ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር። 

 እንግዶቹ አልመው የሚተኩሱ፣ አስበው የሚገድሉ አልመሰሉኝ አሉ። የሚያስቡበትና የሚያልሙበት ሕሊና የሌላቸው ፍጥረታት አድርጌ ላያቸው አልደፈርሁም። ባይሆን ሁሉም ጠላታችሁ ነውና አንዲት ጥይት ጮኸች ወይም አንድ ሰው ትንሽ ድምፅ አሰማ “በለው” በሚል መዘውር የተዘወሩ “መዘውራን” በመሆን በሳሩም በቅጠሉም ኤኬ47ቱን ማንጣጣት ያዙ። ያን ጊዜ በአእምሮዬ ጥግ በምትገኘው የማስታወሻ ሰሌዳዬ ላይ “ይኽ ቀን ገሐነም ባዶውን ያደረበት ዕለት ነው” ብዬ መዘገብሁ። እነዚህ ሰዎች እንደ መሪዎቻቸው በጥላቻ የተጠመቁ ከሆኑ መመለሻው ይቸግረናል። ከቶ ከየት ተነሥተን የት እንደርስ ይሆን? የማልረሳው ማስታወሻዬ ነው። 

  የጥንቱ ጋዜጠኛ ግዮን ሐጐስ ጄኔራል መንግስቱ ንዋይ ተከሰው ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ሪፖርተር ሆኖ ተመድቦ ነበር። ያን ጊዜ እኔ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርሁ። መሬቱ ይቅለለውና ግዮን ሐጐስ ስለ ጄኔራል መንግስቱ ሲያወራኝ “በንግግራቸው መሐል ኰራ ብለውና ችሎቱን እየቃኙ ዓይናቸውን- አራት ማዕዘን እየወረወሩ- “ የተናቀ ከተማ በአህያ ይወረራል” ይሉ ነበር። ( በነገራችሽን ላይ ጄኔራል መንግስቱ አንድ ዓይናቸው ጠፍቶ ነበር። በወንድማቸው በአቶ ገርማሜ ንዋይ በተተኰሰባቸው ጥይት)  የአህያን ሠራዊት ወግ - በቁሙና በእርቃኑ -እንደገና የሰማሁት ከባድመ ጦርነት በኋላ - ከባድመ ጦርነት ጋር ሲዘገብ ነው። የጦርነቱን ዳፋ- ድልና ሽንፈት - ውጤትና ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ ያካተተ አንድ ጥናት እንደሚለው በራስ ስዩም የፈረስ ስም በምትጠራዋ “በይርጋ ጉብታ” ትራያንግል- በባድመ በተደረገው ጦርነት በፊተኛው ረድፍ ተሰልፈው የቀዳሚ- ሰማዕትነትን ሙያ የተወጡ 36ሺህ ኢትዮጵያውያን አህዮች ናቸው። ግፍ የተፈፀመባቸው እንስሳት ይባሉ?..ከጥናቱ እንደ ተረዳሁት ከአርባ ሺህ በላይ የሚሆኑ የሰሜን- ምዕራብ ኢትዮጵያ ገበሬዎች የኢሳይያስ ሠራዊት እንደ ድንች በዚያ አካባቢ የቀበራቸውን ፈንጂዎች እንዲያመክኑ ተደረገ። በአጭሩ አህያውም “ሰውም”- በወያኔ ትርጉም አማራ ሰው ከተባለ- በፈንጂ ማሳ ላይ እየተንደባለሉ አለቁ። አንድ ቀን ነፃነት ከተመለሰ ለዚያ ሁሉ ሕዝብ ውሎ ይደረግ ይሆናል። ለአህዮቻችንም ጭምር! 

 ይህን የጦር ሜዳ መረጃ በቅርቡ ያገኘሁት አይደለም። ዜናው ከዓለም ኅብረተሰብ ተደብቆ የቆየበትን ሁኔታ ሳስብ ግን በውስጤ ያለውን ክርስትና ጌታ ፍትሕ ወደ መጠየቁ አዘነብላለሁ። በዚህ ዓይነት ይህን ሁሉ ሕዝብ ያስጨረሱትን እኩያን ወገኖች ተፋረዳቸው ማለት ኅጢአት ነውን? ብሎ ግማሽ እኔ ይጠይቃል። ግማሽ እኔ ደግሞ ክርስቲያን ፍርድ አይጠይቅም። ምሕረት እንጂ። ጌታም ገዳዮቹን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ይለኛል። አሁን ከሕሊናዬ ጋር ወደ መታረቁና ትክክለኛውንም መንገድ ወደ መከተሉ ነኝ። ከሰባት ጊዜ ሰባት በላይ ይቅር ብለናቸዋል። ስለዚህ ወሎዬ ዘመዴ እንደሚለው “ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ” ይስማማኛል። እናንተንም ይስማማችሁ። እስኪጨርሱን እንቆይ? ጋንዲንና ማርቲን ሉተር ኪንግን እንርሳቸው። ሙሴ ይሻለናል። 

 እንዲህ ዓይነቱን ዜና ታላቅ ወንድማችን (ቢግ ብራዘር) አልስማም? አላወቀም? በቢሊዮን በሚቆጠር የሳር ክምር ውስጥ የወደቀች መርፌ ዋሽንግተን ተቀምጦ ዴዴሳ በረሃ ለሚያይና ለሚለይ የሲአይኤ ሰላይ ሠላሳ ስድስት ሺህ አህያና አርባ ሺህ የሰሜን ምዕራብ ነዋሪ ህዝብ በፈንጂ ማሳ ውስጥ ተንከባልሎ ሲያልቅ አያውቅም “አላወቀም” ብለን የምንገኝ ተላላዎች ነን..? ሐቁ ወደዚህ ሳይሆን ወደዚያ ነው። ይልቁንም የሾሙአቸው አምባገነኖች በመድረኩ ላይ እስካሉ ድረስ ምንኛ እንደሚቆረቆሩላቸው፣ ምንኛ ምሥጢር ጠባቂያቸው ሆነው እንደሚቆዩ..ነው የሚገባን። አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ ከኢትዮጵያ በኩል ያለውን ሰብአዊ ኪሣራ በአንዱ መጽሐፉ ይገልጥልናል። 98ሺህ ይለናል። በመቆርቆር ይሁን ወይም የኤርትራን አሸናፊነት ለመግለጥ አይታወቅም። ሃይማኖቱን አልጠይቅም። ከሕሊና ጋር አልተፈጠረም ደግሞ አልልም። አለዚያ በማን ላይ ትከስሰዋለህ? ከአነስተኛ የሚሊተሪ ሳይንስ ንባቤና ከኤርትራ ግንባር ሰልፌ እንደምረዳው ግን አንድ ሠራዊት ሁነኛ የማጥቂያ ግንባር ይዞና ቀጣናውን በፈንጅ አጥሮ ከተቀመጠ ለማጥቃት የሚመጣው ኅይል ሌላ ስልት መከተል አለበት። ጥበቃው የሳሳ ስፍራ መምረጥ አለበት። እርድ አዘጋጅቶ የተቀመጠውን ኅይል ከዚያ ምሽግ ማስወጣት ዋናው ታክቲክ ነው። በአድዋ ማርያም ሸዊቶ ላይ አጤ ምኒልክ ይህን ነበር ያደረጉት። ለወያኔና ለመለስ ዜናዊ ያንን ያህል “አማራና ኦሮሞ” ማስጨረስ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ኪሳራ ሆኖ አልታየም። ኖሮ አይጠቀምበትም በሞቱም አይጐዳም!  በፈንጂ አማካይነት ብቻ ሳይሆን እንዲሁ የወያኔ ሰፈርም ሆነ የኤርትራው ግንባር ዘመናዊ መሳሪያ ማገዶ ሆነው ያለቁት ስንት የሚሆኑይመስላችኋል? እንደ ወጡ የቀሩትን ወገኖቻችንን የእልቂት ሁኔታ (ወሬ) የሚያቃምሰን ለምንና እንዴት ጠፋ?..ከጦርነቱ - ከእሳቱና ከእልቂቱ አምልጦ መርዶውን የሚያሰማንማ አልነበረም። እነዚህ በየዕለቱ በእጃቸው ላይ ትኩስ ደም ያለባቸውና ራሳቸውም “ትኩስ ደም ትኩስ ደም” የሚሸቱት አምባገነኖች እኛ ከምናስበው በላይ የሰለጠኑባቸው ተንኮሎች ሞልተዋል። ዊንስተን ቸርችል ከጆሴፍ ስታሊን ጋር የሰነበቱባቸውን ቀናት የምታውቁ ይመስለኛል። በጦርነቱ ወቅት ጄኔራ ሊዝሞ ስታሊን፣ ፕሬዚዳንት ሩዝቬልትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ዊንስተን ቸርችል ለተወሰኑ ቀናት በካይሮ በቆዩበት ጊዜ የተፈጠረ ነው። ቸርችልና ስታሊን በጨዋታ ተጠምደው ሳለ ንጥረ ነገሩን (ቮድካና ብራንዲ) ክፉኛ አጥቅተው ኖሮ የሚናገሩት ሁሉ የማይያያዝ - የእብድ ወግ ይሆናል። እንዲያውም ራሳቸውን መቆጣጠር ስላልቻሉ ከአስሩ የስታሊን አንጋቾች አምስቱ ቸርችልን፣ አምስቱ ደግሞ ስታሊንን ክንፍ ክንፋቸውን ይዘው ወደየ ክፍላቸው ወስደው ያስተኙቸዋል። በማግሥቱ ማለዳ ስካሩ ብዙም አልተለያቸውም። ቸርችል ደግሞ በታሪክ ጸሐፊዎቻቸው እንደሚነገረን ገላቸውን ሲታጠቡ እንኳ ሲጋርና ብራንዲ አይለያቸውም። ስለዚህ ከሶቪየቱ መሪ ጋር ሲገናኙ ‘እንደ መጠጥ ያለ አዋራጅ ነገር የለም! ትናንት ተዋረድን። ቢያንስ የርስዎ አጃቢዎች አይተውናል። ተዋርደናል!” ሲሉ ስታሊን “ኒየት! ኒየት! ማንም አያወራብንም። ትላንት የነበሩት ሰዎች እኮ የሉም” አሉ ይባላል። የሰው ነፍስ እጅግ ርካሽ በሆንበት ኢትዮጵያ ሥርዓቱ አንድ ሰሞን ሰማየ- ሰማያት ያጓናቸው ሰዎች በሌላ ወቅት አይኖሩም። ይልቁንም አንዱ ፍልስፍናቸው “ለወሬ ነጋሪነት ማንንም አለማትረፍ” የሚል ነው። እንዲያውም ለታላላቅ የስለላ ድርጅቶች (ኬጂቢ በተለይ) ይነገርላቸው እንደነበረው “ወያኔ እስከመቃብርህ ይከተልሃል” የሚል የውስጥ አዋቂዎች ግምት አለ። አደገኛ ከሆንክ የሞራልን ሕግጋት ሁሉ እየጣሱ ይከተሉሃል። ያጠፉሃል። እስከ ገሐነመ እሳት ይሸኙሃል። 

   የአዲስ አበባ ቃጠሎ ተብሎ ከሚጠቀሰው የግንቦት መድኅኔ ዓለም ማግስት የነበረውን እናንተ ከረሳችሁት እኔ አስታውሳችኋለሁ። በዚያን ዕለት በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግቢ ተገናኝተን አሳብ ለአሳብ የተለዋወጥነው የቀድሞ አምባሰደርና የሃይማኖት ትምህርት እውቀቱ ላቅ ያለ ወዳጄ ምናልባት እንደኔው ያወራው ይሆናል። ልዩ ትርኢትና ልዩ መገለጥ ተብሎ የተወራለት- ማርያም ልጅዋን ታቅፋ (ምስለ ፍቁር ወልዳ) በሰማዩ ላይ እየታየች ነው መባሉ ሲሆን ያንን አየን የሚሉትን ልዩ ቅዱሳን እንበላቸውና ሁለተኛው ከነትርጓሜው አብሮን አለ። በአእምሮዬ ቀርቶአል። ነገሩ እንዲህ ነው። በዚያን ዕለት የታየው ቀስተ ዳመና በቀጥታ ከሰማይ ላይ ወርዶ ምድሪቱ ላይ ተተክሎአል። አጠገቤ ያለ ሰው ሁሉ “እግዜሩ ሊታረቀን ነው። የደግ ቀን ምጽአት ምልክት ነው። እግዜአብሔር ዳግመኛ ምድርን በጥፋት ውኅ አላጠፋትም ብሎ ለኖህ ቃል ኪዳን ሲገባለት እንዲህ ያለ ቀስተ ዳመና በምልክትነት ሰጥቶታል..” ሲሉ እሰማለሁ። ይሁንና ያ የቀድሞ አምባሳደር ወዳጄ ጐተት አደረገኝና “በእኛ ቤተክርስቲያን እምነትና በተለይም በአበው ሊቃውንት ትርጉም መሠረት ይህ ቀስተ ደመና በጥሬው አይተረጐምም። የእልቂት፣ የስደት፣ የደም መፋሰስ ምልክት ነው። ስለዚህ ከሚመጣው አደጋ ሁሉ እንዲሰውረን መጸለይ አለብን፡፤ ቃሌን እንዳትረሳ” አለኝ። ስሙን ብገልጸው ደስ ባለኝ ነበር። የወቅቱ መኳንንት ያንገላቱታል ብዬ ፈራሁለት እንጂ። 

   እንደ ሕልም፣ ትንቢትና ከላይ የጠቀስሁትን የተፈጥሮ ንባብ (ከነትርጓሜው) በተመለከተ አንዳንድ ሳይኪያትሪስቶችን መጠቃቀስ ይቻላል። ፍሮይድን፣ ፓቭሎቭን..በማንበብ ከትርጓሜው ላይ ለመድረስ -አለዚያም ከንቱ እምነትነቱን ለመግለጥ አይመችም። እነሱም አላጠኑትምና። ለምሳሌ እጅግ ጣፋጭ የሆነችውን የሐዲስ አለማየሁን “ትዝታ” ያነበባችሁ ትዝ የሚላችሁ ቁም ነገር አለ። አቶ ሐዲስ እንደሚገልጡት ከጠላት በፊት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስኳላ ሲያስተምሩ አንድ ጥቁር እንግዳ ከቤታቸው ከች ይላል። እንዲያው በችኮላና በቁሙ “ሐዲስ! ኢትዮጵያን ጠላት ይወርራታል። አንተም ትዘምታለህ!” ብሎአቸው ይሄዳል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ይኸው ወዳጃቸው ከአባ አሥራት ገዳም ሲመለስ ወደ ሐዲስ ዓለማየሁ ቤት ይሄድና “ላጫውትህ አልችልም። እቸኩላለሁ። ሐዲስ! ኢትዮጵያ ትወረራለች። አንተም ወደ ጦር ሜዳ ትሄዳለህ። ትዘምታለህ!” ይላቸዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ የጠላት ከምሥራቅና ከሰሜን መንቀሳቀስና ኢትዮጵያን መውረር ወሬ አየሩን ሞላው። የጐጃሙ ገዥ ራስ እምሩ የጐጃምንና የጐንደርን ጦር እየመሩ ወደ ሽሬ ግንባር ይዘምታሉ። ሐዲስ ዓለማየሁ የጦር ሜዳ የፕሮፓጋንዳ ሃላፊና ለጥቆም የብርቱ ምሥጢር ተላላኪ ሆነው ሲሠሩ ቆዩ። ሰውና ከብት በመርዝ ጋዝ ጢስ ያለቀበትን- የከብትና የሰው ደም ተቀላቅሎ ወንዙን (ተከዜን) ያስነፈጠበትን ሁኔታ ጥሩ ገላጭ የሆነችውን የሐዲስ ዓለማየሁን “ትዝታ” ያነብቡአል። (ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ መጽሐፍ ቀስቃሽነት የፈጠራትን “እስከዳር” መጽሐፍን ልመርቅላችሁ። ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ የሆነው ሻለቃ ዳዊት በቅርብ ጊዜ የተጻፉ ታሪካዊ ልብ ወለዶች አንጋፋ ልትባል የምትችል መጽሐፍ በመድረሱ ባርኔጣዬን አነሳለታለሁ) 

 “አምልኮ ወይም ምልኪ ነው” ልትሉኝ ትችላላችሁ። የፈቀዳችሁትን በሉኝ። ያ አምባሳደር (አ.ወ.አ) ግንቦት 28 1983 የነገረኝ የቀስተ ደመና ትርጉም እንደ ወንጌል ቃል አብሮኝ አለ። ወያኔ በምንም ጊዜና ቦታ፣ ሁኔታና እቅድ ረገድ የሚፈጽመውንና ያቀደውን ከመግለጥ ሸብረክ ያለበት ጊዜ የለም። ደበሎ ሰቅሎ ፍላጐቱንና ግቡን ይለፍፋል። ከዚያ ዓላማው ደግሞ ፈቀቅ ያለበት ወይም በመጠኑም ቢሆን አቋሙን ያለዘበበት አጋጣሚ አልነበረም። ከዚህ ውስጥ- ማለትም ከዚህ ጽንፈኛና ሕመምተኛ መንግሥት አውራ ግብ (ማስተር ፕላን) ውስጥ ዋነኛው አንዱን የተወሰነ ሕዝብና ሃይማኖት ማጥፋት ነው። ሕዝብን ለማስተዳደር (በመሰረቱ ለመግዛት) የመጣ አካል አንዱን የቋንቋ ክፍልና (ብሔረሰብ ለማለት የትርጉም ስሕተት አያለሁ) ሃይማኖቱን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ለመደምሰስ እቅድ እንዳለው ሲናገር - በግልጽ በአደባባይ ሕዝቡና ምሑሩ፣ ወጣቱና አእሩጉ፣ ቤተ ሃይማኖቱና ዓለምም በነቂስ አንዲት ትንፋሽ ተቃውሞ አላሰሙም። እንደኔም እንዲህ በሰላም ወጥተው ለመግባትና ሕሊና የሚያዝዘውን አውጥተው ለመናገር የሚችሉ ሁሉ ስለ “አማራው” እልቂት ማውሳት ከወቅቱ የፖለቲካ ፋሽን አንጻር ኋላ ቀር ስለሚያሰኝ ዝምታን መርጠዋል። ሁላችንም- ኦሮሞውም፣ አማራው ራሱም፣ ከምባታውም፣ ሌላ ሌላውም ኢትዮጵያዊ -እኛም የምንጫጭር ሰዎች ስለማንም- በተለይም ስለ አማራው ሕይወትና ንብረት፣ መብትና የግለሰብ ነፃነቱ መጻፍን-ልድገመውና ከፖለቲካው ፋሽን ወደ ኋላ መቅረት አደረግነው። ይኸ ደግሞ አዲስ “ግንዛቤና” አዲስም የፖለቲካ ፈሊጥ አይደለም።
      መለስንና አቋሙን የሚያውቁ ሰዎች በምስክርነት እንደሚያረጋግጡት የሰውዬው ቀዳሚ እምነት “አማራ ከገጸ - ኢትዮጵያና ከገጸ- ምድርም መጥፋት አለበት። አንዳንድ ጊዜ አስተዳደጋችሁና ባሕላችሁ በፈጠሩባችሁ ስሜትና ዝንባሌ ምክንያት ወንጀሉን የሚሰሩት ሰዎች የማያፍሩበትን ኅጢያት እናንተ በመጻፋችሁና በመቃወማችሁ ጭብጥ ታህል ትሆናላችሁ። እዚህ አካባቢ እንደታዘብሁት አንድ ጠንካራ ዜጋ “ አንድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ለምን የጥፋት ዒላማ ይሆናል? ” በማለቱ አንዳንዱ ሰው “የትግሬ ጠላት” አድርጐ ይስለዋል። መለስ ዜናዊ፣ ታምራት ላይኔ…አማራንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ስለማጥፋት ሲናገሩ ምን ተሰማን? ምንስ አልን? ለመሆኑ ትግራዩን ሕዝብ በጠቅላላውም ባይሆን አድዋውያንን ስለ ማጥፋት ቢነሳ ዝምታ የዜግነት ግዴታ ነው እንላለን? ከፖለቲካው ፋሽን ውጭ ነውና በዚያው እንቀጥል ይባላል? የዛሬው የፖለቲካ ፋሽን አማራን ለኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ መክሰስ፣ በኅላፊነት ማጋለጥና መዝለፍ ነው። ያ ቢበቃ ደግ ነበር። አንዳንዶች በእምነት፣ አንዳንዶች ለጣቢታ (ኩርማን እንጀራ) አንዳንዶች ደግሞ “እንደ ንጉሡ አጐንብሱ” በሚለው ፍልስፍና መሠረት የሚያሰሙት አዝማች ነው። ለመሆኑ ሕዝብ እያለቀና የበለጠም እንደ ተደገሰ ይሰማችኋልን? 

   ፕሮፌሰር አሥራት የመላው አማራ ድርጅትን ሲመሰርቱ ከምሁራን መካከል ወዳጆቻቸው የሆኑ ጥቂት ሰዎች በግል እንዳነጋገሩአቸው አውቃለሁ። እኔም በግሌ ከእሳቸው ጋር ባለኝ ራፖርና በተጨማሪም ምክትላቸው ከነበሩት ከአቶ ኅይሉ ሻውል ጋር ፖለቲካ ወደ ጐሳ በሚወርድበት ጊዜ ስለሚከተለው ጣጣና በተለይ የእነሱ ወያኔ በፈጠረው ጉድጓድ ውስጥ መግባት አርአያነቱ የሚያስከትለውን ችግር ሁሉ ዘርዝሬ ሞግቻቸው ነበር። ሙግቴ የበለጠውን ከፕሮፌሰር አሥራት ጋር ሲሆን በእሳቸው በኩል ያለው ጥረት በአርሲ፣ በሐረርጌ..ወዘተ እያለቁ የሚጮህላቸው ያጡትን አማሮች መብት ለመጠበቅ መሆኑንና የፖለቲካ ስልጣን የመፈለግ አዝማሚያ እንዳላሳዩና ወደፊትም እንዳማያሳዩ ገለጡልኝ። ለሁለቱም አንጋፋ ዜጐች በተለያየ ሥፍራና ጊዜ በኢትዮጵያ ስም የሚቋቋም የፖለቲካ አካል (ግንባር፣ ድርጅት ወይም ፓርቲ) ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መብትና ነፃነት ስለሚቆም መአሕድ ወደ ፓርቲ የሚያደርገውን ሽግግር ቢያቆሙት እንደሚሻል ለመምከር ሞከርሁ። ምከሬ ደካማ ሆኖ የመአሕድ ፓርቲ ተመሰረተ። ከኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊጠፉ የማይችሉት ታላቅ ዜጋም የዘመናቸው የአገር ሰማዕት ሆኑ። ወያኔ እስከመቃብር ተከተላቸው። በፖለቲካው አምባ እንደ አባዩ የሩሲያ መነኩሴ እንደ ራስ ፑቲን ይቆጠሩ የነበሩት አባ ጳውሎስ ደግሞ ለአሥራት በተቆፈረው መቃብር ዘልለው ለመግባት ፈልገው ነበር ይባላል። አይ ደበበ እሸቱ! በሞታችን ቴያትር እየተሰራብን ነው። ይኸ የአንድ ሰው ሞት አልነበረም። የሺዎች እልቂት እንጂ! 

    በእኔና እንደኔ ከቀዩ ፍልስፍና መልስ ወደ መንደር መውረድን ዝቅጠት አድርገን ለተመለከትነው ወገኖች በመለስ ዜናዊ በተዘጋጁልን የጐሳ ጉድጓዶች ውስጥ እየሮጡ መወሸቅ አገሪቱን በመበጣጠስ ረገድ ተባባሪ መሆን ይመስለኛል። ይሁንና በዚያው ጊዜ ውስጥየታዘብሁት አንድ አስገራሚ ነገር የማላስባቸው ሰዎችን ከማላስባቸው ሰፈሮች ማግኘቴ ነበር። ለተወሰኑ ሳምንታት ሳይታሰር የቆየና በነበረው ሥፍራ እኔንና ሌሎችን የኢንፎርሜሽን ድርጅቶች ኅላፊዎች እየሰበሰበ ከማለዳ እስከ መንፈቀ ሌሊት እጅ እጅ የሚል ገለጣ ሲሰጠን የኖረን የደርግ አባል ከአንድ የጐረቤት ልቅሶ ላይ አገኘሁ። “ነፍጠኛ….ነፍጠኞች…ብሔር- ብሔረሰብ..ሕዝቦች ” ሲል ሰማሁትና “ጓድ ማለቴን ትቼ ኦቦ ልበልህ…እንደ አመጣጥህና ፍጥነትህ ወደፊት አንዳች አደጋ ካልደረሰብህ የኢህአዴግ አመራር አባል የማትሆንበት ምክንያት አይታየኝም። ቋንቋቸውን ብቻ ሳይሆን ጽንሰ-አሳቡንም …ዓላማቸውንም ዓላማህ በማድረጉ ረገድ ፈጥነህ ራስህን አስተካክለሃል። በእኔ በኩል ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ በጐሳ በመሸንሸኑ ረገድ የለሁበትም። እነሱ ይዘውት የመጡትን ይህን በሽታ ደግሞ ሁላችንም መድን ተከትበን የምንከታተለው መስሎኝ ነበር” አልሁት። የደርግ አባሉ ሌሎቹ አንጋፋ የደርግ አባላት ከተያዙ በኋላም ለሳምንታት በከተማው ውስጥ ሲነዳ ዓይን ስቦ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። በአጭሩ ግን ጥቂት የማይባሉ ከእኛው “የአብዮቱ ሰፈር” ጭቃው ሳይነካቸው፣ ርእዮተ ዓለሙም ሳይጠልፋቸው በአንዳች ኀይል ወደ ወያኔ ሰፈር- የድል አምባ - የተሻገሩ በርከት ያሉ ነበሩ። አሁንም የሉም ትላላችሁ? ሌሎችም አሉ እንጂ! የኢሰፓ አባል ለመሆን ብዙ መከራ አድርገው በሞራላቸው፣ በሥራ አፈጻጸማቸው፣ በየቢሮውና ፋብሪካው በነበራቸው ነውር ተንቀው የቀሩም ግመልና ዝሆን የሚያስገባ አዳራሽ አግኝተው ሲሣይ ማፈስና የጠሉትን መርገጥ ሆነላቸው። የልዩ ዐቃቤ ሕግ ሹም የነበረውን ግርማ ዋቅጅራን ለአብነት ይጠቅሱአል። እነዚህ ሁሉ ዜጐችን ተበቅለው፣ አዋርደውና ገድለው ቢበቃቸው አንድ ነገር ነበር። አገርን በማፍረስና በመናዱ ረገድ ርኅራኄ የተለያቸው ሆኑ! እስመ ዓለም ምሕረቱ! 

     የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ሲሰባሰቡ በአብዛኛዎቹ በጋዜጠኝነት ተገኝቻለሁ። ገና በነፃነት ጎዳና ብዙ ያልተጓዙት “የአፍሪካ አባቶች” ተብለው የሚጠቀሱት መሪዎች መላልሰው ሲናገሩ እንሰማቸው የነበረው ጐሳ በፖለቲካ፣ ፖለቲካም በጐሳ ውስጥ ሲገባ ሰፊ ራእይ ያየንላት አኀጉራችን መመለሻ ወደሌለው እንጦሮጦስ ትወርዳለች እያሉ ነበር። ያ ልክፍት በእኛ ዘንድ እንደ ልዩ ነገር ሳይቆጠር አልቀረም። እንዲያውም የረጅም ዘመን የነፃነት ኑሮአችን ሰፋ ካለ “ኢትዮጵያዊነት”ና አገራዊ አመለካከት እርከን ላይ አድርሶናል ብለን እንወያይ ነበር። በኩራት! 

      ወያኔ ከከፍተኛ ማማና ኅብረተሰባዊ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰናል፣ ሕዝባችን የአንድነት መሰረቱ ጽኑ ነው በምንልበት ሰዓት ነው የተናቀና እጅግ ኋላቀር የፖለቲካ ሥርዓት አምጥቶ የዚያ ባዕድ አምልኮ “ጊኒ ፒግ” ያደረገን። በእኔ በኩል ይህን ሒደት የኢትዮጵያ ውርደት፣ የፖለቲካም መዝቀጥ አድርጌ አየዋለሁ። የመለስ ዜናዊ አድናቂዎችንም የምፋለማቸው በዚህ ዓቢይ ነጥብ ነው። በዚያ ላይ ነው እልቂቱ፣ አገር ሸንሽኖ መሸጡ፣ ታላቂቱን ኢትዮጵያ በአረቡ፣ በሕንዱ፣ በፓኪስታኑ..በቻይናው እግር ሥር ማውረዱ የመጣው። እኔ የመጣሁበት ፖለቲካ (ኢሠፓ ነው አትበሉኝና) ሁሉን ሠርቶ አደሮች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ዜጋ የሚያስተሳስረው - በአንድነትና በአንድ ዓላማየሚያስተባብረው፣ የኢትዮጵያ ልጅነትን የሚያራምደው አንድ ለሁሉም ሁሉም ለአንድ የሚያቆመው የዜግነት መሠረት ነው። እኔከአድማስ ባሻገር የማየው ፖለቲካ በኢትዮጵያ ፍትሕ የነገሠበት፣ ሰው በሰው የማይበዘበዝበት ሥርዓት ነው። ሰውን የሚያከብር፣ የዜጋውን ሰብአዊነትና ሉአላዊነት - ባለስልጣንነት የሚያውቅ ሥርዓተ መንግሥት ነው። የኮሚኒስት ሥርዓት ማለት አይደለም። ከዚያ በላይ የሚያበራ፣ ከዚያ በላይ እምነት የሚጣልበት ሥርዓት ነው። የፖለቲካ ሥርዓት ወይም ሥነ መንግሥት “ኢዝም” ብቻ አይደለም። ከኢዝም በላይ አስባለሁ። አስቡ! ከ1960 ጀምሮ እንዲህ እንዲህ እያለ እየተጠረቃቀመ የሚመጣውን አደጋ በማጤን ኢትዮጵያዊነትና ብሔራዊ ስሜት ከምንም በላይ የሚያበራ ኮከብ ይሆን ዘንድ በግንባር ቀደምትነት ሞክረን ነበር። ውስጥ ለውስጥ ይህን ሲታገሉ የነበሩ ኅይሎች ናቸው ይፋ ወጥተው - ይፋ ግፍ የሚፈጽሙት። አልተኙልንም። አንተኛላቸው። እየገደሉን ናቸው። ጠላትህን መግደል ነው ያልጀመርኸው። 

      ልምዱንና የፖለቲካ ዓላማውን ከተማሪ እንቅስቃሴ ጋር ከሚያዛምደው ትውልድ መሐል አይደለሁም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሕግ እውቅናና የማይገሰስ ሕዝባዊ ሥልጣኑ ከታወቀ የምርጫ መብቱና ክብሩ ከተረጋገጠ እንዲበቃኝ ወስኛለሁ። ስለዚህ ከአጠቃላዩ ነጠላውን በመውሰድ እገሌ መታወቅ ያለበት በጐሳው መሆን አለበት ከሚለው ሰፈር ሥፍራ እንዲኖረኝ ፈልጌ አላውቅም። አንዳንድ ሰዎች ይኸ “ናኢቭ አሳብ ነው” ይሉ ይሆናል። የዋህነት አይደለም። የኦሮሞ ነፃነት፣ የአማራ ነፃነት፣ የጉራጌ ነፃነት፣ የትግሬ ነፃነት በሚለው ሰፈር የለሁበትም። በቶሎሳ፣ በጫኔ፣ በጠንክር፣ በሐጐስ…ነፃነት ግን አምናለሁ። እዚህ ላይ እንረፍ። 

