኛው ጠቅላይ ሚንስትር ነው የሚያወራው?” ብሎ መጠየቁ አይቀርም። “ንጉሱ እንዲህ አሉ ወይም እንዲህ አደረጉ” ሲባል ኃይለስላሌ መሆኑ በጣም ግልፅ ነው። ምክንያቱም ከእርሳቸው በኋላ ሌላ ሰው ስላልነገሰ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲል ግን ትንሽ ግር ይላል፤ ምክንያቱም አሁንም ጠቅላይ ሚንስተር አለ ተብሎ ነው ኃይለማርያም እያስተዳደሩ ያሉት። ወይስ የጠቅላይ ሚንስትርነት መዓርግ ለአቶ መለስ ብቻ ነው የተሰጠው። ለምሳሌ እኔ አንዱን ፖሊስ ጠርቼ “ይሄ ፅሁፍ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማለቱ ነው?” ብለው “አይደለም” እንደሚለኝ በጣም እርግጠኛ ነኝ፤ ቀጥዬ “አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራትና የቁርጥ ልጅ አይደሉም ማለት ነው” ብለው ግን መልስ የሚኖረው አይስለኝም፤ ምናልባት ረዳት ሳጂን ክንፈ ከሆነ የተጠየቀው፣ የስድብና የዱላ መልስ ይኖረው ይሆናል!
በመጨረሻ ኮንዶም መስጫ ሳጥን ከሚል የቆርቆሮ ሳጥን ላይ ዓይኔ አረፈ፤ ይሄ ጥሩ ነው ቢያንስ ለህይወታቸው ዋጋ ይሰጣሉ ማለት ነው አልኩ፤ በዚያም የሌላውን ህይወት ዋጋ መስጠት ቢማሩ እንዴት ጥሩ ነበር!
እዚህ ፖሊስ ጣቢያ እጅግ በጣም ካሰለቸን ነገር እያንዳንዱ ፖሊስ እየመጣ ስማቸን፣ አድራሻችን፣ የምንሰራበት ቦታ፣ ኃይማኖታችን ሁሉ ይጠይቁናል፤ ፆታችንም ያልጠየቁን እነርሱ ሆነው ነው! ከአስር በላይ ጊዜ ቃላችን ሰጥተናል። እኔማ ለመናገር ሁሉ እየደከመኝ መታወቀያዬን እየሰጠሁ ከዚያ እየገለበጡ የተወሰነውን ጥያቄ እንዲቀንስልኝ አድርጌያለሁ።
ከዚያ ወደ ከሰዓት አከባቢ መርማሪዎች ተከፋፍለው ጥያቄ ይቀበሉን ጀመር። ከዚያ በፊት ግን መስክር ተብለው በእኛ ላይ እንዲመሰክሩ ስለተዘጋጁ ፖሊሶች ትንሽ ልበል፤ “ምስክሮቹ የት አሉ?” ሲል መርማሪው ሰምቼ ገርሞኝ ውጭ ውጪ አያለሁ “ምስክር ደግሞ ከየት ሊያመጡ ነው” ብዬ። ነገሩ ለካ ሌላ ኖሯል፤ እዚያ የነበሩን ፖሊሶች ተከፋፈሉን አንዱ ተነሳና በእርሱ ላይ እኔ
እመሰክራለሁ ብሎ በጣቱ እየጠቆመ ያሳያል፤ ይህ ሰው እኔ ስያዝ እንዳልነበረ በፍፅም እርግጠኛ ነበርኩ። በቦታው አልነበረም፤ ነገር ግን የሆነ የሆነ ነገር ሲያደርግ አይቻዋለሁ ብሎ ምስክርነቱን ሰጠ። ከዚያ እኔ ራሴ ቀርቤ ክሱን ተነበበልኝ። “አረቦች ከሀገራችን ይውጡ” ብለሃል “በአርበኛ የተፃፈ ፅሁፍ ይዘህ ስትጮህ ነበር” “የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በዜጎቻችን ጉዳይ እያደረገ ያለ ነገር አንቋሽሸሃል፣ ድንጋይ ወርርሃል” ብዙ ብዙ ማለቂያ የሌለው ክስ አነበበልኝ እና “የምትለው ነገር አለ?” አለኝ፤ “እኔ ሰልፍ መውጣቴ እርግጥ ነው የምትለው ነገር ግን አልፈፀምኩም” አልኩት። በዚህ መሀል መርማሪው ፖሊስ “ቤተሰብ አለህ? ማለቴ ትዳር አለህ?” አለኝ። “አዎ” አልኩኝ በትህትና! “ታዲያ ምን ልታደርግ እዚህ መጣህ?” አለኝ በማስከተል፤ በዚህ ጊዜ በጥያቄው ተገርሜ “ሰልፉ የላጤዎች መሆኑ አላወቁም ነበር” አልኩት። ቱግ ብሎ “እየቀለድክ ነው!” አለኝ። “እየቀልድክ ያለውስ አንተ” ልለው ፈልጌ ቁጣው አይቼ ተውኩት። በጥፊ ቢያላጋኝስ ማን አዛዥ አለው። ቃሌን ሰጥቼ እንደወጣሁ ያ እኔ ላይ የመሰከረው ፖሊስ “አንተ ለመሆኑ እኔ የተያዝኩት የቱ ጋር ነው? የት ላይ ነው ያየኸኝ?” ስለው እየሳቀ “በኢትቪ” ብሎ አላገጠብኝ።
አንዱ ታሳሪ ደግሞ ለመርማሪው ቃሉን እየሰጠ ነው፤ እናም “ብሄር” በሚለው ጉዳይ ላይ ሊግባቡ አልቻሉም ከመርማሪው ጋር። “ብሄርህ ምንድነው?” ይለዋል። ልጁ “ኢትዮጵያዊ” አለ።
“ኢትዮጵያዊ ብሎ ብሄር የለም ትናገር እንደሆነ ተናገር” ይለዋል ፖሊሱ። ልጅ በዚያ አቋሙ ፀና። መርማሪው ደግሞ ይሄ በፀጋ ሊቀበለው አልፈለገም። በዚህ ተነሳ ሌሎች ፖሊሶችም ተደርበው ልጁን ያወክቡት ያዙ “ብሄርህ ተናገር” እያሉ።
እኔ እስከማውቀው ድረስ “ብሔር” ማለት ሀገር ማለት ነው በግዕዝ። ለምሳሌ “አይተ ብሄርከ?” ካለ “ሀገርህ የትነው?” ማለቱ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲባል ሀገራዊ ቡድን ለማለት ነው። “ምን ታደርጌዋለሽ!” አለ ጥላሁን! የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መፅሐፍ ብሄርን ምን ብሎ እንደሚተረጎመው አላውቅም።
መርማሪው ትንሽ ካሰበ በኋላ መላ የዘየደ መስሎት “እሺ የትነው የተወለድከው?” አለው። ልጁም ከእርሱ የባሰ እልሀኛ ኖሯል “ደቡብ” አለው። ከስልሳ በላይ ብሄረሰቦች ወደሚኖርበት ክልል ወስዶ ዶለው!
“ደቡብ የት?”
“አርባ ምንጭ።”
በዚህ ጊዜ ምን ብሎ እንደሚፈርጀው ግራ ገባው። “ደብረማርቆስ” ብሎት ቢሆን ኖሮ እዳው ገብስ ይሆንለት ነበር። አንድ ከአሁን በፊት የሰማሁት ቀልድ ነበር ሰውየው መታወቂያ ሊያወጣ ወደ ቀበሌ ይሄዳል “ብሄር?” ይለዋል። ኢትዮጵያዊ አለው። “አውቄብሃለሁ አማራ ነህ ማለት ነው” ብሎ በመታወቂያው ላይ ሞላለት እየተባለ ይነገር ነበር። እናም መርማሪው ልጁን “ብሄር የለኝም በል እንጂ ኢትዮጵያዊ የሚባለ ብሄር የለም” ብሎ ግግም አለበት። ሌሎቹም በቃ ብሄር የለውም ብለህ ሙላው ሲሉት ጊዜ ብሄር የለውም ተብሎ ተሞላለት። በነገራችን ላይ የታሰርነው ከሁሉም ብሄረሰብ ነበር ማለት ይቻላል። አንዱም አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ ነውና ብሄሩን ለመናገር ብዙ ካገራገረ በኋላ መጨረሻ ላይ “ጉራጌ” አለ!
