የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
በጎቹ ጨፌው ላይ – በፍቅር ያዜማሉ፣
ተኩሎች አድፍጠው – ይጠባበቃሉ፣
ጩኸት ሊበረክት-ሊፈስ ሲል ዕንባ፣
እረኛው በድንገት-መሀል ጣልቃ ገባ።
አገር በደም ባህር-ሊጠመቅ ተፈርዶ፣
ውሀ ጥምቀት ሆነ-ከላይ ዝናም ወርዶ።


ቅንጅት፤ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጠራውን የሚያዚያ 30/1997 ዓ.ም ሰልፍ ለመዘገብ ወደ መስቀል አደባባይ ያመራሁት እኩለ-ቀን ላይ ነው። ከረፋዱ 4 ፡00 ሰ ዐት ጀምሮ ታክሲዎች መደበኛ ሥራቸውን ትተው ሰዎችን በነፃ ወደ መስቀል አደባባይ ማመላለስ በመጀመራቸው፤ሰልፉ ምን መልክ ሊኖረው እንደሚችል መገመቱ ቀላል ነበር።ቀድሜ ወደ ሥፍራው የተንቀሳቀስኩትም፤ ማለፊያ መንገድ ሳይዘጋጋ ወደ አደባባዩ ለመቅረብ እንድችል ነው።እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም መቅረፀ-ድምፄንና ካሜራዬን አንግቤያለሁ። የወቅቱ ሀዳር ቀጥሎም የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ኤዲተር የነበረው ዳዊት ከበደ፤ እንዲሁም የሀዳር ምክትል ዋና አዘጋጅ የነበረው ፈለቀ ጥበቡ አብረውኝ አሉ።
የሰው ጎርፍ ከየአቅጣጫው እየተግተለተለ ወደ አንድ ሥፍራ ተከማችቶ እንደ ረጋ ውቅያኖስ ሆነ።ዳርቻው የማይደረስበት ውቅያኖስ።
መለስ፤ ከአንድ ቀን በፊት ያዩትን የኢህአዴግ ሰልፍ በማድነቅ “ማዕበል” ብለው መጥራታቸውን ያስታወሰው ሪፖርተር ጋዜጣ ፤ከቅንጅት ሰልፍ በሁዋላ ባወጣው ርዕሰ-አንቀጽ ” ለማዕበልም፤ ማዕበል አለው” በማለት ነበር ለመለስ ንግግር ምላሽ የሰጣቸው።
የማዕበሎች ሁሉ ማዕበል።
ምኒልክ ጋዜጣ ደግሞ፦”ሱናሚ”ሲል ነው የጠራው።
የሚገርም ቀን።

ሚያዚያ 30/ 97፦ በኢትዮጵያ የሺህ ዓመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታዬ ህልም ሚመስል ትዕይንት።ሚሊዮኖች ነፃነታቸውን በአደባባይ በማወጅ ዲሞክራሲን በጋራ የዘመሩበት ታሪካዊ ቀን።
ሆኖም፤
የሰልፉ አስተባባሪዎች ለዕለቱ የተሰናዳውን ፕሮግራም ለማቅረብ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ፈፅሞ ያልተጠበቀ ነገር ሆነ-መብራት ጠፋ። በወቅቱ ተቀርፎ የነበረው የአዲስ አበባ የመብራት ችግር፤ ከረዥም ወራት በሁዋላ የቅንጅት ሰልፍ ፕሮግራም ሊጀመር ደቂቃዎች ሲቀሩት እንደ አዲስ ተቋረጠ።
እንደ ትናንት የኢህአዴግን ሰልፍ በተንቦገቦገ መብራት ያስተናገደው አደባባይ፤ዛሬ ሚሊዮኖች ለወጡበት ሰልፍ ብርሀኑን ነፈገ።
በተደጋጋሚ ወደ መብራት ሀይል ባለሥልጣን ስልክ በመደወል የተደረገው ጥረትም ሳይሳካ ቀረ።
ጥቂት ሰዎች- ዕልፎችን፦“የጀኔሬተሩ ቁልፍ በእኛ እጅ እሰከሆነ ድረስ ብርሀን እንድታዩ አንፈቅድላችሁም” አሏቸው።
በሆነው ነገር ህዝቡ ተቆጣ። ከዳር እስከ ዳር የተቃውሞ ጩኸት ማሰማት ጀመረ።
የህዝቡ ቁጣ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን የሰጉ የቅንጅት አመራሮችም ፤ የእጅ ማይክራፎን ይዘው በሰልፉ መሀል በመዟዟር ‘ከመብራት መቋረጥ ጀምሮ ሆነ ተብለው እየተፈፀሙ ያሉትን ማናቸውንም የሚያበሳጩ ድርጊቶች ህዝቡ በትዕግስት እንዲያልፋቸው’ በአደራ ጭምር ተማፀኑ።
“…እነሱ የፈለጉት በብስጭት ወደ ህገ-ወጥ ድርጊት እንድንገባ ነው።እያመቻቹን ያሉት የሀይል እርምጃ ለመውሰድ ነው።ንቁባቸው! እንኳን መብራት ማጥፋት ሌላም ነገር ቢፈጽሙ ከህጋዊና ሰላማዊ መስመራችን የማንነቃነቅ የዲሞክራሲ ሰልፈኞች መሆናችንን እንድናሳያቸው፤ ደግመን ደጋግመን አደራ እንላለን!!”
ህዝቡ የመሪዎቹን ጥሪ ተቀብሎ የሚሆነውን ነገር በትዕግስት መጠባበቅ ጀመረ።
በላዩ፤አናት የሚበሳው የፀሀይ ቃጠሎ አለ።

ግን…ግን…
ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች የተሰባሰቡበት ዝግጅት ሊጀመር ፤ደቂቃዎች ሢቀሩ ሆነ ተብሎ መብራት እንዲጠፋ የተደረገው ለምን ይሆን? ?
አንዳፍታ ከእኛ ጋር በሰልፉ መሀል እየተሻሻችሁና እየተገፋፋችሁ ወደ መድረኩ እንድንሄድ ላስቸግራችሁ…
በግምት፤ መድረኩን በ20 ሜትር ርቀት እስከከበበው አጥር ድረስ ከመጣችሁ ይበቃችሁዋል።በቃ! ከዚህ በሁዋላ ማለፍ አትችሉም። ከመንግስት ጋዜጠኞች በስተቀር ማንም ወደ መድረኩ እንዲወጣ አልተፈቀደም።እዛው ቆማችሁ በመድረኩ ጀርባ ስላለው ነገር የምነግራችሁን አዳምጡ።

እኔና ጓደኞቼ ከመድረኩ ሆነን የታሪካዊውን ሰልፍ ፎቶ ለማስቀረት ስለፈለግን ወደ ሰባት ከሚደርሱት የኢቲቪ፣የኢትዮጵያ ራዲዮ እና የራዲዮ ፋና ጋዜጠኞች ጋር በመቀላቀል የተከለለውን አጥር አልፈን ወደ ፊት መራመድ ጀመርን።
ከፊት እየመራ ጋዝይጠኞቹን ወደተዘጋጀላቸው ቦታ የሚወስዳቸው ሰውዬ፤ የግል ፕሬስ ጋዜጠኞች ይቀላቀላሉ ብሎ ስላልገመተ ያለምንም ጥያቄ “ተከተሉኝ”እያለ ወደ ፊት ወሰደን። የሰልፍ መስመር እንደያዝን በኢትዮጵያ ዓለማቀፍ የሰላምና የልማት ኢንስቲትዩት ጓሮ በኩል ገባን።
እንዴ!?
ምንድነው የሚታየው ጉድ!?
ዐይኔን ማመን አልቻልኩም።
ሁላችንም በድንጋጤ እርስ በእርስ ተያዬን።
ከመድረኩ ጀርባ ዙሪያውን በአጥር በተከለለና እንደ ምድር ቤት ዝቅ ባለ ቦታ ላይ በስድስት ከባድ መኪናዎች ላይ የሠፈሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች መትረየሶችንና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ወደ ህዝቡ ደግነው በተጠንቀቅ ይጠባበቃሉ።
አገር ሰላም ብለው መስኩ ላይ በደስታ የሚዘምሩት በጎች እነዚህን ያደፈጡ ነጣቂዎች አላዩዋቸውም።አዎ! እንደኛ ወደ ውስጥ ያልገባ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊያያቸው አይችልም።

በግዮን ሆቴል ጀርባ በኩል የታችኛውን ቤተ-መንግስትና የመስቀል አደባባይን መድረክ የሚያገኛኝ ልዩ መንገድ እንዳለ በዐይኔ ያየሁት የዛን ዕለት ነው።መንግስቱ ሀይለማርያም መስቀል አደባባይ ንግግር ለማድረግ ይመጡ የነበረው በዛ ስውር መንገድ እንደሆነ ይወራል።ነገሩ እንደነ መለስ መንገዱን ጭር በማድረግ አገር ምድሩን ከማሸበር -ይህን ስውር መንገድ መጠቀሙ ይመረጣል ።
ዛሬም በመድረኩ ጀርባ አድፍጠው የሚጠባበቁት ታጣቂዎች ይህን መንገድ ሳይጠቀሙ አልቀሩም ብዬ እገምታለሁ።ያ ካልሆነ፤ ከአንድ ቀን በፊት- ልክ የኢህአዴግ ሰልፍ እንዳበቃ እዛው ቦታ ላይ ሆነው ሌሊቱን ሙሉ ሢጠባበቁ አድረዋል ማለት ነው።
መድረኩ ጫፍ ወጥተን ሥራችንን ጀመርን። የካሜራችንን “ዙም” እያስረዘምንና እያሳጠርን ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን ማስቀረቱን ተያያዝነው።

ባንዲራ ተጎናጽፈው ዕልልታ የሚያሰሙ አዛውንቶች፣ በገላቸው ላይ የቅንጅትን አርማ የተነቀሱ ወጣቶች፣”ትናንት ለገንዘብ፤ዛሬ ለነፃነት”እያሉ መፈክር የሚያሰሙ ሴቶች፣ በወላጆቻቸው ትከሻ ላይ ሆነው ሁለት ጣታቸውን የሚያሳዩ ህፃናት፣”ይትባረክ እንደ አብርሐም!”እያሉ የሚዘምሩ የሰንበት ተማሪዎች፣ “አላህ ወአክበር!” የሚሉ መድረሳዎች፣”ኢየሱስ ጌታ ነው!”እያሉ የሚጮኹ ጴንጤዎች…ማን ነበር የቀረው?
እኚህ ሁሉ፤ በፍቅር ተያይዘው፣በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ ሆነው ዲሞክራሲን እያወደሱ ነው።ሥርዓትና ህግን በጠበቀና ሥልጡን በሆነ መንገድ።

“ሟርት በያዕቆብ ላይ አይሠራም!” ነው የሚለው ታላቁ መፅሐፍ?
አዎ! ኢትዮጵያውያን በአንድ አገራዊ አስተሣሰብ እንዳይቆሙ ለዓመታት ሢቀመም የቆየው የዘርና የሀይማኖት ሥራይ፤ውሀ እንደነካው የደብተራ ክታብ ፈስዶ ታዬ።
ዕልፎች፦
“የሀይማኖት ካብ- ብትክቡ፣
የዘር ገመድ -ብትስቡ፣
ደከማችሁ እንጂ- በከንቱ፣
እኛ ያው ነን-እንደ ጥንቱ፣
እኛ አንድ ነን-እንደ ፊቱ”
እያሉ ተቃቅፈው በዕልልታ ሲዘምሩ ተስተዋሉ።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካሜራ ፤ ለዜና እንኳ የሚሆን ምስል አላገኘም መሰል፤ ገና ሥራ አልጀመረም።መድረኩ ላይ ካሉት በተጨማሪ ፤ለኢቲቪ ምሽት ዜና የሚሆን ትዕይንት የሚፈልጉ ሌሎች ጋዜጠኞችም በሰልፉ መሀከል ካሜራ ይዘው ተሰማርተዋል።ግን እንደታዘዙት፣እንዳሰቡትና እንደተመኙት ረብሻዎችንና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ማግኘት አልቻሉም።
አሁን ግን ሰልፉ መካከል ላይ የሚሰማን ለየት ያለ ጩኸት ተከትለው ከተለያየ አቅጣጫ ካሜራቸውን ወደ መካከል ማነጣጠር ጀመሩ።
ከጀርባ ያደፈጡት ተኩላዎችም፤ ከአንገታቸው ቀጥ ብለውና ጆሯቸውን ቀስረው በተጠንቀቅ ሆኑ።
“በለው! በለው! በለው!…”
“እንዳትነኩት! እንዳትነኩት! እንዳትነኩት!”
የሚሉ ጩኸቶች ከወደመሀል እያስተጋቡ ነው።
ምክንያቱ ምን ይሆን?
በግምት ከ16 ዓመት የማይበልጠው ታዳጊ ህፃን የንብን(የኢህአዴግን) ቲ-ሸርት ለብሶ፤ በዛ የሚሊዮኖች ሰልፍ መሀከል መገኘቱ ነው።
እስኪ አስቡት፤ በዛ ማዕበል፣ በዛ ስሜትና ትርምስ መሀከል(የሰልፉ እንብርት ላይ) የንብን ቲሸርት የለበሰ ሰው፤ያውም ታዳጊ ህፃን! ለእርድ እየተነዳ የመጣ ንፁህ በግ!

ልጁ፤ የንብን ቲ-ሸርት ለብሶ እንዴት ቅንጅት ሰልፍ መሀል ሊገኝ እንደቻለ በአስተባባሪዎቹ ለቀረበለት ጥያቄ፤ ሰዎች፤ ቲ-ሸርቱን አልብሰውና ከላይ ጃኬቱን እንዲደርብ አድርገው እስከመሀከል ድረስ ካመጡት በሁዋላ፤”እንዳይሞቅህ” በማለት ጃኬቱን አውልቀው እንደያዙለት መጠፋፋታቸውን በማብራራት፤ ስለ ፖለቲካ ምንም ግንዛቤ የሌለው መሆኑን ይናገራል። ሆኖም፤ “እነዛ ሰዎች ማናቸው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ይቀራል።
በዚህ ጊዜ ነው፦”በለው! በለው! ካልተናገረ በለው!…..” የሚል ድምፅ በዙሪያው ከነበሩ ወጣቶች የተሰማው። ሆኖም፦” እንዳትነኩት!” የሚለው ድምፅ በእጥፍ ብልጫ ነበረው።

”እንደውም፤ እሱን አውልቁለትና የቅንጅትን ቲ-ሸርት አልብሱት” የሚሉ ወጣቶች ተሰሙ። ሀሳባቸው የጭብጨባ ድጋፍ አገኘ። ልጁ ሲጠየቅም ፈቃደኛ ሆነ።ስማቸውን ያልጠቀሳቸው ሰዎች አልብሰው የላኩትን የጽልመት ግርዶሽ አውጥቶ በመወርወር ልቡ የፈቀደውን ለበሰ።ጭብጨባው ቀለጠ።ተንኮለኞች ይገደል ዘንድ ፈረዱበት።እግዚአብሔር ግን “አትሞትም፤ገና በህይወት ትኖራለህ!” አለው።
ተቀጥቅጦ ይገደል ዘንድ የተላከው ታዳጊ፤ከወገኖቹ ጋር ተቃቅፎ መዘመር ቀጠለ።
አዎ! የመጀመሪያው የተንኮል ድር በዚህ ሁኔታ ተበጣጠሰ።ህፃን ልጅ ቲ-ሸርት አልብሶ ሰልፈኛ መሀል ላይ በመጣል፤ በሱ ጉዳት ምናልባትም፦ በሞቱ ለመነገድ የተወጠነው ሴራ ከሸፈ። ቀጥ ብሎ የነበረው የተኩላዎቹ ጆሮ ረገበ።
”በቅንጅት አመራሮች አደገኛ ፕሮፓጋንዳ የተለከፉ ጥቂት ቦዘኔዎች ለምን የንብ ቲሸርት ለበስክ? በማለት የ 13 ዓመት ታዳጊ ወጣትን ደብድበው ገደሉ” ተብሎ ከወዲሁ ለምሽት የተዘጋጀው የኢቲቪ ዜና ውድቅ ሆነ። ህዝቡ “ነቄ ነን” አለ።
አሁን፤ ከቀኑ 8፡30 ሊሆን ነው።እስካሁን የተቋረጠው መብራት አልመጣም። ዕልልታውና ዝማሬው ግን ከጫፍ ጫፍ እያስተጋባ እንደቀጠለ ነው።ልደቱ አያሌው በአንገቱ ላይ የባንዲራ ስካርቭ አድርጎና በሰዎች ትከሻ ላይ ሆኖ ድንገት ብቅ አለ።
“ማንዴላ! ማንዴላ!ማንዴላ!…..” በማለት ህዝቡ በሆታ ተቀበለው።
ህዝቡ ለሰልፉ የተዘጋጀውን የመሪዎቹን ንግግር በመብራት መቋረጥ ምክንያት ለመስማት ባለመቻሉ፤ ብስጭቱ እየጨመረ መምጣቱን የተገነዘበው ልደቱም፤ሰልፈኞቹ በኤሌክትሪክ ሀይል አለመምጣት ሳቢያ ወዳልሆነ እርምጃ እንዳይገቡ ደጋግሞ ተማፀነ።
ሰዐታት ነጎዱ።

9፡00፣ 9፡30፣ 10፡00፣10፡15…..
የመድረኩ ዝግጅት በመብራት አለመኖር ሳቢያ መቅረቱ ተነገረ።ህዝቡ ዳግም ቁጣ ማሰማት ጀመረ።የመብራቱ ነገር፦”አውቆ የኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም”እንደሆነ በደንብ ገባው።”ካሁን አሁን ይመጣል”የሚለው ተስፋው ጨርሶ ተሟጠጠ።
አዲስ አበባ በጩኸትና በፉጨት ተናጠች።በእስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ካሉት ወጣቶች ፦
”ኢህአዴግ ሌባ!
አል-አሙዲ ሌባ!” የሚል ቁጭትና ንዴት የወለደው ጭፈራ ተሰማ።
ሦስት ሚሊየን ህዝቦች ለሦስት ሰዐታት መብራት ሲከለከሉ የሚፈጥረውን ስሜት በሰልፉ የነበራችሁ ታውቁታላችሁ፤ ያልነበራችሁም ትረዱታላችሁ።
ስለዚህም ወጣቶቹ ንዴታቸውን መግለጽ ጀመሩ።አደባባዩ በውጥረት ተሞላ።ሲቪል የለበሱ ሁለት ሰዎች በመገናኛ ሬዲዮ መልዕክት እየተቀበሉ ከመድረኩ ጀርባ ላሉት አጋዚዎች የሆነ ነገር ነገሯቸው።መሳሪያቸውን አንቀጫቀጩ። እጃቸውን ወደ ቃታ በመላክ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ሆኑ፡፡እርግጠኛ ነኝ፤ እየጠበቁ ያለው፦”ቀጥል!” የሚለውን ትዕዛዝ ብቻ ነው።
ሁኔታውን እያየን ያለነው ጋዜጠኞች የበለጠ ድንጋጤና ጭንቀት ውስጥ ገብተናል።
በወጣቶቹ የተጀመረው የተቃውሞ ጩኸት ዳር እስከ ዳር መቀጣጠል ጀመረ። ተኩላዎቹ ካደፈጡበት በመነሳት ወደ መድረኩ መውጫ በር ተንቀሳቀሱ።የሰልፉ አስተባባሪዎች መረጃ ደረሳቸው መሰል
፦”እባካችሁ ሰልፈኞች አደራ! ምንም ነገር እንዳታደርጉ! አደራ!አዳራ!…’እያሉ እንደ አዲስ አብዝተው መጮኽ ጀመሩ። ህዝቡ ግን፦” የአገራችንን ብርሀን የሚነፍገን ማነው?” እያለ መጠየቁን ቀጠለ።
“ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም፣
እናት ኢትዮጵያ-የደፈረሽ ይውደም!” የሚል ዝማሬ ተከተለ-በምልዓተ-ሰልፉ።

አስጨናቂ ሰዐት።
“አዲስ አበባ በደም ልትታጠብ ነው” የሚል የባህታዊ ትንቢት የሰማሁት፤ ኢህአዴግ ከተማዋን ለመያዝ በተቃረበበት ጊዜ ነበር።ለነገሩ፤ያኔ በመዲናዋ ውስጥ ሰፍረው ከነበሩት የቀድሞ ሥርዓት ወታደሮች ብዛት አኳያ፤ ” የአዲስ አበባ መሬት በደም ይታጠባል” ብሎ ለመናገር የነቢይነት ቅባት የሚጠይቅ አልነበረም።ለዚህም ነው ከባህታውያኑ ባሻገርም የፖለቲካ ተንታኞችም ፦’ስለ አዲስ አበባ የደም ጎርፍ’ ለመተንተን አፋቸው ያልተሳሰረው።
ትዝ ይለኛል፤ ህዝቡ በየአብያተ-ክርስቲያናቱና በየመስጊዱ በመሄድ ፦”አድህነነ ከመዓቱ ሰውረነ!” እያለ ከጧት እስከ ማታ ወደ ፈጣሪው ሲያለቅስ።

እግዚአብሔር ይመስገን!
በወጀብና በአውሎ ነፋስ መካከል መንገድ ያለው ጌታ ፤ትንቢቱንም፤ትንታኔውንም ሽሮ ከዛ አስጨናቂ ሰዐት ህዝቡን በሰላም አሳለፈው።
ዛሬስ ፤ ከዚህች አስጨናቂ ሰዐት እኚህን በጎች የሚታደጋቸው ማን ነው?ዛሬስ ከደቂቃዎች በሁዋላ በመስቀል አደባባይ ሊፈስ ያለውን የደም ጎርፍ ፤ማን ያቆመው ይሆን?
ማንም!
ተስፋ ቆረጥኩ።
አዎ!ስትዘምር የዋለችው ከተማ ማምሻዋን በዋይታ ልትሞላ ነው።”አኬልዳማ- የደም ምድር..”የሚለው የታምራት ዝማሬ ጆሮየ ላይ ደጋግሞ እያንቃጨለ ነው።
የህዝቡ ጩኸት እጅግ በረታ… አስተባባሪዎቹ ፦”ሰልፉ ስለተጠናቀቀ ወደየቤታችሁ ሂዱ!” ቢሉም ፤ህዝቡ እምቢ አለ። ተኩላዎቹ ፤ ከባለ ሬዲዮ መገናኛዎቹ የመጨረሻውን መልዕክት ተቀበሉ መሰል መሳሪያቸውን እንዳቀባበሉና እጃቸውን ቃታ ላይ እንዳደረጉ ከመኪናቸው በመውረድ ፈጠን ባለ እርምጃ ወደ ግቢው መውጫ በር ሄደው አደፈጡ።አስቀያሚው ትዕይንት ሊጀመር ትቂት ሰከንዶች ቀሩ….አንድ..ሁለ…ት….ሦ…ስ…..
ኦ!
ይህን ማን ያምናል?
በዛ ጠራራ ፀሀይ ዶፍ የቀላቀለ ሀይለኛ ዝናም በድንገት ወረደ።በአስተባባሪዎቹ ተማጽኖ አልነቃነቅ ያለው ሰልፈኛ በራሱ ጊዜ እየተሯሯጠ ተበታተነ።ገሚሱ በየቦታው ሲጠለል፤የተቀረው ዝናሙን ተቋቁሞ ወደ ቤቱ ገሰገሰ።ሰልፉ በዚህ መልክ በሰላም ተጠናቀቀ።
የተወጠነው የዕልቂት ድግስ ተጨናገፈ።
የዛን ቀን ምሽት ፦ “ወጥመድ ተሰበረ-እኛም አመለጥን፤ ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይመስገን!” የሚለውን የዳዊት መዝሙር ደጋግሜ ማንበቤን አስታውሳለሁ።
በሆነው ነገር የተደነቁት ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ከጊዜያት በኋላ ይህን ነገር አስታውሰው፦“ኢትዮጵያን የሚጠብቃት አምላክ አላት የሚባለውን ነገር ያስተዋልኩት ያንጊዜ ነው” ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ።
እኛም ከሞት አመለጥን-የ’ሱም እቅድ አልተሳካ፣
የደበደበን ዶፍ ዝናም- ከሞት ሊያድነን ነው ለካ። (ለበጎ ነው ከሚለው የራሴ ግጥም)
ልክ የዛሬ 18 ዓመት ሚያዝያ 30 ቀን 1989 ዓ.ም አቶ አሰፋ ማሩ ወደ ቤቱ ሊገባ ሲል በወያኔ ተረሽኖ ሕይወቱ አለፈ
የኢመማ ጀግኖች ሰማእታትን እናስብ።

የዛሬ 18 ዓመት ሚያዚያ 30 ቀን 1989 ዓ.ም አቶ አስፋ ማሩ ከቤቱ በሰላም ወጥቶ ወደ ሥራ በመሔድ ላይ እያለ በአዲስ አበባ ሐምሌ19 የሕዝብ መነፈሸ አካባቢ በጠራራ ጸሐይ በወያኔ/ኢህአዴግ ነፍሰ ገዳይ ፖሊሶች የጥይት እሩምታ ሰለባ የሆነ ጀግና ኢትዮጵያዊ ነው።
አቶ አሰፋ ማሩ በጊዜው በወሎ ክፍለሀገር በላስታ አውራጃ መቄት ወረዳ በ1951ዓ.ም ተወለደ። በመምህርነት ሙያ ከማገልገሉም ባሻገር በሙያ ማህበሩ የአመራር አባል በመሆንም የመምህራንን መብትና ጥቅም ለማስከበር ፣ የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅ በሚደረገው ትግል በግምባር ቀደምትነት ከሚታገሉት አንዱ ሆኖ ሕይወቱ በግፈኞች እስካለፈበት ዕለት በጽናት ቆሞ ቆይቷል። በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤም በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የላቀ ድርሻ አበርክቷል።
ባለፈው ወርኃ መጋቢት 19፣ ቅዳሜ ቀትር ላይ ከወዳጆቼ አንዱ ይደውልልኛል፡፡ ለጥሪው ምላሽ ስሰጥ፣ በዚያው ሰዓት ከሸገር ኤፍ. ኤም 102.1 እየተላለፈ የነበረውን የቀትር ወሬዎች እንዳዳምጥ ይጠቁመኛል፡፡ የስርጭት መሥመሩን አስተካክዬ ሳዳምጥ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ከምክትል ፕሬዝዳንቶቹ ጋር ስለ ሰጡት መግለጫ የሚተላለፍ ዘገባ ነበር፡፡ ከመግለጫ አርእስተ ጉዳዮች ውስጥ ዩኒቨርስቲው እኔን እና ዶ/ር መረራ ጉዲናን ስለማባረሩ የተመለከተ ማብራሪያ ይገኝበታል፡፡
ዘገባውን በማዳመጥ ላይ እንዳለኹ በአእምሮዬ የመጣችው ዕውቋ ድምፃዊት አስቴር ዐወቀ ነበረች፡፡ የፕሬዝዳንቱን እና በተለይም የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ጄይሉ ዑመርን ከእውነት የማፍግፈግ እና ሐቅን የመሸፋፈን ድርጊት በተመለከተ ‹‹እስኪ ይሰማለት ምን አለችኝ ይላል›› እና ‹‹ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ፤ በአሉባልታ ፈረስ አገር አዳረሰ›› የሚሉት የድምፃዊቷ ዜማዎች እና የዜማ ስንኞች በአዕምሮዬ ላይ ተመላለሱ፡፡
ለአንባቢያን ግልጽ ይኾን ዘንድ ኹለቱ የዩኒቨርስቲው ሹማምንት፣ ከሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ነአምን አሸናፊ ሲቀርብላቸው የሰማኹት ጥያቄ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፡-
“ከሠራተኛ ምደባ ጋራ በተያያዘ ከመድረኩ የተብራራ ነገር ነበር፡፡ ምደባው የተከናወነው በሕጉ መሠረት አድርጎ ግልጽነት በተሞላበት አኳኋን ነው ተብሏል፡፡ በሚዲያዎች እንደምንሰማው ደግሞ ከኹለት ወይም ከሦስት መምህራን የቅጥር ውል እድሳት ጋራ በተያያዘ የተለያዩ ዘገባዎችን እያዳመጥን ነው፡፡ በተለይም ዶ/ር ዳኛቸውን እና ዶ/ር መረራን ይመለከታል፡፡ ከዶ/ር መረራ ጉዳይ ጋራ በተገናኘ የፖሊቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበር ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ ከሓላፊነታቸው መልቀቃቸውን ሰምተናል፡፡ በነዚኽ ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርስቲው አያያዝ እና ምላሽ ምንድን ነው? የሰዎቹ የኮንትራት ውልስ ያልታደሰው ለምንድን ነው? ”
ለዚኽ ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው የሰጧቸው መልሶች፣ የመጀመሪያው የአሠራር ሒደትን የሚመለከት ሲኾን፣ ኹለተኛው ደግሞ የአካዳሚክ ስታፍን የሥራ አፈጻጸም የሚጠቅስ ነው፡፡ ሹማምንቱ በእኒኽ ኹለት ነጥቦች ላይ በማተኮር ከሰጧቸው ምላሾች የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፤
አንደኛ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ከተናገሩት፡-

“የኹለቱ መምህራን ጥያቄ ከጡረታ ጋራ የተያያዘ ነው፡፡ ይኼ እንግዲኽ መንግሥት ያወጣው መመሪያ አለ፤ ደንብ አለ፤ አንድ የአካዳሚክ ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜው ከደረሰና የሚተካው ሰው ከሌለና ከጠፋ፣ የጡረታ ዕድሜው ሊራዘምለት ይችላል፤ ይኼም ፕሮሰስ አለው፤ ከሦስት እና ከአራት ወራት በፊት ቀደም ብሎ መጀመር አለበት፤ በትምህርት ክፍሉ ይታያል፤ ማስታወቂያ ይወጣል፤ በዚያ ሞያ በገበያ ላይ ሰው ማግኘት የማይቻል መኾኑ ማስታወቂያ ይወጣና ትምህርት ክፍሉ ካየው በኋላ ለኮሌጁ ይላካል፤ ኮሌጁ ለአካዳሚክ ይልከዋል፤ ከዚያ ሒደቱን ተከትሎ ወደ ፕሬዝዳንቱ ይመጣና ለሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ይላካል፤ ጡረታ የማራዘሙ ኹኔታ፤ በዚኽ መሠረት የመጣ ጡረታን የማራዘም ጥያቄ የታገደበት ኹኔታ የለም፥ እውነቱን ለመናገር፡፡
… ለማራዘም ደግሞ ወቅቱን ጠብቆ በትክክለኛው መንገድ ማስታወቂያ ወጥቶ ገበያ ላይ ሰው ሳይኖር ሲቀር ያ በደንብ ተጠናቅሮ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ይላካል፤ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ደግሞ ወደ ሲቪል ሰርቪስ የሚጠይቅበት ኹኔታ አለ፤ በነገራችን ላይ የአንድን ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜ ለማራዘም መሥሪያ ቤቱ ፍላጎት ማሳየት አለበት፤ ሠራተኛው ይጠቅመኛል፤ የሚሠራው ሥራ አለ፤ ብሎ በደንብ አድርጎ ማስታወቂያ ማውጣት አለበት፡፡ ይህ ሒደት አለው፤ ይኼ ሕጋዊ ፕሮሰስ አለው፤ ይኼ ሕጋዊ ፕሮሰስ ተግባራዊ ባልኾነበት ኹኔታ የአንድን መምህር የጡረታ ጊዜ ማራዘም አንችልም፡፡”
ኹለተኛ ዶ/ር ጄይሉ ዑመር በበኩላቸው፡-

“ምናልባት በጡረታው ላይ አንድ ነጥብ ብጨምር ደስ ይለኛል፡፡ በመሠረቱ እንደ ሌላው ሲቪል ሰርቫንት አይደለም ሃየር ለርኒንግ አካዳሚክ ኢንስቲቱሽንስ አካዳሚክ ስታፉን የሚያስተዳድሩበት፡፡ እያንዳንዱ አካዳሚክ ስታፍ በየኹለት ዓመቱ ኮንትራት ይታደስለታል፡፡ ኮንትራት ነው የሚፈርመው፡፡ ስለዚኽ በየኹለት ዓመቱ ውስጥ የአካዳሚክ ስታፉ ፐርፎርማንስ በሚፈለገው ደረጃ ካልኾነ ተቋሙ የፈረመውን ኮንትራት ያለማደስ መብት አለው፡፡ ከጡረታ በኋላ ደግሞ የሚነሡ ጥያቄዎች፣ የሥራው ተፈላጊነት እና በቦታው የሚተካ ብቁ ሰው ያለማግኘት ኹኔታ ነው ከጡረታ በኋላ ‘further extension’ የሚጠየቅበት፡፡ በተቋሙ ጡረታን ማስረዘም እንደ ግዴታ ወይም እንደ መብት ሊነሣም አይችልም፤ በዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግ መሠረት፡፡”
ሹማምንቱ የዩኒቨርስቲውን የአሠራር ሒደት እና የአፈጻጸም ምዘና ሕግ ጠቅሰው የሰጡት መግለጫ የተዛባ እና ዕብለት የተመላበት ነው፤ ለዚኽም ሩቅ ሳንሔድ አልያም የእኔን ማብራሪያ ሳይሻ ወሳኝ ምላሽ አድርጌ የማቅርበው በመጀመሪያ ላለፉት አራት ዓመታት የፍልስፍና ትምህርት ክፍልን በሊቀ መንበርነት የመሩት ዶ/ር ጠና ዳዎ የእኔን የጡረታ ጊዜ ስለማራዘም እና ሳባቲካል ፈቃድ በተመለከተ በወቅቱ የሶሻል ሳይንስ ዲን ለነበሩት ለዶ/ር ገብሬ ይንቲሶ የጻፉትን ደብዳቤ ሲሆን በተጨማሪ ዶ/ር ጠናን ተክተለው እስከ አለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የትምህርት ክፍሉ ዋና ሓላፊ የነበሩት ዶ/ር ዐቢይ ጸጋዬ፣ ለማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኑ ፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በዕውቀት፣ በቅርቡ በፍልስፍና ትምህርት መስክ ለሚከፈተው የሦስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) መርሐ ግብር የሥራ ጊዜዬን፣ የሞያ አስተዋፅኦዬን እና ደረጃዬን አስመልክቶ የሰጡትን የማያሻማ ምስክርነት ነው፡፡
የቀድሞው የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበሩ ዶ/ር ጠና ዳዎ ባለፈው ዓመት ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በጻፉት ሦስት ገጽ ደብዳቤአቸው፣ የጡረታዬ ጊዜዬ እንዲራዘም እና የሳባቲካል ፈቃድ እንዲሰጠኝ ትምህርት ክፍሉ መክሮ በወሰነው መሠረት የሚከተለውን ምስክርነት በመስጠት ጥያቄ አቅርበው ነበር፤
“…ትምህርት ክፍሉ አገልግሎታቸውን አጥብቆ የሚፈልግ በመኾኑ ደብዳቤአቸውን መነሻ በማድረግ የጡረታ ጊዜ እንዲራዘምላቸው መጠየቅ ወይም እርሳቸውን የሚተካ ባለሞያ ማዘጋጀት ነበረበት፡፡ በዚኽ መሠረት በዕድገትም ኾነ በድልድል እርሳቸውን ሊተካ የሚችል ከክፍሉ መምህራን መካከል ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለዚኽ በእርሳቸው ቦታ መቀጠር የሚችል መምህር ለመፈለግ በእርሳቸው ጠያቂነት ዩኒቨርስቲው በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲያወጣ ተደረገ፡፡ ይኹን እንጂ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ያመለከተ ሰው ባለመኖሩ ትምህርት ክፍሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአመለከቱት መሠረት የአገልግሎት ጊዜአቸው እንዲራዘም ጠየቀ፡፡
…. የትምህርት ክፍሉ ባለበት የመምህራን እጥረት ምክንያት የእርሳቸውን አገልግሎት በእጅጉ ይፈልጋል፡፡ በመኾኑም የተጠቀሰው የጡረታ ጊዜ እንዲራዘምላቸውና የሳባቲካል ፈቃዳቸው የሚራዘምበት ኹኔታ እንዲመቻችላቸው የትምህርት ክፍሉ ይጠይቃል፡፡”
ዶ/ር ዐቢይ ጸጋዬ በበኩላቸው የኮንትራት ዉሌ እንዲራዘም ካቀረቡት ምክንያቶቸ ውስጥ በዋናነት የሚከተለውን እናገኛል፡-
‘Launching of the PhD program:
The department is ready to launch the PhD program during the second semester of the current academic year. The program contains two streams of the studies: Africans and Western philosophy. Even though we have excellent instructors in our department in African and Asian philosophy, Dr. Dagnachew is the only Ethiopian staff who has done his PhD in Western philosophy, as a result his services are indispensable in covering the Western stream.
In view of his diligence as a teacher and strong commitment to the world of academia, and also in lieu of his much needed services by the department, the Department is strongly looking forward for your good office to extend his services by three years.’
ይህም የእንግሊዘኛ ጽሑፍ ወደ አማርኛ ሲተረጎም፡-

“የዶክትሬት ዲግሪ መርሐ ግብር ስለ መጀመር፤
የፍልስፍና ዲፓርትመንት በተያዘው የትምህርት ዘመን ኹለተኛ አጋማሽ ላይ የዶክትሬት ዲግሪ መርሐ ግብር ይጀምራል፡፡ መርሐ ግብሩ የአፍሪቃ ፍልስፍና እና የምዕራብ ፍልስፍና የተሰኙ ኹለት የጥናት ዘርፎችን የያዘ ነው፡፡ የትምህርት ክፍላችን በአፍሪቃ እና ኤዥያ ፍልስፍና ጥናት ላቂያ ያላቸው መምህራን ቢኖሩትም በምዕራብ ፍልስፍና አስተምህሮ የዶክትሬት ጥናታቸውን የሠሩ የዲፓርትመንቱ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ባልደረባ፣ ዶ/ር ዳኛቸው በመኾናቸው በዘርፉ ያላቸው አስተዋፅኦ በእጅጉ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው፡፡

ዶ/ር ዳኛቸው ለመምህርነት ሞያ ያላቸው አቅም እና ተነሣሽነት እንዲኹም በአካዳሚው መድረክ (በዩኒቨርስቲው) የሚያሳዩት ትጋት ለትምህርት ክፍላችን ከሚኖረው ጠቀሜታ በመነሣት የአገልግሎት ዘመናቸው መራዘም አስፈላጊ መኾኑ ታምኖበታል፡፡ ስለዚኽም የትምህርት ክፍሉ የዶ/ር ዳኛቸው የሥራ ጊዜ በሦስት ተጨማሪ ዓመታት እንዲራዘም ይደረግ ዘንድ የቢሮውን መልካም ትብብር ይጠይቃል፡፡”
ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው ከተናገሩት በተፃራሪ ከዚኽ በላይ በአስረጅነት የቀረቡት ሰነዶች ለአንባቢያን እውነታውን በሚገባ ያሳያሉ ብዬ አምናለኹ፡፡ በፍልስፍና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች የቀረበው ገለፃ፣ የሁለቱን ሹማምንት እበላ እና ሃሰተኛ አቀራረብ ፍንትው አድርጎ እንደሚያሳይ ብዙም ክርክር አያስፈልገውም፡፡
ምናልባት እነኚህ በትልቅ ተቋም ውስጥ በኃላፊነት የተቀመጡ ግለሰቦች፣ እንዴት ከእውነት ጋር የተጣላ ግንኙነት ሊኖራቸው ቻለ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ይኖራል፡፡ እኔ እስከምረዳው ድረስ ሁለቱ ግለሰቦች የሚከተሉት ፈለግ ከእምሯዊ ግድፈት የመነጨ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ የተደላደለ ኑሮን ለመጎናጸፍ እውነት መሽቀንጠር ካለባት ያለ ምንም ማቅማማት ገፍትረው ለመጣል ምን ግዜም ዝግጁ በመሆናቸው ነው፡፡
የድሎትንና የውሸትን ግንኙነት እና መስተጋብር ለመረዳት፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ‹‹ውይይት›› (Dailogue) በሚል ርዕስ በዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር የሚታተም መጽሔት ላይ የዛሬ አርባ አምስት ዓመት የደጃዝማች ከበደ ተሰማን ‹‹የታሪክ ማስታወሻ›› የሚባለውን አስደናቂ መጽሐፍ ሲገመግሙ፣ በአንድ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል፡-
‹‹… ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ መጠይቅ አይሻም፤ በአንድ በኩል እንጀራቸው ውሸት መሆኑን፣ በአንድ በኩል ደግሞ የእውነትን ግርማና ሥቃይ ያውቁታል፡፡›› ፕ/ሩ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሁለት አበይት የሆኑ ጉዳዮችን አቅርበዋል፡፡ አንደኛ፣ አንዳንድ ሰዎች ውሸትን የሚኖሩት ብቻ ሳይሆን፣ እንጀራቸው ውሸት ላይ የተመሰረተ መሆኑን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ‹‹እውነት ማለት የኔ ልጅ›› ብሎ እውነትን መጨበጥና አብሮ መራመድ አልፎ-አልፎ አደጋ እና ችግር እንደሚያስከትል በተዋበ ስንኝ የነገረንን፣ ከላይ እንዳየነው ቀደም ሲል ፕ/ር መስፍን የእውነትን “ግርማና” ችግር መሸከም አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ ውሸት ማዘንበሉን ይመርጣሉ ሲሉ በሚያምር ገለፃ አቅርበውታል፡፡
በሌላ በኩል ኹለቱ ሹማምንት ስለ ጡረታ ጊዜ ማራዘም ከሰጧቸው ማብራሪያዎች እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ነገሮችን መመልከቱ አስቸጋሪ አይኾንም፡፡ ከኹሉ በፊት፣ ፕሬዝዳንቱ የጡረታ ጊዜን ለማራዘም ዩኒቨርስቲው ጥያቄ ያቀርባል እንጂ፣ ሥልጣኑ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ደግሞ የጡረታ ጊዜውን ለማራዘም ወሳኝ የኾነው ሒደት በዩኒቨርስቲው ተቋማዊ ሥርዐት እና ደንብ ውስጥ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ይኸው በራሳቸው ቃል በወሳኝነት የተገለጸውና ዲፓርትመንቱ እንዲኹም ኮሌጁ ሕጋዊ አካሔዱን ተከትለው ያቀረቡትን የማራዘም ጥያቄ ተቀብለው ተገቢውን ምላሽ መስጠት ተስኗቸዋል፡፡ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴርም ቢኾን በዩኒቨርስቲው የተጠየቀውን የጡረታ ማራዘም ጥያቄ ያለአንዳች ማንገራገር ተቀብሎ ያስተናግዳል እንጂ፣ ፕሬዝዳንቱ ከተጠያቂነት ለመሸሽ እንዳደረጉት፣ ‹‹ሞያዊ አስተዋፅኦው ተፈላጊ ነው›› የተባለን መምህር የማባረሪያ ምክንያት ሊኾን አይችልም፡
ሳባቲካል ፈቃድን በተመለከተ፣ አሠራሩ አንድ መምህር ለስድስት ተከታታይ ዓመት ካስተማረ፣ አንድ ዓመት የጥናት እና ምርምር ፈቃድ ዕረፍት እንደሚያገኝ በሴኔት ሕጉም ኾነ በሥራ ውሉ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡ ኾኖም ፕሬዝዳንቱ አንድ መምህር በማመልከቻ ቅጹ መሠረት ፈቃዱን ሲጠይቅ ጠቅሶ እና አካትቶ የሚያቀርባቸውን የተለመዱ ነጥቦች የማይታወቁ ያኽል፣ ከሳባቲካል ፈቃድ መልስ ‹‹ብቁ አስተማሪ ይኾናል፤ ምርምር እየሠራ አስተዋፅኦ ያደርጋል›› በማለት መናገራቸው ነገሮችን ለማወሳሰብ ካልኾነ በቀር፣ ለተያዘው ጉዳይ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ በእኔ ሳባቲካል ፈቃድ ጉዳይ ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት የሚያመራ ቢኾንም ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው ከተናገሩት በተቃራኒ ከጡረታ ዘመኔ በፊት ማቅረቤን የሚያሳይ ማስረጃ በእጄ ይገኛል፡፡

ነፃነትና ዩኒቨርስቲ


ከግል ጉዳዬ ትንሽ ፎቀቅ ብዬ ስለሰው ልጅ የነፃነት ሕሊና እና ስለ ዩኒቨርስቲ ባህርያት የተወሰኑ ነጥቦችን ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡
Beings who have received the gift of freedom are not content with enjoyment of
comfort granted by others.
[ Immanuel Kant, The Quarrel Between the Faculties (1798) ]
ትርጉም፡- የነፃነትን ጸጋ የተሰጡ ህልዋን (ሰዎች) ከሌሎች በሚናኝ ተድላ እና ምቾት፣ ደስታ እና እርካታ
አያገኙም፡፡ (ኢማኑኤል ካንት)
ነፃነት ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ባሕርያዊ ቢኾንም፣ አልፎ አልፎ ሰው ለቁሳዊ እና ጊዜያዊ ፍላጎቱ ሲል፣ ባሕርያዊ ነፃነቱን አሳልፎ ይሰጣል፤ መጽሐፉም፣ ብኵርናውን በምስር ወጥ ስለለወጠው ዔሳው ያስተምረናል፡፡ በዩኒቨርስቲው ላዕላዊ አመራር ውስጥ ያለው ሰብአዊ እና አእምሯዊ ነፃነትን ከሚፈታተኑ ቁልፍ ችግሮች አንዱ ይኼ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ ከመልካም አስተዳደር የተጣላ ሥርዐት እንዲያብብ ያደረገው በዩኒቨርስቲው አሠራር ውስጥ የሰረገው ጥቅምን መሠረት ያደረገ ሽርክናዊነት (Patrimonialism) ነው፡፡ እንደ ዕውቁ የኻኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሥነ ማኅበረሰብ ተመራማሪ ማክስ ቬበር (Max Weber)፣ ጥቅምን መሠረት ያደረገ ዝምድና በመደበኛ እና በግላዊ የሥራ ድባብ መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡ አንድን ተቋም የሚመለከት ጉዳይ በሙሉ ከተቋሙ ዋነኞች የግል ስንክሳር ጋራ በማቆራኘት ነው የሚወስደው፤ ሲከፋም ተቋሙን ሳይቀር እንደ ግል ንብረት ይቆጥራል፡፡
ለዚኽም ነው፣ ዶ/ር አድማሱ በድርጊቶቻቸው እና በመግለጫዎቻቸው ደጋግመው እንዳረጋገጡት፣ ዩኒቨርስቲው ሲተች እርሳቸው በግል እንደተተቹ፣ የእርሳቸውም የአመራር አቅም ሲጠየቅ፣ የዩኒቨርስቲው ስም እንደ ጎደፈ እና እንደጠፋ የሚመስላቸው፡፡
በዚኽ ጽሑፌ ዋናው መልእክቴ፣ የፕሬዝዳንቱ እና የምክትላቸው ማብራሪያዎች እኔን በትክክል እና በአግባቡ ከሚገልጹ የዩኒቨርስቲው ሰነዶች ጋራ የቱን ያኽል እንደሚራራቁ ማስረዳት ነው፡፡ስለ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ፣ ‹‹የካውንት ሊዮ ቶልስቶይ ጀነራል እና የኢሕአዴጉ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት›› በሚል ርእስ ሰፋ ያለ ሐተታ በቅርብ አቀርባለኹ፡፡ የጥቅቅም ሽርክናው (Patrimonialism) በተመለከተ ግን ለጊዜው፣ ምክትላቸው ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ያሉበትን ኹኔታ በአብነት አቀርቤ ጽሑፌን እቋጫለኹ፡፡
ከላይ እንዳወሳነው፣ ሰብአዊ እና አእምሯዊ ነፃነትን በሚፈታተነው የዩኒቨርስቲው የጥቅቅም ሽርክና የተመላበት የሥራ ዝምድና፣ ለሓላፊነት እና ለሹመት ለመታጨት ቀዳሚ መለኪያው አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ብቃት ሳይኾን፣ በአገሪቱ የፖሊቲካ ክፍል በጠንካራ ዐቃቤ (Patron) መደገፍ ወሳኝ ነው፡፡ በዩኒቨርስቲው ላዕላዊ አመራር ጠገግ ጠንካራ ዐቃቤ እና የፓርቲ ድጋፍ የሌለው ከፍተኛ ሹም ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ይህን የተደገፉበትን ጠንካራ አጋር ሲያጡ በራስ መተማመናቸው ከድቷቸው በሌሎች መገፍተሩ እና መናቁ የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥቂት በማይባሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ዘንድ እንደሚነገረውም፣ የዶ/ር ጄይሉ ዑመር ችግር ከዚኽ ያልተለየ ነው፡፡
አንድ አረጋዊ ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋራ በተያያዘ ያጫወቱኝ ነገር ዶ/ር ጂይሉ ዑመር ያሉበትን ኹኔታ በትክክል ሊያስረዳልኝ ይችላል፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ የሚወዱት ‘ቀንዲል’ የሚባል በሬ ነበራቸው፡፡ በሬው ባሻው ማሳ እየገባ ይበላል፤ በመሸበት ያድራል፤ ገበሬው ይቅርና ሹመኞቹ እንዲሁም ጅብ እንኳን ሳይቀር ዐፄውን ስለሚፈሩ ‹‹ማንም አይነካውም›› ይባል ነበር፡፡
የንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ፍጻሜ ሲቃረብ ግን፣ በሬው ይጠፋል፡፡ ብዙ ቢታሰስም መገኛው ባለመታወቁ በጅብ ሳይኾን በገበሬዎች ታርዶ እንደተበላ ለንጉሡ ጭምጭምታ ይደርሳቸዋል፡፡ ከበሬው መጥፋት በኋላ በአጀብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው ሲሔዱ በአንዳንድ ቦታ ባላገሩ ፍርድ እንዲያገኝ፣ ‹‹ንጉሥ ሆይ፣ ጃንሆይ›› እያለ አቤት ሲል፣ በፈረሳቸው እንዳሉ ወደ አጃቢዎቻቸው ዘወር እያሉ ‹‹አኹን እኮ የእውነት ‹ንጉሥ› እየመሰልኋቸው ነው›› ሲሉ አጃቢዎቻቸው ‹‹በሚገባ እንጂ፣ ንጉሥ ነዎት እኮ›› ሲሏቸው፤ እሳቸውም ‹‹የእውነት ንጉሥ ብኾን ኖሮ ‘ቀንዲልን’ አርደው ይበሉት ነበር ወይ?›› ብለው በመደመም ሳይፈርዱ አልፈው ይሔዱ ነበር፡፡
ዶ/ር ጄይሉ ዑመርም በሥልጣናቸው ክልል ሊታይና ሊወሰንበት የሚችልን ጉዳይ እና አቤቱታ ሲቀርብላቸው፣ በአንድ በኩል መልስ ባለመስጠት (በእኔ ላይ እንዳደረጉት) በሌላ በኩል ወደ ፕሬዝዳንቱ በመግፋት ድርሻቸውን አይወጡም፤ ከሓላፊነትም ይሸሻሉ፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ፍጻሜ መንግሥታቸው የተዳረሰባቸው ንጉሠ ነገሥቱ ‹‹አኹን እኮ ንጉሥ መስዬአቸው ነው›› እንዳሉት ዐቃቤአቸውን ማጣታቸውን ተከትሎ ‹‹አኹን እኮ የእውነት ምክትል አካዳሚክ ፕሬዝዳንት እየመሰልኋቸው ነው›› ሳይሉ ቀርተው ነው ብላችኹ ነው!?
እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው፣ ዶ/ር ጄሉ ዑመር ያለ አጋር እና ድጋፍ (Patron) መሆናቸውን ቀድመው የተረዱት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ናቸው፡፡ ምክትላቸው የበላይ ጠባቂያቸው እንደሌለ ሲያውቁ፣ በመጀመሪያ ያደረጉት ነገር በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመምህራኑን የውል ዘመን የማራዘም ሥልጣን የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሆኖ ሳለ፣ ፕሬዝዳንቱ የሆነ የሲቭል ሰርቪስ አንቀጽ ጠቅሰው ይሄንን ሥልጣናቸውን ወደ ራሳቸው ጠቅልለዋል፡፡ የም/ል ፕሬዝዳንቱን ሥልጣን የመጠቅለል ድርጊት በተለያየ ኹኔታ ስለተከሰተ ማስረጃ ማቅረቡ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ ለዚህም ነው ዶ/ር ጄሉ ዑመር የውሳኔ ጉዳይ ሲቀርብላቸው አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፕሬዝዳንቱ ቢሮ የሚያስተላልፉት፡፡
ጉዳያችንን ከመቋጨታችን በፊት፣ ስለ ዩኒቨርስቲ ምንነት ጥቂት ነጥቦች ማንሳቱ ተገቢ ነው፡፡ ይሄም የሚሆንበት ምክንያት፣ ዩኒቨርስቲ መሆን የሚገባውን አጠቃላይ ገጽታ በጥቂቱም ቢሆን እያቀረብን፣ በአንፃሩ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁን ያለበትን ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ለመቃኘት ይረዳናልና፡፡
ይሄንንም ለመተግበር በቅርቡ በፕሮፌሰር አለን ብሉም (Allan Bloom) The Closing of the American Mind በሚል ርዕስ ስለ ዩኒቨርስቲ በፃፉት ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ ይሆናል፡፡ እንደ እርሳቸው አቀራረብ ዩኒቨርስቲ ቢያንስ- ቢያንስ የሚከተሉትን አራት ባህሪያትን ይይዛል፡፡
አንደኛ- ዩኒቨርስቲ ‹‹ከብርሃነ-ህሊና›› ጋር የተያያዘ ገጽታ አለው፡፡ ይሄም ማለት፣ ዩኒቨርስቲ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚደረግ አዕምሯዊ ወይንም የአመለካከት ሽግግር የሚካሄድበት መድረክ ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ጉዞ ማለት ደግሞ ከአስተያየት፣ ከመላምት፣ ከዘልማድ፣ ከደመነፍስ ወዘተርፈ የምንቀበላቸውን ኹነቶች በአግባቡ ፈትሸን ከአለማወቅ ወደ ማወቅ የምንሸጋገርበት ሂደት ነው፡፡ ጥንታዊ ግሪካዊያን እንደሚሉት ሽግግሩ በአጠቃላይ ከአስተያየት (Doxa) ወደ ሳይንስ (Episteme) ይሆናል ማለት ነው፡፡

ኹለተኛ- ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የተሰጠው ማንኛውም ተቋም በሙሉ፣ ሁለት ቁም ነገሮችን አቅፎ የያዘ ነው፡፡ 1. ዩኒቨርስቲ ማለት የአዕምሮ ህይወት ተዘርቶ የሚኮተኮትበት መስክ ነው፡፡
2. ዩኒቨርስቲ በማያጠራጥር መልኩ ‹ምክንያታዊነትን› በበላይነት አንግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡
ሦስተኛ- ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም በሰው ልጅ ታሪክ የተነሱትን ጥያቄዎች እንዳይረሱና እንደገና እንዲፈተሹ የሚያደርግ ሲሆን፣ አሁን ባለንበት ጊዜም ቢሆን አዳዲስ ጥያቄዎችን አንስቶ የሚወያዩበት እና ከግለሰብ ሆነም ከአገር አስተዳዳሪዎች የሚመጣን ሃሳብ በወል የሚመረመርበት ሥፍራ ነው፡፡ ዩኒቨርስቲ በአንድ በኩል ‹‹ጥቅም አቅራቢ›› በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ችግር ፈቺ›› መሆን አለበት በሚል ፈሊጥ የተነሳበትን ዓበይት ርዕይ እና ዓላማ መሳት የለበትም፡፡

