የኢትዮጵያውያን ከሳ/አረቢያ መውጣት ያስከተለው ችግር

እአአ ከ 610 ዓ ም ጀምሮ የእስልምና ኃይማኖት መገኛ እና ማስፋፊያ ማዕከል በመሆን ትታወቃለች። በማዕከላዊው ምስራቅ በፋርስ ባህረ ሰላጤ እና በቀይ ባህር መካከል በተንጣለለው የዓረቢያ በረሃ ላይ ጆርዳን ኢራቅ ኩዌት የመን ኦማን ቀጠር እና የተባበሩት ኣረብ ኢማራት በምድር ያዋስኗታል። 
ቀድሞ ኢትዮጵያ ኣሁን ግን ከኤርትራም ጋር የባህር ማዶ ጎረቤት ናቸው። ኣሁን ያለውን ኣገራዊ ቅርጽ ይዛ በኣዲስ መልክ እንደ መንግስት የቆመችው ከ 1818 ዓ ም ጀምሮ ሲሆን ስያሜዋንም ያገኘችው እ ኣ ዘ ኣ በ 1932 ዓ ም በንጉስ አብዱልአዚዝ አል ሳዑዲ ኣማካኝነት በንጉሱ የቤተሰብ ስም ተሰይማ መሆኑ ይተረክላታል። ሳዑዲ ዓረቢያ።
በነዳጅ ዘይት ምርቷ በዓለም ቀዳሚነቱን ይዛ የምትገኘው ሳውዲ ኣረቢያ የቆዳ ስፋቷ 2 ሚሊየን ስ ኪ ሜ ገደማ ሲጠጋ በ2010 በተካሄደ ቆጠራ መሰረት 27,5 ሚሊየን ያህል ህዝብም ኣላት። ከእነዚህ መካከል 19 ሚሊየኑ ብቻ የሳውዲ ዜጎች ሲሆኑ ቀሪው ስምንት ሚሊየን ደግሞ በተለያዩ ጊዜና ሁኔታዎች ወደ ኣገሪቱ የገቡ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ነው። ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህጋዊ የኣገር መኖሪያ እንደሌላቸው ሲገመት ለሰሞኑ ኣስደንጋጭ ክስተትም ምክኒያት የሆነው ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህኑ ስደተኞች የማስወጣቱ ዘመቻ ነው።
ጤና ይስጥልኝ የተወደዳችሁ የዶቸቬሌ ታዳሚዎች በዕለቱ የማህደረ ዜና ዝግጅታችንም ይህንኑ ዘመቻ ከኢትዮጵያ ኣንጻር ለመዳሰስ እንሞክራለን።
ዘውዳዊው የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዚህ ጊዜ የዚህ ዓይነት ግራ የተጋባ ጭፍን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚጠቁሙት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በዓረቡ ዓለም የተቀጣጠለውን እና ከቱዚያ ጀምሮ ሊቢያን እና ግብጽን ያናወጠውን እንዲሁም በጎረቤት የመን ኣድርጎ እስከ ኣሁንም ሶርያን በማተራመስ ላይ ያለውን ብሶት ወለድ የዓረብ ኣብዮት ተከትሎ ከወዲሁ ለዜጎቿ የስራ ዕድል ለመክፈት ታስቦ ነው ተብሏል።
በዚሁ መሰረት የሪያድ ኣገዛዝ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው የውጪ ዜጎች ኣንድም ሰነዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ ኣልያም ኣገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የ ሰባት ወር የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህ ጊዜ ውስጥም በሳውዲ ምንጮች መረጃ መሰረት 4 ሚሊየን ያህል የውጪ ዜጎች ሰነዶቻቸውን ኣስተካክሏል። 1 ሚሊየን ገገማ ደግሞ ኣገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቐል።
የተጠቀሰው የምህረት ጊዜ ያበቃው እ ኣ ዘ ኣ ባለፈው ህዳር 3 ቀን ሲሆን ወዲያውኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የሳውዲ ፖሊሶች በእነሱ ኣጠራር ሹርጣዎች በየአካባቢው ተሰማርተው የውጪ ዜጎችን ማሳደድ ጀመሩ። ምንም እንኩዋን እንደ ወትሮው ወደ ጎዳና የወጣ ስደተኛ ባይኖርም በስራ ቦታው እና ከየመኖሪያ ቤቱም እየገቡ ስደተኞችን ማደኑ ቀጠለ። ኣያያዙም ኃይል የተቀላቀለበት እና ስደተኞቹ እንደሚሉት ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ነው የነበረው።
ከፖሊስ ኃይሉ በተጨማሪ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ጋጠ ወጥ የሳውዲ ወጣቶች የፖሊሶቹን ዱካ እየተከተሉ እና ቤት ሰብረው እየገቡ ገንዘብ እና ንብረት መዝረፍ ወንዶችን መደብደብ እና ሴቶችን መድፈሩን ተያያዙት። ምንም እንኩዋን ከየአቅጣጫው የሚወጡት ዘገባዎች እርስ በርሳቸው የሚጣለዙ ቢሆኑም እስከኣሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት ደርሶባቿል። ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ህይወታቸውን ኣቷል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከስደተኞቹ አንደበት መረዳት እንደተቻለው ማሳደዱም ሆነ ጭካኔው የበረታው በተለይ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ነው ተብሏል።
የሴቶቹ እሮሮ ደግሞ በእርግጥም ለየት ያለ እና ዘግናኝም ነው።
የሴት ኢትዮጵያውያን መደፈር በአሰሳው ወቅት በሚደርስባቸው ብቻም ኣልተወሰነም። ተይዘው ወደ ማጎሪያ ካምፕ ከተወሰዱ በኃላም ከካምፑ ተሰርቀው ይወሰዳሉ ተብሏል።
