ባ
ለፈው ሳምንት በእለተ ቅዳሜ (8/10/2005) ማታ አራት ሰዓት ከሃያ አካባቢ በዛሚ 90.7 በኢትዮፒካሊንክ ፕሮግራም አቅራቢዎች የቀረበው እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው፡፡ አስደንጋጩ ዜና በአንድ ስሙ ባልተጠቀሰ ትምህርት ቤት ውስጥ የ10 እና የ11 ዓመት ወንድ ሕጻናት መደፈራቸው ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ ደግሞ የትምህርት ቤቱ ስድስት መምህራን ናቸው፡፡ ልጆቹ በጋንዲ እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደተረጋገጠው በግብረ ሶዶማዊያን ተደፍረዋል፡፡ ተደፍረዋል የሚለው ቃል የነገሩን ክብደት ያቀለዋል፡፡ ከመግደል ሙከራ በላይ ተዶርጎባቸዋል ብል የተሻለ ይመስለኛል፡፡  በተለይ ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት መሆናቸው ለሰሚው ከአስደማሚነት ባለፈ የሚያናድድና ፍጹም ነውረኛነት የተሞላበት ነው፡፡ የአንደኛው ሕጻን እናት የልጇን እና የእሷን ነፍስ ለማጥፋት ሙከራ አድርጋለች፡፡ ይህን ነውረኛ ተግባር ፈጸሙት የተባሉት ስድስቱ ተጠርጣሪ መምህራን
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
መምህርነትን ከሳቴ ብርሃን ተሰማ - የአማርኛ መዝገበ ቃላት “አስተማሪነት፣ መሪነት፣ ካለ ማወቅ ወደ ማወቅ እውቀትን አደራሽነት፣ ገላጭነት” በማለት ይፈክረዋል፡፡ ፡፡ Perceival P. Wren የተባለው የሥነ ትምህርት ባለሙያ ደግሞ “መምህር የእውቀት ማማ (ምንጭ) ብቻ ሳይሆን መሪ፣ ፈላስፋ፣ ጓደኛ፣ ስብዕና ገንቢ፣ አሰልጣኝ እና አዕምሮ አበልጻጊ ነው” በማለት ይገልጸዋል፡፡ መምህር በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡ አሁን አሁን ግን የመምህር ሙያ እና ክብር እንደፊኛ እየሟሸሸ ነው፡፡ መምህርነት የተጠላ ሞያ እየሆነ ነው፡፡ የሆነም ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉም አካላት (መንግስት፣ መምህራን እና  ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች) ተጠያቂ ናቸው፡፡ አሁን በየትምህርት ቤቱ ብትሄዱ መማር የሚፈልግ (ዓላማ ያለው) ተማሪ ማግኜት ይቸግራል፡፡ ሁሉም ቡረቃና ረብሻ ነው የሚወዱት፡፡ መምህራንም ማስተማር ተሰላችተዋል፡፡ ለስሙ አስተማሪ መባል ካልሆነ እና የወር ደሞወዝ ከመቆጠር ያለፈ ለሙያው ፍቅር ያለው መምህር አሁን ማግኜት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሰፊና ጥልቅ የሆኑ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚያ ምክንያቶች ተጠንተው መፍትሔ ካልተፈለገላቸው የኢትዮጵያ ትምህርት አደጋ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡ የአንድን አገር እጣ ፈንታ ወሳኞች መምህራን መሆናቸውን ሁላችንም ያወቅን አልመሰለኝም፡፡ 
ከላይ ወንድ ሕፃናትን የደፈሩ ተጠርጣሪ መምህራን፣ አንደኛ፣ መምህር ማለት ምን እንደሆነ አልገባቸውም፡፡ መምህር እኮ አባት ነው፡፡ አንዳንዴ ባይጋነን ከአባትም በላይ ነው፡፡ ስለዚህ እንዴት የቀለም ልጁን ይደፍራል? ያውም የ10 እና የ11 ዓመት ወንድ ሕጻናትን? ከልጅነት እስከ ጉርምስና ወቅት አካባቢውን ብሎም ይህችን ዓለም የሚያስተዋውቀው መምህር ነው፡፡ ተማሪዎች ብዙ ጊዜያቸውን የሚሳልፉት ከወላጅ ጋር ሳይሆን ከመምህር ጋር ነው፡፡ ስለዚህ አንድን ልጅ ከወላጅ የበለጠ የሚቀርጸው መምህሩ ነው፡፡ መምህር ትውልድን ይገድላልም ያድናልም፡፡
ሁለተኛ እነዚህ መምህራን በዘመኑ የሶዶማዊያን እሳት የተገረፉ ይመስሉኛል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን (Homosexual) ምንም እንኳ በኃይማኖት አስተምህሮ ውስጥ የታወቀ ቢሆንም ብዙዎቻችንን የፈረንጆች ምናምንቴ ወይም ጣጣ ይመስለን ነበር፡፡ አሁን ግን ዓለምን (አፍሪካን ጨምሮ) እየናጣት ያለ ችግር ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መነጋገሪያ ከሆነ አመታት ቢቆጠሩም አሁን አሁን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ውጉዝ ነበረ፡፡ ከአስራ ሁለት ዓመት በፊት ኔዘርላንድ የተመሳሳይ ፆታን ጋብቻ ከፈቀደች በኋላ በተለያዩ ሃገሮች የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ህጋዊ ሆኗል፡፡ ከእነዚህ ሃገሮች መካከል፡- ፈረንሳይ፣ ቤልጄም፣ አርጄንቲና፣ አይስላንድ፣ ዴንማርክ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ስፔን፣ ኖርዌይ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፖርቹጋል እና ስዊድን ይጠቀሳሉ፡፡ በአሜሪካ እና ሜክሲኮ በዛ ባሉ ግዛቶችም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ከተፈቀደ ሰነባብቷል፡፡ ኡራጋይ እና ኒውዝላንድም በቅርቡ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እነ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ፊንላንድ፣ አንዶራ፣ ሉክሰምበርግ፣ አየርላንድ፣ ታይዋን፣ ኔፓል፣ ስኮትላንድ እና በተለያዩ የአሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሜክሲኮ ግዛቶች የተመሳሳይ ፆታ (ግብረ ሶዶማዊያን) ጋብቻን ህጋዊ ለማድረግ  እየተውጠነጠኑ ነው፡፡ ምዕራባዊያንም ያላደጉ ሃራት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድ እንዳለባቸው በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ይህን የማታከብር ሃገር የሚሰጣት እርዳታ እንደሚጤንባት (እንደሚቀሸብባት ብሎም እንደሚቆምባት) ባደባባይ ዲስኩራቸውን አሰምተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የግብረ ሶዶማዊያን ገሃድ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቢሰራ የበለጠ ማወቅ እንችላለን፡፡ ከዚህ በፊት የተሰራ ካለ ግን አላውቅም፡፡ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድ እና በጉዳዩ መሳተፍ፣ እንደ ስልጣኔ እና በአስተሳሳብ ’ርቆ እንደመሄድ የሚቆጥሩት ብዙ አሉ፡፡ ነገር ግን ግብረ ሰዶማዊነት፣ የሰው ልጅ ወደ ፊት የሚያደርገውን ሕይዎታዊ ጉዘት ሊያቆመው ይችላል ብለው ብዙዎች በመጮኽ ላይ ናቸው፡፡ በቅርቡ እንደምናስታውሰው ፈረንሳይ ውስጥ ግብረ ሶዶማዊነት (ተመሳሳይ የፆታ ጋብቻ) ህግ ሆኖ ሲጸድቅ ብዙ ሰዎች በመቃወም ወደ ጎዳና ወጡ፡፡ ነገር ግን በመፈክራቸው ትውልድ፣ ቤተሰብ (እናት፣ አባት፣ ልጅ፣ እህት፣ ወንድም፣ አክስት፣ አጎት …) ወዘተ ሊጠፋ ነው እያሉ ቢጮኹ፤ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡
የግብረ ሶዶማዊያን አብዮት ከአውሮፓና አሜሪካ ወደ አፍሪካ ሰርጎ ከገባ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ፍጥነቱ እንደ ሰደድ እሳት ሆኗል፡፡ በቅርብ ጊዜም የአፍሪካ ሃገራት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ህጋዊ ለማድረግና ላለማድረግ ፓርላማ ውስጥ እንደሚፋጩ አትጠራጠሩ፡፡ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራትም ይህ ዘመቻ (አብዮት) ተጀምሯል፡፡ ከተጀመረ ደግሞ ከጊዜ በኋላ ህጋዊ መሆኑ እንደማይቀር እሙን ነው፡፡ በተለይ አፍሪካ ዲሞከራሲን ማሽተት ስትጀምር ይህ ጉዳይም ከኋላ እንደ እንግዴ ልጅ የማይቀር ነው፡፡ እኛም አንድ ቀን እንደ ፈረንሳዊያን በመቃወም ሰልፍ እንደምንወጣ እኔ አልጠራጠርም፡፡ ጊዜው ይራቅ እንጂ ይህ የሚከሰት ሃቅ ይመስለኛል፡፡ ይህን ለማለት ነብይ መሆን የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ በኢትዮጵያና በዓለም ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በአርምሞ መመልከት በቂ ይመስለኛል፡፡ ፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 5 ቁጥር 164 ህዳር 23 2004 ዓ.ም ይዛ የወጣችውን ዜና ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ “የግብረ ሰዶማዊያን ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል” የሚል ነበር ዜናው፡፡ ስብሰባው አለም አቀፍ እንደ እንደሆነና በጁፒተር ሆቴል እንደሚደረግ በስፋት ተተንትኖ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ዊኪሊክስ ከአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በተገኜ መረጃ መሰረት፣ ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ በጣም እንደተስፋፋ ገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ግብረ ሰዶማዊያን ድህረ ገፅ ወይም ዌብሳይት ከፍተዋል፣ ለምሳሌ www.EthioLGBT.com ፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይም ዘመቻውን እያጧጧፉት ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱም ሕፃናት በዚህ አስነዋሪ ድርጊት እየተለከፉ ነው፡፡
ሰሞኑን ቤቲ የተባለች ኢትዮጵያዊት በቢግ ብራዘር አፍሪካ ላይ የፈጸመችውን ወሲባዊ ትዕይንት ጋዜጦች እና ራዲዮኖች እንዲህውም አብዛኛው ሰው በተቃውሞ ጮኸባት፡፡ አንዳንዶችም “ቤቲ አዋረደችን፣ አስደበችን” ብለው የጻፉም፣ የተናገሩም አሉ፡፡ ምን አዲስ ነገር አለና ነው እንዲህ የምትጮኹት? ዞር ብላችሁ በከተማችን የሚጸመውን ጉድ ለምን አታዩም? ሃገርስ አንዲት እንስት በፈጸመችው እንዴት ሊዋረድ ይችላል? ብለው የሞገቱም ነበሩ፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ሃሳብ ሰጭዎች ላይ ብዙዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡
     የሚገርመው ግን ሰው እና መገናኛ ብዙኃኑ የጮኸው ቤቲ ወዳ በፈጸመችው እንጂ በእነዚህ እምቦቀቅላ ሕጻናት ላይ በተፈጸመው አስነዋሪ ወንጀል አይደለም፡፡ ለምን? ለምን ዝምታን መረጥን? የሚገርመው መጮኽ ያለብንና የሌለብንን ጉዳይ የለየን አይመስለኝም፡፡ አዲስ አበባ እኮ የወሲብ እብድ ነች፡፡ ያውም እራቁቷን የምትደንስ፡፡ እብድነቷ ደግሞ በተፈጥሯዊ ወሲብ ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከተፈጥሯዊ የፍቅር ስሪያ ባፈነገጡ (በጌዮች እና ሌዝቢያኖች) እየተሞላች ነው፡፡ አንድ ሆቴል ወስጥ የሚሰራ ጓደኛ አለኝ፡፡ ከሚሰራበት ሆቴል የሚገጥሙትና የሚያቸው ነገሮች ግን ይህ ትውልድ ወዴት እያመራ ይሆን ያስብላል፡፡ እጅግም ያስጨንቃል፡፡ እናም ታዛቢው ጓደኛዬ ዛሬ ሌዝቢያኖች መጥተው ነበር፣ ዛሬ ጌዮች መጥተው ነበር፣ ዛሬ አንድ ፈረንጅ አንዲት ሚጥጥዬ ተማሪ ጋር መጥቶ _____፣ ዛሬ አንዲት የምታምር የቤት ልጅ ደላላ ደውሎላት ከአንድ አረብ ጋር አብረው ወደ _____ ሄዱ፣ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን “እንዴት ነው ግን ጌዮችን እና ሌዚቢያኖችን የምትለዩአቸው?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ጓደኛዬ እየሳቀ “ጌዮች እኮ አጓጓዛቸው ብቻ ያሳብቅባቸዋል” አለኝ፡፡ እኔም በግርምት “አጓጓዛቸው ስትል” አልሁት፡፡ አሁንም እየሳቀ “በቃ ሲጓዙ ሸከክ ሸከክ ወይም ሸፈፍ ሸፈፍ ነው የሚሉት” አለኝ፡፡ እኔም እንደመሳቅ ብዬ ሌዝቢያኖችንስ አልሁት፡፡ “እነሱን ማወቅ የምትችለው በሚያደርጉት ድርጊት ነው፡፡ በተለይ ሌዝቢያኖችም ሆኑ ጌዮች ሲጠጡ ማንነታቸው ገሃድ ይወጣል” አለኝ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን፣ አሁን አሁን ወደ ጭፈራ ቤቶች የሚሄዱት የወንድና የሴት ጥንድ ሳይሆን የተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች እንደሆኑ በተለያዩ ሰዎችና መገናኛ ብዘኃን እየተገለጹም ነው፡፡
      ታዲያ ትውልድን ለማዳን ምን እናድርግ? ለሚለው ኢ-ተገቢነቱን በህግ ብቻ መከልከል ፋይዳ ያለው አይመስለኝም፡፡ አንድ ቀን ይህ ህግ ሊነሳ ይችላል፡፡ ባይነሳም በምስጢር ዘመቻው ከመስፋፋት የሚያግደው የለም፡፡ እናም እንደኔ ብቸኛው መፍትሔ የሚመስለኝ ትውልድን ማንቃት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡



              ክፍልአንድ 
W. E. B. Du Bois
 ምዕራባዊያንአፍሪካን በበጎ ነገርአያነሷትም፡፡ የቀደምት ስልጣኔዋንምአምነው አይቀበሉትም፡፡ አፍሪካዊያኑምቢሆኑ ስለማንነታቸውና ስለታሪካቸው ያላቸውእውቀት ፈረንጆች አፍሪካንከሚያውቋት እጅግ ያነሰነው፡፡ ይህ ነገርደግሞ አሁን አፍሪካ ካለባት ችግርበተጨማሪ ነገሩ የገለባእሳት ሆኖባታል፡፡ አፍሪካ ባንድወቅት ኃያል ሃገር ነበረች፡፡ ነገር ግን ስልጣኔዋ ተሸመደመደና ወደጨለማው ዘመን ገባች፡፡የስልጣኔ መሽመድመድ በታሪክአፍሪካ ብቻ ሳትሆንአውሮፓንም ደቁሷታል፡፡ ምስጋናይግባቸውና የሰሜን አፍሪካሙሮች (Moors) በሰባተኛውመቶ ክፍለ ዘመን ወደ አውሮፓ ተሻግረው፣ ጨለማውስጥ የምትገኘውን አህጉር አቀኑ፡፡ከዚያ በኋላ አውሮፓ ሰለጠነችና አፍሪካንተቀራመተች፡፡ ይህንን የአፍሪካቅርምጥ የአብርሆት (Enlightenment) ዘመንልሂቃን የሚባሉት ጭምርደግፈውታል፡፡ የአፍሪካ ህዝብሰብአዊ መብቱ ተገፎሰው ያለመሆኑ ታወጀ እናለባርነት ተጋዘ፣ ተገረፈ፣ተሰቃየ፣ ተሰቀለ፣ ታደነ፣ታነቀ፣ ተገደለ፣ ንብረቱተዘረፈ፣ የአገር ባለቤትነቱንተነጠቀ፣ ሳይፈልግ የወራሪዎቹንባህል፣ ትምህርት፣ ኃይማኖትእንዲቀበል ተገደደ ………. ምንያልሆነው አለ? እናምይሄንን ግፍ አሽቀንጥረውለመጣል ሃሳብ ያላቸውጥቁር ልሂቃን በየቦታው ማኮብኮብጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ ሰለእነዚህን ንቅናቄዎች እናኢትዮጵያኒዝም ትንሽ እንመለከታለን፡፡ከዚያም ወደ ፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እናዓላማ፣ በመጨረሻም የፓንአፍሪካኒዝም ራዕይ እንዴትበአፍሪካዊያን አምባገነን መሪዎችእንደጨነገፈ
በሶስት ተከታታይክፍሎች እንመለከታለን፡፡ 19ኛውክፍለ ዘመን መጨረሻ በደቡብ አፍሪካበነጮች ይጨቆኑ የነበሩትእና በእምነቱ ውስጥ ምንምቦታ ያልተሰጣቸው ጥቁሮች ከአንግሊካንእና ሜቶዲስት ደብር (Church) ተገንጥለውበውጣት ኢትዮጵያዊ ደብር(Ethiopian Church) መሰረቱ፡፡ በሰበካቸው ውስጥምአፍሪካ ለአፍሪካዊያንየሚልነበረው፡፡ ይህም እንቅስቃሴኢትዮጵያኒዝም የሚባልአስተሳሰብ እንዲጀመር ረድቷል፡፡የዌስልያን ሚኒስተር ማንጌናሞኮን (Mangena Mokone) ኢትዮጵያኒዝም የሚለውንቃል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተጠቀመብዙዎች ያምናሉ፡፡ የኢትዮጵያኒዝምእሳቤ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራትናይጄሪያ፣ ጋና፣ ካሜሮን፣ሮዶዥያና ሌሎችም አንሰራርቶነበር፡፡ ከአፍሪካ ውጭደግሞ ይህ እሳቤ በካረቢያን እና ሰሜንአሜሪካ እንደሰደድ እሳትተስፋፍቶ ነበር፡፡ አንዳንድጸሐፍት ኢትዮጵያኒዝም የሚለውንጽንሰ ሃሳብ ለማብራራት እንደሚያስቸግር ቢያትቱምዋና ጽንሰ ሃሳቡ ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ፍልስፍናንያካተተ ነው፡፡ በሃይማኖታዊውካየነው ጥቁሮች በነጮችየበላይነት የሚመራውን ደብርትተን፣ የራሳችንን ከማንነታችንጋር ትስስር ያላትን አፍሪካዊት(ኢትዮጵያዊት) ደብር እንመስርትየሚል ነው፡፡ ፖለቲካዊው ደግሞበአለም የሚገኙ ጥቁሮችየነጮችን የፈላጭ ቆራጭገዥነትን ለመገርሰስ ኢትዮጵያንእንደ አርዓያ በመውሰድ የሚደረግእንቅስቃሴ ነበር፡፡ በተለይየአድዋ ድል፣ የኢትዮጵያቀደምትነት ስልጣኔ እናበመጽሐፍ ቅዱስ ስሟመጠቀሱ ለኢትዮጵያኒዝም እሳቤእና ለፓን አፍሪካኒዝም ፍልስፍና ጉልህአስተዋጽኦ ነበራቸው፡

 ፓን አፍሪካኒዝም- በመላውዓለም የሚገኙትን አፍሪካዊያን አንድነት(ሶሊዳሪቲ) የሚቀሰቅስ ርዕዮተዓለምነው፡፡ ፓን አፍሪካኒዝምመነሻውን ከጥንት የአፍሪካዊያንስልጣኔ ጋር ያይዛል፡፡ጥቁሮች ከጥንት ጀምረውእስካሁን ይዘውት የመጡትንናጥንት የነበሩትን ታሪካዊ፣ ባሕላዊ፣ኪነ-ጥበባዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሳይንሳዊናፍልስፍናዊ እሴቶችን በሕዝብዘንድ ማስረጽ አንደኛው ዓላማቸውነው፡፡ የፓን አፍሪካኒዝምንቅናቄዎች ቀደም ሲልየተጀመሩ ቢሆንም ዘመናዊውየፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የተጀመረውግን 1887 በትሪኒዳዱ የህግምሁር ሄነሪ ሲልቬስተር ዊሊያምስ አፍሪካንአሶሴሽንበሚል ስያሜነበር የተቋቋመው፡፡ እዚህ ላይ(ስለ መጀመሪያው የፓን አፍሪካንመስራች) በታሪክ ሰዎችዘንድ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንድየታሪክ መጽሐፍት ላይ(ጸሐፊዎች) የመጀመሪያው የፓንአፍሪካን መስራች (ጽንሰሃሳብ አመንጭ) ላይቤሪያዊው መምህር፣ጸሐፊ፣ ዲፕሎማትና ፖለቲከኛኤድዋርድ ዊልሞት ብላይደንነው ሲሉ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሌሎችደግሞ ሄነሪ ሲልቬስተር ዊሊያምስ ነውይላሉ፡፡ በአፍሪካም ይህንየፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ ካስፋፉትናድርጅታዊ መሰረት ከሰጡትአንዱ የማላዊው ዜጋ የነበረውየባብቲስት ሚሲዮናዊ ዮሴፍቡዝ ነበር፡፡ 
የፓን አፍሪካንየመጀመሪያውን ጉባኤም በሐምሌወር 1900 ለንደን ላይበሄነሪ ሲልቬስተር ዊሊያምስአስተባባሪነት ከአፍሪካ፣ ከዩናትድስቴትስ፣ ከካረቢያን እናከአውሮፓ ሃገራት በተውጣጡ32 ተወካዮች ተካሄደ፡፡ በዚህስብሰባ ላይ ከአፍሪካየጋና (ጎልድ ኮሰት) ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ እናኢትዮጵያ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡የኢትዮጵያው ንጉሰ ነገሰትዳግማዊ ምኒሊክ የሃይቲውንቤኒቶ ሲልቪያን ወክለው ልከውነበር፡፡ በዚሁ ስብሰባፓን አፍሪካን አሶሴሽንየሚል ድርጅትም አቋቋሙ፡፡ ከተሰብሳቢዎቹአንዱ ታዋቂው አፍሮ አሜሪካዊውምሁር ዱቦይስ ( ) ተገኝቷል፡፡  ዱቦይስ ከሃርቫርድዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ጥናትዶክትሬቱን ያገኜ ሲሆንበአሜሪካም በጥቁሮች ታሪክየመጀመሪያ ጥቁር ሰውነው ደኮትሬት በማግኜት፡፡ በአትላንታዩኒቨርስቲም የታሪክ፣ ማህበራዊሳይንስ (ሶሲዎሎጅ) እናምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ነበር፡፡ ዱቦይስየአሜሪካን ጥቁሮች በማንቃትበኩል ያደረገው ትግል እጅግከፍተኛ ነበር፡፡ ብዙመጽሐፍትን ጽፏል፡፡ ታላቅስራው (Magnum Opus) ተደርጎ የሚወሰደውBlack reconstruction in America ሲሆን ሌላውተወዳጅ ስራው ደግሞThe Souls of Black Folk ነው፡፡ National Association for the Advancement of Colored People (NAACP) መስራችሲሆን የዚሁ ድርጅት ልሳን ለሆነውThe Crisis ዋና ኤዲተር ነበር፡፡ ፓንአፍሪካን ከመሰረቱት መካከልግንባር ቀደሙ ነው፡፡ 

1913 የኢትዮጵያኮኮብ (The star of Ethiopia) የሚል ተውኔትደርሶ ለህዝብ እንዲታይ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ኢትዮጵያን የሰውልጆች ሁሉ እናት(መፈጠሪያ)ብሎ ይጠራትእና ያስተምር ነበር፡፡ የዓለምስልጣኔ ሁሉ ከናይልሸለቆ (ግብጽና ኢትዮጵያ) እንደተጀመረምያቀነቅን ነበር፡፡ የፓንአፍሪካን እንቅስቃሴም ለግማሽምዕተ ዓመት ያህል መርቷል፡፡ ከለንደኑ ስብሰባበኋላ አራት የፓን አፍሪካን ስብሰባዎች (1919 ፓሪስ፣ 1921 ሎንዶንናብራሰልስ፣ 1923 ሎንዶንናሊዝበን፣ 1927 ኒውዮርክ) የተዘጋጁት በዚህ ምሁርመሪነት ነበር፡፡ ያለዱቦይስ አሰተዋጽኦ ፓንአፍሪካኒዝም ወይም በተዘዋዋሪየአሁኑ አፍሪካ ሕብረትምን አልባትም ላይኖር ይችላል፡፡የሚገርመው የኢትዮጵያና የአፍሪካዋያንብዙ መገናኛ ብዙሓን ስለዚህጎምቱ የጥቁር ምሁርና የፓንአፍሪካን አባት ሚናሲናገሩ፣ ሲጽፉ ወይምሲዘክሩ አይታይም፡፡ ዱቦይስእና ኩዋሜ ንኩርማህ በፓን አፍሪካንምስረታ ጉዳይ የሚነጻጸሩአይደሉም፡፡ ርቀታቸው የሰማይናየምድር ነው ብሎየዚህ ጦማር ጸሀፊ ያምናል፡፡ ንኩርማህ፣ጁሊየስ ኒሬሬ፣ጆሞ ኬንያታ ወዘተ. 1945የማንቸስተሩ ፓን አፍሪካንስብሰባ ላይ የተገኙየርዕዮቱ ልጆቹ ናቸው፡፡በርግጥ ከማንቸስተሩ የፓንአፍሪካን ስብሰባ በኋላመሪነቱ በአፍሪካዊያን እጅገብቷል፡፡ ዱቦይስ በሶሻሊዝምፍቅር ጋር እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ የወደቀነበር፡፡ የሶሻሊዝም ፍልስፍናውእንዳልገባው ቢናገሩም እሱግን ካፒታሊዝም የሰው ልጆችዘረኛ እንዲሆኑ አድርጓል ይላል፡፡እንም ዘረኝነትን ለማስቀረት ሶሻሊዝምፍቱን መፍትሔ ነው ብሎያምናል፡፡ በዚህ ምክንያትምአሜሪካ አንቅራ ነበርየምትጠላው፡፡ 1957 ጋናነጻነቷን ስታገኝ የክብርእንግዳ አድርጋ ጠራችው፡፡ነገር ግን አሜሪካ ጋና አትሄዳትምአለችና ፓስፖርቱን ቀማችው፡፡ነገር ግን 1960 ፓስፖርቱን ስላገኜወደ ጋና ሄደ፡፡ እናም ለጋናየሪፓብሊክ ምስረታ በዓልላይ ተገኘ፡፡ በዚሁ ሰዓትምከንኩርማህ ጋር ኢንሳክሎፒዲያአፍሪካን ለማዘጋጀት ተስማሙ፡፡በጀቱም በጋናዊያን መንግስትነበር የሚሸፈነው፡፡ እናም 1961 ከአሜሪካ ሚስቱን ይዞበመምጣት ጋና ከተመ፡፡የኢንሳክሎፒዲያውን ስራም ጀመረ፡፡1963 አሜሪካ ፓስፖርቱንለማደስ ፈቃደኛ ስላልሆነችየክብር እንግዳ ሆኖጋና ተቀመጠ፡፡ ነገር በዚያውዓመት በነሃሴ ወር 1963 አክራውስጥ ሕይወቱ አለፈች፡፡ የተቀበረበትቦታም የዱቦይስ መታሰቢያ ማዕከልተብሎ ተሰይሟል፡፡

ሌላው ፓንአፍሪካን ሲነሳ ከመስራቾቹግንባር ቀደም የሆነውናአነጋጋሪው ማርቆስ ጋርቬይንእናገኛለን፡፡ አንዳንዶች ጋርቬይንየጥቁሮች ሙሴ እያሉይጠሩታል፡፡ ሙሴ እስራኤላዊያንንከግብጽ ባርነት አላቆወደ ተስፋይቱ ምድር በመውሰድነጻ እንዳወጣቸው ሁሉ፣ ጋርቬይምጥቁሮቹን ከጭቆናና ከባርነትአላቆ ወደ ተስፋይቱ ምድር አፍሪካለመውሰድ እና ጥቁሮችንአንድ ለማድረግ (ለማስተሳሰር) ያደረገውተጋድሎ ግሩም ነበር፡፡ፍልስፍናውም ጋርቬይዝም ይባልነበር፡፡ ጋርቬይ ዓለምአቀፍ የጥቁሮች መሻሻል ማህበር፣አፍሪካን ኮሚኒቲስ ሊግ፣ብላክ ስታር ላይን ኮርፖሬሽን የሚባሉ ድርጅቶችንአቋቁሟል፡፡ ጋርቬይ የጥቁርአሜሪካዊያን ድርጅት በሆነውኔሽን ኦቭ-ኢዝላም ያለው ክብርበጣም የገዘፈ እና እንደነብይምየሚመለከቱት ነው፡፡ በራስተፈሪያን እምነትም ከንጉስኃይለሥላሴ ቀጥሎ እንደአምላክ (ነብይ) የሚቆጠርሰው ነው፡፡ ነገር ግንእዚህ ላይ አንድ ማንሳት ያለብን ተቃራኒጉዳይ አለ፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያንስትወር፣ ንጉስ ኃይለስላሴ ወደ እንግሊዝ የመሄዳቸውን ጉዳይጋርቬይ እንዲህ በቀላሉአላለፈውም፡፡ ንጉስ ቀዳማዊኃይለ ሥላሴን በአደባባይ ለስጋቸውሳስተው፣ ወገናቸውን ጦርነትውስጥ ማግደው አውሮፓ እጃቸውንሊሰጡ መጡ ብሎ ከመሳለቁም በላይ ቦቅቧቃናፈሪ ብሎ ሰደባቸው፡፡ ስለዚህ ጉዳይበዝርዝር ሌላ ጊዜይዘን እንመጣለን፡፡ 

ጋርቬይ ነጮችንስግብግቦች፣ ራስ ወዳዶችእና ፍቅር የለሾች ሲል በተለያየጊዜ ይገልጻቸው ነበር፡፡ ፍቅር፣መተሳሰብና ለጋስነት ምንጩአፍሪካ ግብጽና ኢትዮጵያእንደሆነ ይሰብክ ነበር፡፡በአሜሪካም በየጎዳነው እናንተየሃያላን ልጆች ሆይአትነሱም ወይ እያለመሳጭ ንግግር ያደርግ ነበር፡፡የሚገርመው ይህ ጥቁሮችንበመላው ዓለም ያንቀሳቀሰናያነቃው ሰው (ጋርቬይ) ከዱቦይስ ጋር  የከረረጠብ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ዱቦይስበመጀመሪያ ብላክ ስታርላይን የተሰኘውን የመርከብ ንግድእቅድ (በማርከስ ጋርቬይ የተነደፈውን) ደግፎት ነበር፡፡ ጋርቬይጥቁሮች በሙሉ ወደአፍሪካ ይመለሱ፣ በአፍሪካአሜሪካዊያንም ይመሩ (ይስተዳደሩ) ሲል፣ ዱቦይስ ደግሞ ወደአፍሪካ እንመለስ የምትለውንሃሳብ እደግፈዋለሁ፡፡ ነገር ግንአፍሪካ በአፍሮ አሜሪካዊያንይመሩ የምትለው ነገር ፈጽሞየማይሆን ነው በማለትይቃወመዋል፡፡  በዚህ ሁለትጽንፍ ሃሳብ ባለመስማማት ባደባባይ እስከመሰዳደብ ደርሰዋል፡፡ ዱቦይስጋርቬይን በአሜሪካና በመላውዓለም ለሚኖሩ ጥቁሮች አደገኛጠላት ብሎ ከመፈረጁም በላይ ይሄሰው ከሃዲ ወይም እብድ መሆን አለበት ሲል ወርፎታል፡፡ጋርቬይ ደግሞ ዱቦይስንአንተ እኮ ነጭ እና የጥቁር ዲቃላ በተጨማሪምየነጭ ኔግሮ (White men’s nigger) ነህ’’ ይለውነበር፡፡ ከዚህ ሌላጋርቬይ ብላክ ስታርላይን የሚባለውን ድርጁቱን ለማጥፋትአሻጥር እየሰራብኝ ነውበማለት ይወቅሰው ነበር፡፡

ሌላው ለፓንአፍሪካኒዝም ድርጅት ምስረታትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከልኢትዮጵያዊውን . ራስመኮነን እናገኛለን፡፡ መኮነንየተወለደው ጉያና (Guyana) ውስጥሲሆን አያቱ ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይበአንድ ስኮትላዳዊ የማዕድንሰራተኛ ነበር የተወሰደው፡፡ስሙን የቀየረው (. ራስመኮነን የተባለው) በሁለተኛውየጣሊያን ኢትዮጵያን ወረራጊዜ ነበር፡፡ ለምን ስሙንቀየረ ካላችሁ፣ አፍሪካዊ ዝርያእንዳለው ለማመልከት ነበር፡፡አሜሪካ ኮርኔል ዩኒቨርስቲከተማረ በኋላ ያቀናውወደ ዴንማርክ-አውሮፓ ነበር፡፡ያኔ ታዲያ ኮፐንሃገን-ዴንማርክ ውስጥየእርሻ ኮሌጅ ውስጥእየተማረ እያለ ዴንማርክለጣሊያን የኢትዮጵያን ንጹሃንሕዝቦች መግደያ የሚሆንጅምላ ጨራሽ መርዝ አምርታ ትሰጣት ነበር፡፡ይህንን ድርጊት ጋዜጦችላይ ጦማር በመጻፍ በግልጽ ተቃወመ፡፡18 ወር ከተቀመጠባት ዴንማርክም ተባረረ፡፡ከዚያ ወደ እንግሊዝ ተጓዘና በእነጆርጅ ፓድሞር በተመሰረተው ኢንተርናሽናልአፍሪካን ሰርቪስ ቢሮንቁ ተሳታፊ በመሆንና የቢሮውምየቢዝነስ ማናጄር በመሆንአገልግሏል፡፡ ከሁለተኛው የዓለምጦርነት በኋላ ግንወደ ማንቸስተር ዩኒቨርስቲ በማቅናትታሪክ አጠና፡፡ በእንግሊዝም የስራፈጣሪ በሆን ብዙ ሆቴሎችን ከፈተ፡፡ ከጆርጅፓድሞር እና ኩዋሜንኩርማህ ጋር በመሆንም1945ቱን የፓንአፍሪካን ኮንግረስ ለማደራጄትብዙ ደክሟል፡፡ 1947 ፓንአፍሪካ የተባለ ህትመትልሳን መሰረተና የአፍሪካን የቀንተቀን ስቃያቸውንና ፍላጎታቸውን ለመላውአፍሪካዊያንና አሜሪካዊያን ያሰራጭነበር፡፡ 

1957 ጋናነጻነቷን ስታገኝ መኮነንከንኩርማህና ፓድሞር ጋርሆኖ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትንለመመስረት ወደ ጋናሄደ፡፡ 1966 ንኩርማህመፈንቅለ መንግስት ከተካሄድባቸውበኋላ መኮነን ወደ እስርቤት ተወረወረ፡፡ ከእስር የተፈቱትበጆሞ ኬንያታ ጥረት ነበር፡፡ከዚያም ጆሞ ኬንያታአገሬ አገርህ ነው በማለትይመስላል ወደ ኬንያወሰዱት፡፡ ከዚያም የኬንያዜግነት ሰጥተው የአገሪቱየቱሪዝም ሚነስተር አድርገውሾሙት፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊዝርያ ያለውን ፓን አፍሪካኒስትብዙዎቻችን አናውቅም፡፡ ምንአልባት የናይሮቢ ዩኒቨርሰትቲፕሮፌሰር የሆኑት ኬኔትኪንግ ከዘጠኝ ወር በላይሞኮነንን ቃለ መጠይቅአድርጎ 1973 ያሳተመውንPan-Africanism from Within ማግኜት ብንችልየበለጠ ሰለማንነቱ ማወቅይቻል ይሆናል፡፡
 ክፍልሁለትን በሚቀጥለው ሕትመትይዘን እንመጣለን፡፡ ቸር ሰንብቱ፡፡

 መጣለን፡፡ ቸር ሰንብቱ፡፡
| Copyright © 2013 Lomiy Blog