4 የአየር ኃይል አብራሪዎች ኮበለሉ መባሉ

በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኀን እንደተዘገበውና የኢትዮጵያ መንግሥትም እንዳረጋገጠው Mi-35 በሚል መለያ በሚታወቅ አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ፣ 3 ኢትዮጵያውያን የአየር ኃይል ባልደረቦች፤ ከድሬዳዋ ኮብልለው ኤርትራ ገብተዋል። ይህ የሆነው ከ 
13 ቀን ገደማ በፊት ሲሆን ፤ ከሰሞኑም ሌሎች 4 የአየር ኃይል አባላት ኬንያ ገብተው ተገን መጠየቃቸው ተወርቷል። ስለዚህ ጉዳይ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል መረጃም ሆነ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት አድርገን ነበር ፤ ማግኘት ግን አልቻልንም። በኬንያ መገናኛ ብዙኀን ፤ በጋዜጣ፤ ራዲዮም ሆነ ቴሌቭዥን ምናልባት የተወሳ ነገር አለ ወይ በማለት ፣ አጠያይቀን ነበር ።

ሻምበል ሳሙኤል ግደይ የተባሉት አብራሪ ከ 2 ባልደረቦቻቸው ጋር Mi 35 በተሰኘው የጦር ሄሊኮፕተር ኮብልለው ከኢትዮጵያ መውጣቸው በተነገረ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ 4 የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ፤ ወደ ኬንያ በመኮብለል በዚያ የፖለቲካ ተገን ጠየቁ መባሉ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። የጋዜጠኞች መሳደድ ፤ እሥራትና የመሳሰለው ነበር በሰፊው ሲያነጋግር የቆየው፤ አሁን ወታደሮች ፤ እዚህም ላይ የጦር አኤሮፕላን አብራሪዎች ኩብለላ በቀጣይነት መካሄዱ ፣ ምክንያትን የሚያጠያይቅ ይሆናል። ምላሹን ከራሳቸው፣ ከኮብላዮቹ አንደበት መስማት እስኪቻል ድረስ! ይሁንና ፣ 4 የአየር ኃይል ጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ኬንያ ገቡ ስለመባሉ በዚያች ሀገር መገናኛ ብዙኀን የተገበ ጉዳይ ይኖር ይሆን ፣ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ----

ጋዜጠኞች ይጽፋሉ ይናገራሉ ፤ ያስተምራሉ ሒስ ይሠነዝራሉ፤ አግባብነት ባለው ጉዳይ ላይ! ሙያቸው ነውና! ዴሞክራሲ በሠፈነባቸው አገሮች ፣ ለሕብረተሰብ ብቻ ሳይሆን በሥልጣን ላይ ለሚገኝ መንግሥትም ተፈላጊዎች ናቸው! ።
በአንድ ሀገር ሕብረተሰብ ውስጥ ነጻ የሐሳብ ልውውጥ ሲኖር
ለሀገርም ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽዖ አለውና! ዴሞክራሲን ከልብ ባልተቀበሉ ፤ ወይም የዴሞክራሲ ጸር በሆኑ አገሮች ግን ጋዜጠኞች እንደ እክል መታየታቸው የታወቀ ነው። የጋዜጠኞችን ያህል በቀጥታ የማያጋፈጡ ወገኖች ተቃውሞን በኩብለላ ሲገልጹ ምን ማለት ይቻላል? ምን የከፋ ችግር ቢያግጋጥም ይሆን?
ኬንያና ኢትዮጵያ ፣ በመከላከያ የጋራ ትብብር ውል የተፈራረሙ አገሮች ናቸው። ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አንስቶ የቀጠለ ጉዳይ ነው። የጦር ኃይል አባል የሆነ ሰው ከብልሎ ኬንያ ቢገባና ተገን ቢጠይቅ አደጋ ይኖረዋል?
Source: DW.DE

No comments:

| Copyright © 2013 Lomiy Blog