By: Ethiopian Reporter
 ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች
በዘካሪያስ ስንታየሁ
አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሱዳን ጠረፍ 40 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብላ በምትገኘውና ቡምባዲ በምትባለው አካባቢ 5,250 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለውን ታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ካደረገች በኋላ፣ ግብፅ የተለያዩ ጫናዎችን በኢትዮጵያ ላይ ለማሳደር እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ ግብፅም በዚህ ግድብ ምክንያት የዓባይ የውኃ መጠን ሊቀንስ ይችላል የሚል ስጋት ስላላት፣ የዲፕሎማሲ ጫና ከማድረጓ በተጨማሪ የጦር ሠራዊቷን በተጠንቀቅ እንዲቆም እስከማዘዝ ደርሳለች፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ግን ይህ እንቅስቃሴ ግብፆች የውስጥ ችግራቸውን ትኩረት ለማስለወጥ ከመሆኑ በተጨማሪ የድርድር ስትራቴጂ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ሚና ከፍተኛ በሆነበት በዚህ ወቅት በእሷ ላይ ጦርነት ማወጅ የማይታሰብ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ግብፆች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር ለመነጋገር የራሳቸውን ልዑክ እንልካለን እያሉ መሆናቸውን አምባሳደር ዲና ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት ከአፍሪካ ዲፕሎማሲ ርቆ ነበር፡፡ ስለሆነም አዲሱ የግብፅ መንግሥት ወደ አፍሪካ ዲፕሎማሲ መቀላቀል ከፈለገ የትብብር ማዕቀፉን የፈረሙ አገሮችን መቃረን እንደሌለበት አምባሳደር ዲና አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱን ሱዳን በቅርብ ጊዜ ትፈርማለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ሱዳኖች ለጊዜው ግብፅ ችግር እንዳትፈጥርባቸው ጉዳዩን በሚስጥር እንደያዙት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሰኞ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ የተጓዘው የግብፅ የልዑካን ቡድን ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር የተወያየ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱ ኡጋንዳ በተፋሰስ አገሮቹ አማካይነት የተመሠረተውን ተቋም የማፍረስ ምንም አቋም እንደሌላት አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ግብፅ ውስጥ የተከሰተው አለመረጋጋት እስኪረጋጋ ድረስ ኡጋንዳ ስምምነቱን እንደማታፀድቀውና ግብፅን ልትጠብቃት እንደምትችል፣ ሙሴቪኒ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ጋማል አብደል ናስር ልጅ ለሚመራው የግብፅ ልዑካን ቡድን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንዳሉት፣ ‹‹ኡጋንዳዎች በመጀመሪያም ወደ ስምምነቱ ሲገቡ ጥቅማቸውን አይተው ስለሆነ ወደኋላ ይመለሳሉ ብለን አናምንም፡፡›› ኡጋንዳዎች ይህን ያሉት ምክንያታዊ ለመሆን ይሆናል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ በማናቸውም ሁኔታ በኡጋንዳ በኩል ያለውን ቁርጠኝነት አንጠራጠርም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ኡጋንዳ ካመራው የግብፅ ልዑክ ውስጥ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሦስት ግለሰቦች በመኖራቸው ይህን ጉዳይ ለምርጫ መቀስቀሻነት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ የጦርነት እንቅስቃሴውም ቢሆን በዓባይ ላይ በፕሮፓጋንዳ ድምፅ ማግኘት ስለሚፈልጉ እንጂ ዘላቂ ነገር አይደለም ብለዋል፡፡
- ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች
በዘካሪያስ ስንታየሁ
አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሱዳን ጠረፍ 40 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብላ በምትገኘውና ቡምባዲ በምትባለው አካባቢ 5,250 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለውን ታላቁ የሚሌኒየም ግድብ ፕሮጀክት ይፋ ካደረገች በኋላ፣ ግብፅ የተለያዩ ጫናዎችን በኢትዮጵያ ላይ ለማሳደር እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ ግብፅም በዚህ ግድብ ምክንያት የዓባይ የውኃ መጠን ሊቀንስ ይችላል የሚል ስጋት ስላላት፣ የዲፕሎማሲ ጫና ከማድረጓ በተጨማሪ የጦር ሠራዊቷን በተጠንቀቅ እንዲቆም እስከማዘዝ ደርሳለች፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግን ይህ እንቅስቃሴ ግብፆች የውስጥ ችግራቸውን ትኩረት ለማስለወጥ ከመሆኑ በተጨማሪ የድርድር ስትራቴጂ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ሚና ከፍተኛ በሆነበት በዚህ ወቅት በእሷ ላይ ጦርነት ማወጅ የማይታሰብ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ግብፆች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር ለመነጋገር የራሳቸውን ልዑክ እንልካለን እያሉ መሆናቸውን አምባሳደር ዲና ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት ከአፍሪካ ዲፕሎማሲ ርቆ ነበር፡፡ ስለሆነም አዲሱ የግብፅ መንግሥት ወደ አፍሪካ ዲፕሎማሲ መቀላቀል ከፈለገ የትብብር ማዕቀፉን የፈረሙ አገሮችን መቃረን እንደሌለበት አምባሳደር ዲና አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱን ሱዳን በቅርብ ጊዜ ትፈርማለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ሱዳኖች ለጊዜው ግብፅ ችግር እንዳትፈጥርባቸው ጉዳዩን በሚስጥር እንደያዙት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ሰኞ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ የተጓዘው የግብፅ የልዑካን ቡድን ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር የተወያየ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱ ኡጋንዳ በተፋሰስ አገሮቹ አማካይነት የተመሠረተውን ተቋም የማፍረስ ምንም አቋም እንደሌላት አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ግብፅ ውስጥ የተከሰተው አለመረጋጋት እስኪረጋጋ ድረስ ኡጋንዳ ስምምነቱን እንደማታፀድቀውና ግብፅን ልትጠብቃት እንደምትችል፣ ሙሴቪኒ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ጋማል አብደል ናስር ልጅ ለሚመራው የግብፅ ልዑካን ቡድን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንዳሉት፣ ‹‹ኡጋንዳዎች በመጀመሪያም ወደ ስምምነቱ ሲገቡ ጥቅማቸውን አይተው ስለሆነ ወደኋላ ይመለሳሉ ብለን አናምንም፡፡›› ኡጋንዳዎች ይህን ያሉት ምክንያታዊ ለመሆን ይሆናል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ በማናቸውም ሁኔታ በኡጋንዳ በኩል ያለውን ቁርጠኝነት አንጠራጠርም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ኡጋንዳ ካመራው የግብፅ ልዑክ ውስጥ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሦስት ግለሰቦች በመኖራቸው ይህን ጉዳይ ለምርጫ መቀስቀሻነት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ የጦርነት እንቅስቃሴውም ቢሆን በዓባይ ላይ በፕሮፓጋንዳ ድምፅ ማግኘት ስለሚፈልጉ እንጂ ዘላቂ ነገር አይደለም ብለዋል፡፡
አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረጉ፡፡ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ” የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ቅዱስ ኤልያስ በ2000 ዓ.ም ከመንግስተ ሰማያት ወደ ቅድስት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አስተምሯል ያሉት የማህበሩ በቅዱስ ኤልያስ፣ በሄኖክና በመልከፄዴቅ የተባረኩ በመሆናቸው እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የዳዊት መዝሙር ላይ በመመስረትና፣ ፓትሪያርኩ የቅዱሳን ሊቃውንት ክብረ በዓላት በብሔራዊ ደረጃ ለማስከበር በቦታው መገኘት ይገባቸዋል በማለት ፓትርያርኩን አሳስበዋል፡፡ የማህበር አባላት በኢትዮጵያ ደረጃ መስከረም 7፣ 12፣ 21 እና የካቲት 21 ብሔራዊ በዓላት እንዲሆኑ ነው ፓትሪያሪኩን ለመጠየቅ የፈለጉት፡፡
የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ ናቸው” (መኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ)
ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በተያያዘ የክልሉን የስራ ሃላፊዎችና መንግስትን ለመክሰስ፣ ሰማያዊ ፓርቲና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥብቅና ያቆሟቸው አለም አቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማሪያም፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸው ተገለፀ፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ከትናንት በስቲያ ከሠዓት በኋላ በሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ በሠጡት መግለጫ፤ ተፈናቃዮቹ አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን፣ ልጆቻቸው ትምህርት ማቋረጣቸውን፤ በሚዲያ እንደሚነገረው ወደ ቀድሞ ኑሯቸው አለመመለሳቸውንና በአጠቃላይ ችግር ላይ መሆናቸውን
በማስረጃ በማስደገፍ፣ የጉራፈርዳንና የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮችን በማነጋገርና በበርካታ መረጃዎች የተደገፉ ዶክሜንቶችን በማያያዝ ዶ/ር ያዕቆብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላኩትን ደብዳቤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፈርሞ መቀበሉንም ፓርቲዎቹ ገልፀዋል፡፡
የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን በፓርላማ ቀርበው ማመናቸውን፣ ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት የክልልና የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ከስራ መሰናበታቸውን፣ ተፈናቃዮቹ ወደነበሩበት ተመልሠው በሠላም እየኖሩ እንደሆነ የገለፁ ቢሆንም እውነታው ግን ከዚህ በተቃራኒው መሆኑን ዶ/ር ያዕቆብ ከተፈናቃዮች ጋር በመነጋገር ማረጋገጣቸውን ጠቁመው፣ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ከመሄዱ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሠጡ ዶ/ር ያዕቆብ ለጠ/ሚኒስትሩ በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ፤ አፋጣኝ ምላሽ ያሻቸዋል ያሏቸውን አራት ዋና ዋና ነጥቦች በደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀድሞ ቦታቸው በመንግስት ወጪ ተመልሠው መሬታቸው፣ የንግድ ተቋሞቻቸውና ቤት ንብረታቸው በአስቸኳይ እንዲመለስላቸው፣ ተፈናቃዮቹ ለደረሰባቸው ቁሳዊ ጉዳት፣ አካላዊና ሞራላዊ እንግልት መንግስት ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፍላቸው የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያዝዙ፣ በቤኒሻንጉል የሚኖሩ የማንኛውም ብሄር ተወላጆች ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፀምባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እና ተዋዶና ተፋቅሮ የሚኖረውን ህዝብ በመከፋፈል የማፈናቀል ድርጊት የፈፀሙ የመንግስት ባለስልጣናት ህግ ፊት ቀርበው ቅጣት እንዲያገኙ ውሳኔ እንዲያሳልፉ የሚሉት ነጥቦች ተቀምጠዋል፡፡
መንግስት ወንጀለኞች ያላቸውን የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ከስራ ማሠናበቱንና ጉዳያቸው በፍ/ቤት እየታዩ ያለ ባለስልጣናት እንዳሉ፣ ተፈናቃዮቹም ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ተመልሠዋል እየተባለ ነው የተፈናቃዮቹን ጉዳይ ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት ፈለጋችሁ በሚል ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ “ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲከኛ ለመሆን በርካታ ምክንያቶች አሉ” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ነገር ግን ተፈናቃዮች አሁንም በችግር ላይ ናቸው ቤት ንብረታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተቀራምተውት በክረምት ሜዳ ላይ የወደቁ አሉ፣ በፋሲካ በዓል ቤታቸው የተቃጠለባቸው ተፈናቃዮች አሉ፣ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ያልተመለሱትም በርካቶች ናቸው ካሉ በኋላ “ጠበቃችን ዶ/ር ያዕቆብ ይህንን ጉዳይ ከተፈናቃዮቹ በተጨባጭ አረጋግጠዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡ የመኢአድ ዋና ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በበኩላቸው፤ የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች በችግር ላይ ለመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫውን እስከሠጡበት ሰዓት እንኳን መረጃዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ገልፀው፣ በጠበቃው ዶ/ር ያዕቆብ በኩል ደብዳቤ መፃፋችን ጉዳዩ በፍ/ቤት እልባት እስኪያገኝ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሠጣቸው ነው ብለዋል፡፡
ችግሩ መቆም ያልቻለው ከመረጃ እጥረት ይሆናል በሚል ምን ያህል ሰዎች በችግር ላይ እንዳሉ፣ ቤት ንብረታቸውን ቆጥረው የተመዘገቡበት መረጃ ከየምርጫ ጣቢያው የወሠዱትን ካርድ መልሠውና ንብረታቸውን አስመዝግበው እንዲወጡ በሀላፊዎች ፊርማና በመንግስት ማህተም የታዘዙበት ደብዳቤና በርካታ ዶክሜንቶችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደብዳቤው ጋር አያይዘው መላካቸውም ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱ መሪ እንደመሆናቸው ችግሩንም በፓርላማ ቀርበው ማመናቸው እንደ ማስረጃ ተቆጥሮ የአገሪቱ የስራ አስፈፃሚ ከፍተኛ አካል በመሆናቸው ስለሚከሰሱ “መረጃው የለኝም አላየሁም” እንዳይሉ ታስቦ፣ ዶክሜንቱ እንደተላከላቸውም በፓርቲዎቹ ተገልጿል፡፡ ወደ ክስ ከሄዳችሁ ደብዳቤው ለምን አስፈለገ? ጠ/ሚኒስትሩ ምላሽ ከሠጡስ ክሱ ይቆማል ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ “ችግሮች መፍትሄ ካገኙ ክሱ ቀድሞውኑ ለምን ያስፈልጋል” ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “መንግስት ይህን ወንጀል የፈፀሙትን አስሬያለሁ ከስራ አሠናብቻለሁ” የሚለው ጉዳዩ አለም አቀፍ ስለሆነበት ውጥረቱን ለማርገብ ነው ብለዋል፡፡ ምላሽ ካላገኛችሁ በትክክል ክስ መቼ ትጀምራላችሁ ለሚለውም፤ ወንጀሉ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው ዶ/ር ያዕቆብ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ሲመለሱ ይጀመራል፣ በአገር ውስጥ ፍ/ቤት ካልተሳካ ጉዳዩ ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ያመራል ብለዋል - የመኢአድ ዋና ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፡፡ እስካሁንም በጉራፈርዳ ከሚኖሩ 78ሺህ የአማራ ተወላጆች መካከል 21ሺህ ያህሉ መፈናቀላቸውንና በቤኒሻንጉልም ከአምስት ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሹ የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡
          Source: http://www.addisadmassnews.com/
ወደ ፖለቲካ የምገባው ህዝብ ማገልገል ስለምፈልግ ነው
*
ኢትዮጵያን አርቀንና በረጅም ጊዜ የማናይ ከሆነ፣አባይን መገደብ አያስፈልገንም
*
በውጭ ሆነው የሚቃወሙ አገራቸው ላይ መታገል አለባቸው ባይ ነኝ

ከጥቂት ዓመታት በፊት /ሚኒስትር የመሆን ፍላጐት እንዳለው ገልፆ የነበረው አትሌት ኃይሌ /ሥላሴ፤ ሰሞኑን ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረገው ቃለምልለስየአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆን እፈልጋለሁበማለቱ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡ 2007 . በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተወዳድሮ ፓርላማ ለመግባት ያሰበው አትሌቱ፤ ከዚያም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ህዝብን ማገልገል እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡ 
አትሌት ኃይሌ፤ ከጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ፤ ለምን ወደ ፖለቲካ ሊገባ እንዳሰበ፣ ፕሬዚዳንት ሆኖ ቢመረጥ ለመስራት ስላቀዳቸው ተግባራትና ተያያዥ ጉዳዮች አውግቷል።

እነሆ:- የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ከአትሌት ኃይሌ ጋር
ሰሞኑንፕሬዚዳንት መሆን እፈልጋለሁማለትህን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከዘገቡ በኋላ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ እንዴት ነው ነገሩ?
እኔ የምልሽ ---- ፕሬዚዳንት እንድሆን ኖሚኔት (አጭታችሁኛል) አድርጋችሁኛል እንዴ? ፕሬዚዳንት የሚመረጠው በገዢው ፓርቲ ኖሚኔት ሲደረግ እና ሁለት ሶስተኛውን የፓርላማና የፌደሬሽን /ቤት ይሁንታ ሲያገኝ ነው፡፡ እና ይሄ ነገር ሲደጋገምብኝ ---- እንዴት ነው ተጠይቆልኝ ይሆን እንዴ እላለሁ፡፡
ለአሶሽየትድ ፕሬስ በሰጠኸው ቃለ - ምልልስ ላይ ነው ፕሬዚዳንት መሆን እንደምትፈልግ የተናገርከው---
እኔ በእርግጠኝነት የምነግርሽ 2007 . ፓርላማ እንደምገባ ነው፡፡ ለዚህም ዝግጅት እያደረግሁ ነው፡፡
የት ነው የምትወዳደረው? እዚህ ነው አርሲ?
ኧረ እዚሁ አዲስ አበባ ነው፡፡ የካ ክፍለከተማ ላይ ነው የምወዳደረው፡፡
ለምርጫ ውድድር የሚጠየቁ መስፈርቶችን እንደምታሟላ አረጋግጠሃል?
በሚገባ! በክ/ከተማው ለመወዳደር ህጉ አምስት አመትና ከዚያ በላይ መኖር አለብሽ ይላል፡፡ እኔ ደግሞ እዚያ /ከተማ ውስጥ 10 ዓመት ኖሬአለሁ፡፡ ምርጫው በሚካሄድበት 2007 . ደግሞ 12 ዓመት ይሆነኛል ማለት ነው፡፡ እርግጥ በትውልድ ስፍራዬ ሄጄም ብወዳደር እንደማሸንፍ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡
ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንደምትፈልግ ተናግረህ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ፕሬዚዳንትነቱ ዞረሃል--- የመጀመርያውን እቅድ ለምን ተውከው?
ምን መሰለሽ? በአሁኑ ሰዓት እንኳን እኔ ልጆቼም ሲቪክስ ስለሚማሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ለመመረጥ ምን መደረግ እንዳለበት ያውቃሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በጣም ረጅም ጊዜ ይወስዳል፡፡ ፓርቲም ማቋቋም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ፕሬዚዳንት ለመሆን ግን ፓርቲም አያስፈልግም፡፡ ገዢው ፓርቲ ካመነበትና ብቁ ሆነሽ ከተገኘሽ መሆን ይቻላል፡፡ እኔ ደግሞ ለዚህች አገር መስራት አለብኝ ብዬ የማምን ሰው ነኝ፡፡ ገና ጠቅላይ ሚኒስትር እስከምሆን እርጅና ሊጫነኝ ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ወደ ፕሬዚዳንትነት የዞርኩት፡፡ በነገራችን ላይ ለዚህች አገር ሥራ ለመስራት ጠቅላይ ሚኒስትርም ፕሬዚዳንትም ሆኖ መመረጥ ላያስፈልግ ይችላል፡፡
ፕሬዚዳንት ለመሆን መፈለግህን በተመለከተ ከአገር ውስጥ ሚዲያዎች ይልቅ ለውጭ ሚዲያ በቅድሚያ መንገርህ ቅሬታ የፈጠረ ይመስላል፡፡ አንተ ምን ትላለህ?
የሚገርመው ለአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ኢንተርቪው የሰጠሁት በጠቅላላ ጉዳዮች ላይ እንጂ በፕሬዚዳንትነት ላይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በጭውውት መሃልፕሬዚዳንት ብትሆንስ እንዴት ነው?” በሚል ጥያቄ ሲነሳ፣ ከተሳካ ለምን አልሆንም የሚል ምላሽ ሰጥቻለሁ፡፡ ጋዜጠኛው ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ እሱ የላከላቸው ሙሉ ቃለምልልሱን ነው፡፡ እነሱ ፕሬዚዳንት የምትለዋን ሃሳብ መዘዙና ሲያጐሏት የሁሉም መነጋገሪያ ሆነ፡፡ ከዚያም እነ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ጋርዲያን፣ ቢቢሲ ትኩረት ሰጥተው ሲዘግቡት፣ይሄን ያህል ትኩረት መሳብና ተጽእኖ መፍጠር እችላለሁ እንዴበሚል ግርምት ውስጥ ገባሁ፡፡ፕሬዚዳንት መሆን ትፈልጋለህ ወይሲሉኝአዎ ለምን አልሆንምአልኳቸው፡፡ እነሱም ከዚህ ተነስተው ነውወደፊት ፕሬዚዳንት ይሆናልያሉት፡፡ ስለዚህ ፕሬዚዳንት እሆናለሁ ብዬ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቤበት ለውጭ ሚዲያ ኢንተርቪው አልሰጠሁም፡፡ በዚህ መልኩ የረዱት ካሉ ግን በጣም አዝናለሁ፡፡
የፕሬዚዳንትነት ጥያቄ ቢቀርብልህ ግን ትቀበላለህ?
አሁን ፕሬዚዳንት መሆን የሚጠላ አለ! (ረጅም ሳቅ)
የሚጠላ ሊኖር ይችላል፡፡ መቼም ሁሉም ይፈልጋል አይባልም፡፡
እኔ ግን የሚጠላ ያለ አይመስለኝም---
ስለዚህ እኔም አልጠላም እያልከኝ ነው?
አዎ! ለምን እጠላለሁ --- ግን ለምን ትገፋፊኛለሽ? እንደምታውቂው ከዚህ በፊት በፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጐት እንዳለኝና 2007 እንደምወዳደር ቆርጫለሁ፡፡ እንደነገርኩሽ ለመወዳደር እየተዘጋጀሁ ነው፡፡ ፓርላማ መግባቴ የራሴን ሚና ለመጫወት ያግዘኛል፡፡ አሁን ዋናው ትኩረት የሰጠሁት ፓርላማ መግባት ላይ ነው፡፡
በፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎትህ ከምን የመነጨ ነው?
