በነመቶ አለቃ ፈንቲ ትእዛዝ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ቁጥራቸዉ አስር የሚሆኑ ፖሊሶችና ቁጥራቸዉ ያልታወቀ ሚሊሻዎች የደ/ጎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀሀፊና የፋርጣ ሁለት የተወካዮች ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሰለሞን ታደሰ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ።
ሰለሞን ታደሰ ሰማያዊ ፓርቲ ካፈራቸዉ ምርጥ ወጣቶች አንዱ ሲሆን ለወያኔ የእግር እሳት በመሆን በአደባባይና በህዝባዊ ስብሰባዎች የገዥዉን አፈና ያለ ምንም መሸማቀቅ ያጋለጠና በወጣቱ ዘንድ ድጋፍና አድናቆት ያለዉ ወጣት ነዉ።ይህ ወጣት ከአንድነት ጀምሮ በተለያዩ ወረዳዎችና እንዲሁም በእግሩ በመጉዋዝ በየ ቀበሌዉ ወጣቱን ሲያደራጅ የቆየ ነዉ።ሰሞኑን ሰማያዊ ፓርቲ ባደረገዉ ሰልፍ ከፍተኛ አስተዋፆ አበርክቷል።
ይህን የቁርጥ ቀን ጀግና ወጣት ሆድ አደር ባለ ድርሻ አካላት መገደል እንዳለበት የወሰኑ መሆኑን ምንጮች የገለፁ ሲሆን ወጣቱ ባሰማዉ የድረሱልኝ ጥሪ ህዝቡ ሲወጣባቸዉ አንገለዉም ህግ አቅርቡ ብሎን ነዉ በማለት እስር ቤት ወሰዱት።ሌሊቱን በሙሉ ሲደበድቡት አድረዉ በአካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እስኪ ሰማያዊ ያድንህ በማለት ሲሳለቁበት እንዳደሩ ከወጣቱ አንደበት እና ከታሰሩ ሰዎች ለማወቅ ተችሏል። አሁን በመቶ አለቃ ፈንቲ አማካኝነት ከጧቱ አራት ሰአት ምንም አይነት ዋስና ክስ ሳይከሰስ እንዲፈታ ተደርጉዋል። ሸር በማድረግ ለሁሉም ይድረስ
የጀግና ልጅ ነኝ – Millions of voices for freedom -
No comments: