በኢትዮጵያ ተወልደው፣ በ 3 ዓመታቸው እሥራኤል በመግባት ፤ በዚያ ያደጉ የተማሩና የፓርላማ (ክኔሰት) አባል የሆኑት ፔኒና ታማኖ-ሻታ የተባሉት የ 32 ዓመት ወ/ሮ ፣ ከትናንት በስቲያ ደም ለመለገሥ ተዘጋጅተው ፤ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር መመሪያ
ደንብ መሠረት እንደማይፈቀድላቸው ከአምቡላንስ አገልግሎት እንደተነገራቸው ፣ ድርጊቱ ፣ አስቆጥቶ፣ እ ጎ አ በ 1996 ዓ ም ተከሥቶ የነበረውን ፣ ቤተ እሥራኤላውያን ለደም ባንክ የለገሡት ደም እንዲደፋ የተደረገበትንና ብርቱ የተቃውሞ ሰልፍ ያስከተለበትን የቁርሾ ስሜትም ቀስቅሶ በእሥራኤል ሕብረተሰብ እንደገና ዐቢይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል።
የፓርላማ አባል ፤ ወ/ሮ ታማኑ ሺታ ፤ መምህርት፤ ጠበቃና የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያ ሲሆን፤ በቅርቡ በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ፤ በምክትል የፓርላማ አፈ ጉባዔ ሥልጣናቸው ፣ እሥራኤልን በመወከል ከፓርላማው አፈ ጉባዔ ጋር ደቡብ አፍሪቃ ደርሰው መመለሳቸውም ታውቋል። እኒህ የታወቁ ሴትዮ የተጠቀሰው ዓይነትችግር ካጋጠማቸው ብዙዎች ያልታወቁ ቤተ እሥራኤላውያን ምን -ምን እየደረሰባቸው ይሆን? የእሥራኤል መገናኛ ብዙኀን ሕብረተሰቡስ ምን ይላል? ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን--
ከጤና ጥበቃ ሚንስትሯ ያኤል ጀርማንም ሆነ ከሀገሪቱ
ፕሬዚዳንት ሺሞን ፔሬስ ጭምር ዘለፋ ነው የተሰነዘረው። እ ጎ አ ከ 1977 አንስቶ ከተወለዱ አፍሪቃውያን የደም ልገሣ ላለመቀበል የወጣው ደንብ፣ አግባብነት አለው? ዘረኛ ደንብ ነው አይደለም?
ክርክሩ ቀጥሏል። ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ድርጊቱን ከማውገዝ ባለፈ የሚወሰድ እርምጃ የለም ማለት ነው ወይ?---
ሌላ እምነት ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ወደ እሥራኤል በመግባት በዚያ የሚኖሩ የክፍለ ዓለሙ ተወላጆችም አሉ። በእሥራኤል ሕብረተሰብ የተለያዩ የማህበረሰ ሰብ ክፍሎች ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ምን መማር ይችሉ ይሆን!
በህግ ፊት ይሁዲዎች ሁሉ እኩል ናቸው ፤ አድልዎ የለም በማለት ህገ መንግሥቱ ከደነገገ ተፈጻሚ ማድረጉ የከበደበት ምክንያት ምን ይሆን?
በእሥራኤል ሀገር የሚኖሩ የተለያዩ የአፍሪቃ ተወላጆችም ሆኑ ቤተ እሥራኤላውያን የዘር መድልዎ ይደርስባቸዋል የሚባለው በቆዳ ቀለም ልዩነት ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ
Source: www.dw.de

No comments: