በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኀን እንደተዘገበውና የኢትዮጵያ መንግሥትም እንዳረጋገጠው Mi-35 በሚል መለያ
በሚታወቅ አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ፣ 3 ኢትዮጵያውያን የአየር ኃይል ባልደረቦች፤ ከድሬዳዋ ኮብልለው ኤርትራ
ገብተዋል። ይህ የሆነው ከ
13
ቀን ገደማ በፊት ሲሆን ፤ ከሰሞኑም ሌሎች 4 የአየር ኃይል አባላት ኬንያ ገብተው ተገን መጠየቃቸው ተወርቷል።
ስለዚህ ጉዳይ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል መረጃም ሆነ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት አድርገን ነበር ፤ ማግኘት ግን
አልቻልንም። በኬንያ መገናኛ ብዙኀን ፤ በጋዜጣ፤ ራዲዮም ሆነ ቴሌቭዥን ምናልባት የተወሳ ነገር አለ ወይ በማለት ፣
አጠያይቀን ነበር ።
ሻምበል
ሳሙኤል ግደይ የተባሉት አብራሪ ከ 2 ባልደረቦቻቸው ጋር Mi 35 በተሰኘው የጦር ሄሊኮፕተር ኮብልለው ከኢትዮጵያ
መውጣቸው በተነገረ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ 4 የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ፤ ወደ ኬንያ በመኮብለል በዚያ
የፖለቲካ ተገን ጠየቁ መባሉ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። የጋዜጠኞች መሳደድ ፤ እሥራትና የመሳሰለው ነበር በሰፊው
ሲያነጋግር የቆየው፤ አሁን ወታደሮች ፤ እዚህም ላይ የጦር አኤሮፕላን አብራሪዎች ኩብለላ በቀጣይነት መካሄዱ ፣
ምክንያትን የሚያጠያይቅ ይሆናል። ምላሹን ከራሳቸው፣ ከኮብላዮቹ አንደበት መስማት እስኪቻል ድረስ! ይሁንና ፣ 4
የአየር ኃይል ጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ኬንያ ገቡ ስለመባሉ በዚያች ሀገር መገናኛ ብዙኀን የተገበ ጉዳይ ይኖር
ይሆን ፣ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ----
ጋዜጠኞች
ይጽፋሉ ይናገራሉ ፤ ያስተምራሉ ሒስ ይሠነዝራሉ፤ አግባብነት ባለው ጉዳይ ላይ! ሙያቸው ነውና! ዴሞክራሲ
በሠፈነባቸው አገሮች ፣ ለሕብረተሰብ ብቻ ሳይሆን በሥልጣን ላይ ለሚገኝ መንግሥትም ተፈላጊዎች ናቸው! ።
በአንድ
ሀገር ሕብረተሰብ ውስጥ ነጻ የሐሳብ ልውውጥ ሲኖር
ለሀገርም ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽዖ አለውና! ዴሞክራሲን
ከልብ ባልተቀበሉ ፤ ወይም የዴሞክራሲ ጸር በሆኑ አገሮች ግን ጋዜጠኞች እንደ እክል መታየታቸው የታወቀ ነው።
የጋዜጠኞችን ያህል በቀጥታ የማያጋፈጡ ወገኖች ተቃውሞን በኩብለላ ሲገልጹ ምን ማለት ይቻላል? ምን የከፋ ችግር
ቢያግጋጥም ይሆን?
ኬንያና
ኢትዮጵያ ፣ በመከላከያ የጋራ ትብብር ውል የተፈራረሙ አገሮች ናቸው። ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አንስቶ
የቀጠለ ጉዳይ ነው። የጦር ኃይል አባል የሆነ ሰው ከብልሎ ኬንያ ቢገባና ተገን ቢጠይቅ አደጋ ይኖረዋል?
Source: DW.DE
No comments: