ካሣሁን ዓለሙ:-

ሃይማኖት በሥርዎ ቃሉ ማመንና መታመን የሚሉ ፅንሣተ-ሐሣብን የያዘ ቃል ነው፡፡ ማመን በአንድ ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲሆን መታመን ደግሞ ላመኑበት ነገር መታገልና መቆም ነው፡፡ ይህንን ይዘን ወደ ፍልስፍናው መከራከሪያ ስንገባ በዓለማችን የሚገኙ የሃይማኖት ይዘቶችን በሦስት ከፍለን ልንያቸው እንችላለን፡፡
1) በእግዚአብሔር ህልውነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Theist)
የእግዚአብሔር ህልውነትን በማመንና እሱን በመመሥከር እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ግኑኝነት የሚያደርግ በሥራው ፍፁም የሆነ አምላክ መሆኑን ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆች ከእነሱ በላይና ፍጹም ከኾነ ኃይል ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ፤ እሱም በመገለጥ ስለ ዐለማትና ፍጥረታት አፈጣጠር፣ ስለ ሰው ልጆች መፈጠርና ህልውና ነግሯቸዋል፤ ያነጋግራቸዋል ብሎ ያምና፤ ለዚህም ጥብቅና ቆሞ ይመሠክራል፤ ይከራከራል፡፡
2) በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት (Atheist)
ይኸየእግዚአብሔርን ህልውነት የሚክድና ለዚያም አቋም ጥብቅና የቆመ ሃይማኖት መሰል አስተምህሮ ነው፡፡ይህም ሃይማኖት የራሱ መታወቂያ አለው፡፡ በአንድ በኩል ሰይጣንን በግል እያመለከ የእግዚአብሔርን ህልውነት የሚቃወም ሲሆን በአብዛኛው በኢሉምናቲ የሚሥጢር ማኅበራት የሚቀነቀን ነው፤ ምሥጢራዊነቱም ያመዝናል፡፡ ስለዚህ በግልፅና በተቋማዊ አደረጃጀት የማይታወቅ ቢመስልም በአብዛኛው በሳይንስና በፍልስፍና አስተምህሮ ተወሽቆ እምነቱ ተቀባይነት አግኝቶ እንዲስፋፋ ጥረት ይደረግለታል፡፡ የዚህ ሃይማኖት አቀንቃኞች በዋናነትዝግመተ ለውጠኛችና ቁሳካላዊያን ናቸው፡፡ለምሳሌ እንደ ፈርደሪክ ኒቼ፣ ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ዳሪዊን፣ ሪቻርድ ዳውኪንስና መሰሎቻቸውን መጥቀስይ ቻላል፡፡
3) ‹አሊለም› (እግዚአብሔር አለ-የለም) ሃይማኖት (Agnostic)
የእዚህ ሃይማኖት መነሻው ልቃዊነት (Liberalism) ማሳለጫው ምንፍቅና (Skeptic) ተግባሩምውልአልባነትና ግደለሽነት (indifference) ነው፡፡ የመከራከሪያ ስልቱም ዥዋዥዌ መጫወት ነው፡፡