      አሁን ደርሶ የመጣው ልክፍት ለአንዱ ተሰጠ የሚባለው ነፃነት ሌላውን ከገጸ- ምድር የሚያጠፋው ሲሆን ወጣ ብለህ (አፈፍ ብለህ) ከትግሉ ግንባር ውስጥ የሚያሰልፍህ ነው። የፖለቲካው ፋሺን የሚጋብዘው የተወሰኑት የቋንቋ ክፍሎች ተነስተው ከተላለቁ በኋላ የተወሰኑት ደግሞ የመላዋ ኢትዮጵያ ገዢዎች ይሆኑ ዘንድ ነው። ወጣ እናድርገውና አማራና ኦሮሞ ሲጫረሱ፣ ይልቁንም የገዥነት ሚና ነበረው የሚሉት አማራ እስኪያልቅ ድረስ ከተመታ አብዛኛው የአገዛዝ ችግር ይቀረፋል። ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ሰዎች በአእምሮ ቅልጥፍናና በምሁራዊ ዝንባሌው ሲያደንቁት እሰማለሁ። እንዲህ ያለ የተበላሸ እንቁላል በአእምሮው ውስጥ ይዞ የኖረ ሰው “ቀልጣፋ፣ ምሁር..አሳቢ..ፈጣን…” የሚሉ ቃላትን በእሱ ላይ የሚነሰንሱ ሰዎች ናቸው ሊታዘንላቸው የሚገባ። ትልቁና ዋና ዓላማው የሕዝብ ፍጅት፣ የአገር መበታተንና የሚጠላውን ሁሉ ማጥፋት የሆነውን ሰው እስከ ማወደስ የሚደርስ ሰው በግድ ሳይክያትሪስት ማየት የሚገባው ነው። ከቀን አንድ ቀን ጀምሮ የነበረው ሁሉ አስደንጋጭ ነው። እንደዚያ ግንቦት 28 ቀን 1983 የታየውን ቀስተ ደመና የእልቂት ደመና አድርጐ እንደ ተረጐመው አምባሳደር በአማራውና በኦሮሞው መካከል የሚፈጠር ፍጅት ያሳሰባቸው አባቶችም ነበሩ። “የፖለቲካውን ፋሽን” ሳልፈራ ሁለት የተከበሩ ዜጐች መኖሪያ ቤት ሄድሁ። አንደኛው ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ነበሩ። ሁለተኛው ደግሞ ቢተወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት ሲሆኑ ከጠላት በፊት ጀምሮ በአስተማሪነት፣ በዲፕሎማሲና በአገር አመራር ሰፊ ልምድና እውቅት ያካበቱ አባት ነበሩ። ሁለቱንም በተለያዩ ጊዜያት ቀጠሮ ይዤ አነጋገርኳቸው። ያን ጊዜ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ ዲማ የሚባል ሰብአዊ ፍጡር አማራ እያባረረ ይገድላል፤ በሐረርጌ በአሰቦት ነፍጠኛ ሁሉ እየተረሸነ ነው የሚባልበት ጊዜ ነበር። ያንን ደግሞ የሚያራግቡ፣ ትልልቁንና በጀግንነቱ የሚታወቀውን ኦሮሞ ጄኔራልና ራስ ሳይቀር በዘላን ቋንቋ የሚዘልፉ ጋዜጦች ወጣ ወጣ ማለት የጀመሩበት ነበር። ይኸ አካሄድ ለቢትወደድም ለኮሎኔል ዓለሙም አልጣማቸውም ነበርና ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በማሰብ በሰፊው ተወያየንበት። 

     ሁለቱንም ጐምቱ ዜጐች ገጽ ለገጽ ማገናኘት አልቻልሁም። ዓላማችን ግን ኮሎኔሉ በኦሮሞ አባትነት፣ ቢተወደድ ደግሞ በአማራ አባትነት አደባባይ ወጥተው “ሕዝቡን ለማጫረስ የተጠነሰሰውን ሴራ በሚያጋልጥ መልክ እንዲያወግዙ ነበር። ሁለቱም የሚወክሉትን ኅብረተሰብ ባሕልና ሥርዓት ስለሚያውቁ ተቃቅፈው ፍቅራቸውን በመግለጥ፣ የሁለቱንም ታሪክና የደም ትስስር በማብራራት እያሳሰበ የመጣውን የፖለቲካ ደመና እንዲያከሽፉት ለመሞከር ነበር። በሦስተኛው ቀን ኰሎኔል ዓለሙ “ሁሉም ነገር ጥሩ ነበር። ትናንትና ከበቀለ ነዲ ጋር ስንነጋገርበት ከእኛ መካከል ወደ እብደት የወሰዳቸው አክራሪዎችን ይጠንቀቁ። እዚሁ አጠገባችን ያለውን..ሰው ይህን ቢያዋዩት ሊገድልዎ ይችላል። አላወቁትም መሰለኝ እንጂ አለኝ” አሉ። በዚህ የተነሣ ፕሮጀክቴ ወደቀ። እኔም አሜሪካ ከሚሉት አገር ገባሁ። ከአንድ የብስጭትና የጭንቅ መንፈስ፣ ከአንድ ማንም ያለመልሰልኝ ጥያቄ ጋር ቀረሁ። እንዲህ ያለውን ጭካኔና ጥላቻ ከቶ ከየት አመጡት? የተወሰኑ ባለስልጣኖች ልትጠላ ትችላለህ። አገር ሙሉ ሕዝብ- ግዑዝዋ አገር..እንዴት የጥላቻ ዒላማና የእልቂት ሰላባ ይሆናሉ? ለመሆኑ እነዚህ ዛሬ በወያኔ ገፋፊነት ከፍልፈል ዋሻ ወጥተው የሚጫጩት ትንንሽ ነፍሳት መጫረስና መፋጨት ለሕዝብ አንዳች መፍትሔ ይሰጣል ብለው እንዴት ሊያስቡ ቻሉ? ወይስ አጀንዳቸውንና የወደፊት ጉዞአቸውን ለምን በግልጽ አይነግሩንም? ሌላውም ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያ በቀር ሌላ አጀንዳ ስለሌለው ጅቡ- ቲበላው በልቶት ቄደር ለመጠመቅ ዝግጁ ሊሆን ይችላል። 

      በሰፊው ሲታይ ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የወያኔን ጡጫና ካራ ያልቀመሰ የለም። ኦሮሞዎች አውቀውታል። ጉራጌው፣ የደቡቡ  ኅብረተሰብ፣ አኝዋኩ…ጋምቤላው ተራ በተራ ሰይፍ ተመዞባቸዋል። ችግሩ አንዱ በሚረፈረፍበት ጊዜ ሌላው ሊጮኽለት አለመቻሉ ነው። ከእነዚህ የሕዝብ ክፍሎች መካከል የወጣነው አንዳችም ጩኸት ማሰማት ቀርቶ ጥቂት ጥቂት ተቆርቋሪነት የሚሰማቸውን ጭምር ተቃዋሚዎች መሆናችን ነው። አለዚያ በኢትዮጵያ አብዮት ዘመን የነበርን ሁሉ የወያኔን “ታላቅ ሴራ” እናውቃለን። ሰምተናልም። ከቶውንም እንደማስታወሰው የቀድሞው መሪያችን ጓድ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኅይለማርያም ሦስት ቀን በራቸውን ዘግተው የጻፉትን ዲስኩር እንድንሰማ ተደርጐ ነበር። የዚያን ዕለት ንግግራቸው “ወያኔ በአማራው ላይ ያነጣጠረ፣ እልቂት ማቀዱ..ከቶ ምክንያቱ ምንድነው?” የሚል ነበር። ከዚያ መንግስት የማይሻል የለም በሚል ብቻ የጓድ መንግሥቱን ንግግር አጣጣልነው።  ከሩዋንዳ የ1994 እልቂት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየትኛውም አገር ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት መከላከያ መዘየዱን ገልጦ እንደነበረ እናስታውሳለን። እንደ እውነቱ ደግሞ በዚሁ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ አባላት የነበሩ አምባገነን ሥርዓቶች በሕዝቦቻቸው ላይ ወደር የሌለው ጭካኔ ሲያሳዩና እልቂቶችንም ሲፈጥሩ ድርጅቱ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አናውቅም። ከ1975- 1979 በካምቦዲያ ከአንድ ሚሊዮን እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በገዥው (ካይመር ሩዥ) ሲጨፈጨፍ አንዳች ጠያቂ አልነበረበትም። በኋላም አረመኔው ፓልፓት ፍትሕን ፊት ለፊት ሳያይ በእርጅናና በበሽታ ሞቶአል። 

    በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ..በጉራፈርዳ..በወያኔና ባሰለፋቸው ጭፍሮቹ በጥይት የተቆሉትን ዜጐች ..ከዚያም በፊትና በኋላ በየሰበቡ በየአደባባዩ የወደቁትን ዜጐች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን የሚያስበልጡ ሰዎች አሉ። ብዙዎች እልቂቶች ደግሞ አደባባይ እንዳይወጡ፣ በየአገሩ በሚታወቁ የመገናኛ አውታሮች እንዳይነገሩ ተደርገዋል። ይኸም ባሰለፋቸው ልዕለ ኅያል ግፊት መፈጸሙ ምሥጢርነት የለውም። እስከናካቴውም ግዙፋን ማስረጃዎችን ይዘው የዓለምን ፍርድ ቤት ጥሪ የሚጠብቁ እንደ ሒዩማን ራትስዎች፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ጄኖሳይድ ዎች ወዘተ ያሉ ድርጅቶች ከነመለስና መንግሥታቸው ደጋፊዎች የሚደርስባቸው የጨለማ ጡጫ የሚቻል አይመስልም። ስለዚህ “አማሮችንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በጠላትነትና በአላስገዛም ባይነት ገዥም ተባባሪም ተስማምተዋል። ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረጉ ሰልፎች ላይ ተሳትፌ አውቃለሁ። ለስቴት ዲፓርትማንት ተወካይ መግለጫ የሚሰጥ ሲፈለግ እኔና ወዳጄ አረጋዊ በርሄ በግንባር ቆመን የሰልፉን ዓላማ መግለጥ ጀመርን። ወዲያው የአማራን የጠላትነት አቋም እንደ አንድ ነገር የተጋተው የመሥሪያ ቤቱ ሰውዬ “የአማሮች ሰልፍና የአማሮች አላማ ይገባናል” ይላል። ወደ አረጋዊ በርሄ እያሳየሁ “እሱ ወንድሜ ትግራዊ ከመሆኑም በላይ ቲፒኤልኤፍንም የመሰረተ ነው። የራሱን ድርጅት ፀረ ሕዝብነት በመረዳት ራሱን ያገለለም ነው። እኔ ደግሞ እንዲሁ ተራ ኢትዮጵያዊ ነኝ” አልሁት። “አገር አገር፣ ነፃነትና አንድነት…መብትና..” የሚል ሁሉ በአማራነት ይመደብ ጀምሮአል። ኢትዮጵያዊነትንም ሰብስበው ለአማራው አሸክመውታል። ስለዚህ ከአንዳንድ ፈረንጆች ጋር ስትነጋገሩ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ስለ አገሪቱ ክብር ካነሳችሁ “ማን መሆንህን አወቅሁት። አማራ ነህ” ትባላላችሁ። በእኔ በኩል ይህ አነጋገር የኦሮሞውም፣ የከንባታውም፣ የትግሬውም መሆን አለበት። እነዚህ ወገኖቼ በወያኔ ሰንሰለት እግር ከወርች ካልታሰሩ በቀር ይኽ እምነት የሁላችንም ነው። ከፋም ለማም፣ ጊዜ ፈጀ አልፈጀም ኢትዩጵያ የሁሉም እናት ትሆናለች። እስከዚያው የሚከፈለው ሰማዕትነት ግን በዛ። ከበሮ እየተመታ ነው። አላጋንንም። አንዲት ሰረዝ የአጋንኖ አልጨምርበትም። የጦርነትን አቅጣጫ እሱ ባለቤቱ እያዘወረው ነው እንጂ እልቂቱ ከተጀመረ ውሎ አድሮአል። “ተነስ” የሚልህስ 
ማነው? ተኝተሃል እንዴ ተነሥ የምትባለው? 

    ገብረመድኅን አርአያ ለብዙ ጊዜያት ብቻውን በምድረ በዳ የሚጮኽ ባህታዊ ሆኖ ቆይቶአል። ጓደኞቹን እንኳ ሳያስተርፍ፣ ለጥላቻቸው ዋጋ ሳይሰጥ ይህንን የኢትዮጵያ አንድና ዋነኛ የሕዝብ ክፍል ለመጨረስ የወያኔን እቅድ ገልጦልን ነበር። ምዕራፍና ቁጥር እየጠቀሰ። ከየትም አቅጣጫ ከማንም ግለሰብ ማስተባበያ አልተሰጠበትም። “በዓለም ላይ በአንዳች ሥፍራ አንድን የሕዝብ ክፍል ለመጨረስ የሚቀነባበር ሴራ ሲያጋጥማችሁ አመልክቱ” የሚለው ከሩዋንዳው እልቂት በኋላ የወጣ መግለጫ ነበር። 

     በኢትዮጵያ ሁኔታ በሁሉም ሕዝብ ላይ ለሚቀነባበረው ሴራ ፊሽካ ነፊው ወያኔ ነው። የእልቂት አሰልጣኙ ወያኔ ነው። እንደ ሩዋንዳ እልቂት ዝግጅት 1400 ካድሬዎችንና የግድያ ቡድኖችን አሰልጣኝና ቦታ ቦታ አስያዥ ወያኔ ነው። ምናልባት ተኳሾቹ ኦሮምኛ የሚናገሩ ወይም መናገር የሚችሉና በኦሮሞ ስም ኬላውን ለማለፍ የሚችሉ ይሆናሉ። ትርኢቱ የወያኔ፣ ደራሲው ወያኔ፣ መሪው ወያኔ! ዝግጅቱ ብዙ ዘመን ጠይቆአል። ወያኔዎች ለድርሰቱ አልተቸገሩም። ተስፋዬ ገብረአብ የተባለ ወጣት ፕሮፖጋንዲስት ትከሻ ላይ ኅላፊነቱን ሁሉ መጣል ውጤት ያስገኛል ብለው ጣጣቸውን ጨርሰውታል። ተስፋዬ በቃላት መጫወት ይሆንለታል። ቃላትን ከድንጋይ ጋር ያወያያቸዋል። በአንድ ክፍል ውስጥ “ቃላት” ሰብስቦ ያለ ተናጋሪ ያንጫጫል። አዎን ተስፋዬ- ማናቸውም ባለቋንቋዎቹ በማይሆንላቸውና በማይደፍሩበት ሁኔታ ደስታውንና መከፋቱን፣ ዳር ድንበር የሌለውን የወሲብ ረሃቡን የሚናገርለትና የሚናገርበት አማርኛ አለው። ይኸ ጥበብ (ታለንት) ገበያ መውጣት ነበረበት። ወጣ- የቡርቃ ዝምታ ተወለደ። ይኸ የተስፋዬ መንፈስ ዛሬ ኢትዮጵያን እያመሰ ይገኛል። ሐውልት አሠርቶአል። ጦር አማዝዞአል። 

      ሁላችንም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመሮጥ ሞክረናል። ተስፋዬ ብቻ ያወቀውና የሚያውቀው ታሪክ ሌላ ነው። ይኸውም በቡርቃ ዝምታ መጽሐፉ ውስጥ አጤ ምኒልክ የጨረሱአቸው የኦሮሞ ጀግኖችና ጡታቸውን የተቆረጡ ሺህ በሺህ ሰዎች ናቸው። ተስፋዬ ይህን መሳይ እንቁላል ጥሎ ወደ ስደት እንደ ሄደ ይነግረናል። ባይነግረንም እናውቃለን። ከዚያ በኋላ ደግሞ እንደገና በቃላት አፍዝ አደንግዝ (ሒፕኖታይዝ ሲያደርገን) የጋዜጠኛው ማስታወሻን፣ የደራሲው ማስታወሻንና በመጨረሻም የስደተኛው ማስታወሻን አዘጋጀልን። “ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ! ጠላቶችህ በዛሬ ቀንና በዚሁ ሥፍራ በእጅህ ገብተዋልና ዝምታው ምንድነው? አታውቅም እንጂ አማራ አያት ቅድመ አያትህን ጨርሳለች። አንተንም ቢሆን ገድላሃለች- አላወቅህም እንጂ!” ካለ በኋላ ለእኛ ለውጭዎቹ ደግሞ የትኛው የወያኔ ሹም ከየትኛይቱ ኮረዳ…ካልሆነም መለኮን ጋር እንደ ተዳራ፣ ምን እንደ ተጠጣ..ማን ኮንትራባንድ እንደሚነግድ ..ማን ብዙ እንደሚሰክር..ነገረን። ይኸ ቅማል ነበር እንዴ የበላን? የተስፋዬ በማርታ አሻጋሪ ዘፈን እንደ ወንድ አህያ አውሬአዊ የወሲብ አመሉን በሕዝብ እይታ ፊት መፈጸም ም ይፈይድልናል? በቋንቋው ኅይል ያንከራተታቸው ሰዎች አሉ። መሞታቸውን ከእሱ የሰሙ። ታሪካቸውንና ውርደታቸውን ከእሱ ያነበቡ። እስከ ዓለም ምሕረቱ! 
       ተስፋዬ በስደቱ ዓለም በቆየባቸው ዓመታት ልብ ወለድ መጽሐፉ- የቡርቃ ዝምታ- በአገር ቤትም ሆነ በውጭው (ዳያስፖራ) 
የፈጠረችውን ቱማታ መለካቱ አልቀረም። “ኦሮሞ ነን” የሚሉ ጉርባዎችን አስከትሎ “ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ወዳጅ” ተብሎ በሚሞገስበትና በሚሸለምበት ሥፍራ ሁሉ ዲስኩር አድራጊ ሆነ። ጥፋትን አብሮ በማቀድና አብሮም በአንድ ግብ ስር ተሰልፎ ወደ አፈጻጸሙ የመንደርደር  ተግባር ሁሉ እስካከናወነ ድረስ በእኔ በኩል ተስፋዬ ምን ጊዜም ከወያኔ ጋር የሚያስተሳስረው እትብቱ አልተቆረጠም። ይልቁንም ልብ ወለድ ድርሰቱ ሐውልት ሊያሠራ መቻሉና የገንዘብና የማቴሪያል ጥቅም ማግበስበስ ላይ መገኘቱ ቀላል ግምት አያሰጠውም። እነሆ በኢትዮጵያ ሕዝብ መሐልም የሚቆም የጥላቻ ግድግዳ፣ የበቀል ግንብና ለትውልዶች የሚተላለፍ መርዝ አበረከተ። መርዝ መርዝ! ነብዩ ኢያሱ በአፍሪካ ቀንድ መጽሔት ላይ ያወጣት አንዲት ግጥም ትዝ አለችኝ። “ወይ ውረድ ወይ ፍረድ!” ነበር የምትለው ( በነገራችን ላይ ተስፋዬ ገብረአብ በግል እኔን ያሞጋገሰኝ ሰው ነው። እንዳልናገር በቅድሚያ የተከፈለ ጉቦ ከሆነ የከመረብኝን ቋንቋ ሁሉ ይውሰድልኝ) በታሪክ ካላደረቅኋችሁ ጥቂት ጊዜና ትዕግስት ስጡኝ። ወጌን አላበቃሁም። አንድ ቃል ልጨምር። ከ “የቡርቃ ዝምታ” በኋላ ነው የስደት ማስታወሻ ቢያንስ በነፃ የተለቀቀው። አነበብሁት። ኢትዮጵያንና አማራ የተባለውን ሕዝብ የሚገልጥበት፣ ተጨቁነዋል የሚላቸውን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አሥር ቶን በሚሆን ውሸት የሚያንቆለጳጵስበትን ሁሉ አንብቤለታለሁ። መላልሼ ለራሴ ያቀረብሁት ጥያቄ “ለምን ይሆን ተስፋዬ ይህን ሕዝብ ይህን ያህል ለመጥላትና በመቃብሩ ላይም ድንጋይ ለመመለስ የፈለገው? ኢትዮጵያስ በአንድ ሰው ተመስላ የበደለችው ምን ይሆን? ሕዝቡ እንዲጫረስ መንፈሱን ያነሳሳው ምንድነው?” 

 እንደሚወራው ተስፋዬ በብዙሃኑ ዲያስፖራ የማርያም ጠላት ቢባልም ለራሳቸው አዲስ ስያሜ የሰጡትና አንዲት ቅጠል የኢትዮጵያን ታሪክ አንብበው የማያውቁ ግለሰቦች ደግሞ እጅብ እጅብ እያደረጉት ነው። በሦስተኛው ክፍል ጥቂት አሹዋፊዎች አሉበት። ተስፋዬ የሚነግረን ሁሉ ትክክል ነው። ይህን ሁሉ መከራ እንዴት ቻልነው? ሳናውቀውና ሳይሰማን እንዴት እስካሁንዋ ቀን ደረስን? ይሉታል። ለካንስ ይህን ያህል ተበድለን ነበር? ከተገረፈው ገላችን፣ ከቆሰለው አጥንታችን በላይ የተስፋዬ ቃላት ይናገራሉ። ለካ አልቀን ነበር? የተስፋዬ የእልቂት አዋጅ የሆነው የቡርቃ ዝምታ በሌላውም ምሽግ የምትታወቅ ከሆነች መልሱ “ጅብ ቲበላህ..በልተኸው ተቀደስ” መሆን አለበት። ጋንዲንና ማርቲን ሉተርኪንግን ተዋቸው። 

Source: ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com 

-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ግብፅ ለድርድር ፈቃደኛ ናት ብለዋል:: 
በግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ የሆኑት አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያን በመጐብኘት የሁለቱን አገሮች የዓባይ ውኃ ግጭት በውይይት ለመፍታት እንደሚጥሩ አስታወቁ፡፡
በተመሳሳይም የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነቢል ፋህሚ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኗን መግለጻቸውን፣ የግብፅ ጋዜጣ አል አህራም ዘግቧል፡፡

ከ‘አል አህራም’ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የቀድሞው የጦር ኃይሉ መሪ አልሲሲ፣ ‹‹የግብፅና የኢትዮጵያን ቀውስ ለመፍታት ምርጡ መንገድ የሁለትዮሽ ድርድርና መግባባት ነው፤›› ማለታቸውም ተጠቅሷል፡፡ ከግጭትና ከጠላትነት ይልቅ ስምምነት የተሻለ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው የገለጹት አልሲሲ፣ ግብፅን የሚጠቅም ከሆነ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት ዝግጁ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ 
‹‹ይህ ወደ ግጭት ከመግባትና ከማንም ጋር ጠላት ከመሆን የተሻለ ነው፤›› ሲሉም አስታውቀዋል፡፡ 
የቀድሞ የግብፅ የጦር ኃይል አዛዥ የግብፅ የውኃ መብት ጉዳይ የሕይወትና የሞት ጉዳይ መሆኑን ግን አስረግጠው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነቢል ፋህሚ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ኅብረት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር አገራቸው ለመደራደር ያላትን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያደረጉት ድርድር ፍሬያማ እንዳልሆነ መጠቆማቸውን የገለጸው የአል አህራም ዘገባ፣ ሚኒስትሩ ይህ ሌላ ውይይት ለማድረግ ግብፅን እንደማያዳግት መግለጻቸውን ገልጿል፡፡ 
ከቀናት በፊት አሜሪካ ሁለቱ አገሮች ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጓን መዘገባችን ይታወሳል፡፡    
Source: Reporter

Egypt’s presidential front runner Abdel-Fattah al-Sisi has said that he is ready to visit Ethiopia for talks on resolving their Nile water dispute.“Dialogue and understanding are the best way to resolve the crisis,” al-Sisi said in an interview with the state-run Al-Ahram daily on Saturday.“This is better than going into a dispute or an enmity with anyone,” he added.The former army chief, who led the army to unseat elected president Mohamed Morsi last July, said that he is ready to visit Ethiopia “if this serves Egypt’s interests”.“I will not hesitate in making any effort for my country and its water rights, which is a life-or-death issue,” he added.Relations between Cairo and Addis Ababa soured last year over Ethiopia’s plans to build a $6.4-billion hydroelectric dam on the Blue Nile, which represents Egypt’s primary water source.The project has raised alarm bells in Egypt, which fears a reduction of its historical share of Nile water.Water distribution among Nile basin states has long been regulated by a colonial-era treaty giving Egypt and Sudan the lion’s share of river water. Ethiopia, for its part, says it has never recognized the treaty.Source: .worldbulletin.net

ኢትዮጵያ ለጀመረችው የታላቁ ህዳሴ ግብድ ግንባታ የአሜሪካ መንግሥት ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠውና ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያና የግብፅ መንግሥታት ያቋረጡትን ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀረበ፡፡ 
የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ባለፈው ረቡዕ የአሜሪካ መንግሥት ከሰሐራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን ትኩረት አስመልክቶ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ጋር ከአሜሪካ ሆነው በቀጥታ ቪዲዮ ኮንፈረንስ ተነጋገረው ነበር፡፡ ‹‹የአሜሪካ መንግሥት ከታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያና ከግብፅ መንግሥታት ጋር ትልቅ ውይይት በማካሄድ፣ ሁለቱ አገሮች ልዩነታቸውን አቻችለው በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርቧል፤›› ሲሉ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ባለችው የታላቁ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያለውን አቋም አስመልክቶ በተጨማሪ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በመጀመሪያ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የሚስተዋለው የቃላት ጦርነት የአሜሪካ መንግሥትን እንደሚያሳስበው ገልጸዋል፡፡
ግድቡን በተመለከተ የአሜሪካ መንግሥት አቋም ሁለቱ መንግሥታት ወደ ንግግር መምጣት እንዳለባቸውና ተገናኝተው ሊወያዩ ይገባል፣ ያሉት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ፣ ልዩነታቸውን ሊያስታርቁ ይገባል ሲሉ በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በሁለቱ ኢትዮጵያና ግብፅ መካከል የተወሰነ ድርድር እንደነበር የአሜሪካ መንግሥት የሚገነዘብ መሆኑን የገለጹት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ፣ አሁንም ሁለቱ መንግሥታት ያቋረጡትን ድርድር በድጋሚ በመጀመር ለሁለቱ አገሮች የጋራ ጥቅም የሚበጅ መፍትሔ ላይ ቢደርሱ እንደሚሻል አስረድተዋል፡፡ 
ረዳት ሚንስትሯ ሊንዳ ቶማስ ከአፍሪካ ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ያደረጉት ውይይት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆን ኬሪ፣ የአፍሪካ ጉብኝት በቅርቡ በአሜሪካ በሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በቅርቡ በሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ የኤርትራ፣ የዚምባቡዌ፣ የሱዳንና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች እንደማይጋበዙ ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በደቡብ ሱዳን የሚስተዋለውን የእርስ በእርስ ግጭት አስመልክቶ ሁለቱ የግጭቱ ተዋናዮች የሰላም ስምምነቱን ወደ መተግበር እንዲገቡ፣ ካልሆነ ግን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው አስታውቀዋል፡፡
Source: Reporter



  • • ‹‹የፓትርያርኩን ሥልጣን ይገድባል›› በሚል ተተችቷል
  • ‹‹አመራራቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ነው›› /የሕግ ረቂቁ/
  • ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚያስተላልፉት በብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ይኾናል:: 

  • ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕድገትና ነባራዊ ኹኔታዎች ጋራ በማገናዘብ ያሻሽላል የተባለው የሕግ ረቂቁ ለውይይት የቀረበው፣ ባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጎች ኹሉ የበላይ ነው የተባለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ÷ ርእሰ አበውና ለካህናቷና ለምእመናንዋ ኹሉ መንፈሳዊ አባት ለኾኑት ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚሾም በአንቀጽ 24 ላይ ማስፈሩ ተመልክቷል፡፡ እንደራሴው ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን የተጣለበትን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንዲችል የሚያግዝ›› መኾኑ በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ተገልጧል፡ ፡

  •        የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ፓትርያርኩን የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽና የፓትርያርኩን ሓላፊነትና ተጠያቂነት በጉልሕ የሚያሳዩ አንቀጾችን ባካተተ የሕግ ረቂቅ ላይ እየተወያየ እንደኾነ ተገለጸ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በ1991 ዓ.ም. ያወጣችውን ሕግ ከሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣጣም፣
  • እንደራሴው የሚመደበው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ብቻ በሚሳተፉበት ምርጫ ሲኾን፣ ለምርጫው ሦስት ዕጩዎች በፓትርያርኩና በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ጥቆማ እንደሚለዩ ተጠቅሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖናና ትውፊት የማስጠበቅ እንዲሁም ያለአድልዎ የማስተዳደር ሓላፊነት ላለበት ለፓትርያርኩ በእንደራሴነት የሚመረጠው ሊቀ ጳጳስ ማሟላት የሚገባው መመዘኛ በሕጉ መመልከቱ የተጠቆመ ሲኾን መመዘኛው ለእንደራሴው ከ50 - 60 ዓመት የዕድሜ ገደብ ሲያስቀመጥ፣ የአስተዳደር ችሎታና የመንፈሳዊ አመራር ልምድን፣ መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት አጣምሮ መያዝን እንደሚጠይቅም ታውቋል፡፡ ‹‹ግለሰባዊ የሥልጣን ፈላጊነት ስሜት የሚገንበት፣ የፓትርያርኩን ሥልጣን የሚጋፋና መካሠስን የሚያበረታታ ነው›› በሚል አንቀጹን የተቃወሙ የቤተ ክህነት ሓላፊዎች፣ ምደባው አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘም እንደራሴው በፓትርያርኩ ጥቆማ ብቻ መመረጥ እንዳለበት የቃሉ ትርጉም እንደሚያስገደድ በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡
    የአህጉረ ስብከት የሥራ ሓላፊዎች በአንጻሩ፣ የእንደራሴው ምደባ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ብልሹ አሠራር እንዲታረም የአደረጃጀትና የአሠራርለውጥ ጥናት በማድረግ ላይ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አመራር መጠናከር የራሱ አስተዋፅኦ አለው በሚል እንደሚደግፉት ተናግረዋል፡፡ እንደራሴው ፓትርያርኩን ከማገዝ ውጭ ‹‹ለቅዱስ ፓትርያርኩ ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ የሚጋራው የተለየ ሓላፊነት አይኖረውም፤›› በሚል በረቂቁ የሰፈረውን አንቀጽ በመጥቀስ ምደባው ፓትርያርኩን የመጋፋት ሚና እንደሌለውም ገልጸዋል፡፡ ተጠያቂነትን በተመለከተም ፓትርያርኩን ብቻ ሳይኾን ኹሉንም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ ከማድረግ፣ በአስተዳደር በደልና በአመራር ጉድለት የካህናቱንና የምእመናኑን አመኔታና ተቀባይነት ማጣትን ጨምሮ ከሀብትና ንብረት ባለቤትነት ጋራ የተያያዙ ዝርዝር የተጠያቂነት አንቀጾች በረቂቁ በመካተታቸው በፓትርያርኩ አልያም በወቅታዊ እይታ ላይ ብቻ የታጠረ ረቂቅ እንዳልኾነ ያስረዳሉ፡፡
    ጉዳዩ በዋናነት የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አመራር ከማጠናከር አንጻር ሊታይ ይገባል የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ምልዓተ ጉባኤው የሕግ ማሻሻያ ረቂቁን በጥልቀት በማዳበር የቅዱስ ሲኖዶሱ ሉዓላዊ ሥልጣን በማንም የማይገሠስበት መሣርያ አድርጎ እንደሚያጸድቀው እንጠብቃለን ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ፓትርያርኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ በዓላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ እየተገኘ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚሰጠው እንዲሁም በብዙኃን መገናኛ መንፈሳዊ መልእክት የሚያስተላልፈው በአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ብቻ እንደሚኾን በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ላይ መስፈሩ ተጠቅሷል፡፡
  • Source: Addis Admass

    (አፈንዲ ሙተቂ):-
    ይህንን አነስተኛ መጣጥፍ ከዚህ በፊት (በታህሳስ ወር 2006) ለጥፌው ነበር፡፡ ነገር ግን በርካታ ወዳጆቼ ከፌስቡክ ግድግዳህ ላይ ልናገኘው አልቻልንም” ስላሉኝ እንደገና መድገሙ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለፍለጋ ቀለል የሚለው ብሎግ ስለሆነ በኔ ብሎግ ላይም እለጥፈዋለሁ፡፡
    እነዚህ ሰነዶች በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳርፈዋል በማለት በዝርዝሩ ውስጥ የያዝኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ዝርዝሩ በሌሎች ምሁራንም ሆነ የጥናት ተቋማት እውቅና አልተሰጠውም፡፡ ማንም ሰው የክፍለ ዘመኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ አካሄድ ገምግሞ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድረዋል ያላቸውን ሰነዶች ሊጠቁም ይችላል፡፡ እኔም ይህንኑ ነው ያደረግኩት፡፡

    ሰነዶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
    1. አዕምሮ ጋዜጣ- 1904
    2. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ህገ-መንግሥት- 1923
    3. የኤርትራ ፌዴሬሽን ህገ-መንግሥት 1944
    4. የተሻሻለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ህገ-መንግሥት- 1948
    5. የጀብሃ ቻርተር- 1954
    6. የሜጫና ቱለማ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ-1955
    7. የብሄር ጥያቄ በኢትዮጵያ (በዋለልኝ መኮንን የተጻፈ ጽሑፍ)-1961
    8. “ንህናን ዓላማናን”(እኛና ዓላማችን)- ሻዕቢያ ከጀብሃ የተገነጠለበት አነስተኛ ጥራዝ-1964
    9. ደርግ ስልጣን የያዘበት አዋጅ- መስከረም 2/1967
    10. የገጠር መሬትን ለህዝብ ያደረገው አዋጅ- የካቲት 25/1967
    11. ዲሞክራሲያ ጋዜጣ (የኢህአፓ መመስረት ይፋ የሆነበት የፓርቲው ህቡዕ ጋዜጣ)- ነሐሴ 27/1967
    12. የተሓሕት/ህወሐት ማኒፌስቶ- የካቲት 1968
    13. የብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት ፕሮግራም አዋጅ- ታህሳስ 1968
    14. የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት የተመሰረተበት አዋጅ- ሚያዚያ 1968
    15. የኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም- ሰኔ 1968
    16. ኢሰፓአኮ የተቋቋመበት አዋጅ-ሰኔ 1971
    17. ኢሰፓ የተመሰረተበት አዋጅ- መስከረም 1977
    18. የኢህዲሪ ህገ-መንግሥት-ጳጉሜ 1979
    19. የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ቻርተር- ሀምሌ 1983
    20. የፕሬስ አዋጅ- የካቲት 1984
    21. የክልሎች ማቋቋሚያ አዋጅ- ጥቅምት 1985
    22. ኢትዮጵያ ለኤርትራ ነጻነት እውቅና የሰጠችበት ደብዳቤ (በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈ)-ሚያዚያ 1985
    23. የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት- ህዳር 29/1987
    24. የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ያበቃበት የአልጀርስ ስምምነት -ታህሣስ 1993
    25. አብዮታዊ ዲሞክራሲና ቦናፓርቲስታዊ የመበስበስ አደጋዎች (በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈ ጥራዝ)- ጥር 1993
    26. የቅንጅት ማኒፌስቶ-1997
    ከላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች በኔ እይታ በ100 ዓመት (ከ1900-2000 በነበረው) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አድርሰዋል፡፡ እያንዳንዱን ሰነድ ልብ ብላችሁ ካያችሁት የፖለቲካ ሚናው ከፍተኛ እንደነበረ በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ አቶ መለስ “ቦናፓርቲዝም” በሚል ርዕስ የጻፉት ጽሑፍ በ1993-95 የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በከፍተኛ ጡዘት ውስጥ የጨመረ ነው፡፡ እነ ስዬ አብርሃን ከማባረር ጀምሮ የክልሎችን አስተዳደራዊ መዋቅር እስከመቀየር እና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመሳሰሉት ፐሮግራሞች ትግበራ ጥርጊያ ጎዳና ያመቻቸ ነው (የጸረ-ሙስና ኮሚሽንም የርሱ ውልድ ነው)፡፡ የህዝብ ድርጅት ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅም “ቀበሌ” የሚለውን የአስተዳደር አከፋፈል ከማስተዋወቅ ጀምሮ በቀይ ሽብር ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን የጥበቃ ጓዶች እስከ ማስታጠቅ ድረስ ላሉት ታላላቅ ክስተቶች መፈጠር እንደ እርሾ ሆኖ አገልግሏል፡፡
    በናንተ በኩል በዚህ ዝርዝር ውስጥ መካተት አለባቸው የምትሏቸው ሰነዶች የትኞቹ ናቸው? በናንተ ሚዛን ፖለቲካዊ ሚናቸው ሀይለኛ የሆኑትን መጠቆምና በኔ ያቀረብኩትን ዝርዝር መተቸት ትችላላችሁ (የኤርትራ ሰነዶች በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ስለነበራቸው ነው)፡፡
    ሰላም
    ———————–
    አፈንዲ ሙተቂ
    ግንቦት 4/2000
    Source: Zehabesha.com
     
    መስፍን ወልደ ማርያም:- 
    ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።
    የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ
    የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ
    ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።
    ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።
    በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።
    ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።
    ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!
    ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤… ኢሳይያስ 9/18-21

    ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

    (Reuters) - The World Food Programme will help to feed nearly 6.5 million Ethiopians this year, the U.N. agency said on Tuesday, with the country hit by locusts, neighboring war and sparse rainfall. 


    "We are concerned because there is the beginning of a locust invasion in the eastern part of the country, and if it's not properly handled it could be of concern for the pastoralist population living there," WFP spokeswoman Elizabeth Byrs told a U.N. briefing in Geneva.
    "And in the northern part of Ethiopia there has been less rain than average for the third or fourth consecutive year."
    Ethiopia is also dealing with growing refugee numbers due to the conflict in neighboring South Sudan, sapping WFP's budget for feeding new arrivals in the country, which is at risk of a shortfall as soon as next month.
    More than 120,000 South Sudanese have crossed over into Ethiopia in the past six months, mostly women and children who are arriving "famished, exhausted and malnourished", WFP said in a statement.
    The recent influx has brought total refugee numbers to 500,000 in Ethiopia. The U.N. also provides food for millions of needy or undernourished Ethiopians, including 670,000 school children and 375,000 in HIV/AIDS programs.
    Ethiopia's overall situation has vastly improved over recent years and the economy now ranks as one of the fastest growing in Africa. But deep problems remain.
    Malnutrition has stunted the growth of two out of every five Ethiopian children and reduced the country's workforce by 8 percent, WFP said, citing Ethiopian government data.
    The International Monetary Fund expects Ethiopia's economy to grow 7.5 percent in each of the next two fiscal years but says the government needs to encourage more private sector investment to prevent growth rates from falling thereafter.

    (Reporting by Tom Miles Editing by Jeremy Gaunt)
    Source: Reuters

    እስረኞች፤ ድብደባና ግርፋት ደርሶብናል አሉ::
             ከአለማቀፍ የመብት ተሟጋች ተቋም ጋር በገንዘብና በሃሳብ ተደራጅተው በኢንተርኔት አገሪቱን ለማሸበር አሲረዋል በሚል የታሰሩት 9 ጋዜጠኞችና የ“ዞን 9” ፀሐፊዎች ላይ ምርመራ እንዳልጨረሰ በመግለጽ ተጨማሪ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፖሊስ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍ/ቤት የ10 ቀን ቀጠሮ ሰጠ፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ተጠርጣሪዎች ሀገሪቱን ለማሸበር በኢንተርኔት ማህበራዊ ሚዲያዎች አሲረዋል ያለው ፖሊስ፤ ሰሞኑን ተጠርጣሪዎቹ ፍ/ቤት ሲቀርቡ፣ የተያዙት በማህበራዊ ድረገፆች ላይ በፃፉት ሳይሆን ከውጭ አሸባሪ ኃይሎች ጋር በመደራጀት፣ አገሪቱን ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ለማሸበር እና የሽብር ሴራውንም ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ነው ማለቱን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሀ መኮንን ተናግረዋል፡፡
    ተጠርጣሪዎቹ መንግስትን ከምርጫው በፊት ለመጣል፣ ከ5 ጊዜ በላይ እንደ ኬንያና ስውዲን ባሉ አገራት ስልጠና መውሰዳቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ማስረዳቱንም ጠበቃው አክለው ገልፀዋል፡፡ በሶስት መዝገብ ተከፋፍለው በአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው የሚታየው ጋዜጠኞችና ፀሃፊዎች፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ለባለፈው ረቡዕ እና ሀሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መቀጠሩ
    ይታወሳል፡፡ ረቡዕ ዕለት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ኤዶም ካሳዬ፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፍ ብርሃነ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን በመቀጠል ተስፋዓለም ወ/የስ፣ አስማማው ሃ/ጊዮርጊስ እና ዘላለም ክብረት ችሎት ቀርበዋል፡፡ ጉዳያቸው በዝግ ችሎታ የታየ በመሆኑ ቤተሰብ፣ እንዲሁም የውጭና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ሂደቱን መከታተል አልቻሉም፡፡
    የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሀ መኮንን፤ ከችሎት መጠናቀቅ በኋላ ለጋዜጠኞችና ለተጠርጣሪ ቤተሰቦች በሰጡት ማብራሪያ፤ ተጠርጣሪዎቹ መጀመሪያ ከተጠረጠሩበት ጉዳይ በተለየ በውጭ ከሚገኙ አሸባሪ ሃይሎች ጋር በመደራጀት፣ እንደ ኬኒያና ስዊድን ባሉ አገሮች ከአምስት ጊዜ በላይ ስልጠና በመውሰድና ገንዘብ በመቀበል፣ ከመጪው ዓመት ምርጫ በፊት አገሪቱን ለማሸበርና የሽብር ሴራውን ለመምራትም ጭምር ሲንቀሳቀሱ እንደደረሰባቸው ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ማስረዳቱን ገልፀዋል፡፡ ከውጭ አሸባሪ ሀይሎች በተቀበሉት ገንዘብ፣ ላፕቶፕና ኮምፒዩተር እንደገዙም ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ማስረዳቱን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ገልፀው፤ “ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ ከሽብርተኝነት ጋር አያይዞታል” ብለዋል፡፡
    ደንበኞቻቸው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው መጠየቃቸውን ያወሱት ጠበቃው፤ ፖሊስ ስድስት የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ፣ የዋስትና መብታቸው እንዳይከበር መሟገቱን ገልፀዋል፡፡ ፖሊስ የዋስትና መብታቸው ቢከበር ይጐዳኛል ካለባቸው ምክንያቶች ውስጥ ተጨማሪ ግብረ አበሮች ስላሏቸው ቢለቀቁ እነሱን ያስመልጡብኛል፣ ከውጭ አሸባሪ ሀይሎች ገንዘብ ተቀብለው የገዟቸውን ላፕቶፖችና ኮምፒዩተሮች ገና አልያዝኩም፣ ተጠርጣሪዎቹ የተገኙባቸው ሰነዶች በእንግሊዝኛ የተፃፉ በመሆናቸው አስተረጉማለሁ፣ ተጨማሪ ሰነዶችን ሊያሸሹብኝ ይችላሉ፣ ምስክር ገና አላሰማሁም እና የቴክኒክ ምርመራ አልጨረስኩም በማለት ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን የተናገሩት አቶ አመሀ፤ የዋስትና መብታቸው አይከበር የሚለው የፖሊስ ጥያቄ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ፤ በቤተሰብና በወዳጅ ዘመድ እንዲጐበኙ ፍ/ቤቱን መጠየቃቸውን የተናገሩት ጠበቃው፤ ከሐሙስ እለት ጀምሮ በወዳጅ ዘመድ እንዲጐበኙ መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት የቀረቡት እነ ማህሌት ፋንታሁን፣ አቤል ዋበላና በፍቃዱ ሀይሉም የተጠረጠሩበት ጉዳይ ረቡዕ እለት ከቀረቡት ከእነ ኤዶም ካሣዬ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አቶ አመሀ መኮንን ገልፀዋል፡፡ በሀሙሱ ችሎት ተጠርጣሪዎቹ በብሎግ፣ በፌስቡክና በቲዊተር ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ተጠርጥረው አለመያዛቸውን ፖሊስ መግለፁን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
    ረቡዕ ዕለት የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ የታየው በዝግ ችሎት ቢሆንም በሀሙሱ ችሎት የሶስቱ ተጠርጣሪ አንድ አንድ የቤተሰብ አባላት ወደ ችሎቱ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ “ችሎቱ በዝግ እንዲሆን ተፈልጐ ሳይሆን ፍርድ ቤቱ የሚይዘው የሰው ብዛት አነስተኛ በመሆኑ ነው” ያሉት አቶ አመሀ፤ ባለችው ጠባብ ቦታ ቅድሚያ ለማን እንስጥ በሚል ስንነጋገር፣ ለቤተሰቦች በመባሉ፣ አንድ አንድ የቤተሰብ አባላት እንዲገቡ ተፈቅዷል፤ ተጨማሪ ማን ይግባላችሁ ተብለው የተጠየቁት ተጠርጣሪዎቹ፤ “ለጊዜው በቂ ነው” በማለት ምላሽ እንደሰጡ ጠበቃው ተናግረዋል፡፡ ከሶስቱ ተጠርጣሪዎች ሁለቱ አቤል ዋበላና በፍቃዱ ሀይሉ በእስር ቤት የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ለፍ/ቤቱ መናገራቸውን ያወሱት ጠበቃው፤ በደረሰባቸው ድብደባና ግርፋትም ለጉዳት መዳረጋቸውን ጠቁመው፤ የሚመለከተው አካል የሰብአዊ መብት ጥሰቱን እንዲያስቆምላቸው መጠየቃቸውን ገልፀዋል፡፡
    በደንበኞቻቸው ላይ የሚፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ከፖሊስ ጋር መነጋገራቸውንም ጠበቃው አክለው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ የጠቀሰው የሰነድ ምርመራና ማስተርጐም እንዲሁም የቴክኒክ ምርመራ ሂደት ደንበኞቻቸውን በእስር የሚያስቆይ ስላልሆነ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር፣ ካልሆነም አጭር የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ ፍ/ቤቱን መጠየቃቸውን ያወሱት ጠበቃው፤ እነ ኤዶም፣ ናትናኤል፣ አጥናፍ እንዲሁም ተስፋለም፣ አስማማውና ዘላለም ለግንቦት ዘጠኝ ሲቀጠሩ፤ ማህሌት፣ አቤልና በፍቃዱ ለግንቦት 10 ተቀጥረዋል ብለዋል፡፡ ማህሌት፣ አቤልና በፍቃዱ ከፍርድ ቤት ሲወጡ ፉጨት፣ ጭብጨባና የማበረታቻ ጩኸት ውጭ ከተሰበሰቡ ቤተሰቦችና ወዳጆች የተስተጋባ ሲሆን ጠበቃው ጩኸትና ጭብጨባው ሌሎች ችሎቶችን እየረበሸ ነው በሚል ከፍ/ቤት ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ገልፀው፤ “ጩኸትና ጭብጨባው ደንበኞቼን ስለሚጐዳ እንዳይደገም” በማለት ለቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
    በሌላ በኩል፤ በረቡዕ ዕለት ችሎት ከሌሎች ጓደኞቹና ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጋር የጓደኞቹን ጉዳይ ውጭ ሆኖ ሲከታተል የነበረው የ“አዲስ ስታንዳርድ” መጽሔት የቀድሞ አምደኛ ኪያ ፀጋዬ፤ ተጠርጣሪዎቹ ከችሎት ሲወጡ ባልታወቀ ምክንያት ፖሊስ እየደበደበና እየተጎተተ ከታሳሪዎቹ ጋር የወሰደው ሲሆን ሃሙስ እለት ማምሻውን መለቀቁን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከአንድ ቀን እስር በኋላ የተለቀቀው ኪያ ፀጋዬ በምን ጉዳይ እንደተያዘ ጠይቀነው “ወደ ማዕከላዊ የተወሰድኩት ፎቶ አነሳህ ተብዬ ነው” ብሏል፡፡ “ፎቶ ማንሳት በወቅቱ አልተከለከለም፤ ፈረንጆችም ሲያነሱ ነበር፤ ፎቶ ያነሳሁትም ፍ/ቤት ውስጥ ሳይሆን ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው” ያለው ኪያ፤ ፎቶ ያነሳሁት አንዳንድ ኮመንተሪዎችን ስፅፍ ፎቶ ለመጠቀምና ለማስታወሻም ጭምር ነው ሲል ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ማእከላዊ ከተወሰደ በኋላ ለምን ፎቶ አነሳህ፣ ፎቶ እንድታነሳ የቀጠረህ አካል ማን ነው፣ ለማን ነው የምትሰራውና መሰል ምርመራዎች እንደተደረጉበት ጠቁሞ ባለሙያ እንደሆነና፣ ፎቶውን ያነሳው ለማስታወሻ መሆኑን ለመርማሪዎቹ ካስረዳ በኋላ በአይፎን ስልኩ ያነሳቸው ፎቶዎች ተሰርዘው፣ በነፃ መለቀቁን ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
    Source: Addis Admass
     
    San Jose, California–U.S. President Barack Obama has agreed with journalist Abebe Gellaw’s demand to support freedom in Ethiopia and help free bloggers, journalists and political prisoners jailed by the tyrannical regime.