አራተኛ- ብዙ ጊዜ ሀገር የሚያስተዳድሩ ባለሥልጣናት አንድ ፖሊሲ ወይንም መመሪያ ከቀረጹ በኋላ፣ ለህዝቡ ይህ ከመሆን በቀር ‹‹ሌላ አማራጭ የለም›› በማለት ሃሳባቸውን ያለ ምንም ተገዳዳሪ ሃሳብ ለመተግበር ይፈልጋሉ፤ በአንፃሩ ዩኒቨርስቲ ይበጃል ተብሎ በብቸኝነት የቀረበን ሃሳብ አሻሽሎ ወይንም ሽሮ አሊያም በርካታ የሆኑ አማራጭ ሃሳቦችን ማቅረብ የሚችል ተቋም ነው፡፡
ስለዩኒቨርስቲ ባህሪያት ይሄንን ካልን ዘንዳ፣ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥቂት ነገሮችን ብለን ብዬ ጽሑፌን አጠናቅቃለሁ፡፡ የዩኒቨርስቲ ልዕልና ወይም የአካዳሚክ ነፃነት፣ ከሀገሪቱ የፖለቲካ ሥርዓት ጋራ በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሊብራል ዴሞክራሲ በሰፈነበት ቦታ የአንድ ዩኒቨርስቲ ልዕልና የተከበረ ይሆናል፡፡
ወደ እኛ ሀገር በምንመጣበት ጊዜ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ፓርቲ የምከተለው ሥርዓት ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ነው ብሎ ያምናል፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እንደተመለከትነው ደግሞ ሥርዓቱ ለማንም ተቋም ልዕልና እና በራስ የመወሰንን መብት የማይሰጥ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ገዢው ፓርቲ አንድን ነፃ ተቋም መቆጣጠር ሲፈልግ አስቀድሞ የእርሱን ፍልስፍና እና ፈለግ የማይከተሉትን አስተዳዳሪዎች ይሽርና የራሱን ሰዎችና ካድሬዎች በቦታው ላይ ይሾማል፡፡ በቅርብ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ውስጥ የተካሄደው ይሄው ነው፡፡
ወደ ፕሮፌሰር ብሉም መጽሐፍ ልመለስና አንድ ያስደመመኝን ነገር ላቅርብ፤ በጀርመን አገር ‹‹ናሽናል ሶሻሊስት ፓርቲ›› (የሂትለር ፓርቲ) ሥልጣን ሲይዝ በአገር ውስጥ ያሉትን ዩኒቨርስቲዎች በሙሉ በቁጥጥር ሥር ያውልና የፓርቲውን ተቀዳሚ ካድሬዎች በአስተዳዳሪነት ይሾማል፡፡ ይሄንን የታዘበ አንድ የሕገ-መንግሥት ኅልዮት ባለሟል፣ ምንም እንኳን እርሱ ራሱ የፋሽስት ፓርቲ አቀንቃኝ ቢሆንም ነገሩ አንገሽግሾት ‹‹አሁን ገና ሄግል በጀርመን ሞተ›› ብሎ ትዝብቱን ተናገረ፡፡ይህንንም በዋነኛነት ያለበት ምክንያት ሄግል ለብዙ ዓመታት በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያገለገለ ስለሆነ ነው፡፡
እኔም አሁን በከፍተኛ አመራር ላይ ያለውን የዩኒቨርስቲ የካድሬ ስብስብ በምመለከትበት ጊዜ የተሰማኝ ልክ ‹‹ሄግል አሁን ገና በጀርመን ሞተ›› እንደተባለው፣ በኢትዮጵያም እነ ታደሰ ታምራት፣ ሠርገወ ሀብለሥላሴ፣ መርዕድ ወልደ አረጋይ፣ ካሳ ወልደማርያም፣ ዮናስ አድማሱ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ደበበ ሠይፉ እና ሌሎችም በህይወት የሌሉ በዩኒቨርስቲ ያስተማሩ አሁን ገና እንደሞቱ ተሰማኝ፡፡

ያሬድ ጥበቡ በትግል ስማቸው ጌታቸው ጀቤሳ ይህን ጽሁፍ ያሰፈሩት በፌስቡክ ገጻቸው ነበር:: ለግንዛቤ ይረዳል ብለን በማሰብ አካፍለናችኋል:: 

ይህ ፎቶ ከተነሳ 30 አመት ሆነው ። የካርቱምን የአራዊት መናኸሪያ (ዙ)፣ ስንጎበኝ የተነሳነው ነው ። ከግራ ወደቀኝ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታምራት ላይኔ፣ ዳዊት፣ ሙሉአለም አበበና እኔ ነን ። ህላዌ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ሲሆን፣ እኔ ታምራትና ዳዊት በአሜሪካ ስደተኞች ነን ። ሙሉአለም የኢህአዴግ የአዲስ አበበሰ ከንቲባ ሆኖ ካገለገለ በሁዋላ፣ አጨቃጫቂ ነበረ ከተባለ የብአዴን ስብሰባ መልስ፣ ባህርዳር ቤተመንግስት አልጋው ላይ ተንጋሎ ሳለ፣ መስኮቱ ክፍት ስለነበር ከውጪ በተወረወረ የእጅ ቦምብ መገደሉን ሰምቻለሁ ።
ዳዊት የወያኔ ባታሊየን ኮማንደር የነበረ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተሰዶ መጥቶ 22ኛ ና ፒ ስትሪት መገናኛ ላይ የቤንዚን ማደያ ተቀጣሪ ሆኖ ሲሰራ አየሁት ። እናም አዘንኩ ። በስንት ጦር ሜዳ ጀግንነቱን ያስመሰከረ የጦር መሪ ዝቅ ብሎ ለእለት ጉርሱ ሲማስን ማየት ልብ ደሰብራል ። ዝም ብሎ የወያኔ ጄኔራል በመሆን የፎቆች ባለቤት እንደማይኮንና፣ የፖለቲካ ሰልፍን ካላሰመሩ ትግሬነትም ሆነ ጀግንነት ብቻውን ፋይዳ እንደሌለው ዳዊት ጥሩ ምስክር ይመስለኛል ።
ታምራት ከእስር እንደተለቀቀ በስልክ የተገናኘን ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ የጴንጤዎች ስብሰባ ላይ ሲያለቃቅስ በዩቱብ ከማየት ውጪ ሰምቼውም አግኝቼውም አላውቅም ። ወደ ሃይማኖት ፊቱን ማዞሩን አልጠላሁትም ነበር ። እኔ ራሴም ፊቴን ወደመንፈሳዊ ጥናቶች መልሼ እነ ኤካርት ቶሌን ማጥናት ጀምሬ ስለነበር፣ ታምራት “ከእንግዲህ ስለ ፍቅር አስተምራለሁ” ማለቱን ወድጄው ነበር ። በብቸኛው የስልክ ወሬያችንም ያንን የገለፅኩለት ይመስለኛል ። ሆኖም አሜሪካ ሲመጣ መገናኘት አልፈለገም ። የመጨረሻዎቹ የበረሃ አመታት ላይ አርሱ ከነመለስ ወግኖ የቆመ ቢሆንም፣ አግኝቼ ላወራው ግን ይናፍቀኛል ። የሆነው ሁሉ እንዴት እንደሆነ የርሱን ግንዛቤና አስተያየት ለማወቅ ሁሌም እፈልጋለሁ።
ከኢህአፓና ኢህዴን የበረሃ ህይወታችን በኋላ ከህላዌ ጋር የተገናኘነው ሁለት ጊዜ ነው ። አንዱ ከምርጫ 97 ሁለት ወራትበፊት አዲስ አበባ በሄድኩበት ወቅት፣ ምክትል ከንቲባ ሳለ አርከበ ቢሮ ውስጥ ያደረግነው አጭር ውይይት ነው ። ሌላ ጊዜ የተገናኘነው ከበረከት ጋር ዋሽንግተን መጥተው፣ አምባሳደር ብርሀኔ በቤቱ የራት ግብዣ አድርጎላቸው ሳለ ነው ። አመሻሽ ላይ ውጪ እናውራ ተባበለን በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ሳለ፣ ቃል አቀባይ ሶሎሜ ታደሰ መጣችና “ደህነታችሁን ለማረጋገጥ ነው” ብላ ቀለደች ። ህላዌም ሲመልስ “ነገ አንቺ ከሰልፈኛው ጎን ቆመሽ ይሰቀሉ እያልሽ ስትፈክሪ ሰለ ንፅህናችን የሚመሰክርልን ጀቤሳ ነው” ብሎ መለሰና ተሳሳቅን ። በቅርቡ ሶሎሜ ነፃ እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ሆና ስትቀርብ በሎተሪ መጣሏን ስሰማ ይህችን ምሽት አስታወስኩ ።
የዚህ ፎቶና መጣጥፍም መልእክት ይሄው ይመስለኛል ። ትናንት የት ነበርን፣ ዛሬ የት ነን? የሚል ። ፖለቲካ ውስጥ መፋታትና መለያየት ተፈጥሯዊ መሆኑን ። ሆኖም መቃቃርና ጠላትነት ቦታ ሊኖረው እንደማይገባ። መለያየትም እስከመጨረሻው መሆን እንደሌለበተ ። እኔና ታምራት ከድርጅታችን ከተለየን ያካበትነውን የእውቀት፣ የመንፈሳዊነት ሀይል ይዘን ብንመለስ ኢህአዴግን እንዴት አድርገን ከገባበት አረንቋ ልናወጣው እንደምንችል ሳስበው “ወይ አለመታደል” እላለሁ ። እኔ እንደዚህ በአግራሞት ብዋጥም፣ ዛሬ ጠዋት ባህርዳር የሚገኘው የሰማእታት ሃውልት አስጎብኚ፣ ግድግዳው ላይ ከተሰቀለው ፎቶዬ ሥር ቆማ “ይህ ደግሞ ጌታቸው ጀቤሳ ይባል የነበረው የአመራር አባላችን ነው ። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የግንቦት ሰበት መሥራች ሆኖ፣ ዴሞክራሲያችንን በመፈታተን ላይ ይገኛል” እንዳለች ጉብኝት ላይ ከሚገኝ የሥራ ባልደረባዬ የቫይበር መልእክት ደረሰኝ ። አይገርምም የሰው ነገር? የአስቴር አወቀን “ለሰው ሞት አነሰው ትላለች ቀበሮ” ን እያዳመጣችሁ እስቲ አላምጡት ይህን ነገር ።
ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ ገባች። ግብጽ የአሜሪካን “ጸረ-ሽብር” ዘመቻ በማገዝዋ ምስጋና ማግኘት ሲገባት በተቃራኒው ተወገዘች።   ከጥቂት ድብደባ በኋላ ፔንታጎን ግብጽን አስጠነቀቀ[0]።  የኦባማ አተዳደርም ደብደባው በአፋጣኝ እንዲቆም ቀጭን መልእክት ላከ። ይህ ድርጊት ከዚህ ቀደም ስለ አይሲስ አፈጣጠር ኤድዋርድ ስኖደን[1] የለቀቀው ምስጢራዊ መረጃ ጋር ተዳምሮ በአሜሪካ ላይ የነበረውን ጥርጣሬው አጠናከረው።

ነገሩን ለማመን ያዳግት ይሆናል። በግልጽ የሚታዩ መረጃ እና ማስረጃዎች ግን ተአማኒነታቸው ጥርጥር ውስጥ የሚገባ አይደለም። “በአይሲስ እየታረዱ ያሉት ዜጎች የፊልም ቅንበር እንጂ እውነት አይደለም![2]” የሚሉ ባለሞያዎችም የትንተናቸው መነሻ ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዛል።
ይህ አሸባሪ ድርጅት ስራውን ከጀመረ አንድ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከመቶ ሺ በላይ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለ ይናገራል። ቦምብ እንደዝናብ የሚወርድባቸው ሃገሮች፤ ሶማልያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ አፍጋኒስታን፣ፓኪስታን… ተደምረው አይሲስ ከሚነግረን ግድያ ሩብ ያህሉንም አላደረጉም።  የሃያላን ሃገሮች ምላሽ ግን በአፍ ከማውገዝ ያለፈ አለመሆኑ በአይሲስ አሰራር ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ይፈጥራል።
አይሲስ የእስራኤል፣ የኢንግሊዝ እና አሜሪካ የጋራ ፕሮጀክት መሆንን ያጋለጠውን፤ የኤድዋርድ ስኖደን መረጃ እንደገና እንድንመረምረው ይገፋናል። በአይሲስ ዙርያ የሚተነትኑ አንዳንድ ጸሃፊዎች እጃቸውን በአሜሪካ ላይ መቀሰር ከጀመሩ ሰነበትበት ብለዋል። አሸባሪ ሃይልን መፍጠር ለአሜሪካ የመጀመርያ አይደለም። አላማው ይለያይ እንጂ ኦሳማ ቢን ላደንም የአሜሪካ ስሪት መሆኑ በይፋ ተገልጿል። የአሜሪካ ቁጥር አንድ ጠላት የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በአሜሪካው የስለላ ተቋም፤ በሲ.አይ.ኤ እንደተፈጠረ በግልጽ ተቀምጧል። እ.ኤ.አ. በ1979 ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን በወረረች ግዜ ኦሳማ ቢን ላደን አማጺውን የሙጃህዲን  ሃይል በመቀላቀል ወደ አፍጋኒስታን አመራ። በወቅቱ አሜሪካ ሙጃህዲንን ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ ሶስት ቢሊየን ዶላር እንዳፈሰሰች የብሪታንያው ዜና አገልግሎት ቢ.ቢ.ሲ. ዘግቧል። እንደ ቢ.ቢ.ሲ. ዘገባ ሲ.አይ.ኤ. ለኦሳማ ቢን ላደን በግል ደረጃውን የጠበቀ የኢንተልጀንስ ስልጠናም አድርጎለታል። ቀዝቃዛው ጦርነት ሲያበቃ እና ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን ለቅቃ ስትወጣ ነው ቢን ላደን አሜሪካ ላይ የዞረው።
የዘመናችን ዘግናኝ የሽብር ድርጅት የሆነው አይሲስንም የፈጠረችው አሜሪካ ናት የሚሉ ጸሃፍት ጥቂት አይደሉም። የእነዚህ ተንታኞች መረጃ በከፊል የሚንተራሰው ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ሰነድ የጠለፈው ኤድዋርድ ስኖደንን ነው። የአሜሪካ ስለላ ድርጅት NSA ውስጥ ይሰራ የነበረው ይህ ሰው የአሜሪካን ብሄራዊ ምስጢሮች ካጋለጠ በኋላ ሩስያ ውስጥ ተደብቋል።  እርግጥ ነው። ኤድዋርድ ስኖደን የለቀቀው ሰነድ የአይሲስን አፈጣጠር ምስጢር በጥቁርና – ነጭ አስቀምጦታል። ሾልኮ የወጣው ይህ ሰነድ የአይሲሱ መሪ አቡባክር አል ባግዳዲ የአሜሪካ ደህንነት ግብአት እንደሆነ ይገልጻል። እንደ  ምስጢራዊው የኬብል መረጃ ከሆነ ለአይሲስ መመስረት ሃላፊነቱን የሚወስዱት እስራኤል፣ ታላቋ ብሪታንያ እና አሜሪካ ናቸው። “ምክንያቱም” ይላሉ ዶክመንቱን የሚተነትኑ አምደኞች፣”ምክንያቱም እስላማዊ ጦረኞች የሚሏቸው ሃይሎች ሁሉ ከአለም ዙርያ እየሄዱ ሶርያ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው።” ይህ ስትራቴጂ እውን ሲሆን፤ በአንድ በኩል በእነሱ የሚመራ ህይል ለማስቀመጥ እና በሌላ በኩል ደግሞ እስራኤል በቅርብ አደጋ ላይ መውደቋን ለማስመሰል የተወጠነ ታክቲክ ነው። መካከለኛው ምስራቅ ሽብር ያለ ማስመሰሉ አካባቢውን ዘልቆ ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል።  ይህን ለማድረግ አይሲስን እንደ ምክንያት ይጠቀሙበታል።”
የኤድዋርድ ስኖደን ምስጢራዊ መረጃ በጥሬው ተቀብለን፣ ስነዱን እንደማስረጃ ወስደን ለድምዳሜ መቸኮል የለብንም።  ጉዳዩ ትንሽ ከበድ ያለ ነውና ሌሎች ተጓዳኝ ነገሮችን መመርመርም ተገቢ ይሆናል።
የእስላማዊ ዲሞክራቲክ ጂሃድ ፓርቲ መስራች እና ቀደም ሲል ከፍተኛ የአልቃይዳ ኮማንደር የነበረው ናቢል ናኢም ለሜዲያ የተናገረው መረጃ የኤድዋርድ ስኖደንን ማስረጃ ያጠናክረዋል። ናቢል ናኢም ለቤይርቱ ፓን አረብ ቴሌቭዥን በሰጠው ቃል፤ “አይሲስን ጨምሮ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ደርጅቶች ሁሉ፤ በአሁን ሰዓት እየሰሩ ያሉት ለአሜሪካው የስለላ ተቋም ለሲ.አይ.ኤ. ነው።” ሲል በዚህ ወር መግቢያ ላይ ተናግሯል[3]።
ናቢል ናኢም በቴሌቭዥን የሰጠው አስደንጋጭ ምስጢር በዚህ አላበቃም፤ ሌላም ለማመን የሚከብድ ነገር አክሎበታል። አይሲስ በደንብ የሰለጠነ እና በደንብ የታጠቀ የሽብር ድርጅት ነው። መጠነ ስፊ የሆኑ የኢራቅን እና የሶርያን ክልሎች ተቆጣጥሯል።
የባህሬኑ “ዘ ገልፍ ዴይሊ ኒውስ” ጋዜጣም ባለፈው አመት አጋማሽ ላይ በዋና ገጹ  የአይ.ሲስ መሪ አቡ ባክር አል ባግዳዲን የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በጦር፣ በመንፈሳዊ ትምህርት እና በንግግር ክህሎት እንዳሰለጠነው ጽፏል[4]።
የዮርዳኖስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ “ወርልድ ኔት ዴይሊ” የተሰኘው ጋዜጣ የአሜሪካ ወታደሮች በዮርዳኖስ ግዛት ውስጥ የአይሲስ አባላትን እንዳሰለጠኑ ዘግቧል[5]።
እነዚህን መረጃዎች በአንድ ወገን እንያዛቸው እና ወደ ሌሎች ምልከታዎች ደግሞ እንሂድ። ታላላቅ የአሜሪካ ጋዜጠኞችም የአይሲስ መጠናከር እና የአለም ዝምታ እንቆቅልሽ ነው የሆነባቸው።  የፎክስ ኒውስ አምደኛ የሆነችው ግሬታ ቫን ሱስተረን እንግዳ የሆነባትን አስደንጋጭ የአይሲስ ግድያ እና የምእራባውያን ዝምታ እጅግ በመደነቅ ታነሳለች። አይሲስ በሺዎች የሚጠጉ ክርስቲያኖችን እያረደ፤  የተባበሩት መንግስታት፣ አሜሪካም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ጉዳዩን ከምንም አልቆጠረውም ብላለች። ጋዜጠኛ ግሬታ ንግግርዋን ቀጠለች። “ያለነው በሂትለር ዘመን አይደለም። ዘመኑ የመረጃ ነው። እልቂቱን የሚያሳዩ መረጃዎች በግልጽ ይታያሉ። አሰቃቂ መረጃዎችን እየተመለከተ አለም ግን ዝም ነው ያለው። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊጋባን በማይችል ምክንያት ጉዳዩን ችላ ብሎታል። …” ትላለች።
ሌላው ሉ ዶብስ የተባለ በአሜሪካ ታዋቂ የቴሌቭዥን አቅራቢና ጸሃፊ፤ ህዝብ እየታረደ አለም ግን በአይሲስ ላይ ችላ ማለቱ እንዳስገረመው ይናገራል።  ጋዜጠኛ ሉ ዶብስ ሜሪካዊውን ደራሲ ጆኒ ሞር በጉዳዩ ማብራርያ እንዲሰጥም አድሮታል።  ጆኒ ሞር “Defying ISIS”  “ውጉዝ መአሪዮስ አይሲስ” የሚል መጽሃፉ አይሲስን ከናዚዎች ጋር እያመሳሰለ ነው ያስቀመጠው።  ጆኒ ሞር በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርቦ የተናገረው ያስደምማል። “የ አይሲስ አራጆችን የጫኑ አርባ መኪናዎች በአንዲት የሶሪያ መንደር በነጻነት እየተዘዋወሩ 3000 ክርስቲያኖችን አፍሰው ወሰዱ። … ቦስንያ ላይ በቀን 140 ቦምብ ሲጥሉ የነበሩ የኔቶ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ በኢራቅ እና ሶርያ ላይ በቀን ከ 7 – 12 ቦምብ ሲጣል አይሲስ ግን ችላ ነው የተባለው።”
ጆን ዊልገር የተሰኘ የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ በአንድ ጥናታዊ ጽሁፉ፤ “አይሲስ የአሜሪካ ፍጡር ነው” ከማለት አልፎ፣  አይሲስን ከካምቦዲያው ካመሩዥ ጋር ያመሳስለዋል። በ 1969 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ኒክሰን ካምቦዲያን በቦንብ አስደብድበው ሲያበቁ አንባገነኑ ፖል ፖትን አበቀሉ። የፖልፖት ካመሩዥ ከአይሲስ ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። “ሁለቱም የአሜሪካ ውጤቶች፣ ሁለቱም የጨለማው ዘመን ጨካኞች ናቸው” ሲል ጽፏል።
ይህን ክስተት ስከታተል “ሲ. አይ. ኤ – ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” የተሰኘው መጽሃፍ ታወሰኝ።  ቪክቶር ማርቼቲ የተባለ የቀድሞ ሲ.አይ.ኤ አባል የጻፈው “ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” መጽሃፍ አሚሪካኖች ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የማያደርጉት ነገር እንደሌለ ይነግረናል። ሲ. አይ.ኤ. የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ሲያስከብር ለሞራል እሴቶች፣ ለሰዎች ስብዕና እና ለፍትህ ቦታ እንደማይሰጥ ደራሲው ቪክቶር ማርቼቲ ይነግረናል። መጽሃፉ በከፊል በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳንሱር ተደርጎ የወጣ ነው።  እንደዚህም ሆኖ ሲ.አይ.ኤ.  ከረቀቀ ቴክኖሎጂ እስከ ረቀቀ ወንጀል እንደሚሰራ ይተነትናል።  አሜሪካኖች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ዝናብ ማዘነብ ካለባቸው እንኳን፤ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ያንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መጽሃፉ ያሳየናል።
የአይሲስ አራጆች የሚናገሩት እንግሊዝኛ በአሜሪካ ቅላጼ (አክሰንት) ነው።  አሜሪካ ተወልደው ያደጉ ሽብርተኞች ሊሆኑ ይችላሉ ብለን እንውሰድ። አይሲስ የሚለቅቃቸውን የቪድዮ ምስሎች የሚጠራጠሩ ባለሙያዎች፤ ጉዳዩን ከፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ከሙያ አንጻርም ይመለከቱታል።  የጃፓን ዜጎች ሲታረዱ የሚያሳየውን ቪድዮ ፍሬም፣ በፍሬም እያሳዩ  የአይሲስ ግድያ ውሸት መሆኑን ለመግለጽ የሚሞክሩ የፊልም ባለሞያዎች የሚናገሩት ሙሉ በሙሉ ባያሳምንም  ተመልካቹን ማደናገሩ አልቀረም[6]። እየወጡ ያሉት የግድያ ፊልሞች በአረንጓዴ ጨርቅ green screen  በስቱዲዮ ውስጥ የሚሰሩ የትራይካስተር ቴክኒኮች ናቸው ብለው ነው እርግጠኝነት የሚናገሩት።  ግሎባል ሪሰርች የተባለ አንድ የካናዳ የምርምር ተቋም፤ ISIS Video ‘Execution’ of Ethiopians in Libya Appears Fake [2] ሲል በሊቢያ የተሰዉት የኢትዮጵያ ሰማእታት ጉዳይ፤ የቪድዮ ቅንብር እንጂ እውነት አይደለም ሲል የምስሉን ፍሬም እየከፋፈለ በስሎው ሞሽን አቅርቦታል። ትንተናው አሳማኝ ላይሆን ይችላል። አይቶ መፍረዱ ግን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ምኞታቸውም ከሆነ ይህ  እውነት ይሆን ዘንድ ጸሎታችን ነው።
ያልተፈታ እንቆቅልሽ!
ለመሆኑ እስራኤል፣ የኢንግሊዝ እና አሜሪካ በጋራ ሆነው የአይሲስን ፕሮጀክት ለምን ፈጠሩ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ካገነ እንቆቅልሹን ይፈታው ይሆናል።  ተንታኞች እና ተቺዎች ለዚህ በርካታ ምክንያቶችን ይደረድራሉ። አንደኛው ምክንያት እስራኤል በመሃከለኛው ምስራቅ ውስጥ ሁከት በመፍጠር የሁከቱ ተጠቃሚ ለመሆን እንድትችል ነው ይላሉ። ይህ ከሆነ እስራኤል በክልሉ ሃያልነቷን ሙሉ ለሙሉ ለማስከበር ይረዳታል ይላሉ። አይሁዶች ክርስትና እና እስልምና ጠላት ባይሆኑም በሁለቱም እምነቶች ላይ ችግር አለባቸው።  ይሁንና አላማቸው የአይሁድን እምነት ለማስፋፋት ሳይሆን የእስራኤልን በሄራዊ ጥቅም ማስጠበቁ  ላይ ነው። የእስራኤል አላማ የሁለቱ ሃይማኖት ተከታዮችን እርስ-በእርስ ማፋጀትና ማዳከም ነው ብለው የሚጽፉም አሉ። በእርግጥ አረቦች በሙሉ ጸረ-አይሁድ ናቸው። አረቦች በሙሉ ደግሞ ሙስሊሞች አይደሉም። እንደፍልስጤም፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፤ ሊባኖስ እና ሶርያ ባሉ አረብ አገሮች ክርስቲያኖችም አሉ።
አሜሪካ እና እንግሊዝም ከዚህ ሽብር ጀርባ የሃገራቸውን ብሄራዊ ጥቅም ያስከብራሉ። አለምን በአሜሪካ አምሳል መፍጠር ከሚለው የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲን በሌላው ከመጫን  ባሻገር ከመካከለኛው ምስራቅ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያገኙት ጥቅምም ቀላል የሚባል አይደለም። አንደኛው “ሽብርን መዋጋት” በሚል ምክንያት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በመሳርያ ሽያች በአመት ከአራት ትሪልዮን ዶላር በላይ ገቢ ያገኙበታል። መካከለኛው ምስራቅ ሃገር ያሉ ዋና ዋና የነዳጅ ክምችቶችን ለመቆጣጠርም የእነሱ የሆነን ሃይል በሽብር ሰበብ በስፍራው ማስቀመጥ ግድ ነው።
አሜሪካ ለሃገሯ ብሄራዊ ጥቅም ስትል በሌሎች ላይ ቁማር መጫወት አይገዳትም። በዚያን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት አሜሪካኖች ከምስራቁ ጎራ ጋር የቃላት ጦርነት ነበር ያካሂዱ የነበረው። ያ ወቅት ለእኛ ግን ቀዝቃዛ አልነበረም። ለሁለቱ ሃያላን ሃገሮች የጦር ቀጠና ነበርን። አይሲስ የአሜሪካ ፍጡር ይሁንም አይሁን ገፈቱን የምንቀምሰው እኛው ሆነናል። በሰማዕታቱ እልቂት ምክንያት ከገባንበት ብሄራዊ ሃዘን ገና አልተላቀቅንም። ሁኔታው ሰቅጣጭ፣ ድርጊቱ ቅስም ሰባሪ ነውና የሃዘኑ ሸክም በቀላሉ የሚወርድ አይመስልም። ከዚህ ሁሉ ሃዘን በኋላም በአልጃዚራ ቴሌቭዥን ላይ የቀረቡ ወጣቶች ከአገር ቤቱ ኑሮ ወደውጭ መውጣቱን እንደሚመርጡ ተናግረዋል።  አሁን ያለውን መረጃ ብቻ ይዞ አይሲስን የፈጠረችው አሜሪካ ናት ብሎ መደምደም ባይቻልም፤ ጥቅሟን ካስጠበቀላት ይህንን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ያለፉ ተመክሮዎች ይጠቁሙናል።  የሌላው ማለቅ፣ መረበሽና መተራመስ ለአሜሪካ ደንታ አይሰጣትም።
[0]http://www.americanthinker.com/blog/2015/02/obama_administration_egypt_bad_iran_good_israel.html
[1]http://www.hangthebankers.com/?s=snowden
[3]http://www.infowars.com/former-al-qaeda-commander-isis-works-for-the-cia
[4]http://www.gulf-daily-news.com/NewsDetails.aspx?storyid=381153
[5]http://www.infowars.com/blowback-u-s-trained-isis-at-secret-jordan-base/
[6]https://www.youtube.com/watch?v=QrdDavSw_Fg
ኑርሁሴን እንድሪስ:-
በሁለቱ ታላላቅ እምነቶች ውስጥ (ክርስትና እና እስልምናን ማለቴ ነው) ለሰው ዘር በሙሉ የተላለፈ አንድ መለኮታዊ መልዕክት አለ፡፡ ይህ መልዕክት በሁለት ቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ ቢገኝም መልዕክቱ ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ የሰው ልጅን ነፍስ ማጥፋት የተወገዘ ተግባር መሆኑን መጽሐፍ
ቅዱስ እና ቁርአን ያወሳሉ፡፡ ይህን መልዕክት ለሰው ልጆች የላከው ደግሞ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እንዲሁም የሰው ልጆችን ጨምሮ በሁለቱ መካከል ያሉትን በሙሉ ያስገኘው አምላክ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ምዕራፎቹ ውስጥ የሰው ልጅ ግድያን ይከለክላል፡፡ በማቲዎስ 5፡21፣ ምፅአት 20፡13፣ ሮሜ 13፡14፣ ዘፍጥረት 9፡5-6 … ወዘተ፤ በጣም ብዙ አንቀፆች ሰውን መግደል የማይፈቀድ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በማቲዎስ 5፡21 ውስጥ የሰፈረው ቃል እንዲህ ይላል፡-
ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ
ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ
ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላላን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞትን ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡

ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡
ስለራሴ ላውራ፤ ከእኔ የሚፈልጉት ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፤ የሚፈልጉት የምኖርበትን አፓርትመንት እንደሆነም አላውቅም፤ በእኔ ቤት ያለ ሀብት የሚባል ለወያኔ አገልጋዮች የሚጠቅም ሁለት የገብረ ክርስቶስ ስዕሎች ብቻ ናቸው፤ (በዚህ አጋጣሚ እነዚህን ስዕሎች ለመግዛት የሚፈልግ ያነጋግረኝ)፤ ከዚህ ሌላ ለወያኔ ዋጋ የሌላቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ስለዚህም አሁን በእኔ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እኔን ወደስደት ለመግፋት የሚደረግ ሙከራ ይሆናል፤ በ1992 ግድም ተሞክሮ ነበር፤ አልሠራም፤ ዛሬ ይበልጥ አይሠራም፤ ለማናቸውም ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ባልችልም በእኔ ላይ ዘመቻ መጀመሩን አንድ በቅርብ ከማውቀው ወያኔ በትክክል ተረድቻለሁ፤ ይህንን ዘመቻ በመምራት ላይ ያለውንም ሰው ማንነት ተነግሮኛል፡፡
ይህ አገር የአንድ ጉልበተኛ ቡድን ነው ብዬ አልቀበልም፤ የአባቶቼና የእናቶቼ፣ የኤቶቼና የቅድማያቶቼ አጥንትና ደም የገነባው አገር ነው፤ ማንም ለስደት አይዳርገኝም፤ ማንም አስፈራርቶ ኢትዮጵያዊነት መብቴን መግፈፍ አይችልም፤ አልፈቅድለትም፤ በግልጽ በማያጠራጥር ቋንቋ ኑሮዬም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም እዚሁ ነው፤ ከኢትዮጵያ አፈር የሚለየኝ የለም፡፡
እኔን ለማጥቃት ላሰፈሰፉት ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው አንድ እውነት ልንገራቸው፤– በፈለጉትና በተመቻቸው መንገድ በእኔ ላይ በጉልበታቸው ግፍ ቢፈጽሙ ነገ በነሱ ላይ የባሰ ግፍ እንደሚደርስባቸው ይወቁት፤ ሁልጊዜም ከሕግ የወጣ ጉልበተኛነት ጉልበተኛነትን ያነግሣል፤ በመግደል ድል ይገኛል ብለው የሚያምኑ ወያኔዎች ትንሽ ቆም ብለው ያስቡ፤ በመሞትም ድል ይገኛል፤ በመሞትም ማሸነፍ ይቻላል፡፡
በእኔ ላይ የዘመተው ወያኔ ወይም ሎሌ ማናቸውም ሥራ ውጤት እንዳለው ማወቅ አለበት፤ አንድ ነገር አድርጎ ምንም ዓይነት ውጤት አያስከትልም ብሎ ማሰብ ድንቁርና ነው፤ ይህ የሳይንስ ሕግ ነው፤ For every action there is a reaction ይላል!
አሰግድ ታመነ

ህወሃት መሪ ያጣ ድርጅት ነው። እኔ ለህወሃቶች የምመኝላቸው፣ እውነተኛ እራእይ ያለው መሪ እንዲያገኙ ነው።
ለነገ ሳይስቡ ዛሬ ሆድን በኪሳራ ከሞምላት፣ እራስን ከማወደስ፣ ሌሎችን ከማኮሰስ፣ አፈናቅሎ ከመውረስ፣ አምታቶ ከመዝረፍ፣ በሃሰት ከመክሰስ፣ ህዝብን ፈርቶ ከመኖር፣ በደካማ ዜጎች ስቃይ ከመደሰት፣ በዘርና በጎጥ ከመከፋፈል፣ በባዶው ከመጎረር፣ የሃሰት ክብርና ዲግሪ ከጥቁር ገበያ በርካሹ ከመሰብሰብ፣ ጥራት የሌላቸው የሰው አሻንጉሊቶች ከመሰብሰብ የሚያድን መሪ ያስፈልጋቸዋል።
ህወሃቶች ቆራጥ መሪ ሲያገኙ የትናንቱ ስህተታቸው ሁሉ ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል። የበደሉትን ሁሉ ይቅርታ ይለምናሉ። አገር ማለት ሁሉም ያልአድርኦ በዜግነቱ ተከብሮ ከማንም ሳይበልጥ ከማንም ሳያንስ ሊኖርበት የሚገባው ምድር መሆኑ ይገለጥላቸዋል። ህወሃቶች መሪ ሲያገኙ ወደ ገደል ቁልቁል ከማብረር ይድናሉ። ፍሬን ይይዛሉ! ቆም ብለው ያስባሉ…
“ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! በነጻነት ስም፣ ለችግር፣ ለመከራ፣ ለስደት፣ ለእስራት፣ ለግድያ፣ ለግፍ፣ ለዝርፊያ፣ ለአድልኦ፣ ለስርአት አልባነት፣ ተዘርዝሮ ለማያልቅ በደልና ግፍ ዳርገንሃል። ለሁላችንም የሚሆን አዲስ ምዕራፍ መክፈት ግድ ሆኖብናል። ይቅርታህን እንለምናለን!” የሚል ደፋር መሪ ያሳፈልጋቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁል ግዜም ይቅር ባይ ነው።
መንደር መሃል እንደነጋበት ጅብ መሄጃ ከማጣቱ በፊት ህወሃት ደፋር መሪ እንዲኖረው እመኝለታለሁ። የእነ መለስን ስህተት ከሚደግም መሪ ይልቅ እወነተኛ ራእይ ያለው ቆራጥ መሪ ያስፈልገዋል። አርቆ አሳቢ፣ ከአድልኦ እና ጠባብነት የጸዳ ከዛሬ ከንቱነት ይልቅ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የሚያስብ መሪ..

የዘንድሮ ምርጫ ኣሸንፎ ለመውጣት የህወሓት መንግስት ኣርባው ሲያስወጣ “…ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሬ ድጋፍ ኣገኛለው…” ብሎ ኣስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ በመውለድ ያሁሉ ጥረቱ መና ሁኖ መቅረቱ ህወሓት ተረድተዋል። ድሮም በወከባ የሚገኝ ህዝባዊ ድጋፍ እንደሌለ የሚታወቅ ነው።

ህወሓት ጥረቱ ከንቱ ሲቀር የዘየደው መላ በትግራይና የሚያዋስኑት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኤርትራ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የምርጫው ኣቅጣጫ ለማስቀየስ እየሞከረ ነው። የዚህ ማሳያ “..የኢትዮዽያ ኣየር ሃይል የወርቅ መዓድንና የትጥቅ መጋዘን ደብድበው ጉዳት ኣድርሰዋል..” የሚል በፌስቡክ ካድሬዎቹና በድህንነት ኣካላት በሰፊ እንዲወራ ኣድርገዋል።
የዚህ ምላሽ ተብሎ የተገለፀው ደግሞ “..ሻእብያ ሶሎዳ ተራራን(ኣድዋ ከተማ ኣጠገብ የሚገኝ) በሚሳይል እንደደበደበ..” እነ ዳኒኤል ብርሃነ ኣበሰሩን። ምድረ ካድሬም “..ኣሸው..” እያሉ ለኣየር ሃይላችን ኣንቆለዻዸሱት።
ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለይም ስለ የኣየር ጥቃቱ ሲጠየቁ “..ተደበደብኩ የሚል ኣካል ሲኖር መልስ እንሰጣለን…” የሚል ኣመላካች የእምነት ቃል ገለፁ።
ከብዙ ዓመታት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ የኢሳይያስ አፈወርቂና የድርጅቱ አቀንቃኝ ነበረ፤ ዛሬ ከሌሎች ብዙዎች ጋር በመቃብር ውስጥ ያለው የመጀመሪያው የሪፖርተር መጽሔት በሙሉ ውዳሴ ኢሳይያስ አፈወርቂ ነበር፤ የሞተው መለስ ዜናዊ እያለ የሪፖርተር መጽሔት ኢሳይያስን
በመጀመሪያ እትሙ ሲያወድስ ነበር፤ በቅርቡ ደግሞ ደፋሩ የወያኔ አባት ስብሐት ነጋ ለኤርትራ ያለውን ልዩ ፍቅር በሚያስገርም ሁኔታ ገልጾ ነበር፤ ለኤርትራ ቆመን እንዋጋለን አስከማለት ደርሶ ነበር፤ መለስ ዜናዊ በልዩ ጥበቡ መጀመሪያ ኤርትራን ባዕድ አደረገ፤ ቀጥሎም ጠላት አደረገ፤ ክፉ ጦርነት ተደረገ፤ በጦርነቱ ያሸነፈ የለም፤ በፍርድ ግን ኤርትራ አሸነፈች ተባለ፤ ፍርዱ ዋጋ-ቢስ ቦሆንም!
ዛሬ ደግሜ ሪፖርተር ሌላ ስብከት ይዞ መጥቶአል፤ በመጀመሪያ ሪፖርተር ጋዜጣ ለኢትዮጵያዊነት ያለውን ወይም የሌለውን ስሜት ከየት አመጣው? ብዬ እንድጠይቅ እገደዳለሁ፤ አንዱ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝብሀል መንነት የለን፤›› ብሎ በአጽንኦት ጽፎ ነበር፤ ዛሬ በሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ ላይ ያነበብሁት ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት እንዳለ ነው! ለመግቢያ ያህል ይበቃኛል፡፡
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡
ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
‹‹እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም›› አብርሃ ደስታ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)
“እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡
ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡
እኔ እስር ቤት እንድገኝ ያደረገኝ ወንጀል አይደለም፡፡ መቃወሜና ይህን ተቃውሞየን በጽፍም በፊት ለፊትም መግለጼ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ብዙ ኢትዮጵያውያን ያውቁልኛል፡፡ ሌላው ቢቀር ጥቂት የህወሓት ሰዎችም ያለ መረጃ እንደታሰርኩኝ በማመን እስሩን እየተቃወሙ ይመስለኛል፡፡ አንድ ቀን ወደ ህሊናቸው ከተመለሱ ስህተታቸው በህዝብ ፊት ያዋርዳቸዋል፡፡”
በእስር ላይ ያለው የተደናቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁለተኛውንና ‹የኢትዮጵያ መንግስት ገበና› የተሰኘው ጦማር ከዝዋይ እስር ቤት ወጥቷል፡፡ ተመስገን አብረውት የታሰሩ የፖለቲከኛ እስረኞች በሚታወቅበት የጋዜጠኝነት ችሎታው እየጠየቀና እያውጣጣ መፈጠራቸው የሚያስምሙ ታሪኮችን ለመልቀም እንደቻለ ጽሁፉን ያነበበ ይረዳዋል፡፡
ክፍል 2
ተመስገን ደሳለኝ
በዚህ አውድ ለማቅረብ የተገደድኩበትን ዘግናኝ ታሪክ፣ ወደር በሌለው አስከፊነቱ የተነሳ ለንባብ ባላበቃው በወደድኩ ነበር፡፡ ግና! ይህ መንግስታዊ የጭካኔ ተግባር፣ ዛሬም በምስኪን ዜጎች ላይ እየተፈፀመና ብዙዎችን ሰለባ እያደረገ በመሆኑ ህዝቡ ይህን ሊሸሸግ እየተሞከረ ያለውን መከራ ተረድቶ ሥርዓቱን በአደባባይ ዓመፅ “ሃይ!” ይል ዘንድ ትርክቴን ለማጠናቀር ተገድጄያለሁ፡፡ ለእስር ያበቃኝ የጋዜጠኝነት ሙያዬም ተጨማሪ ዕዳ ጭኖብኛል፡፡


“ጄል-ኦጋዴን”
ጄል ኦጋዴን በሱማሌ ክልል ርዕሰ-መዲና የሚገኝ፤ ለ800 እስረኞች ታቅዶ በ1992 ዓ.ም የተገነባ እስር ቤት ነው፡፡ የግቢውን ዙሪያ ከከበበው አጥር በግምት 15 ሜትር ፈንጠር ብሎ ሌላ ተደራቢ የድንጋይ አጥር ተበጅቶለታል፡፡ እስከ ሚያዝያ 24 1999 ዓ.ም ድረስ እስር ቤቱ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ካሉ መሰል ማጎሪያዎች ብዙም የተለየ አልነበረም፡፡ በዚህ በተጠቀሰው ቀን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ታጣቂዎች፣ አቦሌ እና ሰንደሬ ወታደራዊ ካምፖችን ጨምሮ፣ በነዳጅ ዘይት ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ቻይናውያን ባለሙያዎች መኖሪያ ሰፈር ላይ የሰነዘሩትን ከባድ ጥቃት ተከትሎ የፖለቲካ እስረኞች ብቻ የሚታጎሩበት እስር ቤት ከሆነ ወዲህ ግን በዋይታ የሚናወፅና በደም ጅረት የሚጥለቀለቅ ምድራዊ ሲኦል ለመሆን በቅቷል፡፡ መንግስት በጥቃቱ ከዘጠኙ ቻይናውያን ጋር 74 ሲቪል ዜጎችና ወታደሮች መገደላቸውን ቢያምንም፤ የአካባቢው የአይን እማኞች ከሰራዊቱ ብቻ እስከ 300 እንደተሰዉ ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኦብነግ እንደ አል-ቃይዳ እና አል-ሸባብ የአባላቱን አስከሬን ትቶ የመሸሽ ልምድ ስለሌለው በቡድኑ ላይ የደረሰውን ጉዳት በትክክል ለማወቅ አዳጋች እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
የሆነው ሆኖ ከዚህ ጥቃት በኋላ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የሚመራ አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ የደህንነትና (ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ጌታቸው አሰፋ ያሉበት) የፀጥታ ኮሚቴ ተቋቁሞ የሚከተሉትን (ዛሬም ድረስ እየተተገበሩ ያሉ) አስቸኳይ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ ‹‹ከጅጅጋ ውጭ ባሉ በክልሉ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ፣ ትዕዛዙን ጥሶ የተገኘ ከነጭነቱም ሆነ ተሳፋሪዎቹ በከባድ መሳሪያ እንዲመታ፤ አብዛኛውን ህዝብ በፍጥነት ከመኖሪያ ቀዬው በማፈናቀል ለቁጥጥር ወደሚያመቹ ከተሞች ማስፈር (በ2006 ዓ.ም መጀመሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ካሳ ተክለብርሃን 2300 መንደሮችን ወደ ተመረጠ ቦታ ማስፈሩ እንደተሳካ መናገሩን ልብ ይሏል)፤ ወታደራዊ መኪና ላይ ምንም አይነት የደፈጣ ጥቃት ከደረሰ በአቅራቢያው የሚገኝ መንደርን ያለርህራሄ ማውደም (ለማሳያ ያህልም ፍልቼ፣ ቃሙዳ፣ ሳስባኒ፣ ሁለሌ፣ ለንካይርተ፣ ቻለሌን… የመሳሰሉ ከተሞች ወደ ፍርስራሽነት መቀየራቸውን መጥቀስ ይቻላል) እና ከአንድ ሻምበል ያነሰ ኃይል ለአስቸኳይ ጉዳይም ቢሆን ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ›› የሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዚህ በኋላም ኤታማዦር ሹሙ ጄነራል ሳሞራ የኑስ በክልሉ የሚገኘውን የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ወታደራዊ አዛዦችን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሰብስቦ ማብራሪያ ሰጥቶ ሲያበቃ ውሳኔውን ያለምንም ማቅማማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት በጥብቅ አሳስቧል፡፡
ደቡብ ምስራቅ ዕዝ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት (ከ1993 ዓ.ም) በኋላ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሰፈረ ሲሆን እስከ ታህሳስ 1999 ዓ.ም ድረስ በሜ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ሲመራ ቆይቷል፡፡ ከታህሳስ 1999 እስከ 2000 ዓ.ም ደግሞ ብርጋዴር ጄነራል ስዩም አስተዳድሮታል፤ በዚሁ ዓመት ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ ድረስ ባሉት ጊዜያትም በብ/ጄነራል ሙሉጌታ በርሄ ስር የቆየ ሲሆን፤ ከሚያዚያ 2000 ዓ.ም አንስቶ አሁን ድረስ እየተመራ የሚገኘው በሌ/ጄነራል አብርሃም ወ/ማርያም (ቅፅል ስሙ ‹‹ኳርተር››) እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከዚህ ዕዝ ውስጥ በዋናነት ሶስት ክፍለ ጦሮች (12ኛ፣ 13ኛ እና 32ኛ) ክልሉን ሶማሊያ ድንበር ድረስ እንዲቆጣጠሩት ተመድበዋል፡፡ ሰፈራቸውን ነገሌ ቦረና ያደረጉት 43ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦሮችም፣ ኦጋዴን ድረስ እንዲንቀሳቀሱ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በአናቱም የአግአዚ ኃይል በቀድሞ ምክትል አዛዡ ብ/ጄኔራል ገ/መድህን ፈቀደ (‹‹ወዲ ነጮ››) ስር ሆኖ አልፎ አልፎ በተደራቢነት እየተላከ በነዋሪዎቹ ላይ በደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ እና ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፈ ስለመሆኑ ከወታደራዊ መረጃ ምንጮቼ ሰምቻለሁ፡፡ ይህም ሆኖ ለደረሱ እልቂቶችና ጭፍለቃዎች በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂ ተደርገው የሚጠቀሱት ከጄነራል ሳሞራ፣ ከጀኔራል ‹‹ኳርተር›› እና ከክልሉ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ በብ/ጄነራል በየነ ገ/እግዚአብሔር (‹‹ወዲ አንጥር››) የተመራው 12ኛ ክ/ጦር እና በብ/ጄነራል ፀጋዬ ገ/ጨርቆስ (‹‹ጀብጀብ››) ዕዝ ስር የነበረው 13ኛ ክ/ጦር እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኦብነግ በስፋት ይንቀሳቀስባቸዋል ተብለው የሚታሰቡት፡- ደገሃቡር፣ ቀብሪደሃር፣ ዋርደር፣ ጎዴ እና ቪቅ ከተሞች መደበኛ የጦር ቀጠናዎች ከሆኑ 15 አመት ያለፋቸው በመሆኑ፣ ከሌሎች የክልሉ አውራጃዎች በተለየ ሁኔታ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም የሚፈፅማቸውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ለመሸፈን እንደ ቀይ መስቀል፣ ዓለም-አቀፍ ሚዲያዎች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና መሰል ተቋማት ከጅጅጋ ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ በኃይል አግዷል፡፡ ይህ ኩነትም በ ዙ-23 እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ተደብድበው ከምድረ-ገፅ የጠፉ መንደር ነዋሪዎች፣ የቤት እንስሳት እና ቁሳዊ ንብረቶች በአንድነት ተቃጥለው መውደማቸውን ዛሬም ድረስ በምስጢርነት ሸሽጎ ለማቆየት አስችሎታል፡፡
የሆነው ሆኖ የመከላከያ ሰራዊቱ እና በክልሉ ከ70-80 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ላይ መንቀሳቀስ የቻለው ኦብነግ፣ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ከባድ ውጊያ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ በእርግጥ ግጭቱ አሁንም ሳያበራ የመቀጠሉ ምክንያት አማፂው ቡድን ያን ያህል ከመንግሥት አቅም በላይ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የጄነራሎቹ እጅ በዘወርዋራ ስላለበት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮቼ ያስረግጣሉ፡፡ ‹‹የኦብነግ ህልውና በተለይም ለከፍተኛ መኮንኖች ዋነኛ ንግድ (ቢዝነስ) ነው›› ይላሉ፡፡ የክልሉ መንግስት ‹‹የመረጃ እና ፀጥታ ባጀት›› በሚል ሽፋን በዓመት የሚመድበውን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ሀብት እንዲያወራርዱ አዛዦቹ አይገደዱም፡፡ መከላከያ ራሱም ‹‹የመረጃ እና የበረሃ ፍሳሽ›› በሚል የሚበጅተው አመታዊ ወጪ በብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚቆጠር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ በጀት እስከ ኃይል አመራሮች ድረስ ወርዶ እንደየድርሻቸው መጠን የሚመዘበርበት አሰራርም ተዘርግቶለታል፡፡ እናም ጀነራሎቹ ኦብነግ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ የገቢ ምንጫቸው እንዳይደርቅም ሆነ፤ ከአቅም በላይ ተጠናክሮ በብቃት ማነስ እንዳያሳጣቸው (እንዳያስወቅሳቸው) ተቆጣጥረው ለመዝለቅ የቻሉበትን ቀመር እንዲከተሉ ይህ የገቢ ምንጭነት ገፊ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከመከላከያ ሠራዊቱ እና ከፌዴራል ፖሊስ በተጨማሪ በቀጥታ የክልሉ አስተዳደር የሚያዝዘውና ‹‹ልዩ ኃይል›› ተብሎ የተቋቋመው ታጣቂ ቡድን ዛሬም ድረስ የሎጅስቲክ አቅርቦቱን ያለጨረታ ጠቅላላ የያዘችው የሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ (በአሁኑ ወቅት ጀነራል አበባውን ተክቶ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ነው) ባለቤት ሃዋ መሆኗ በራሱ የሚነግረን ነገር አለ፡፡ (በነገራችን ላይ ክልሉን የሚያስተዳድሩት በህዝብ የተመረጡት ሳይሆኑ ‹‹የፀጥታ አማካሪ›› በሚል በየወረዳው የተመደቡ የሻለቃ ወይም የሻምበል አዛዦች ከጀርባ ሆነው ነው፡፡ ለነርሱ ያልተመቸ ኃላፊን በሌላ እስከመቀየር ድረስ የሚንጠራራ ስልጣን አላቸው፡፡ የፕሬዚዳንት አብዲና እና የጄነራል ‹‹ኳርተር››ን የ‹‹ሥራ ግንኙነት›› መመልከቱ ጉዳዩን ፍንትው አድርጎ ለመረዳት ያስችላል፡፡ በርግጥም አስራ ሦስት ፕሬዚዳንቶች የተፈራረቁበት ክልል ዛሬ እንዲህ በጨካኙ አብዲ መርጋት መቻሉ እንቆቅልሽ ሊሆን አይችልም)፡፡
‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ከደረቅ ወንጀለኞች ማረሚያነት፣ በኦብነግ አባልነት የሚጠረጠሩ ንፁሃንን ወደማሰቃያ እስር ቤት እንዲቀየር የተደረገበት መግፍኤ ከላይ የጠቀስኩትን (የ1999 ዓ.ም የኃይል ጥቃትን) ተከትሎ ሟቹ አምባ-ገነን ጠ/ሚኒስቴር በደህንነት ኮሚቴው ስም የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡ መቼም ዕድል ፊቷን አዙራበት ወደዚህ ግቢ የተላከ ምስኪን፣ በቀን አንድ መናኛ እንጀራ እየተወረወረለት፣ በ‹‹ምርመራ›› ስም የተወለደበትን ቀን ከመርገም አልፎ ዘላለማዊ ዕረፍት የሚያጎናፅፈው መልአከ-ሞት ቶሎ መጥቶ እንዲገላግለው እስከመናፈቅ ለሚያደርስ ስቀየት (ቶርቸር) ይዳረጋል፡፡ እስር ቤቱ የተገነባው 800 ታሳሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ ቢሆንም፣ ወደምድራዊ ገሃነም ከተቀየረ ወዲህ ግን ከ5000 በላይ ሰዎች የሚታጎሩበት የሰቆቃ ግቢ ሆኗል፡፡ ሁሉም ታሳሪዎች ከጠዋት 2፡30 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ አንድ ቦታ ተሰብስበው ክብርን፣ ሞራልን እና ሰብዕናን የሚያጎድፍ ግፍ ይፈፀምባቸዋል፡፡ በተለይም ሴት እስረኞች በየተራ እንዲቆሙ ይደረግና ወንዱ አንድ በአንድ እየተነሳ ሴተኛ አዳሪ መሆኗን፣ እሱ እና ጓደኞቹ ከእርስዋ ጋር ግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀማቸውን፣ ወዘተ እንዲናገር ይገደዳል፡፡ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ሆኖ ካልተገኘም በጨካኝ ታጣቂዎቹ ፍዳውን ይበላል፡፡ ሁኔታውን መራር የሚያደርገው ደግሞ ‹‹ስብሰባው›› ሲጠናቀቅ፣ ሰብሳቢው እስረኞቹ ወደየክፍላቸው እንዲገቡ ትዕዛዝ የማይሰጥ መሆኑ ነው፤ ይልቁንም ወፋፍራም ዱላ ጨብጠው ዙሪያውን ለከበቡት ፖሊሶች በአይኑ ምልክት ያስተላልፋል፤ ይሄኔ በያዙት ቆመጥ ከአቅራቢያቸው ያገኙትን ሁሉ መቀጠቀጥ ይጀምራሉ፤ እስረኛውም ከዱላው ውርጅብኙ ለማምለጥ ባገኘው አቅጣጫ ይተራመሳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት በየቀኑ የተለመደ በመሆኑ የዕለቱ ፕሮግራም ሊገባደድ በተቃረበ ቁጥር፣ ሁሉም ለመሸሽ ዝግጁ ሆኖ ይጠባበቃል፤ ከድብደባው ማምለጡ ግን ብዙም የሚሳካ አይሆንም፡፡
በ‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ሴት እስረኞችን አስገድዶ መድፈር፣ ሙዝ ልጦ እንደመብላት ቀላል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በዚህም በርካቶች በየጊዜው ለውርጃ ወደሆስፒታል ሲላኩ ይስተዋላል፡፡ አልፎ አልፎ እዚያው ለመውለድ የሚገደዱ እህቶችም አሉ፡፡ አብዛኞቹ ሴት እስረኞች ፀጉራቸውን ከማሳደግ ይልቅ መላጨትን ይመርጣሉ፤ ምክንያቱ ደግሞ የሚፈፀምባቸው ስቅየት የበሰበሱ ቆሻሻዎችንና ፈሳሽ-ሰገራዎችን ፀጉራቸው ላይ መደፋትን ስለሚያካትት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እዚህ ቦታ ሴቶች አንድ ላይ እንዲሰበሰቡ እና ልብሶቻቸውን እንዲያወልቁ ከተደረገ በኋላ እርቃናቸውን የሚገረፉበት ጊዜም እንዳለ ከአይን እማኞች ሰምቻለሁ፡፡ ከሁሉ የከፋው ደግሞ ንፅህናን ካለመጠበቅና በምግብ እጥረት የሚነዛው ወረርሽኝ ነው፡፡ በ2004ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ በሽታው ተከስቶ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ 700 ያህል ሰዎች በሞት መቀጠፋቸው ይነገራል፡፡ በወቅቱ አስከሬን ቶሎ ስለማይነሳ እስረኞቹ ከአስከሬኑ ጋር እስከ 3 ቀን ድረስ ጋር ለመቆየት ይገደዱ ነበር፡፡
በ‹‹ጄል-ኦጋዴን›› ግቢ ከሚገኙ ማጎሪያዎች መካከል 3ኛ፣ 4ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ‹‹የቅጣት ቤት›› ሲሆኑ፤ አሰራራቸውም ሶስት በሶስት ሜትር የሆነ እጅግ በጣም ጠባብ፤ ውስጣቸውም ሃምሳ ሳንቲ-ሜትር ጥልቀት ባለው ውሃ የተሞላ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክፍልም የግድ ከ25 እና ከዚያ በላይ እስረኞች እንዲይዝ ስለሚደረግ ለቅጣት ወደግቢው የተላከ እስረኛ ለሳምንት ያህል እንቅልፍ በዓይኑ ሳይዞር ለመሰንበት ይገደዳል፡፡ በአናቱም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደዚህ ግቢ እየተላኩ ስቅየትም ሆነ ግድያ እንደሚፈፀምባቸው ሰምቻለሁ፡፡ በግቢው ለአራት ወራት ገደማ ያሳለፈው ሀሰን፣ በውል በማያስታውሰው በአንድ የተረገመ ቀን 3 ወታደሮች ሲረሸኑ ማየቱንና ከመካከላቸው አንዱም ‹‹እባካችሁ አትግደሉኝ! የ3 ልጆች አባት ነኝ!›› እያለ ሲማፀን መስማቱን ያስታውሳል፡፡ እስረኞቹ ላይ የጭካኔ ተግባር የሚፈፅሙት ደግሞ ከዚህ ቀደም ‹‹አል-ኢትሀድ አል-ኢስላሚያ›› በሚል ስም ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ፤ በኦብነግ ተሸንፎ ከኦጋዴን የተባረረው አማፂ ቡድን አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መንግስት ምህረት አድርጎላቸው ወደ ሰላማዊ ህይወት ከተመለሱ በኋላ የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዛኛውን አሰባስቦ ‹‹ልዩ ኃይል›› ብሎ አደራጅቷቸው ሲያበቃ፤ ከኦብነግ ጋር ተያይዞ የሚጠረጠሩ እስረኞች ላይ ያሻቸውን እንዲፈፅሙ ባልተፃፈ ሕግ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም የቀድሞ ሽንፈታቸውን ለመበቀል እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ዛሬ በክልሉ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ የእስር ቤት ግቢዎች ውስጥ የጅምላ መቃብር መመልከት አስገራሚነቱም አስደንጋጭነቱም እየቀረ የመጣው ከዚህ አኳያ ይመስለኛል፡

| Copyright © 2013 Lomiy Blog