ሆኖምከዚህበላይከተጠቀሱት ሦስት አማሮጮች ውስጥ ከመጀመሪያው በስተቀር ሌሎቹ የሃይማኖትን ትርጉም በትክክል የሚያሟሉ አይደሉም፡፡ ሁለተኛው አማራጭ (Atheist) ምንም እንኳን ፍልስፍና እና ሳይንስን በማመንና ለእነሱም ጥብቅና በመቆም መታመኑን የሚመሰክር ቢመስልም በውስጡ የተለያዩ ችግሮች አሉበት፡፡አንደኛ ፍልስፍና (በተለይዓለማዊፍልስፍና) የሚታመን መሠረት የሌለው ገና በእውን ነገር (existence) መኖርና አለመኖር ላይ የሚሟገት የንፀሮተ-ዓለም ፅንሰ-ሐሣብ ነው፡፡ በእውን ነገር መሠረት መኖርና አለመኖር ላይ ጭቅጭቅ አለበት፤ በዚህ የተነሣም ከሰዎች አንጻር ብቻ የሚቃኝ አመለካከት ለመኾን ይገደዳል፡፡ ሳይንስ ደግሞ የተለዋዋጩ ዓለም ተለዋዋጭ ዕውቀት ነው፡፡ ሰዎች ለማወቅ እስከጣሩበት ያለውን በመቀበል ከዚያ ውጭ ያለውን ዕውቀት ይሸፍናል፤ መሠረቱም ሰዎች ፍልስፍናዊ ዕይታ ነው፤ ስልቱም የሚጨበጥ ናሙናን በመጠቀም መገመት ነው፡፡ ስለዚህ ሳይንስም የሚታመን አካልን በመሠረትነት በመቀበል ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይሁንና ኹለቱም ለክፍላቸው የታመነ ምስክርነት አሏቸው፤ ስለኾነም ነው ዕይታቸው እንደ ሃይማኖት ሊወሰድ የቻለው፡፡ ችግሩም ያለው በመታመናቸው ሳይኾን የታመኑበት ነገር አስተማማኝ አለመኾኑ ነው፡፡ አስተማማኝ የማይኾነውም የተመሠረቱት በሰው (በራስም ሊሆን ይችላል) ናሙናዊ የምጣኔ ግመታና ቁሳዊ ዕውቀት ላይ ብቻ ስለኾነ ነው፡፡ ለምሳሌ ፍልስፍና በራሱ አይተማመንም፤ ስለዚህ መርሁእመነኝ!› በማለት ላይ ሳይሆንጠይቅ!› በማለት ላይ ነው፡፡ መጠየቅ ደግሞ መልስ ይፈልጋል፤ ትክክለኛው መልስ እስከሚገኝ ድረስም ማመን አይቻልም፤ ስለሆነም ፍልስፍናን ለማመን ያስቸግራል፡፡ ሳይንስም እንደዚሁ ለመታመን አይበቃም፤ አንደኛ ዛሬ የታመነው ነገር ነገ ትርጉም የለሽ ሊሆን ይችላል፤ ሁለተኛ የሚመሠረተው በቁሳዊ ዕውቀት ጥርቅሞሽና ልምድ ላይ ስለሆነ ረቂቅና ምጡቅ ለኾነ ዕውቀት አይመጥንም፡፡ ስለዚህ በሳይንስና በፍልስፍና ላይ የተመሠረተ አመለካከት አስተማማኝነት እስካላገኘ ድረስ ሃይማኖት የሚለውን ፅንሠ-ሓሳብ አያሟላም፡፡ ስለኾነም ምንምጊዜ የሠጠው ቅልኾኖ ትክክለኛ ሃይማኖትን ቢያጣጥልም በእግዚአብሔር አለመኖር ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብ ሃይማኖት የሚለውን ፅንሰ-ሓሣብ በአግባቡ የማያሟላ ነው፤ በመኾኑም ተቀባይነት የለውም፡፡
ሦስተኛውአሊለምየሚለው የሃይማኖት መሰል አቋምየመፎለል አባዜእና ግራ መጋባት የፈጠረው አስተሳሰብ ይመስላል፡፡ መፎለሉ ከልቃዊነት (liberal or free thinking?) የመጣ ነው፤ ስለሆነም ውል የለው፤ የአስተሳሰብ ግራመጋባት (Indifferent thinking) ደግሞ የእምነትመድረሻ አይኖረውም፡፡ ልቃዊነት ለአስተሳሰብ ግራ መጋባት ምክንያት ነው፤ መርሁም አንድም ምንንም ነገር ባለማመን በምንፍቅና (ጥርጣሬ) መኖር ነው፤ ኹለትም ግራ ተጋብቶ እስከ ማቀወስ መድረስ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ መፈላሰፍ ያቀውሳል የሚለውን አስተሳሰብ ያመጣውም ይህ የልጓም አልባነት ፉለላ ነው፡፡) ልቃዊነትን ከአንድ የልቃቂት ፈትል ጋር በማነጻጸር መረዳት ይቻላል፤ አንድ ሰው የአንድ ልቃቂት ፈትልን ጫፏን ሳይዝ ሲመዝ ቢውል ያወሳስባል እንጂ በትክክል በመተርተር ፈትቶ ሊያጠነጥናት አይችልም፤ እንደዚህም ልቃውነት በዚህ በውስብስብና በሰፊው ዓለም ውስጥ ኾኖ ያንንም ያንንም እየነከሰ ሲያደማ ይኖራል እንጂ አንድት የዓለማችን የመፍትሔ ዕውቀትን ማበርከት አይችልም፤ ምክንያቱም የመከራከሪያ ውል ስለሌለው ከማላገጥ ያለፈ የክርክር ርዕስን አንስቶ በተጠየቅ አይሞግትም፡፡ ምሳሌ እንጥቀስ፡-
ልቃውነት እግዚአብሔር አለም አይል ወይም የለም አይልም፤ ለመንቀፍ ግን የሚቀረው ስድብ የለም፡፡ ነገር ግን የአስተሳሰብ ውል ቢኖረው ኖሮ አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ መከራከር ነበረበት፤አለም የለምየሚለው ግራ ገብ መደምደሚያ ላይ ከደረሰ ግን መነሻም መድረሻም የለውም ማለት ነው፤ ስለዚህ ሥራው መዛቆን ብቻ ይሆናል፡፡ ቆይአለም የለምአልልም ካለዐላውቀም!› ማለቱ ነው፤ አላውቅም የሚል ከሆነም ክርክር የለም፤ የማያውቅን ምን ሊያስረዳን ነው የሚከራከረው፤ ወይም ከመከራከሩ በፊት ለማውቅ ይጠይቅ፤ ከዚያ ያለፈ የማያውቁት ውስጥ ገብቶ መፈትፈት ግን አንጋረ ፈላስፋዐያውቅም፤ አለማወቁንም ዐያውቅምያለው የድንቁርና ባህር ውስጥ መዋኘት ነው፡፡ የሚገርመው ግን ልቃውያንዐለማወቃቸውን ዐለማወቃቸውብቻ አይደለም ችግሩ፤ ምክንያቱም ዐለማቃቸውን ብቻ መሥክረው ዝም አይሉም ይልቁንም ከዚያ አልፈውእነ ሹፈት! ማላገጥ! ማንጓጠጥ!› የሚባሉ ሀብቶች እንዳሏቸው ጨምረው ይነግሩናል፤ ምናልባት እነሱ ችግራቸውን ለመደበቅ ብለው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ልቃዊነት፤ ግራ ገብነትን ይዞ መጣ፤ ግራ ገብነት ደግሞ መሸሸጊያ ሹፈትን አወረሰ፤ በዚህ የተነሣም ማላገጥ ዕውቀት ኾኖ ነገሠ፡፡ ግዛቱንም በኢትዮጵያ አስፋፍቶ እየፈነጭብን ነው፡፡ አደጋውም ዕውቀት ሆኖ መታየቱ ነው፤ ያውም የምጡቃን!
ልቃዊነት መያዣ መጨበጫ የሌለው ዕውቀት መሰል ሃይማኖት ነው ስንል ዝም ብለን አይደለም፡- ከተፈጥሮው በመነሳት ነው፡፡ ምክንያቱምሃይማኖት ማመንና መታመንን የያዘ ፅንሰ ሓሳብ ነውባልነው መሠረት ብዙ ሰዎች ልቃዊነትን አምነው በመቀበል ጥብቅና ቆመውለት እየተከራከሩለት ይገኛል፤ ስለዚህ በሥርዎ ቃል አኳያ መሥፈርቱን ሟሟላት ችሏል ማለት ነው፤ ለራሱ በራሱ ሃይማኖት ኾኗል፡፡ ችግሩ ያመነው በምንድን ነው ስንልእግዚአብሐየር አለም የለምበማለት ወይምአለም የለም አልልምበማለት መኾኑ ነው፡፡ ልቃዊነትእግዚአብሔር የሚባል የለምቢለን ኖሮ ችግር አልነበረውም፤ ማስረጃህን አምጥተህ አሳምነን ብለን እንሞግተው ነበር፤አለምበማለት ጥርጣሬውን ቢገልጽልን መኖሩን ለምናምን ማስረጃዎችን እናቀርብለት፤ ካላመንም በአፀፋ መልስ ምክንያታችንን ደርደርን እንሞግተው ነበር፤ አቶ ልቃዊነት ግን ሊያዝልን አይችልም፡- ‹ሁሉም ጋር የለም፤ ሁሉም ጋር አለ- በውል አልባነቱ ግራ ገብቶት ግራ ያጋባናል፡፡ በዚህ አቋሙና እምነቱ እንደተሙለጨለጨ ይኖራል እንጂ መከራከር ግን አይችልም፡፡
ምክንያቱም ለመከራከር የክርክር አጥንትና ሥጋ የሆኑት የነጥብ መነሻና መደምደሚያ ያስፍልገዋል፤ በዚህም አሳማኝነት ያለው ክርክር ለማቅረብ መነሻው ሐሳብ ትክክልና እውነት በመሆን ተቀባይነት ሊኖረው ግድ ነው፤ በዚህ ስምምነት መሠረትም ክርክሩ ትክክልና አውነት ከኾነ አሳማኝነት ኖሮት መርታት ይቻላል፤ ማለት ደግሞ በአሳማኝነቱ ይታመንበታል፡፡ ነገር ግን ልቃዊነት የመከራከሪያ መነሻው ምንድን ነው? የሚከራከረውስ ምን ጋር ለመድረስ ነው? የእግዚአብሔርን መኖር ለመመስከር ወይስ አለመኖሩን ለማረጋገጥ? ኹለቱንም ካልኾነስ ለምን መከራከር ያስፈልገዋል? ከእነዚህ ኹሉ ካልኾነስ ለምን የማያገባውን እየገባና የማይመለከተውን ጉዳይ እያነሳ ይዘባርቃል? ስለዚህ ልቃዊነት ምንም የክርክር መስመር ስለሌው ስለ እግዚአብሔር ጉዳይ መከራከር አይችልም፤ ማላገጡም ያላዋቂነት ዳፍንቱ ውጤት ነው፡፡ አበውከማያውቅ፤ አለማወቁን ከማያውቅሰው ተጠበቁ የሚሉት ለዚያ ነው፡፡
ያምአለግንልቃዊነት የዘመናችን ሃይማኖት ልንለው ብንችልም፤ የእሙንነትን መሠረት ስለለቀቀ ግንጥል ነው፡፡ ኾኖም የታመኑለት ተከታዮቹ ሽንጣቸውን ገትረው ስለሚያላግጡለት፤ የዘመናችን ዕውቀት መሠል አስተሳሰብ ነው፡፡ በሃገራችንምሽው በይ! ሽው በይ! ሽው በይ! ባራዳእያለ የዕውቀት በሽተኛ ዜጎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ስለዚህልቃዊነት የዘመናችን የፋሽን ሃይማኖተኝነት ችግር ነውብንል የተሳሳትን አይመስለኝም፡፡
በእውነታው ከሔድን ግን ሃይማኖት የሚታመኑለት መሠረትን ይፈልጋል፤ ለእዚህ ለታመኑለት ጉዳይም ጥብቅና በመቆም ያረጋግጡታል፤ ወይ የሚታመኑበት መሠረት ከሌለ ወይም የአመኑትን ካልመሠረኩረለት ሃይማኖት መኾኑ ይቀራል፡፡ ከዚህ አንጻርበእግዚአብሔር አለመኖርላይ የተመሠረተ ሃይማኖት እምነቱን የሚመሠክርለት ማስረጃ ስለሌለው ለአዕምሯዊ ሰው የሚመጥን ሃይማኖት አይደለም፡፡ በሌላ በኩልአሊለምሃይማኖት ደግሞ በልቃዊነት ፋሽን የሚቦርቅ ጥጃ እንጂ መነሻውም ኾነ መድረሻው ግራ የገባው ነው፤ የሚያምኑትልቅየኾኑ ልጆች ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህየለሞችምኾናችሁግራገቦች› (እስከነ ስሙ ግራገብ) ንስሐ ግቡ ብለናል፡፡ አይ! ካላችሁ ማስረጃ አቅርባችሁ በመሞገት ሃይማኖታችሁን አስረዱን፤ አሳምኑን፡፡ አይሻልም?
see more: kassahunalemu.wordpress.com

| Copyright © 2013 Lomiy Blog