ምን መሰለሽ --- ብዙ ጊዜ እንደምንሰማውና እንደምናየው ሁሌ እንተቻለን እንነቅፋለን፡፡ እንደዚያ ከምናደርግ ለምን የምንነቅፈውን ነገር ውስጥ ገብተን ተሳትፈን አናየውም? ብዙ ነገሮች በውጭና በውስጥ ሆነን ስናያቸው ይለያያሉ፡፡ መቃወምም ካለብሽ ውስጥ ገብተሽ ነው፡፡ መንቀፍም ካለብሽ እንደዛው፡፡ ውስጥ ሆነሽ ስትቃወሚ፣ ይሄ ልክ አይደለም ስትይ፣ ልክ ነው ያልሽውን አማራጭ ሃሳብ አብረሽ ታቀርቢያለሽ፡፡ እንደው ዝም ብሎ በደፈናው ይሄ ልክ አይደለም ይባላል፡፡እሺ አማራጭ አቅርብሲባል የለም፡፡ ይህ አይነት ነገር ትንሽ ያናድደኛል፡፡ ስለዚህ እኔ ፓርላማ ውስጥ ገብቼ በሌላው አለም ስዞር በፖለቲካው ዘርፍ ያገኘሁትን ተሞክሮ ማካፈልና አማራጭ ሃሳቦችን ማቅረብ፣ ህዝብ ማገልገል ስለምፈልግ ነው፡፡ በፖለቲካ የመሳተፍ ፍላጐቴም ከዚህ የመነጨ ነው፡፡
በሌላም አለም ስዞርስትል---በሩጫው ማለትህ ነው አይደል?
አዎ! እኔ ከመቶ በላይ የአለም አገሮችን አይቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደኔ አለምን የዞሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡ በተለይ 1983 . ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወጥቼ ቤልጂየምን ካየሁ በኋላ፣ ኢትዮጵያ እንድትሆን የምመኘው ነገር አለ፡፡ ስለዚህ ልምዴን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማካፈል አለብኝ፡፡
አንተ እንደልብህ መንቀሳቀስ፣ በነፃነት መሮጥ የለመድክ ሰው ነህ፡፡ ፕሬዚዳንት ሲኮን ግን ነፃነት አይኖርም፡፡ እንቅስቃሴህ ሁሉ በጋርድ የታጀበ ነው የሚሆነው፡፡ እንደፈለጉ መሆን የለም፡፡ የምትችለው ይመስልሃል?
እንዲህ አይነት ነገሮች ሲደጋገሙ ያስቁኛል (ረጅም ሳቅ…) ይህንን ጥያቄ ጓደኞቼም ይጠይቁኛል፡፡ በተደጋጋሚ ማለቴ ነው፡፡ከእንግዲህ ጫካ ውስጥ ላናይህ ነውይላሉ፡፡ ያው በልምምድ ላይ ማለታቸው ነው፡፡ እኔምየበለጠ የምንሰራው እንደውም ያን ጊዜ ነውእላቸዋለሁ፡፡ እርግጥ እዛ ደረጃ ላይ ስትደርሺ ያንን ህግና ስርዓት ማወቅ አለብሽ፡፡ ህግና ሥርዓት ደግሞ ለሀይሌ ብቻ ተብሎ የሚደረግ አይደለም፡፡ ቦታው ስለሚያዝ ነው የሚሆነው፡፡ ቦታው ያዛል ስልሽ ----- ሃይሌ /ስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚደርስበትና እንደ ሃይሌ /ስላሴ እንደራሱ ሆኖ የሚደርስበት ነገር የተለያየ ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች የግድ ማወቅ አለብኝ፡፡ የአንድ አገር መሪ ስትሆኚና እንደማንኛውም ሰው ስትሆኚ ይለያያል፡፡
ሰው መሆንና ባለስልጣን መሆን ይለያያል እንደማለት ነው?
አዎ! ለምሳሌ እኔ መሪ ብሆን ከማጣቸው ነገሮች አንዱ ነፃነት የሚባለው ነገር ነው፡፡ እኔ አሁን ሁልጊዜ ግን ሁሉ ነገር እንደሚጠፋ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ይህን ይህን ሳላስብ ፕሬዚዳንት መሆን እፈልጋለሁ ማለት የማይመስል ነገር ነው፡፡
ሌላው ነገር ፕሬዚዳንትነት የሙሉ ሰዓት ሥራ ነው፡፡ አንተ ደግሞ እጅግ በርካታ ቢዝነሶችን የምታንቀሳቅስ ሰው ነህ፡፡ ይህንንስ እንዴት ታስተናግደዋለህ?
ዋናውና ጠቃሚው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ በድርጅቴ ስር ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞች ይተዳደራሉ፡፡ እነዚህንም አስቀድሜ ቦታ ማስያዝ አለብኝ፡፡ ቦታ ማስያዝ አለብኝ ስልሽ --- እንደ እኔ ሆኖ ይህን ሃላፊነት ሊሸከም የሚችል ሰው ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ እነዚህ እነዚህ ነገሮች ቀድሞ ሊታሰብባቸው እንደሚገባ አይጠፋኝም ማለቴ ነው፡
በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አሁን ዝግጁ ነህ?
አሁን ተዘጋጅተሃል ወይ ላልሽው አሁን አልተዘጋጀሁም፡፡ ጊዜ የሚፈልጉ ነገሮች ናቸው፡፡ ስዘጋጅ እነግርሻለሁ፡፡
ፕሬዚዳንት ብትሆን ምን ለውጥ አመጣለሁ ብለህ ታስባለህ? አሁን እንደ ጉድለት የምታያቸውና እሰራቸዋለሁ የምትላቸው ነገሮች ካሉ ብትነግረኝ ----
እኔ እርግጠኛ ሆኜ የምነግርሽ ሥልጣን ባገኝ ብዙ የምሠራቸው ነገሮች እንዳሉ ነው፡፡ ሥልጣኑ የሚኒስትር ይሁን ፕሬዚዳንት በይው--- ምንም በይው ግን በርካታ ስራዎችን እንደምሠራ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ቀላል ልምድ ያካበትኩ አይመስለኝም፡፡ የሰሞኑን የእኔን ዜና ዝም ብለሽ ብታይው ይገርምሻል፡፡ ቅድም እንዳልኩሽ ---- ይህን ያህል ተደማጭና ተጽእኖ ፈጣሪ ነኝ ወይ እስከማለት ደርሻለሁ፡፡ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የእኔን ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት በጣም ትኩረት ሰጥተውት ነበር፣ ስለዚህ ይህንን ነገር ተጠቅሜ የራሴን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ የሚል ፍላጐት አደረብኝ፡፡ እንደ ዲፕሎማትም በይው እንደምንም ሆኜ ማለቴ ነው፡፡
ቀደም ሲል ለአገር ለመስራት የግድ ፕሬዚዳንትም ጠቅላይ ሚኒስትርም መሆን እንደማያስፈልግ ነግረኸኛል፡፡ ታዲያ የምትፈልገውን ነገር ለመስራት ምን የሚያግድህ ነገር አለ?
እውነት ነው የሚያግደኝ ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ነገሮች እየተለወጡ ነው፡፡ ነገር ግን ውስጥ ሆነሽ ነገሮችን ብትመለከቺና ልምድሽን ብታካፍይ የበለጠ ይህቺን አገር መለወጥ ይቻላል ለማለት ነው፡፡ ለዚህም እርግጠኛ ሆኜና አስረግጬ የምነግርሽ 2007. በየካ /ከተማ እንደምወዳደርና ፓርላማ ለመግባት እንደምጥር ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ብትሆን ምን ምን ሥራዎችን እንደምታከናውን አልነገርከኝም ----
ቅድም እንዳልኩሽ ብዙ ስራዎችን መስራት እንዳለብኝ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ ብዙ በውጭ የሚኖሩ ሰዎች ነገሮች ተስተካክለውላቸው አገራቸው ላይ እንዲኖሩ ማመቻቸት አንድ ሥራ ነው፡፡ መሪ ስትሆኚ የገዢውን ፓርቲ አላማ ነው የምታራምጂው፣ ይሄ ግድ ነው፡፡ የገዢውን ፓርቲ ፕሮግራም ስታራምጂ አብረሽ ተዛማጅ በሆኑ ሥራዎች ላይ ትሳተፊያለሽ፡፡ ግን ፖለቲካውን የማይነኩ ነገር ግን ለዚህች አገር በጣም ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች አሉ፡፡ ሁልጊዜ አገር ስትመሪ መመልከት ያለብሽ፣ የዛሬን፣ የነገን ሳይሆን የሩቁንና የወደፊቱን መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጵያን አርቀንና በረጅም ጊዜ የማናይ ከሆነ፣ አባይን መገደብ አያስፈልገንም፡፡ ስለዚህ በዚያ ዙሪያ ብዙ ነገሮችን አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ፣ ፓርላማ መግባት አንዱም ጥሩ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት እንኳን ባይኮን ማለት ነው፡፡ ሰሞኑን በፓርላማ ምን ተዓምር እየተሰራ እንደሆነ ለአንቺ አልነግርሽም፡፡ ሌላው በስራ አጥነት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በኤክስፖርት ላይ ብዙ መስራት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም ኤክስፖርት የምታደርገው በጣም ጥቂት ነው፣ እሱን ማሳደግ ላይ መሠራት አለበት፡፡ ጠቃሚ ያልሆኑ ባህሎቻችን ላይም እንዲሁ፡፡ በእኛ አገር ሰርጋችንም ሀዘናችንም ከአንድ ሳምንት በላይ ይወስዳል፣ ሠርግ ጥሩ ነው? አዎ ጥሩ ነው፣ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ ሊወስድ አይገባውም፡፡ ይሄ ወደ ኋላ የሚጐትት ነውና መቅረት አለበት፡፡
ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጐትህን ባለቤትህ / አለምን ጨምሮ በርካታ ጓደኞችህና ወዳጆችህ ተቃውመውታል ይባላል፡፡ የአንተ ፍላጐት ደግሞ እየበረታ ነው፡፡ እንዴት ልትቋቋማቸው ነው?
