መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው
ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።
ድርጊቱን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች አከታትለው በመተኮሳቸው ህዝቡ ሁኔታውን ለማየት  ወደ አደባባይ ሲወጣ  ወደያውኑ መብራት እንዲጠፋ ተድርጓል።
አዣዡ በህዝቡ ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽም እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት አሁንም በአካባቢው እያንዣበቡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።
| Copyright © 2013 Lomiy Blog