    While Obama was wrapping up his speech last night at a glitzy Democratic National Committee reception in San Jose’s Fairmont Hotel, journalist and activist Abebe Gellaw interrupted the president and called support for freedom in Ethiopia. The event jointly hosted by Yahoo CEO Marissa Mayer and and Y Combinator CEO Sam Altman was mainly attended by Silicon Valley business and political leaders.
    Abebe began his message with a positive note. “Mr. Obama, we Ethiopians love you. We demand freedom for Ethiopia,” he said.

    The President, who was talking about winning both Congress and the Senate from the Republicans in the next election, replied “I agree with you although why don’t I talk about it later because I am just about to finish. You and me will talk about it. I am going to be coming around.”
    But Abebe continued his message and loudly called for help to free jailed bloggers and journalists. “Stand with the people of Ethiopia, don’t support tyranny,” he said to which the president answered again, “I agree with you.”
    “We have tyranny in Ethiopia,” Abebe said and added, “We love you!”
    “I love you back,” the present replied and noted that his speech was kind of screwed up.
    “That is okay. And we got free speech in this country,” he said before wrapping up his speech.
    In a letter Abebe handed to the President at the end of the event, he noted that he wanted to take the rare opportunity to raise the voices of the oppressed people Ethiopia.
    “Mr. President, as an exiled journalist and freedom activist trying to raise the voices of the oppressed people of Ethiopia, I can tell you that Ethiopians have genuine respect for this great land of freedom and your inspirational leadership,” he wrote.
    “But it pains and frustrates me and millions of Ethiopians to see that for over two decades the United States has overridden its core values and forged a questionable alliance with the Tigray People’s Liberation Front, a terrorist group that has continued to oppress, massacre, jail, torture and displace defenseless Ethiopians.”
    According to Abebe, the rare opportunity was another unmissable chance to demand our freedom and expose the tyrants at such a high profile platform of the most powerful decision makers in the world. “I am glad I took the chance though security was extremely tight. At the end of the day,we should consistently demand the U.S to the review its questionable foreign policy towards Ethiopia. That was also the heart of my demand,” he said
    Source: Zehabesha
    JONGLEI - A dozen of Egyptian soldiers fighting alongside the government of South Sudan were caught yesterday in a fierce battle with the rebels' white army in Ayod, Jonglei State. Government forces last week managed to capture Ayod after outmuscling hundreds of white
    army stationed in that strategic town of Jonglei. The government after overrunning the white army burned down the commissioner's office building, market complex and all the huts within the town.

    The battle continued till yesterday when white army reinforcement from Duk came and chased the government, UPDF and Egyptian soldiers onwards to the sudd swamp. 400 of the government soldiers were found dead as well as 16 Egyptians and 4 UPDF forces. The white army said to have lost 90 people.
    However, in the aftermath of the yesterday's assault by the white army, 12 Egyptians and 2 Ugandans who lost track of the direction of their forces were captured.
    The Egyptians based on their names batches were:
    1. Aches Ahmed Gou

    2. Cpt. Abaur Ahmose
    3. Amran Saleh
    4. Amun Thori
    5. Abduraman Petei
    6. Salatis Omar
    7. Osman Gosh
    8. Abdulahi Said
    9. Mohamed Raad
    10. Yusuf Abdu
    11. Cpt. Ali Semut
    12. Shemstedin Tihrak

    The two Ugandan soldiers were:

    1. Akiki Lutalo
    2. Samuel Munyiga

        The 14 were in the custody of the white army captains who promised to transfer them to Fangak as prisoners of war. But according to a white army soldier, Mabor Gatluak the Upper Nile Times spoke to, 10 government soldiers who were caught along with the above foreign troops were killed.
    The presence of Egyptian soldiers adds to the battalions of Ugandan, JEM, and SPLM-N forces already fighting alongside the government.
    Source: The Upper Nile Times

    GAMBELLA - The regional state government  of Gambella caught today 3 Egyptian nationals who penetrated to the the region via the war torn South Sudan in what the regional government of Ethiopia believed to be a spying mission to find information about the country's  Renaissance Dam. The the three men named as Yusuf Haj, Ismail Azizi and Hassan Garai were caught in separate locations of the region. 

    Yusuf went to Abobo on a fake tourist pass to see the Abobo dam of the Abobo county (Woreda). The locals in Abobo worried about the suspicious activities he was making near the dam and that prompted his arrest by the local police. He was then transferred to the regional  administration in Gambella for further investigation and detentions.
    The other two were caught at a bus station in Gambella trying to board a bus to Benshangul - Gumuz state without security passes. Benshangul-Gumuz near blue Nile is where the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) is located.

    Egypt and Ethiopia have been at odds over the construction of GERD. Egyptian government threatened to bomb the dam as they feel that if the dam becomes operational, it would compromise their fair share of the Nile water. Ethiopia however denied any impact the flow of water would do to Egypt. 

    Moreover, South Sudan government recently signed a military agreement with Egyptian government. The agreement was received with too much skepticism by Addis Ababa who think that any deal by their neighbour with Egypt would invite an attack on the dam.

    Last week, the South Sudanese rebels claimed to have captured 12 Egyptians in Jonglei who fought alongside the government of South Sudan.

    Source: The Upper Nile Times


    አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ :: 
    የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች የተነሳው ተቃውሞ ለኦሮሞነት ያላዘነ ባዶ መፈክር ነው ሲሉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናት አማካሪና የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኩማ ደመቅሳ ገለጹ፡፡ 
    አቶ ኩማ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተፈጠረው ተቃውሞና ውጥረት ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች እንዳሉት፣ እነሱም ኦሮሚያን ቆርጦ ለማስቀረት የታለመ ማስተር ፕላን ነው የሚልና ፕላኑ ለምን በሚስጥር ተሠራ የሚል ሥጋት የፈጠሩት ናቸው ብለዋል፡፡ 
    የተዘጋጀው ማስተር ፕላን ምንም ዓይነት የድንበር እንዲሁም የአስተዳደር ጥያቄ አለመያዙን የተናገሩት አቶ ኩማ፣ ሌላ የፖለቲካ ተልዕኮ ያላቸው ግን ጉዳዩን ከኦሮሞነት ጋር በማያያዝ የኦሮሞ ሕዝብን እያደናገሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ‹‹ኦሮሞነት አደጋ ውስጥ ገባ የሚለው ባዶ መፈክርና ሚዛን የማያነሳ ክርክር ነው፤›› ያሉት አቶ ኩማ፣ ይህንን በማለት ለማደናገር የሚፈልጉ አጀንዳ ያላቸው ክፍሎችን ማብራሪያ በመስጠት መመለስ አይቻልም ብለዋል፡፡

    ‹‹ጉዳዩ የሕዝብ አይደለም፡፡ ከሕዝብ አንፃር ችግር አለ ብለን አናስብም፤›› ሲሉ ችግሩ የመደናገርና የሌሎች አጀንዳ ያላቸው ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እንደሆነና እልባትም እንደሚያገኝ ጠቁመዋል፡፡ 
    የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ባለፈው ዓርብ ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዓርብ ዕለት መቀዛቀዙን ገልጿል፡፡ ከኅብረተሰቡ ጋርም ውይይት እየተደረገ ችግሩ ከመባባስ ይልቅ በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል ብሏል፡፡
    ከሳምንት በፊት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በመጠኑ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ባለፈው ረቡዕ በከፍተኛ ደረጃ ተቀጣጥሎ ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ማለፉ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ በባሌ ዞን በመደወላቡና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞው ተስፋፍቶ ነበር፡፡
    ከላይ በተጠቀሱት ዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው ተቃውሞ ባለፈው ሐሙስና ዓርብ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ላይ ውጥረት ፈጥሮም ነበር፡፡
    በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ በግምት ወደ 150 የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ‹‹የኦሮሞ ጥያቄ ይከበር፣ ፍትሕ ለኦሮሞ፣ የአዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ መስፋፋት እንቃወማለን…›› የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተስተውለዋል፡፡
    ይህ የሆነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተማሪዎቹን ባለፈው ሐሙስ ጠዋት ሰብስበው ካነጋገሩና በማግሥቱ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያዩ ከገለጹላቸው በኋላ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
    የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ከግቢው ውስጥ አልፎ አልወጣም፡፡ ነገር ግን ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጪ በርካታ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተስተውለዋል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ለአብነትም በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) እና በቡራዩ ከተሞች ተመሳሳይ ተቃውሞ ተከስቶ እንደነበር የአካባቢው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
    የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከቅጥር ግቢያቸው በመውጣት መጠነኛ ተቃውሞ ባለፈው ዓርብ ያካሄዱ ቢሆንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፖሊስ መበተናቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በቡራዩ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ ታይቶ እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
    ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተካሄደው ተቃውሞ በተለይ በአምቦ፣ በመደወላቡና በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተው ተቃውሞ ከባድና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭትን ያስከተለ መሆኑን፣ በዚህም በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ የዓይን እማኞች በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ እየገለጹ ነበሩ፡፡
    ይሁን እንጂ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 11 መሆኑንና 70 ያህል ተማሪዎች ደግሞ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በተጣለ ፈንጂ መቁሰላቸውን ገልጿል፡፡
    ‹‹በኃይል በታጀበ ግርግር ሳቢያ በመደወላቡ የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ በተለይም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰው ሁከት ወደ ከተማ በመዝለቁ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት በአምቦ ከተማ ቢዝነስና ኮንስትራክሽን ባንክ ላይ በተደረገው የዘረፋ ሙከራና ሌሎችም ሕገወጥ የነውጥ እንቅስቃሴዎች፣ በአምቦና ቶኬ ኩታዩ ከተሞች የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ በፌዴራልና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሁከቱ በተፈጠረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ተችሏል፤›› ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መግለጫ ያትታል፡፡
    ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በቴሌቪዥን የእግር ኳስ ጨዋታ በመከታተል ላይ በነበሩ የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ፈንጂ በመወርወር 70 ያህል ተማሪዎችን ያቆሰሉ መሆኑና የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
    ‹‹በተደረገው ማጣራት ከበስተጀርባ በመሆን ሁከቱን በማነሳሳትና በማቀነባበር ተግባር ላይ የተሰማሩ ጥቂት ፀረ ሰላም ኃይሎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፤›› ሲል መግለጫው ያስረዳል፡፡
    ተቃውሞው የተቀሰቀሰው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኘውን የኦሮሚያ ልዩ ዞን በልማት ለማስተሳሰር የተነደፈውን የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን አስመልክቶ፣ ከፕላኑ ፋይዳና ዓላማ ጋር የሚቃረን መሠረተ ቢስ አሉባልታ በአንዳንድ ወገኖች በስፋት በመሰራጨቱ መሆኑን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል፡፡
     Source: Reporter

    -ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በነፃ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው::
    -መንግሥት አደገኛ ወንጀል ፈጽመዋል እያለ ነው::
    የመብት ተሟጋቾች ነን ከሚሉ የውጭ ድርጅቶች ጋር በገንዘብና በሐሳብ በመስማማት፣ ሕዝብን ለአመፅ ለማነሳሳትና ለማተራመስ በኢንተርኔትና በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ቀስቃሽ መጣጥፎችን ለማሰራጨት ሲዘጋጁ ተደርሶባቸዋል በሚል፣ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጦማርያን (Bloggers) ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡


    ሚያዝያ 25 እና 26 ቀን 2006 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በ48 ሰዓታት ውስጥ በዕለተ እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡበት ወቅት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መርማሪ ፖሊስ፣  ተጠርጣሪዎቹ ከውጭ ድርጅቶች ጋር በገንዘብና በሐሳብ ተስማምተው ሕዝቡን ለአመፅ ለማነሳሳት ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል ከሚል የወንጀል የጥርጣሬ ውጪ ያለው ነገር ስለሌለ፣ ‹‹ወንጀሉ ምድነው?›› የሚል ጥያቄ ከማንሳት ጀምሮ የተለያዩ መላ ምቶችን በማንሳት የተለያዩ አካላት እየተነጋገሩበት ነው፡፡

    ሲፒጄ (ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት)፣ ‹‹ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ የከፋ ከሚባሉ ዕርምጃዎች አንዱ ነው፤›› በማለት በጋዜጠኞቹና በጦማርያኑ ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰደውን ዕርምጃ አውግዟል፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁም ጠይቋል፡፡
    አምኒስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ፣ ‹‹ይኼ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን የማሰር የረዥም ጊዜ ልምድ ነው፤›› በማለት ጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን ማሰር ተገቢ አለመሆኑን አስታውቆ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል፡፡
    ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያን መንግሥት በማውገዝ የጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን መታሰር የሚያነሱትን ወቀሳና ጥያቄ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ለውጭ ሚዲያ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ በአደገኛ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው፡፡ ፖሊስ በተጠረጠሩበት ጉዳይ ዙሪያ ምርምራ እያደረገ ነው፤›› ብለዋል፡፡
    ሒዩማን ራይትስ ዎች ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ የተባሉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጋር ባደረገው የስልክ ውይይት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩትን ጋዜጠኞችና ጦማርያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
    የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጆን ኬሪ ተጠርጣሪዎቹን እንዲፈቱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በስልክ ያስተላለፈውን መልዕክት አስመልክቶ አቶ ጌታቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መንግሥት የጋዜጠኞችን የመናገር መብት አላፈነም፣ አንዳንዶች ሙያውን ተገን በማድረግ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ሲሳተፉ ይገኛሉ፣ ይኼን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አይፈቅድም፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ትዕዛዝን አንቀበልም፤›› ብለዋል፡፡ 
    በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ጦማርያን ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በሦስት የምርመራ መዝገብ ተከፋፍለው ሲሆን፣ ቀደም ሲል በአዲስ ነገር ጋዜጣ፣ በፎርቹን ጋዜጣና በአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ላይ ይሠራ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ነው የተባለው ጦማሪ ዘለዓለም ክብረትና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ አንድ ላይ ናቸው፡፡
    በሁለተኛው የምርምራ መዝገብ የተካተቱት የአዲስ ዘመን ጋዜጠኛ የነበረችው ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀና ጦማሪ አጥናፉ ብርሃኔ ሲሆኑ፣ የአየር መንገድ ሠራተኛ ነው የተባለው ጦማሪ አቤል ዋበላ፣ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በሦስተኛው የምርምራ መዝገብ ተካተው ለሚያዝያ 29 እና 30 ቀን 2006 ዓ.ም. መቀጠራቸው ታውቋል፡፡
    በምሥረታ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋማ) የጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን መታሰር በማስመልከት ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው ጠቁሞ፣ መታሰራቸው ግን እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ ባስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል፡፡
    በአገር ውስጥ ያሉ የግል የኤሌክትሮኒክስና የሕትመት መገናኛ ብዙኃን፣ ከመንግሥትና ከቅርብ ወዳጆቻቸው እንዳገኙት አድርገው በተጠርጣሪዎቹ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ላይ እያስተላለፉት ያለው መረጃ፣ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ ፍርድ ቤቱ በምርመራ መዝገቡ ላይ ካሰፈረው የተለየ በመሆኑ፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በቀጣይ የሚቀርበውን የምርምራ ውጤት ከመጠባበቅ ባለፈ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