ልክ ነው፡፡ ሚስቴም ልጆቼም፣ ዘመድ ወዳጆቼም ሁሉ አልደገፉትም፡፡ ይሄ ግን መጀመሪያም እዚህ ውሳኔዬ ላይ ስደርስ የምጠብቀው ነገር ነው፡፡ ማንም እንደማይደግፈኝ ማለቴ ነው፣ ለምን እንደሆነ ልንግርሽ? ባለቤቴም ቤተሰቦቼም የእነርሱና የእነርሱ ብቻ እንድሆን እንደሚፈልጉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር የማረጋግጥልሽ ከበፊት ጀምሮ ወደ ፖለቲካው መግባት ምኞቴ ነበር፡፡
ቤልጂየምን ካየሁ በኋላ ኢትዮጵያ እንድትሆን የምመኘው ነገር አለ፡፡ ድሮ ድሮ አውሮፓ ሄጄ ስመጣ፣ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ህንፃ ቢኖራት፣ እንዲህ አይነት መንገድ ቢኖራት፣ የሚል ምኞት ነበረኝ፣ እሱ እየተሳካልኝ ነው፡፡ ለዚህ ነው በማገኘው ገንዘብ ወዲያውኑ እዚህ እየመጣሁ የምሠራው፡፡ ውጭ ወጥቶ የመስራትና የመኖር አጋጣሚው ስለሌለኝ ግን አይደለም፡፡ እንደነገርኩሽ ያልረገጥኩት አገር የለም፡፡ ዜግነት እንስጥህ ያሉኝ በርካታ አገራት አሉ፣ የሰጡኝም አሉ፣ የተቀበልኳቸውም ያልተቀበልኳቸውም አሉ፡፡ እኔ ግን የማረጋግጥልሽ ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነው፡፡ ለምን ብትይ --- አማራጭ የለኝም፡፡ ሌላ ምርጫ አላካትትም፡፡ ሰዎች ይህንን ቢረዱልኝ ደስ ይለኛል፡፡ ተደማጭና ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆንኩ ሰርቼ ማሳየት አለብኝ፡፡ እኔ አገር ጥሎ መጥፋትን ለሰው ማሳየት አልፈልግም፣ አላደርገውም፡፡
ቤተሰቦቼ ፖለቲካ ውስጥ ለምን ገብተህ ትቸገራለህ ይሉኛል፣ ግን የአቅሜን መስራት አለብኝ እላለሁ፡፡ በውጭ ሆነው የሚቃወሙትም እዚሁ አገራቸው ላይ መታገል አለባቸው ባይ ነኝ፡፡ እንደ ግብጽ፣ እንደ ሶሪያ ባለ መንገድ ዴሞክራሲን ለማምጣት ከውጭ የሚመጣ ካለ እኔም እራሴ እዋጋዋለሁ፡፡ እነ ግብጽ ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ችግሮች ካሉ ፓርላማ ገብቶ በሰለጠነ መንገድ መከራከር፣ ችግሮችን ማስተካከል የኢትዮጵያዊያን ሃላፊነት ነው፣ ምክንያቱም ሰላም፣ ጥሩ ኑሮ፣ መልካም አስተዳደር እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡ እነዚህ ነገሮች ደግሞ ዝም ብለው እንደ ዳቦ የሚታደሉ አይደሉም፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ አድርገን፣ ችግሮቻችንን መፍታት መነጋገር እንጂ አገር ጥሎ ሄዶ እሰው አገር ፖለቲከኛ መሆን አያዋጣም፡፡ ለዚህ ነው የቤተሰቦቼን ተቃውሞ ተቋቁሜ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጐቴን ያጠነከርኩት፡፡
ሀይሌ አሁን ሩጫ የሚያቆምበት ዘመን ስለሆነ ላለመረሳት ነው ወደ ፖለቲካው ለመግባት ያሰበው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ አንተ ምን ትላለህ?         
*ይህን ጽሑፍ ያገኜሁት ከአዲስ አድማስ ድህረ ገጽ ነው፡፡ ነገር ግን ቃለ መጠይቁ በሙሉ አልተለጠፈም፡፡ እናም ድህረ ገጹ ገብታችሁ በፒዴፍ ተጭኗል እና አንብቡት፡፡
                         Source:- http://www.addisadmassnews.com


| Copyright © 2013 Lomiy Blog