በዚህ ጊዜ “የአዲስ አበባ ልጅ በቦታ እንጂ በብሄር መጠራት አይወድም” የሚባለውን አስታውሼ ፈገግ ማለቴ አልቀረም። የጨርቆስ ልጅ፣ የቦሌ ልጅ፣ የፒያሳ ልጅ ማለትን ነው የሚቀናው። ለአዲስ አባባ ልጆች ብሄር በሚለው ቦታ ላይ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ቢሞላላቸው እኔም ደስ ይለኝ ነበር። ምክንያቱም የብሄር መለኪያ በዚህ ሀገር በጣም ግልፅ አይደለም። በቋንቋ ነው እንዳትለው ቋንቋ የሚለመድ ነገር ነው፤ ለምሳሌ ደርግ በሰፈራ ወደ ወለጋ ያመጣቸው የትግራይ ሰዎች አሁን ልጆቻቸው ኦሮምኛን ልክ የአከባቢው ሰዎች ያህል ነው የሚናገሩት። በኦሮሚኛ ችሎታቸው እነ ፕሮፌሰር መራራ ጉዳና ሳይቀር ሊያስንቁ ይችላሉ፤ ነገር ግን ኢህአደግ ኦሮሞ ናቸው የሚላቸው አይመስለኝም። አቶ ገብሩ አስራት አባቱ ሙሉ አማራ ናቸው፤ ነገር ግን ትግራዋይ ቁጠር ብባል ከአቶ ገብሩ አስራት አንድ ብዬ ልጀምር እችላለሁ። አቶ መለስም ከኤርትራ እስከ ጎጃም ድረስ ይወለዳሉ። እንዲህ በዘመቻና በንግድ ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀስ እየተዋለደ የኖረን ህዝብ እንዴት አድርገህ ነው የምትለየው!
(ቀሪውን ሳምንት ይቀጥላል)
Source: Fact Magazine
 
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራት በመገናኛ ብዙሃንና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ተጠናክሮ የቀጠለው ጥቃት እንዲቆም እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ብራሰል ቤልጂግ ውስጥ ለተካሄደው የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽኖች የሰብዓዊ መብቶች የጋራ መድረክ አሳስቧል ። 

የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት በአፍሪቃ ለሰብዓዊ መብት መከበር ለሚታገሉና አውሮፓ ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ዜጎች የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቁ ። የአውሮፓ ህብረትም ለውጭ ዜጎችና ለተገን ጠያቂዎች የተሻለ ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሬ ቀርቦለታል ። ሂሩት መለሰየአፍሪቃ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት ኮሚስዮኖች ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ካካሄዱት ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ውይይት ዋነኛ ትኩረቶች አንዱ አፍሪቃ ውስጥ በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በጋዜጠኖችና በሲቪል ማህበራት ላይ የሚፈፀመው ጥቃት
እየከፋና እየተወሳሰበ መሄዱ ነው ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ አውሮፓ የሚሰደዱ ሰዎች መንገድ ላይ እንዲሁም አውሮፓ ከደረሱ በኋላም የሚያጋጥማቸው ችግርም ሌላው የመነጋገሪያ ርዕስ ነበር ። ለነዚህ ሁለት አብይ ችግሮች የሁለቱ ክፍለ ዓለማት ኮሚስዮኖች የጋራ መፍትሄ እንዲፈልጉ ውይይቱ ከመካሄዱ በፊት ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ አቅርቦ ነበር ። ከኮሚስዮኖቹ ስብሰባ አስቀድሞ በተመሳሳይ ርዕስ ላይ በተካሄደው በብራሰልሱ ስብሰባ ላይ የተገኙት በሂዩመን ራይትስ ዋች የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ በተለይ በብዙ የአፍሪቃ ሃገራት በጋዜጠኞችና በሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በሁለት መንገድ መከላከል ይቻላል ይላሉ ።


ሂዩመን ራይትስ ዋች እንደሚለው ባለፉት 20 ዓመታት በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቁጥር ማደግና የመገናኛ ብዙሃንም መስፋፋት የሚበረታታ ነው ይሁንና በተለይ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት ባሉባቸው የአፍሪቃ ሃገራት በመገናኛ ብዙሃንና በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ተባብሷል ። ስደትን ከሚያባብሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚደመሩትን እነዚህን ድርጊቶች የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ምዕራባውያን መንግሥታት ከማውገዝ ባለፈ በነዚህ ጨቋኝ መንግሥታት ላይ ተጨባጭ እርምጃ ባለመውሰድ ይተቻሉ ። ይህ ጉዳይ የብራሰልሱ የውይይት መድረክ አፅንኦት ሰጥቶት ካነሳቸው ነጥቦች አንዱ ነበር ። አቶ ዳንኤልሰብዓዊ መብትን በመጣስ የተወቀሱት አፍሪቃውያኑ ብቻ አይደሉም ። የአውሮፓ ህብረትም በተለይ ተገን ለሚያሻቸው የውጭ ዜጎች ድንበሩን በመዝጋት ተተችቷል ። ወደ አውሮፓ በባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች መንገድ ላይ ችግር ሲያጋጥማቸው አይቶ እዳላየ በማለፍ ብዙዎች ለሞት የሚዳረጉባቸው አጋጣሚዎች በምሳሌነትም ተነስተዋል ። ከመካከላቸው ከአንድ ወር በፊት የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከ 350 ሰዎች በላይ ህይወት የጠፋበት አደጋ አንዱ ነው ። አቶ ዳንኤል የአውሮፓ ህብረት በዚህ ረገድ የሚያራምደውን መርህ እንዲመረምር መጠየቁን ተናግረዋል ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ
Source: www.dw.de

- «ፕሬዚዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ» አቶ የማነ ገብረመስቀል
- አሜሪካ ዜጎችዋ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች
ከመገናኛ ብዙኃንና ከሕዝብ እይታ ከራቁ ከአንድ ወር በላይ የሆናቸው  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤንነት ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡

አስማሪኖ የተባለውና መቀመጫውን በካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደረገው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ድረ ገጽ እንደጻፈው፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወትሮው በተለየ ከመገናኛ ብዙኃን ርቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለመጨረሻ ጊዜ በሚዲያ የታዩት ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የአንበጣ መቆጣጠሪያ ድርጅት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 58ኛ ጉባዔ ላይ መሆኑን ድረ ገጹ ጽፏል፡፡
ከዚያም በጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በጉበት ሕመም ምክንያት አስመራ በሚገኘው የአየር ኃይል ሐኪም ቤት ለስድስት ሰዓታት ያህል ሕክምና ተደርጐላቸው  ወደ ቤተ መንግሥት መመለሳቸውን ጽፏል፡፡ በመቀጠልም ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ወይም ኳታር ለተጨማሪ ሕክምና መሄዳቸው እንዳልቀረ አትቷል፡፡
ስለ ጉዳዩ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ የማነ ገብረመስቀልን በትዊተር ገጻቸው ለሪፖርተር ማብራሪያ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ «አስቂኝ ቅዠት ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
«ፕሬዚዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው፤» በማለት መሠረተ ቢስ የሆነ ወሬ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ «ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ አስማሪኖ ውሸት ማውራት ስለፈለገ ነው፡፡ ማንኛውንም የአስመራ ነዋሪ መጠየቅ ይቻላል፤ ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮአቸው ሲገቡ ያዩአቸዋል፤» ብለዋል፡፡
 ከዚህ ቀደም ከሚያዝያ 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ ከመገናኛ ብዙኃን መጥፋታቸው መነጋገሪያ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 
በተያያዘ ዜናም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የቆንስላ ጉዳዮች ቢሮ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኤርትራ ምንም ዓይነት ጉዞ እንዳያደርጉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ በአገሪቷ ላይ የሚታየውን የፀጥታ ችግር እንደ ምክንያት በመግለጽ ከአሁን በፊት በግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ያወጣውን የጉዞ ማዕቀብ ማስጠንቀቂያ አጠናክሯል፡፡
ስቴት ዲፓርትመንት በመግለጫው እንዳስታወቀው፣ የአሜሪካና የኤርትራ ድርብ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ያለምንም ምክንያት እየታሠሩ ነው፡፡ በተጨማሪም በመርከብ የሚጓዙ የአሜሪካ ዜጎች በኤርትራ የባህር ዳርቻ እንዳይጓዙና መልህቆቻቸውን እንዳይጥሉ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡ 
የኤርትራ መንግሥት መቀመጫው ሶማሊያ ለሆነው የአልሸባብ አክራሪ ቡድን ድጋፍ ያደርጋል በማለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በታኅሳስ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የመሣሪያ ማዕቀብ መጣሉ ይታወቃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያና የኤርትራ አጣሪ ኮሚቴ ግን የኤርትራ መንግሥት ለአልሸባብ «ቀጥታ» ዕርዳታ እንደማያደርግ ሐምሌ 9 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡
Source: http://www.ethiopianreporter.com
 
| Copyright © 2013 Lomiy Blog