    Source: Reporter
     ጸሓፊ፡-አፈንዲ ሙተቂ:-
    ፕሮፌሰር መስፍንን በአካል ያየሁት ሁለት ጊዜ ያህል ብቻ ነው፡፡ በነዚህም ጊዜያት ከመጨባበጥ በቀር ሌላ ነገር ማውጋት አልቻልንም፡፡ ብንጨዋወት እንኳ በፖለቲካ አመለካከታችን የምንግባባ አይመስለኝም፡፡ ለምሳሌ እሳቸው “ኢትዮጵያ ውስጥ ነገዶችና ጎሳዎች እንጂ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የሉም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድ ብሄር ብቻ
    ነው” ነው የሚሉት፡፡ እኔ ግን “በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ፤ ነገድና ጎሳ የብሄር ቅርንጫፎች እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ህዝቦች አይደሉም” ነው የምለው፡፡ በሌላ በኩል ፕሮፌሰር መስፍን “የብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር በብሄር መደራጀቱ ለሀገር አንድነት አደጋ አለው” የሚል እምነት አላቸው፡፡ እኔ ግን “ለመጥፎ ዓላማ እስካልሆነ ድረስ በብሄር መደራጀቱ መጥፎ አይደለም” የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሌላም ብዙ ልዩነት ማስቆጠር ይቻላል፡፡
    ይሁንና በፖለቲካ እንዲህ የተለየኋቸውን ምሁር ለአንድም ቀን እንደ ጠላት አይቼአቸው አላውቅም፡፡ በተቃራኒው ህሊናን በሚያምራምሩ ብዙ ባህሪያቶቻቸው በጣም ያስቀኑኛል፡፡ “እኛስ መቼ ነው እንደርሳቸው ሆነን ለሀገራችንና ለህዝባችን ክብር የምንቆረቆረው” እላለሁ፡፡ ከዚህ ፈቅ የሚሉት አንዳንድ አድራጎታቸው ግን በነቢያትና በቅዱሳን ካልሆነ በቀር ከኛ ዘመን ሰው የሚጠበቁ አይደሉም፡፡

    በእርግጥ እላችኋለሁ! ፕሮፌሰር መስፍን በብዙ አጋጣሚዎች “ሰው ማለት… ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ ዕለት” የተሰኘውን ብሂል በተግባር ከውነው ያሳዩን ብሄራዊ ጀግና ናቸው፡፡ እኝህ ታላቅ ሰው ሀገራችን ሰው በምትፈልግበት ልዩ ልዩ አጋጣሚዎች በልዩ ድፍረትና ልበ ሙሉነት በከወኗቸው ድርጊቶቻቸው የህዝብ ልጅ መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡
    ፕሮፌሰር መስፍን ለብቻቸው ሆነው የፈጸሟቸውን በርካታ ገድሎች መዘርዘር እንችላለን፡፡ ለዛሬው ግን በጣም ጥቂቶቹን ብቻ እንዲህ እንዘክርላቸዋለን፡፡
    === የትግራይና ድርቅና ረሃብ===
    ብዙዎቻችን በ1965 ስለተከሰተው የወሎ ረሃብ በቂ መረጃ አለን፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በ1950ዎቹ ስለተከሰተው የትግራይ ረሃብ ግን ብዙም ሲጻፍ አላነበብኩም፡፡ ችግሩ የተከሰተው የያኔው ረሃብ እንደ 1965ቱ ረሃብ በቂ የሚዲያ ሽፋን ባለማግኘቱ ይመስለኛል፡፡
    በርግጥም ያ ረሃብ ከፍተኛ እልቂት የታየበት ነበር፡፡ የንጉሡ መንግሥት የረሃቡ ወሬ ታፍኖ እንዲቀር በማድረጉ በልዮ ልዩ ክፍለ ሀገራት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለትግራይ ወገኑ ሊደርስለት አልቻለም፡፡ መኳንንቱና መሳፍንቱ ከድሮም ጀምሮ የደሃው ህይወት ስለማያሳስባቸው የረሃቡን ጉዳይ ከቁብ አልቆጠሩትም፡፡ በዚያ ወቅት ድምጹን ያሰማው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መስፍን ወልደማሪያም ነበር፡፡
    ፕሮፌሰር መስፍን የረሃቡን ወሬ የሰሙት ከተማሪዎቻቸው ነው፡፡ ረሀብ በትግራይ መኖሩ ሲነገራቸው ለንጉሡ መንግሥት ባለስጣናት አቤት አሉ፡፡ ሆኖም መንግሥቱ ለወሬው ደንታ አልነበረውም፡፡ በመሆኑም ፕሮፌሰር መስፍን የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ ከተማሪዎቻቸው ጋር እየዞሩ ከህዝቡ እርዳታ መለመን ነው፡፡ በዚህም የተፈለገውን ያህል ውጤት ለማግኘት ባይችሉም የተወሰኑ ዜጎቻችንን ህይወት ለመታደግ በቅተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በወቅቱ ድምጻቸውን ያሰሙ ብቸኛው ሰው ሆነው በታሪክ ተመዝግበዋል፡፡
    ===የአጣሪ ኮሚሽን===
    የቀዳማዊ ሃይለ ሥላሤ መንግሥት ሲንኮታኮት በርካታ ባለስልጣናት በስልጣናቸው አላግባብ በልጽገዋል በሚል ታስረው ነበር፡፡ የነዚያን ባልስጣናት ጉዳይ አይቶ ለፍርድ የሚያቀርብ አጣሪ ኮሚሽንም ተቋቁሞ ነበር፡፡ የዚያ ኮሚሽን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መስፍን ነበሩ፡፡
    አጣሪ ኮሚሽኑ ምርመራውን በከፍተኛ ሃላፊነትና በሰከነ መንፈስ ማካሄድ ጀመረ፡፡ ይሁንና የኮሚሽኑ አካሄድ ተናዳፊዎቹን የደርግ መኮንኖች ሊያረካ አልቻለም፡፡ በመሆኑም የደርጉ ም/ሊቀመንበር የነበረው ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማሪያም በኮሚሽኑ ስራ ጣልቃ ገብቶ ማወክ ጀመረ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍንንም “ቶሎ ቶሎ መታ አድርግና ጨርስ እንጂ! እስከመቼ ነው እነዚህን አሳማ ባለስልጣናት የምንቀልበው” አላቸው፡፡ ይሁንና ፕሮፌሰር መስፍን ለጓድ መንጌ ጫና አልተበገሩም፡፡ እንዲህ የሚል የድፍረት መልስ ሰጡት፡፡
    “ጓድ ሊቀመንበር! የሀገር መሪ ለታሪክ ጭምር ማሰብ አለበት፡፡ ታሪክ ማለት ዛሬ ስለናንተ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚጻፈው እንዳይመስልዎት፡፡ ታሪክ ጊዜው ሲደርስ እውነቱ ከሐሰቱ ተጣርቶ የሚቀረው ቅሪት ነው”
    ሻለቃ መንግሥቱ በፕሮፌሰር መስፍን አነጋገር ተናደደ፡፡ ወዲያኑ አጣሪ ኮሚሽኑን በመበተን በባለስልጣናቱ ላይ የሞት እርምጃ እንዲወሰድ አደረገ፡፡
    === የብሄራዊ እርቅ ጥያቄ===
    ደርግ ከሻዕቢያና ከህወሐት ጋር የሚያደርገው ጦርነት እየተጠናከረ በመጣበት ወቅት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በጭንቀት ውስጥ ወደቀ፡፡ ብዙዎች “ሀገራችን እንደ ሶማሊያና ላይቤሪያ ልትሆን ነው” በማለት ተወጠሩ፡፡ ይሁንና አንድም ሰው ጦርነቱን ለማስቆም ይበጃል ያለውን ሀሳብ ለመሰንዘር አልቻለም፡፡ በተለይም የጊዜው መሪ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም የርሳቸውን ሃሳብ የሚጻረረውን ሁሉ ያጠፋሉ እየተባለ ይነገር ስለነበር ሁሉም ኢትዮጰያዊ በቤቱ ከትቶ ፈጣሪውን መማጸኑን ነው የመረጠው፡፡
    አንድ ሰው ግን አላስቻለውም፡፡ “ሀገሬ በጦርነት አዙሪት ከምትጠፋ የመሰለኝን ሃሳብ ልሰንዝርና የሚሆነውን ልጠብቅ” በማለት የመሰለውን እርምጃ ለመውሰድ ተነሳ፡፡ “ጦርነቱን ለማቆም ብቸኛው መፍትሔ ብሄራዊ እርቅና ማድረግና የሽማግሌዎች ባለአደራ መንግሥት ማቋቋም ነው” በማለት ለፕሬዚዳንቱ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ፡፡ በሚቋቋመው መንግሥት አወቃቀር ላይ በሂልተን ሆቴል ማብራሪያ ሰጠ፡፡
    ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ “የባልና የሚስት ጥል እንጂ የኢትዮጵያ ጉዳይ በሽማግሌ አይፈታም” በማለት የሰላም ፎርሙላውን አጣጣሉት፡፡ በታሪክ አጋጣሚ የተሰጣቸውን የመጨረሻ እድል አበላሹት፡፡ በመሆኑም መንጌ በወሰዱት የጀብደኝት እርምጃ ለዘልዓለሙ የታሪክ ተወቃሽ ሆነው ቀሩ፡፡ የሰላም ፎርሙላውን ያቀረበው ሰውዬ ግን በታሪክ መዝገብ ስሙን በደማቁ አስጻፈ፡፡
    እንግዲህ ያ ሰውዬ ማለት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ናቸው፡፡ ሰው በጠፋ እለት ሰው ሆነው የተገኙ ደፋር ሰው!!
    ===የለንደን ኮንፈረንስ===
    በግንቦት ወር 1983 የተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫ ከአዲስ አዙሪት ጋር ሊያመጣ እንደሚችል ብዙዎች አስቀድመው ገምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል በማለት በኮንፈረሱ ቦታ የተገኘ ሰው አልነበረም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ግን ስምንት ያህል ምሁራንን በማስተባበር ከኮንፈረንሱ ቦታ ሄደው ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ በተለይም “የኢትዮጵያና ኤርትራ ፍቺ የሁለቱን ህዝቦች ፍላጎት ያገናዘበ ካልሆነ በስተቀር በሁለቱ ህዝቦች መካከል መቃቃርን ይፈጥራል” በማለት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ያ አነጋገር ከሰባት ዓመታት በኋላ እውነት ሆኖ ብዙዎችን አስደንቋል፡፡
    በዚያ ኮንፈረንስ ላይ በጣም አስገራሚ ሆኖ የተገኘው ሌላኛው ነገር ፕሮፌሰር መስፍን ከሻዕቢያው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የነበራቸው ቆይታ ነው፡፡ ከኢሳያስ ጋር እንደ ወንድማማች ሆነው ሲጨዋወቱ ያዩዋቸው ሰዎች “ሁለቱ ሰዎች ከዚያ በፊት ይተዋወቁ ነበር እንዴ?” የሚል ጥያቄ አጭረዋል፡፡ ከአቶ ኢሳያስ ጋር ያወሩትን ያህል ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር አለመቀራረባቸውም ሌላኛው አስገራሚ ነገር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
    === የሰብዓዊ መብት ጉባኤ===
    በሰኔ 1983 የተመሰረተው የሽግግር መንግሥት ያጸደቀው ቻርተር በኢትዮጵያ ውስጥ የሃሳብና የመደራጀት ነጻነት መፈቀዱን አብስሮ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚያ በፊት ባልታየ መልኩ እንደ አሸን ፈሉ፡፡ ህብረ ብሄራዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ተመሰረቱ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ “ሰብዒ መብት” የሚል ለብዙዎች እንግዳ የሆነ ጽንሰ-ሃሳብ በሚዲያ መንሸራሸር ጀመረ፡፡
    አብዛኛው ምሁር ከአንዱ የፖለቲካ ቡድን ጋር ራሱን አቆላለፈ፡፡ የዘመኑ እንግዳ ደራሽ የሆነውን የሰብዓዊ መብት ጽንሰ-ሃሳብ የሚያብራራ ሰው ግን ጠፋ፡፡ በዚህ መሀል ነው ታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር ብዙዎች የረሱትን የሰብዓዊ መብት አጀንዳ በማንሳት ለህዝቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማስረጃ ለመሞገት የተነሱት፡፡ እርሳቸው ያቋቋሙት ድርጅትም ባለፉት ሀያ ሁለት ዓመታት የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠበቃ በመሆን ያሳለፈው ውጣ ውረድ እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡
    ስለ ሰብዓዊ መብትና መከራከርና በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥ በዋነኛነት በመንግሥት መፈጸም የነበረበት ስራ ነው፡፡ በመሆኑም ፕሮፌሰር መስፍን በሰሩት ስራ መንግሥት ከፍተኛ ሽልማት ሊያበረክትላቸው ይገባ ነበር፡፡ ይሁንና የተደረገው የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ የመንግሥት ካድሬዎች ከኢትዮጵያዊ ባህልና ስነ-ምግባር ውጪ ፕሮፌሰር መስፍንን በአጸያፊ ስድቦች ሲያብጠለጥሏቸው ነው የሰነበቱት፡፡ እርሳቸው ግን ስድቡንም ሆነ እስሩን ችለው ለህዝቡ መከራከራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ለህዝባቸው ሲሉ ሁሉንም የተጋፈጡ ጀግና ምሁር!
    ===የኤርትራዊያን መባረር===
    የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተከሰተበት ወቅት “የዐይናቸው ቀለም አላማረንም” የሚል ያልተለመደ ምክንያት እየተሰጠ በርካታ ኤርትራዊያን (በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ) ተባረዋል፡፡ ታዲያ የመንግሥት እርምጃ ከተቃዋሚዎችም ሆነ ከሌሎች ወገኖች ብዙም ተቃውሞ አልገጠመውም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ግን አላስቻላቸውም፡፡ “ሻዕቢያ ወረረን ተብሎ ኤርትራዊያንን በጅምላ ማባረር ታሪካዊ ስህተት መፈጸም ነው፤ ሰዎቹ ከተባረሩም እንኳ የሰብዓዊ መብታቸውን በማይነካ መልኩ መሆን አለበት” በማለት ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ ታዲያ በዚያን ጊዜ የተፈጸመው ነገር እስከ አሁን ድረስ ለብዙዎች እንግዳ ነው፡፡ ለወትሮው ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር በሃሳብ የሚጣጣሙት የግል ጋዜጦችም እንኳ በእርሳቸው ላይ ጀርባቸውን አዙረው የሚበቃቸውን ያህል አብጠለጠሏቸው፡፡ አንዳንዶቹ ጭራሽ ከሻዕቢያ ጉቦ የተቀበሉ አስመሰሏቸው፡፡
    ጥቂት ወራት አለፉ፡፡ ኤርትራዊያንን በጅምላ ማባረር ስህተት መሆኑን ሁሉም አመነ፡፡ መንግሥት ካባረራቸው መካከል ጥቂት የማይባሉት እንደገና ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደረጉ፡፡ በ1997 እንዲያውም “ኖርማላይዜሽን” የሚል እቅድ በተግባር ላይ እንዲውል ተደረገና “በጣም ድንቅ ሃሳብ” ተብሎ ተሞካሸ፡፡ ይሁንና ሁሉንም አስቀድመው የተናገሩት ፕሮፌሰር መስፍን ነበሩ፡፡ ሌሎች የርሳቸውን ሃሳብ ቀምተው ተወደሱበት፡፡ እንዲህ ነች የኛ ኢትዮጵያ!
    ————————
    ፕሮፌሰር መስፍን ማለት በዚህች አጭር ጽሑፍ የሚገለጹ ሰው አይደሉም፡፡ ብዙ ድርሳናትን የሚያስጽፉ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ እኝህ ደፋርና ለህሊናቸው ታማኝ የሆኑ ምሁር በቅርቡ ሰማኒያ ሁለተኛ ዓመታቸውን ያከብራሉ፡፡ ታዲያ አንድ የሚያሳዝነኝ ነገር አለ፡፡ ብዙዎች ግለ-ታሪካቸውን እየጻፉ የህይወት ልምዳቸውን በጥቂቱ እንድንመለከት እያደረጉን ነው፡፡ በዚህ ረገድ ፕሮፌሰር መስፍን እጅግ ዘግይተዋል፡፡ የ20ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ጥልፍልፍ የታሪክ ጉዞ ሊያስተምሩን የሚችሉት ሰው ዝም ብለውናል፡፡
    እነ ልደቱ አያሌውን የመሳሰሉ ትንንሽ ፖለቲከኞች እንኳ “ታሪኬን እወቁልኝ” እያሉ በሚነዘንዙበት ዘመን መስፍንን የመሰለ “አንድ ለእናቱ” የሆነ ሰው ዝም ማለቱ አግባብ አይመስለንም፡፡ ስለዚህ እኝህ የሀገር ቅርስ የሆኑ ታላቅ ሰው በቀሪው የህይወት ዘመናቸው በዚህ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል እላለሁ፡፡
    ————————
    አፈንዲ ሙተቂ
    መጋቢት 6/2006
    ሸገር -አዲስ አበባ