በዚያ ላይ የማጎሪያ ካምፑ እስረኞችም ቢሆኑ ለበረኃ ግመሎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ ማቆያ ኣይመስልም የሚሉት የሪያድ እስረኞች ከዚሁ የተነሳ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መታመማቸውንም ይናገራሉ።
በዚህ ጭፍን ዘመቻ ወቅት እጅግ ኣነጋጋሪ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሳውዲ ወጣቶች በነቂስ ወተው ፖሊሶችን መከተል እና ስደተኞችን መዝረፍ መደብደብ እና በተለይ ሴቶችን የመድፈሩ ጉዳይ ነው።
የተገደሉትን ስደተኞች ቁጥር ኣስመልክቶም ከኢትዮጵያ እና ሳውዲ መንግስታት የወጡ ዓኃዞች ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ ቢሆኑም ዘገባዎች ግን ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ይጠቁማሉ።
«ነሲም በተባለች ከዚህ ከሪድ ኣንድ 30 እና 50 ኪ ሜ ርቃ በምት ገኘው ከተማ ባለፈው ሐሙስ ምሽት የሳውዲ ፖሊሶች ግርግር ፈጥረው 3 ሰዎችን ገግሏል። ሶስቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ብዙ ሰው እኮ ነው የተገደለብን። ሰው ሲገደል ወዲያውኑ ኣንስተው ወደማይታወቅበት ቦታ ስለሚወስዱት ለጊዝው ኣይታወቅም እንጂ በጣም ብዙ ሰው ነው የተገደለው። እኔ እራሴ የማውቃቸው ከአስር ሰው በላይ እገሌ እገሊት ብዬ ልቆጥርልህ እችላለሁ።»
እስከ ኣሁን ከ 3000 በላይ ስደተኞች ኣገር ቤት ደርሷል እየተባለ ባለበት በኣሁኑ ወቅትም ከተደበቁበት ገና ያልወጡ እና ባሉበትም በረኃብ እየተቸገሩ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ለዚህ ጭፍን እርምጃ የሳውዲ አረቢያን መንግስት መኮነናቸው ባይቀርም ስደተኞቹም ሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውናን ይበልጥ የሚያማርሩት ግን ሪያድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲን እና የኢትዮጵያን መንድስትም ጭምር ነው ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ጉዳይ ከልብ እያየው ኣይመስለንም። እንዲያውም ውስጥ ውስጡን ከሳውዲዎች ጋር እየሰራ ያለ ነው የሚመስለው የኢትዮጵያ መንግስት። ኢምባሲው በተለይ ልክ የዚህ ኣገር ፖሊሶች ገድለው ኣስክሬን እንደሚደብቁት እሱም አብሮ እየደበቀ ነው እንጂ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ በትኩረት እያየው ኣይደለም።
የሳውዲዎች ዘመቻ በተለይ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ማተኮሩን ኣስመልክቶ የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እርምጃውን ማውገዙ የሚታወስ ሲሆን ቃል ኣቀባዩ ኣምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለዶጨቤሌ እንደገለጹት ስደተኞቹን ወደ ኣገራቸው የመመለሱ ሂደት በተቻለፍጥነት እየሄደ ነው።
የሆነ ሆኖ በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲም ሆነ ከአዲስ ኣበባም የኃይለማሪያም ደሳለኝ ኣስተዳደር በኣጠቃላይ ከዘመቻው በፊትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ዜጎቹን ለመታደግ የወሰዷቸው እርምጃዎች በቂ ኣይደሉም ሲሉ ብዙዎች ይከሳሉ። በዚሁ ምክኒያት ጭምር ይመስላል በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከዚያ ወዲህ በቁጣ ገንፍለው ዋሽንግተን ዲ ሲ ን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ እና የኣውሮፓ ከተሞች አደባባይ ወቷል። ወደ ሳውዲ ኢምባሲ እየሄዱም ተቃውሞኣቸውን ኣሰምቷል።
በኣገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ኣድራጎቱን በመኮነን መግለጫ ኣውጥቷል። ባለፈው ዓርብ ስማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ግን አዲስ ኣብባ ላይ ልክ እንደ ሪያድ በሳውዲ ፖሊስ ሳይሆን ግን በኢትዮጲያ ፖሊሶች እርህራሄ በሌለው ድብደባ መበተኑ በኣሳኝነቱ ተዘግቧል።
በተያያዘ ዜና የሰሞኑ የሳውዲ አረቢያ እርምጃ ታሪካዊ ስህተት ነው የሚሉ ወገኖችም ኣሉ። ኣንዱም ሼክ ነጂብ መሐመድ ሲሆኑ በዋሽንግተን ዲ ሲ የሚኖሩት ሼክ ነጂብ በኣሁኑ ጊዜ « ዘ ፈርስት ሂጂራ» የተባለው ዓለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ የኢትኆጵያውያን እስላማዊ ተቐም መሪ ናቸው።
በእስልምና ኃይማኖት እንግዳ ይከበራል እንጂ ኣይነካም የሚሉት ሼክ ነጂብ በእስላማዊው የሸሪኣ ህግ እመራለሁ የሚለው የሳውዲ ኣገዛዝ ይህንን በማድረጉ ተጠያቂ ከመሆን ኣያመልጥም ይላሉ።
ጃፈር አሊ
አርያም ተክሌ
Source: www.dw.de

No comments:

| Copyright © 2013 Lomiy Blog