    ጸሓፊ፡-አፈንዲ ሙተቂ:-
     ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስለገለምሶው መምሬ ሙላቱ የምትተርክ አንዲት ጽሑፍ ለጥፌ ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ግን ያቺ ጽሁፍ መሀል መንገድ ላይ ተቆርጣ የቀረች ሆና እየታየችኝ ነው፡፡ ስለዚህ ለናንተም፤ ለወገንም፣ ለታሪክ ጸሓፊያንም እንዲጠቅም ይህችኛዋን ሐተታ እጨምርበት ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

      በ1981 የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ይመስለኛል፡፡ ከትምህርት ቤት መልስ የጨዋታ ጓዶቼን ፍለጋ “ኒብራ” ከተሰኘው የገለምሶ ከተማ ዋነኛ ጎዳና ወረድኩ፡፡ ጓዶቼን ብዙም ርቀት ሳልሄድ ከትልቁ የጋሽ መሐመድ በከር መደብር በረንዳ ላይ አገኘኋቸው፡፡ እዚያም የኳስ ጨዋታ ሰዓታችን እስኪደርስ ድረስ በትረባና በፉገራ መናቆር ጀመርንና አንዱ ሌላውን ለማብሸቅ ይሞካክር ገባ (በጊዜው ትረባ፣ ፉገራና ለከፋ ጊዜያችንን የሚገፋልን ትልቅ መዝናኛችን ነበር)፡፡ እኛ የነበርንበትን በረንዳ በስተግራ በኩል ተጎራብቶ ወደ ታላቁ የሼኽ ዑመር አሊዬ መስጊድና “ሐድራ” ወደሚባለው እስላማዊ ማዕከል (መስጊዱ የሐድራ አንድ ክፍል ነው) የሚያስወጣ መንገድ አለ፡፡ መንገዱ በወቅቱ በጎርፍ ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበር ወደ አስር የሚደርሱ የቀን ሰራተኞች ድንጋይ እየቀጠቀጡ የተቦረቦረውን የመንገዱን የመሀለኛውን ክፍል ይሞሉትና በድንጋዩ ላይ አሸዋ እየመለሱ ይደመድሙት ነበር፡፡
    ይህ የምላችሁ መንገድ በጎርፍ የተጠቃው በዚያን ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ዘወትር ክረምቱን ጠብቆ ከካምቦ ተራራ በሚወርደው ሀይለኛ ጎርፍ እየተደረመሰ አሳሩን ያያል፡፡ የከተማው ማዘጋጃ ቤት በመንገዱ ዳርና ዳር የፍሳሽ መውረጃ ቢሰራለትም ጎርፉ በጣም ከባድ በመሆኑ የተሰራለትን መውረጃ በመተው ወደ መሀል መንገድ ዘው ብሎ እየገባ መንገዱን ማበላሻሸቱ የየዓመቱ ትዕይንት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ መኪና ይቅርና ሰዎችና የጋማ ከብቶችም በዚያ ዳገታማ መንገድ ሲወጡና ሲወርዱ መከራቸውን ነው የሚያዩት፡፡
    ክረምቱ ካለፈ በኋላ መንገዱ ይጠገናል፡፡ ጥገናው የሚከናወነው በአብዛኛው በነጋዴ ግለሰቦች እንጂ በማዘጋጃ ቤቱ አይደለም፡፡ ታዲያ ከላይ በጠቀስኩትና ወሩንና ቀኑን በዘነጋሁት የ1981 አንደኛው ዕለት መንገዱን የሚያስጠግነው ግለሰብ ከወትሮው የተለየ ሆነብኝና በደንብ አየሁት፡፡
    ሰውየው ቄስ ነው፡፡ መንገዱ ደግሞ ወደ መስጊድ የሚያስወጣው ትልቁ መንገድ፡፡ ቄሱ ወደ መስጊድ የሚያስወጣውን ትልቁን መንገድ ያስጠግናል!! አጃዒብ! በልጅነት አዕምሮዬ ተገረምኩ፡፡ በጣም ተደመምኩ፡፡ እናም በአቅራቢያችን የነበሩትን ጋሽ መሐመድ በከርን ስለሰውየውና ስለመንገድ ጥገናው ጠየቅኳቸው፡፡
    “ዛሬ መንገዱን የሚያስጠግነው ቄስ ነው እንዴ?”
    “አይ ቄሱ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ነው”
    “የቱ ቤተክርስቲያን?”
    “መድኃኒ ዓለም ቤተክርስቲያን ነዋ! በገለምሶ ስንት ቤተክርስቲያን ነው ያለው?”
    “ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል? የመስጊድን መንገድ ነው እንዴ ቤተክርስቲያን የሚያስጠግነው?”
    “እንዴት ሊሆን አይችልም? እነርሱስ ቢሆኑ የኛ ሰዎች አይደሉም እንዴ? እኛስ ቤተ ክርስቲያናቸው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ቢጠቃ ዝም ብለን እናያለን እንዴ?”
    ጋሽ መሐመድ የነገረኝ ነገር እውነት መሆኑን በደንብ ያረጋገጥኩት በአስር ሰዓት ገደማ ቄሱ ለሰራተኞቹ ክፍያ በፈጸሙበት ወቅት ነው፡፡ በነጋታውም እኒያ ቄስ ሰራተኞችን አሰማርተው መንገዱን ሲያስጠግኑ ነበር የዋሉት (እኚያ ቄስ የአካባቢያችን ተወላጅ አልነበሩም፤ ለዚህም ነው ስማቸውን ያልያዝኩት፡፡ ሆኖም ቀጠን ብሎ ዘለግ ያለው ሰውነታቸው፣ ጠይም መልካቸውና ሰልካካ አፍንጫቸው እስከ አሁን ድረስ ይታወሱኛል፤ ብዙ ጊዜም ሰማያዊ ቀለም ያለው ቆብ ነው በራሳቸው ላይ የሚያደርጉት)፡፡
    ልብ ያለው ይበል! እንዲህ አይነት ታሪክ በገለምሶ ተፈጽሟል፡፡ የገለምሶ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወደ ሼኽ ዑመር አሊዬ መስጊድ የሚያስወጣውን መንገድ በራሷ ገንዘብ አስጠግናለች፡፡ በገለምሶ የክርስቲያንና ሙስሊሙ ፍቅር እስከዚህ ድረስ ነበር፡፡ ዛሬ በአካል እዚያ ባልኖርም ይህ የጥንት ፍቅራችን አሁንም ድረስ እንዳልቀዘቀዘ ቤተሰቦቼ ያወጉኛል፡፡
    ***** ***** *****
    “የሼኽ ዑመር አሊዬ መስጊድስ ለክርስቲያኖችና ለቤተክርስቲያኒቷ ምን አድርጎ ያውቃል?” ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም መቼስ! እንዲያ ከሆነ የሚከተለውን ታሪክ ላጋራችሁ፡፡
    የሼኽ ዑመር አሊዬ መስጊድ “ሐድራ” የሚባለው እስላማዊ ማዕከል አንዱ ክፍል ነው- ከላይ እንደጠቀስኩት፡፡ ይህ ሐድራ የሚባለው ማዕከል ከትልቁ መስጊድ ሌላ የቁርአን መማሪያ (ቁርአን ጌይ)፣ የዒልሚ መማሪያ (ቤይተል ዒልሚ)፣ የሴቶች መማሪያና መስገጃ፣ የዚክሪና አውራድ ማድረጊያ፣ የአዛውንቶችና የሽማግሌዎች መኖሪያና ሌሎች በርካታ ቤቶች አሉት፡፡ እንዲሁም “ቤይቱል ሐድራ” የሚባለውና የሁሉም እንግዶች ማረፊያ የሆነው ቤት (በስፋቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲውን ልደት አዳራሽ የሚያክል) በዚሁ ሐድራ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ እነዚህ ቤቶች ሁሉ ከዓመት እስከ ዓመት ተመሳሳይ አገልግሎት ነው የሚሰጡት፡፡ በመውሊድ ጊዜ ግን አገልግሎታቸው ይቋረጥና በበዓሉ ለመታደም የሚመጡትን እንግዶች ያስተናግዳሉ፡፡ በየቤቶቹ ውስጥ ሰለዋትና መንዙማ ይደረጋል፡፡
    በገለምሶ የሚከበረው መውሊድ ሞቅ ደመቅ ያለ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የሚታደሙ እንግዶች ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍለሀገራት ይመጣሉ፡፡ ከዚህም አልፎ ከጎረቤት ሀገራት ጭምር (ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና የመን) በርካታ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ እነዚህን እንግዶች ለማስተናገድ በትንሹ አስራ አምስት በሬዎችና ሶስት ግመሎች ይታረዳሉ፡፡ ግመሎችና በሬዎቹን የሚገዙት ግን የሐድራው ሰዎች አይደሉም፡፡ ድሮ በሼኽ ዑመር አሊዬ እጅ የተማሩ ሼኮችና ሌሎች የሼኽ ዑመር ወዳጆች ናቸው ከብቶቹን የሚያመጡት፡፡
    ታዲያ የሐድራው ሀላፊዎችና የመስተንግዶ መሪዎች ወደነርሱ የሚመጡትን ከብቶች በሙሉ አያርዷቸውም፡፡ በቅድሚያ አንድ ወይም ሁለት በሬ ለሴቶች ይሰጥና የከተማው ሴቶች ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት የሚመጡ ወይዛዝርትን እንዲያስተናግዱበት ይደረጋል (በሐድራ ውስጥ ሴትና ወንድ መቀላቀል ክልክል ነው፤ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ምግባቸውን ለየራሳቸው ነው የሚያዘጋጁት፤ ደግሞም የሁለቱም ጾታ ሰዎች ከተፈቀደላቸው ክልል ውጪ መውጣት የለባቸውም)፡፡
    በማስከተልም አንድ በሬ ለስጋ ደዌ በሽታ ተጠቂዎች ይሰጣል፡፡ እንዲህ የሚደረግበትን ምክንያት በትክክል ባላውቅም በዘመኑ በነበረው ልማድ የተነሳ የበሽታው ተጠቂዎች መሸማቀቅ ሳይደርስባቸው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተናግዱ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ይመስለኛል፡፡ በሬዎቹ ለሴቶችና ለስጋ ደዌ ህሙማኑ የሚላኩት ግን ለግብዣና ለፌሽታ ብቻ አይደለም፡፡ በመስተንግዶው የሚታደሙት ሰዎች ሰለዋት ስለሚያደርጉና የነቢዩን ገድል በመንዙማ ስለሚያወድሱ ነው፡፡ እንዲያ የማያደርግ ጀመዓ ለመውሊድ ከመጣው በሬ አንዳች ድርሻ የለውም፡፡
    ነገር ግን ይህ መመሪያ የማይመለከተው አንድ ክፍል አለ፡፡ የገለምሶ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን! በዓሉን የማታከብር ሆኖም ከመውሊድ በሬዎች የራሷ ድርሻ የነበራት ብቸኛ አካል እርሷ ነበረች፡፡ ለዚያውም ለርሷ የሚደርሳት አንድ በሬ ብቻ አይምሰላችሁ! ሁለት በሬዎችን ነው በየዓመቱ የምታገኘው፡፡
    የዚህ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ዕድሜዬ ከፍ ካለ በኋላ ግን ምክንያቱን የሐድራው መሪ የሆኑትን ሼኽ ሙሐመድ ሲራጅን ጠይቄ ከአንደበታቸው ተረዳሁ (ሼኽ ሙሐመድ ሲራጅ የሐድራው መስራች የነበሩት የሼኽ ዑመር አሊዬ ልጅ ናቸው- አሁን ዕድሜአቸው ከዘጠናው ተሻግሮ ወደ መቶ ዓመት እየተጠጋ ነው)፡፡
    ሼኽ ሙሐመድ ሲራጅ ሁለት በሬዎች በየዓመቱ ለቤተክርስቲያን የሚሰጥበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ነበር ያስረዱኝ፡፡
    “እነዚህ ክርስቲያኖች ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንደኛው የአዳም ልጆች ናቸው፡፡ በሀይማኖት ብንለያይም የአንድ ሀገር ሰዎች ነን፡፡ ከዚያም አልፎ የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ነን፡፡ በሬዎቹ ወደኛ የሚመጡት በዓላችንን በደስታ ለማክበር እንድንችል ነው፡፡ እኛ በሬዎቹን አርደን በዓላችንን በደስታ ስናከብር ክርስቲያን ወገኖቻችንን መዘንጋት የለብንም፡፡ እስልምናችን ጎረቤቶቻችንንም ማስደሰት እንዳለብን ያዘናል፡፡ ስለዚህም ነው በሬዎቹን ወደ ቤተክርስቲያን የምንልከው”፡፡
    ***** ***** *****
    እንዲህ ዓይነቱን ውብ ባህል ምንድነው የምትሉት? “መቻቻል” ነው የሚባለው ወይስ ሌላ ስም አለው? እኔ ግን “መቻቻል” አልለውም፡፡ ይህ በተመን የማይመነዘር ፍቅር ነው እንጂ “መቻቻል” የሚለው ዘመን ወለድ ታፔላ የሚለጠፍለት አይሆንም፡፡ “መቻቻል” ሲባል አንዱ ወገን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሌላውን የሚያስከፋ ድርጊት በሚፈጽምበት ጊዜ ሌላኛው ወገን በትዕግስት ችሎ ማለፍ ይገባዋል የሚል እድምታ ያለው ይመስለኛል፡፡ በኔ ከተማ ግን ፍቅር ሰባኪ የሆኑት ሼኮች እና ቄሶች ክፋት ሊፈጸም የሚችልባቸውን ሽንቁሮች ሁሉ ቀድመው የደፈኗቸው በመሆኑ “መቻቻል” የሚባለው አነጋገር እዚያ ዘንድ ተራ ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡ በዚያች እትብቴ በተቀበረባት መሬት ያየሁትና የሰማሁት “ፍቅር” ነው እንጂ “መቻቻል” አልነበረም፡፡
    በኔዋ የገለምሶ ከተማ እንዲህ ዓይነት ፍቅር ነበረን፡፡ በሌላው ኢትዮጵያስ ቢሆን? ዲግሪው (መጠኑ) ይለያይ ይሆናል እንጂ ተመሳሳይ ታሪኮች ሞልተዋል፡፡ እንዲህ በህብረት የኖረውንና ፍቅርን የተቋደሰውን ህዝብ የፖለቲከኞች ወሬ ሆድና ጀርባ ሊያደርገው ከቶ አይቻለውም፡፡ ፖለቲከኞች ይህንን በሌሎች ሀገራት በስለት እንኳ ተፈልጎ የማይገኝ ውብ ባህላችንን በዓለም ዙሪያ ቢያስተዋውቁልን ነው የሚያምርባቸው፡፡
    እኛ አንድ ነን፡፡ ወንድማማቾች ነን፡፡ ፍቅር ነን፡፡ ክብር ነን፡፡ ህብር ነን፡፡ ሰሞነኛ ወሬ አያለያየንም፡፡

    አፈንዲ ሙተቂ
    ነሐሴ 21/2005


    | Copyright © 2013 Lomiy Blog